መዝሙር 59 – NASV & CCBT

New Amharic Standard Version

መዝሙር 59:1-17

መዝሙር 59

ክፉዎችን በመቃወም የቀረበ ጸሎት

ለመዘምራን አለቃ፤ “አታጥፋ” በሚለው ቅኝት የሚዜም፤ ዳዊትን ለመግደል ሰዎች ቤቱን ከብበው እንዲጠብቁት ሳኦል በላካቸው ጊዜ፤ የዳዊት ቅኔ59 ርእሱ የሥነ ጽሑፉን ቅርጽ ወይም የመዝሙሩን ሁኔታ የሚያሳይ ሊሆን ይችላል።

1አምላክ ሆይ፤ ከጠላቶቼ እጅ አድነኝ፤

ሊያጠቁኝ ከሚነሡብኝም ጠብቀኝ።

2ከክፉ አድራጊዎች ታደገኝ፤

ደም ከተጠሙ ሰዎችም አድነኝ።

3እነሆ በነፍሴ ላይ አድብተዋልና፤

እግዚአብሔር ሆይ፤ ጨካኞች ያለ በደሌ፣ ያለ ኀጢአቴ

በላዬ ተሰብስበው ዶለቱብኝ።

4እነርሱ ያለ በደሌ ሊያጠቁኝ ተዘጋጅተው መጡ፤

አንተ ግን ትረዳኝ ዘንድ ተነሥ፤ ሁኔታዬንም ተመልከት።

5የሰራዊት አምላክ የሆንህ፣ አንተ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፤

ሕዝቦችን ሁሉ ለመቅጣት ተነሥ፤

በተንኰላቸው በደል የሚፈጽሙትንም ሁሉ አትማራቸው። ሴላ

6እንደ ውሻ እያላዘኑ፣

በምሽት ተመልሰው ይመጣሉ፤

በከተማዪቱም ዙሪያ ይራወጣሉ።

7ከአፋቸው የሚወጣውን ተመልከት፤

ሰይፍ በከንፈራቸው ላይ አለ፤

“ማን ሊሰማን ይችላል?” ይላሉና።

8እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ ግን ትሥቅባቸዋለህ፤

ሕዝቦችን ሁሉ በንቀት ታያቸዋለህ።

9ብርታቴ ሆይ፤ አንተን እጠብቃለሁ፤

አምላክ ሆይ፤ አንተ መጠጊያዬ ነህና።

10እግዚአብሔር በምሕረቱ ይገናኘኛል፤

አምላኬ የጠላቶቼን ውድቀት ያሳየኛል።

11ጋሻችን59፥11 ወይም ልዑል ተብሎ መተርጐም ይችላል። ጌታ ሆይ፤ አትግደላቸው፤

አለዚያ ሕዝቤ ይረሳል፤

በኀይልህ አንከራትታቸው፤

ዝቅ ዝቅም አድርጋቸው።

12ከአፋቸው ስለሚወጣው ኀጢአት፣

ከከንፈራቸውም ስለሚሰነዘረው ቃል፣

በትዕቢታቸው ይያዙ።

ስለ ተናገሩት መርገምና ውሸት፣

13በቍጣ አጥፋቸው፤

ፈጽመህም አስወግዳቸው፤

በዚህም እግዚአብሔር የያዕቆብ ገዥ መሆኑ፣

እስከ ምድር ዳርቻ ይታወቃል። ሴላ

14እንደ ውሻ እያላዘኑ፣

በምሽት ተመልሰው ይመጣሉ፤

በከተማዪቱም ዙሪያ ይራወጣሉ።

15ምግብ ፍለጋ ይራወጣሉ።

ካልጠገቡም ያላዝናሉ።

16እኔ ግን ስለ ኀይልህ እዘምራለሁ፤

በማለዳም ስለ ምሕረትህ እዘምራለሁ፤

አንተ መጠጊያዬ፣

በመከራም ቀን ዐምባዬ ነህና።

17ብርታቴ ሆይ፤ ውዳሴ አቀርብልሃለሁ፤

እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ መጠጊያዬ፣

የምትወድደኝም አምላኬ ነህና።

Chinese Contemporary Bible (Traditional)

詩篇 59:1-17

第 59 篇

祈求上帝佑護

大衛作的詩,交給樂長,調用「休要毀壞」。當時掃羅派人去監視大衛的家,要殺害大衛。

1我的上帝啊,

求你救我脫離仇敵,

保護我免遭其害。

2求你救我脫離作惡之徒,

脫離嗜血成性之人。

3看啊,他們要暗害我。

耶和華啊,我並未犯罪作惡,

兇殘的人卻攻擊我。

4我沒有過錯,

他們卻準備攻擊我。

求你起來幫助我,

顧念我的困境。

5萬軍之耶和華,以色列的上帝啊,

求你起來懲罰列國,

不要姑息奸詐的惡人。(細拉)

6他們夜晚回來,

嚎叫如狗,在城中遊蕩。

7他們出口傷人,舌如利劍,

還說:「誰聽得見?」

8但你耶和華必嗤笑他們,

嘲諷列國。

9上帝啊,

你是我的力量,我的堡壘,

我仰望你。

10我的上帝愛我,

祂會幫助我,

讓我欣然看見仇敵遭報。

11保護我們的主啊,

求你不要殺掉他們,

免得我的百姓忘記教訓。

求你用你的能力驅散他們,

使他們淪為卑賤。

12他們的嘴巴充滿罪惡,

口中盡是咒詛和謊言,

願他們陷在狂傲中不能自拔。

13求你發烈怒毀滅他們,

徹底剷除他們,

使普天下都知道上帝在雅各家掌權。(細拉)

14他們夜晚回來,

嚎叫如狗,在城中遊蕩,

15四處覓食,

吃不飽就狂吠不止。

16但我要歌頌你的能力,

在清晨頌揚你的慈愛,

因為你是我的堡壘,

是我患難時的避難所。

17上帝啊,你是我的力量,

我要頌讚你,

你是我的堡壘,

是愛我的上帝。