መዝሙር 126 – NASV & NUB

New Amharic Standard Version

መዝሙር 126:1-6

መዝሙር 126

የስደት ተመላሾች መዝሙር

መዝሙረ መዓርግ።

1እግዚአብሔር የጽዮንን ምርኮ126፥1 ወይም እግዚአብሔር ሀብቷን ይመልሳል። በመለሰ ጊዜ፣

ሕልም እንጂ እውን አልመሰለንም።126፥1 ወይም የሰዎቿ ጤንነት ይታደሳል።

2በዚያን ጊዜ አፋችን በሣቅ፣

አንደበታችንም በእልልታ ተሞላ፤

በዚያን ጊዜም በሕዝቦች መካከል፣

እግዚአብሔር ታላቅ ነገር አደረገላቸው” ተባለ።

3እግዚአብሔር ታላቅ ነገር አደረገልን፤

እኛም ደስ አለን።

4እግዚአብሔር ሆይ፤ በኔጌቭ እንዳሉ ጅረቶች፣

ምርኳችንን መልስ።126፥4 ወይም ሀብታችንን መልስ

5በእንባ የሚዘሩ፣

በእልልታ ያጭዳሉ።

6ዘር ቋጥረው፣

እያለቀሱ የተሰማሩ፣

ነዷቸውን ተሸክመው፣

እልል እያሉ ይመለሳሉ።

Swedish Contemporary Bible

Psaltaren 126:1-6

Psalm 126

Återställd lycka

1En vallfartssång.

När Herren förde tillbaka Sions fångar,

var det som om vi drömde.

2Vi skrattade högt och sjöng av glädje, vi jublade.

Bland folken sades det:

Herren har gjort stora ting för dem!”

3Ja, Herren har gjort stora ting med oss,

och vi är glada.

4Återställ vår lycka, Herre,

liksom bäckarna i Negev!

5De som sår med tårar

ska få skörda med glädje.

6Gråtande går de ut med säden de ska så,

men med jubel kommer de tillbaka och bär sina kärvar.