ኢሳይያስ 8 – NASV & CCB

New Amharic Standard Version

ኢሳይያስ 8:1-22

አሦር የእግዚአብሔር መሣሪያ

1እግዚአብሔርም እንዲህ አለኝ፤ “ትልቅ ሰሌዳ ወስደህ፣ ‘ማኸር-ሻላል-ሃሽ-ባዝ’8፥1 በዚህና በቍጥር 3 ላይ፣ ማኸር-ሻላል-ሃሽ-ባዝ ማለት፣ ምርኮ ፈጠነ፤ ብዝበዛ ቸኰለ ማለት ነው። ብለህ በተለመደው በሰው ፊደል ጻፍበት። 2እኔም፣ ካህኑን ኡሪያንንና የበራክዩን ልጅ ዘካርያስን ታማኝ ምስክሮቼ እንዲሆኑ እጠራቸዋለሁ።”

3እኔም ወደ ነቢዪቱ ሄድሁ፤ እርሷም ፀነሰች፤ ወንድ ልጅም ወለደች። እግዚአብሔርም፣ እንዲህ አለኝ፤ “ስሙን ማኸር-ሻላል-ሃሽ-ባዝ ብለህ ጥራው። 4ሕፃኑም፣ ‘አባባ’ ወይም ‘እማማ’ ብሎ መጥራት ከመቻሉ በፊት፣ የደማስቆ ሀብትና የሰማርያ ምርኮ በአሦር ንጉሥ ይወሰዳል።”

5እግዚአብሔርም እንደ ገና እንዲህ ሲል ተናገረኝ፤

6“ይህ ሕዝብ በጸጥታ የሚፈስሰውን

የሰሊሆምን ውሆች ትቶ፣

በረአሶንና

በሮሜልዩ ልጅ ተደስቷልና።

7ስለዚህ ጌታ ታላቁንና ብርቱውን

የጐርፍ ውሃ8፥7 የኤፍራጥስ ወንዝ ነው።

የአሦርን ንጉሥ ከነግርማ ሞገሱ ሁሉ ያመጣባቸዋል።

ውሃውም ከቦዩ ዐልፎ ተርፎ

በወንዙ ዳር ያለውን ምድር ሁሉ ያጥለቀልቃል፤

8እየጠራረገ ወደ ይሁዳ ይወርዳል፤

እያጥለቀለቀ ያልፋል፤

እስከ ዐንገትም ይደርሳል፤

ዐማኑኤል8፥8 ዐማኑኤል ማለት፣ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ማለት ነው። ሆይ፤

የተዘረጉ ክንፎቹ ምድርህን ከዳር እስከ

ዳር ይሸፍናሉ።”

9እናንተ አሕዛብ፣ ፎክሩ8፥9 ወይም፣ የከፋውን ነገር አድርጉ፤ ነገር ግን ደንግጡ።

በሩቅ አገር ያላችሁ አድምጡ፤

ለጦርነትም ተዘጋጁ፤ ነገር ግን ደንግጡ፤

ለጦርነትም ተዘጋጁ፤ ነገር ግን ደንግጡ፤

10ተመካከሩ፤ ግን አይሳካም፤

ዕቅድ አውጡ፤ ሆኖም አይጸናም፤

እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነውና።8፥10 ዕብራይስጡ፣ ዐማኑኤል ይላል።

እግዚአብሔርን ፍሩ

11እግዚአብሔር ብርቱ እጁን በላዬ አድርጎ የእነዚህን ሰዎች መንገድ እንዳልከተል አስጠነቀቀኝ፤ እንዲህም አለኝ፤

12“እነዚህ ሰዎች፣ ‘አድማ’ ብለው የሚጠሩትን፣

ማንኛውንም ነገር፣ ‘አድማ’ አትበሉ፤8፥12 ወይም ለስምምነት አትጥሩ፤ እነዚህ ሰዎች ሁልጊዜ ለስምምነት ይጠራሉ

እነርሱ የሚፈሩትን አትፍሩ፤

አትሸበሩለትም።

13ልትቀድሱ የሚገባው የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔርን ብቻ ነው፤

ልትፈሩት የሚገባው እርሱን ነው፤

ልትንቀጠቀጡለት የሚገባውም እርሱ ነው።

14እርሱም መቅደስ ይሆናል፤

ለሁለቱ የእስራኤል ቤት ግን

የሚያደናቅፍ ድንጋይ፣

የሚያሰናክልም ዐለት ይሆንባቸዋል፤

ለኢየሩሳሌም ሕዝብም

ወጥመድና አሽክላ ይሆናል።

15ከእነርሱ ብዙዎች ይሰናከላሉ፤

ይወድቃሉ፤ ይሰበራሉ፤

ወጥመድ ይገባሉ፤ ይያዛሉም።”

