ኢሳይያስ 32 – NASV & CCB

New Amharic Standard Version

ኢሳይያስ 32:1-20

የጽድቅ መንግሥት

1እነሆ፤ ንጉሥ በጽድቅ ይነግሣል፤

ገዦችም በፍትሕ ይገዛሉ።

2እያንዳንዱ ሰው ከነፋስ መከለያ፣

ከወጀብም መጠጊያ ይሆናል።

በበረሓም እንደ ውሃ ምንጭ፣

በተጠማም ምድር እንደ ትልቅ ቋጥኝ ጥላ ይሆናል።

3የሚያዩ ሰዎች ዐይን ከእንግዲህ አይጨፈንም፤

የሚሰሙም ጆሮዎች ነቅተው ያዳምጣሉ።

4የችኵል አእምሮ ያውቃል፤ ያስተውላልም፤

የተብታባም ምላስ የተፈታ ይሆናል፤

አጥርቶም ይናገራል።

5ከእንግዲህ ሰነፍ ጨዋ አይባልም፤

ጋጠወጥም አይከበርም።

6ሰነፍ ስንፍናን ይናገራል፤

አእምሮው ክፋትን ያውጠነጥናል፤

ፈሪሀ እግዚአብሔር የሌለበትን አድራጎት ይፈጽማል፤

በእግዚአብሔርም ላይ የስሕተት ቃል ይናገራል፤

ለተራበ ምግብ ይከለክላል፤

ለተጠማ ውሃ አይሰጥም።

7የጋጠወጥ ዘዴ ክፉ ነው፤

የችግረኛም አቤቱታ ትክክል ቢሆን፣

ድኻን በሐሰት ለማጥፋት፣

ክፋት ያውጠነጥናል።

8ጨዋ ግን ሐሳቡም ጨዋ ነው፤

በጨዋነት ምግባርም ጸንቶ ይገኛል።

የኢየሩሳሌም ሴቶች

9እናንት ትዕቢት የወጠራችሁ ሴቶች፣

ተነሡ፤ ድምፄን ስሙ፤

እናንት ተደላድላችሁ የምትኖሩ ሴቶች ልጆች ሆይ፤

የምነግራችሁን አድምጡ።

10ዓመቱ ገና እንዳለፈ፣

ተደላድላችሁ የነበራችሁ ትንቀጠቀጣላችሁ፤

የወይን ተክል ፍሬ አይሰጥም፤

የፍራፍሬም ወቅት አይመጣም።

11እናንት ትዕቢት የወጠራችሁ ሴቶች ተንቀጥቀጡ፤

እናንት ተደላድላችሁ የምትኖሩ ሴቶች ልጆች፣ በፍርሀት ተርበትበቱ፤

ልብሳችሁን አውልቁ፤

ወገባችሁን በማቅ ታጠቁ።

12ስለ ለሙ መሬት ደረታችሁን ምቱ፤

ስለ ፍሬያማው የወይን ተክል ዕዘኑ፤

13ስለ ሕዝቤ ምድር፣

እሾኽና አሜከላ ስለ በቀለበት ምድር፣

ስለ ፈንጠዝያ ቤቶች ሁሉ፣

ስለዚህችም መፈንጫ ከተማ አልቅሱ።

14ዐምባ ምሽጉ ወና ይሆናል፤

ውካታ የበዛበት ከተማ ጭር ይላል፤

ምሽጉና ማማው ለዘላለሙ ዋሻ፣

የዱር አህያ መፈንጫ፣ የመንጋም መሰማሪያ ይሆናል፤

15ይህም የሚሆነው መንፈስ ከላይ እስኪፈስስልን፣

ምድረ በዳው ለም መሬት፣

ለሙ መሬትም ጫካ እስኪመስል ድረስ ነው።

16በምድረ በዳ ፍትሕ ይሰፍናል፤

በለሙም መሬት ጽድቅ ይኖራል፤

17የጽድቅ ፍሬ ሰላም፣

የጽድቅ ውጤትም ጸጥታና ለዘላለም መታመን ይሆናል።

18ሕዝቤ ሰላማዊ በሆነ መኖሪያ፣

በሚያስተማምን ቤት፣

ጸጥ ባለም ስፍራ ዐርፎ ይኖራል።

19ደኑ በበረዶ ቢመታ፣

ከተማውም ፈጽሞ ቢወድም፣

20በየወንዙ ዳር ዘር የምትዘሩ፣

በሬዎቻችሁንና አህዮቻችሁን በነጻነት የምታሰማሩ፣

ምንኛ የተባረካችሁ ናችሁ።

Chinese Contemporary Bible (Simplified)

以赛亚书 32:1-20

公义的君王

1看啊,必有一位君王以公义治国,

官员们必秉公施政。

2每人都像躲避狂风暴雨的庇护所,

如荒漠中的溪流,

又似干旱之地遮荫的大磐石。

3人们的眼睛必不再迷蒙,

耳朵必能听见。

4急躁的人必慎思明辨,

口吃的人必说话清楚流利。

5愚昧人必不再被奉为尊贵之人,

恶棍必不再受尊重。

6因为愚昧人说愚昧话,

心里邪恶,行事不义,

亵渎耶和华,

使饥饿的人没饭吃,

使口渴的人没水喝。

7恶棍们手段邪恶,

用阴谋诡计和谎言毁灭困苦的人,

即使穷人的诉求有理也是枉然。

8高尚的人计划高尚的事,

在高尚的事上持之以恒。

9生活安逸的妇女啊,

来听我的声音!

无忧无虑的女子啊,

要侧耳听我的言语!

10无忧无虑的女子啊,

再过一年多,

你们必因恐惧而战抖。

那时,必没有葡萄可摘,

没有果子可收。

11生活安逸的妇女啊,战抖吧!

无忧无虑的女子啊,颤栗吧!

你们要脱下衣服,

腰束麻布,

12为美好的田地和硕果累累的葡萄树捶胸痛哭吧!

13为我百姓那长满荆棘和蒺藜的土地,

为那曾经充满欢乐的城邑和家庭哀哭吧!

14王宫必被遗弃,

繁荣的城邑必荒芜,

山冈和瞭望塔必永远成为野驴的乐园、羊群的草场。

15等到圣灵从上面浇灌我们的时候,

旷野要变为沃野,

沃野上庄稼茂密如林。

16那时,公平必充满旷野,

公义必遍布沃野。

17公义必带来平安,

公义所结的果子是永远的和平与安宁。

18我的子民必住在平安之地、

安稳之处、平静之所。

19但冰雹必扫平森林,荡平城邑。

20你们这些在河边撒种、自由地牧放牛驴的人有福了!