መዝሙር 147 – NASV & CARS

New Amharic Standard Version

መዝሙር 147:1-20

መዝሙር 147

መዝሙር ለሁሉን ቻይ አምላክ

1ሃሌ ሉያ።147፥1 አንዳንዶች ከ20 ጭምር እግዚአብሔር ይመስገን ይላሉ።

አምላካችንን በመዝሙር ማወደስ እንዴት መልካም ነው!

እርሱን ማመስገን ደስ ያሰኛል፤ ይህ ተገቢም ነው።

2እግዚአብሔር ኢየሩሳሌምን መልሶ ይሠራታል፤

ከእስራኤል የተበተኑትን ይሰበስባል።

3ልባቸው የተሰበረውን ይፈውሳል፤

ቍስላቸውንም ይጠግናል።

4የከዋክብትን ብዛት ያውቃል፤

እያንዳንዱንም በስሙ ይጠራዋል።

5ጌታችን ታላቅ ነው፤ እጅግ ኀያልም ነው፤

ለጥበቡም ወሰን የለውም።

6እግዚአብሔር ትሑታንን ከፍ ያደርጋል፤

ክፉዎችን ግን ወደ ምድር ይጥላል።

7ለእግዚአብሔር በምስጋና ዘምሩ፤

ለአምላካችንም በመሰንቆ ምስጋና አቅርቡ።

8ሰማይን በደመናት የሚሸፍን እርሱ ነው፤

ለምድርም ዝናብን ይሰጣል፤

በተራሮችም ላይ ሣር ያበቅላል።

9ለእንስሳት ምግባቸውን፣

የቍራ ጫጩቶችም ሲንጫጩ የሚበሉትን ይሰጣቸዋል።

10እርሱ በፈረስ ኀይል አይደሰትም፤

በሯጭም ብርታት ላይ ደስታውን አያደርግም።

11ነገር ግን እግዚአብሔር በሚፈሩት፣

በምሕረቱ በሚታመኑትም ይደሰታል።

12ኢየሩሳሌም ሆይ፤ እግዚአብሔርን አመስግኚ፤

ጽዮን ሆይ፤ አምላክሽን አወድሺ፤

13እርሱ የደጆችሽን መወርወሪያ አጽንቷልና፤

ልጆችሽንም በውስጥሽ ባርኳል።

14በድንበርሽ ውስጥ ሰላም ያሰፍናል፤

ማለፊያ ስንዴም ያጠግብሻል።

15ትእዛዙን ወደ ምድር ይልካል፤

ቃሉም እጅግ በፍጥነት ይሮጣል።

16ዐመዳዩን እንደ በርኖስ ይዘረጋል፤

ውርጩን እንደ ዐመድ ይነሰንሳል።

17የበረዶውን ድንጋይ ቍልቍል ይወረውረዋል፤

በውሽንፍሩስ ቅዝቃዜ ፊት ማን ሊቆም ይችላል?

18ቃሉን ልኮ ያቀልጣቸዋል፤ ነፋሱን ያነፍሳል፤ ውሆችንም ያፈስሳል።

19ቃሉን ለያዕቆብ፣

ሥርዐቱንና ፍርዱን ለእስራኤል ይገልጣል።

20ይህን ለማንኛውም ሌላ ሕዝብ አላደረገም፤

እነርሱም ፍርዱን አላወቁም።

ሃሌ ሉያ።

Священное Писание

Забур 147:1-9

Песнь 147Песнь 147 В тексте оригинала песни 146 и 147 объединены в одну песнь.

1Восхваляй, Иерусалим, Вечного;

восславь, Сион, своего Бога!

2Он укрепляет затворы твоих ворот

и благословляет твоих жителей.

3Он утверждает мир в твоих пределах

и насыщает тебя отборной пшеницей.

4Он посылает Своё слово на землю;

быстро бежит Его повеление.

5Он даёт снег, как белую шерсть,

сыплет иней, как пепел,

6бросает Свой град, словно камни.

Кто может устоять перед Его морозом?

7Он посылает Своё слово, и тает всё,

подует Своим ветром, и текут воды.

8Своё слово Он возвестил потомкам Якуба,

Свои установления и законы – Исраилу.

9Для других народов Он этого не сделал;

они не знают Его законов.

Славьте Вечного!