16ምስክርነቱን አሽገው፤

ሕጉንም በደቀ መዛሙርቴ መካከል አትመው።

17ፊቱን ከያዕቆብ ቤት የሸሸገውን

እግዚአብሔርን እጠብቃለሁ፤

እርሱንም ተስፋ አደርጋለሁ።

18እነሆ፤ እኔና እግዚአብሔር የሰጠኝ ልጆች በጽዮን ተራራ ከሚኖረው ከሰራዊት ጌታ ከእግዚአብሔር ለእስራኤል ምልክትና ድንቅ ነን።

19ሰዎች፣ የሚያነበንቡትንና የሚያንሾካሽኩትን ሟርተኞችንና መናፍስት ጠሪዎችን ጠይቁ ቢሏችሁ፣ ሕዝቡ አምላኩን መጠየቅ አይገባውምን? በሕያዋን ምትክ ሙታንን መጠየቅ ለምን አስፈለገ? 20ወደ ሕጉና ወደ ምስክር ቃሉ ሂዱ! እነርሱም እንዲህ ያለውን ቃል ባይናገሩ የንጋት ብርሃን አይበራላቸውም። 21ተጨንቀውና ተርበው በምድሪቱ ላይ ይንከራተታሉ፤ ክፉኛ ሲራቡም ይቈጣሉ፤ ወደ ላይ እየተመለከቱ ንጉሣቸውንና አምላካቸውን ይራገማሉ። 22ከዚያም ወደ ምድር ይመለከታሉ፣ የሚያዩትም ጭንቀት፣ ጨለማና የሚያስፈራም ጭጋግ ብቻ ነው፤ ወደ ድቅድቅ ጨለማም ይጣላሉ።

Chinese Contemporary Bible (Simplified)

以赛亚书 8:1-22

预言灾难降临

1耶和华对我说:“你去拿块大的写字板,用通用的文字在上面写上‘玛黑珥·沙拉勒·哈施·罢斯8:1 玛黑珥·沙拉勒·哈施·罢斯”意思是“快速掳掠,迅速抢夺”。2我会吩咐忠信的祭司乌利亚耶比利迦的儿子撒迦利亚为这事做见证。” 3以赛亚与妻子同房,她就怀孕生了个儿子。耶和华对我说:“给他取名叫玛黑珥·沙拉勒·哈施·罢斯4因为这孩子会叫父亲母亲之前,亚述王必把大马士革的财富和撒玛利亚的战利品洗劫一空。” 5耶和华又对我说: 6“因为这些人拒绝接受我如西罗亚河缓缓流水般的温柔照顾,反倒因与利迅利玛利的儿子结盟而欢喜, 7我要差来亚述王的军队,使他们像幼发拉底河的洪流一样汹涌而来,淹没一切水道,漫过河岸, 8席卷犹大,使整个犹大几遭灭顶之灾。他必展开双翼横扫你的土地。”愿上帝与我们同在!

9列国啊,你们必被打垮、击溃!

远方的人啊,你们要听!

整装备战吧,但你们必被击垮!

整装备战吧,但你们必被击垮!

10你们设计谋吧,但休想得逞!

你们定策略吧,但休想成功!

因为上帝与我们同在。

当敬畏主

11耶和华大能的手按在我身上,警告我不可效法这些人。祂说: 12“他们认为是阴谋的,你们不要认为是阴谋。他们所怕的,你们不要怕,也不要畏惧。 13你们当尊万军之耶和华为圣,当敬畏祂,畏惧祂。 14祂必作人的圣所,也要作以色列犹大的绊脚石和使人跌倒的磐石,作耶路撒冷居民的陷阱和网罗。 15许多人必被绊倒,摔得粉身碎骨;他们必被网罗缠住、捕获。” 16我的门徒啊,你们要把上帝的训诲卷起来,用印封好。 17虽然耶和华掩面不顾雅各家,但我仍要等候祂,冀望于祂。 18看啊,我和祂所赐给我的儿女在以色列是征兆。这征兆来自住在锡安山的万军之耶和华。 19有人让你们去求问那些念念有词的巫师和术士,你们不要去。你们要去求问你们的上帝,活人的事怎能求问死人呢? 20人应该遵循耶和华的训诲和法度。人若不遵循祂的话,必看不到曙光。 21他们必困苦,饥饿,到处流浪,并在饥饿中怒气冲冲地咒骂他们的君王,亵渎上帝。 22他们抬头望天,低头看地,看到的尽是患难、痛苦和黑暗。他们必被扔进黑暗中。