መዝሙር 45 – NASV & JCB

New Amharic Standard Version

መዝሙር 45:1-17

መዝሙር 45

የንጉሣዊ ሰርግ መዝሙር

ለመዘምራን አለቃ፤ “በጽጌረዳ” ዜማ፤ የቆሬ ልጆች ትምህርት፤ የፍቅር መዝሙር45 የሥነ ጽሑፉን ቅርጽ ወይም የመዝሙሩን ሁኔታ የሚያሳይ ሊሆን ይችላል።

1ልቤ መልካም ሐሳብ አፈለቀ፤

የተቀኘሁትን ቅኔ ለንጉሥ አሰማለሁ፤

አንደበቴም እንደ ባለሙያ ጸሓፊ ብርዕ ነው።

2አንተ ከሰዎች ሁሉ ይልቅ ውብ ነህ፤

ከንፈሮችህም የጸጋ ቃል ያፈልቃሉ፤

ስለዚህ እግዚአብሔር ለዘላለም ባርኮሃል።

3ኀያል ሆይ፤ ሰይፍህን በወገብህ ታጠቅ፤

ግርማ ሞገስንም ተላበስ።

4ስለ እውነት፣ ስለ ትሕትና፣ ስለ ጽድቅ

ሞገስን ተጐናጽፈህ በድል አድራጊነት ገሥግሥ፤

ቀኝ እጅህም ድንቅ ተግባር ታሳይ።

5የሾሉ ፍላጻዎችህ በንጉሥ ጠላቶች ልብ ይሰካሉ፤

ሕዝቦችም ከእግርህ በታች ይወድቃሉ።

6አምላክ ሆይ፤ ዙፋንህ ከዘላለም እስከ ዘላለም ይኖራል፤

የመንግሥትህ በትር የቅንነት በትር ናት።

7ጽድቅን ወደድህ፤ ዐመፃን ጠላህ፤

ስለዚህ እግዚአብሔር አምላክህ፣

ከጓደኞችህ ይልቅ አንተን የደስታ ዘይት ቀባህ።

8ልብስህ ሁሉ በከርቤ፣ በአደስና በጥንጁት መዐዛ ያውዳል፤

በዝኆን ጥርስ ከተዋቡ ቤተ መንግሥቶችም፣

የበገናና የመሰንቆ ድምፅ ደስ ያሰኙሃል።

9ከተከበሩት ሴቶችህ መካከል የነገሥታት ሴቶች ልጆች ይገኛሉ፤

ንግሥቲቱም በኦፊር ወርቅ አጊጣ በቀኝህ ቆማለች።

10ልጄ ሆይ፤ አድምጪ፤ አስተውዪ፤ ጆሮሽንም አዘንብዪ፤

ሕዝብሽንና የአባትሽን ቤት እርሺ።

11ንጉሥ በውበትሽ ተማርኳል፤

ጌታሽ ነውና አክብሪው።

12የጢሮስ ሴት ልጅ እጅ መንሻ ይዛ ትመጣለች፤45፥12 ወይም፣ የጢሮሳውያን ልብሰ ተክህኖ ከስጦታዎቹ መካከል አለ

ሀብታሞችም ደጅ ይጠኑሻል።

13የንጉሥ ልጅ ከላይ እስከ ታች ተሸልማ እልፍኟ ውስጥ አለች፤

ልብሷም ወርቀ ዘቦ ነው።

14በጥልፍ ሥራ ባጌጠ ልብስ ወደ ንጉሥ ትወሰዳለች፤

ደናግል ጓደኞቿም ተከትለዋት፣

ወደ አንተ ይመጣሉ።

15በደስታና በሐሤት ወደ ውስጥ ይመሯቸዋል፤

ወደ ንጉሡም ቤተ መንግሥት ይገባሉ።

16ወንዶች ልጆችህ በአባቶችህ እግር ይተካሉ፤

ገዦችም አድርገሽ በምድር ሁሉ ትሾሚያቸዋለሽ።

17ስምሽን በትውልድ ሁሉ ዘንድ መታሰቢያ አደርጋለሁ፤

ስለዚህ ሕዝቦች ከዘላለም እስከ ዘላለም ያወድሱሃል።

Japanese Contemporary Bible

詩篇 45:1-17

45

1私の心は美しい思いであふれています。

さあ、うるわしい詩を王にささげましょう。

またたくまに物語をつづる詩人のように、

ことばがわき上がってくるのです。

2あなたはだれより美しい。

あなたのことばは優しさにあふれている。

あなたは永遠に神の祝福に包まれる人。

3力強い方よ、

威風堂々として、腰に剣を着けよ。

4威厳をまとい、勝ち進め。

真理と謙遜と正義のために、

恐るべきわざがなされるよう、粛清を推し進めよ。

5あなたの矢は鋭く、敵の胸に突き刺さる。

敵はあなたの目の前に倒れる。

6神の王座は永遠、神の笏は正義。

7真実を愛し、悪を憎むあなたに、

神は格別大きな喜びをお授けになった。

8あなたの服には

没薬、アロエ、シナモンの芳香がただよいます。

象牙をちりばめた宮殿では、

ここちよい音楽がかなでられています。

9諸王の娘があなたに仕える女たちに加わり、

王妃は、オフィル産の最高級の金の飾りを着け、

あなたのかたわらに立っています。

10-11「娘よ、私の忠告を聞きなさい。

遠い故国の父や母を思って悲しんではいけません。

あなたには王という夫があり、

王はあなたの美しさを喜んでおられます。

主人である王に、うやうやしく仕えなさい。

12当世で最も金回りのよいツロの人々が、

あなたの歓心を買おうと、

贈り物を山と積んで来るでしょう。」

13花嫁姿の王女は、金の糸で織った

美しい晴れ着をまとい、自室で控えています。

14侍女にかしずかれ、しずしずと王の前に出る、

その姿の美しいこと!

15王宮の門をくぐる行列は、

なんと楽しげで、うれしそうなのでしょう。

16「あなたから生まれる子どもは、

いつか父の跡を継いで王となり、世界を支配します。

17わたしはあなたの名を、のちの世までも輝かせます。

諸国民はいつまでも称賛してやまないでしょう。」