መዝሙር 107 – NASV & CARS

New Amharic Standard Version

መዝሙር 107:1-43

አምስተኛ መጽሐፍ

ከመዝሙር 107–150

መዝሙር 107

ከመከራ ሁሉ የሚታደግ አምላክ

1ቸር ነውና እግዚአብሔርን አመስግኑ፤

ምሕረቱም ለዘላለም ነውና።

2እግዚአብሔር የተቤዣቸው፣

ከጠላት እጅ የታደጋቸው ይህን ይበሉ፤

3ከምሥራቅና ከምዕራብ፣ ከሰሜንና ከደቡብ፣107፥3 ዕብራይስጡ ሰሜንና ባሕሩ ይለዋል።

ከየአገሩ የሰበሰባቸው እንዲህ ይናገሩ።

4አንዳንዶቹ ጭው ባለ በረሓ ተቅበዘበዙ፤

ወደሚኖሩባት ከተማ የሚያደርስ መንገድ ዐጡ።

5ተራቡ፤ ተጠሙ፤

ነፍሳቸውም በውስጣቸው ዛለች።

6በተጨነቁ ጊዜ ወደ እግዚአብሔር ጮኹ፤

እርሱም ከመከራቸው አዳናቸው።

7ወደሚኖሩባትም ከተማ፣

በቀና መንገድ መራቸው።

8እግዚአብሔርን ስለ ምሕረቱ፣

ለሰው ልጆችም ስላደረገው ድንቅ ሥራ ያመስግኑት፤

9እርሱ የተጠማችውን ነፍስ አርክቷልና፤

የተራበችውንም ነፍስ በበጎ ነገር አጥግቧል።

10አንዳንዶቹ በብረት ሰንሰለት ታስረው የተጨነቁ፣

በጨለማ፣ በጥልማሞት ውስጥ የተቀመጡ ነበሩ፤

11በእግዚአብሔር ቃል ላይ በማመፅ፣

የልዑልን ምክር አቃልለዋልና።

12ስለዚህ በጕልበት ሥራ ልባቸውን አዛለ፤

ተዝለፈለፉ፤ የሚደግፋቸውም አልነበረም።

13በተጨነቁ ጊዜ ወደ እግዚአብሔር ጮኹ፤

እርሱም ከመከራቸው አዳናቸው።

14ከጨለማና ከጥልማሞት አወጣቸው፤

እስራታቸውንም በጠሰላቸው።

15እግዚአብሔርን ስለ ምሕረቱ፣

ለሰው ልጆችም ስላደረገው ድንቅ ሥራ ያመስግኑት፤

16እርሱ የናሱን በሮች ሰብሯልና፤

የብረቱንም መወርወሪያ ቈርጧል።

17አንዳንዶቹ ከዐመፃቸው የተነሣ ቂሎች ሆኑ፤

ከበደላቸው የተነሣ ችግር ውስጥ ገቡ።

18ሰውነታቸው የምግብ ዐይነት ሁሉ ተጸየፈች፤

ወደ ሞትም ደጆች ቀረቡ።

19በተጨነቁ ጊዜ ወደ እግዚአብሔር ጮኹ፤

እርሱም ከመከራቸው አዳናቸው።

20ቃሉን ልኮ ፈወሳቸው፤

ከመቃብርም አፋፍ መለሳቸው።

21እግዚአብሔርን ስለ ምሕረቱ፣

ለሰው ልጆችም ስላደረገው ድንቅ ሥራ ያመስግኑት፤

22የምስጋናም መሥዋዕት ያቅርቡለት፤

ሥራውንም ደስ በሚል ዝማሬ ይግለጹ።

23አንዳንዶቹ በመርከብ ወደ ባሕር ወረዱ፤

በታላቅም ውሃ ላይ ሥራቸውን አከናወኑ፤

24የእግዚአብሔርን ሥራ በዚያ አዩ፤

ድንቅ አድራጎቱንም በጥልቁ ውስጥ ተመለከቱ።

25እርሱ ተናግሮ ዐውሎ ነፋስን አስነሣ፤

ነፋሱም ማዕበሉን ከፍ ከፍ አደረገ።

26ወደ ሰማይ ወጡ፤ ወደ ጥልቅም ወረዱ፤

ከመከራቸውም የተነሣ ሐሞታቸው ፈሰሰ።

27እንደ ሰከረ ሰው ዞሮባቸው ወዲያ ወዲህ ተንገዳገዱ፤

መላው ጠፍቶባቸው የሚያደርጉትን ዐጡ።

28በተጨነቁ ጊዜ ወደ እግዚአብሔር ጮኹ፤

እርሱም ከመከራቸው አዳናቸው።

29ዐውሎ ነፋሱን ጸጥ አደረገ፤

የባሕሩም ሞገድ ረጭ አለ።

30ጸጥ በማለቱም ደስ አላቸው፤

ወዳሰቡትም ወደብ አደረሳቸው።

31እግዚአብሔርን ስለ ምሕረቱ፣

ለሰው ልጆችም ስላደረገው ድንቅ ሥራ ያመስግኑት፤

32በሕዝብ ጉባኤ መካከል ከፍ ከፍ ያድርጉት፤

በሽማግሌዎችም ሸንጎ ይወድሱት።

33ወንዞችን ወደ ምድረ በዳ፣

የውሃ ምንጮችንም ወደ ደረቅ ምድር ለወጠ።

34ከነዋሪዎቿ ክፋት የተነሣ፣

ፍሬያማዋን ምድር በጨው የተበከለች አደረጋት።

35ምድረ በዳውን ወደ ውሃ መከማቻ፣

ደረቁንም ምድር ወደ ውሃ ምንጭ ቀየረ።

36የተራቡትን በዚያ አስቀመጠ፤

የሚኖሩባትንም ከተማ ሠሩ።

37በዕርሻውም ዘሩበት፤ ወይንም ተከሉ፤

ብዙ ፍሬም አመረቱ።

38ይባርካቸዋል፤ እነርሱም እጅግ ይበዛሉ፤

የከብቶቻቸውም ብዛት እንዲያንስ አያደርግም።

39በጭንቅ፣ በመከራና በሐዘን፣

ቍጥራቸው አንሶ፣ ተዋርደው ነበር፤

40በመኳንንቱም ላይ መናቅን አዘነበባቸው፤

መውጫ መግቢያው በማይታወቅ በረሓ ውስጥም አንከራተታቸው።

41ችግረኞችን ግን ከጭንቀታቸው መዝዞ አወጣቸው፤

ቤተ ሰባቸውንም እንደ በግ መንጋ አበዛ።

42ልበ ቅኖች ይህን አይተው ሐሤት ያደርጋሉ፤

ጥመትም ሁሉ አፏን ትዘጋለች።

43እንግዲህ ማንም ብልኅ ቢሆን፣ ይህን ነገር ልብ ይበል፤

እርሱም የእግዚአብሔርን ምሕረት ያስተውላል።

Священное Писание

Забур 107:1-14

Песнь 107

(Заб. 56:8-12; 59:7-14)

1Песнопение Давуда.

2Сердце моё твёрдо, Всевышний;

буду петь и славить Тебя всей душой.

3Пробудитесь, лира и арфа!

Я проснусь на заре.

4Восхвалю Тебя, Вечный, среди народов,

воспою Тебя среди племён,

5потому что милость Твоя превыше небес,

и верность Твоя достигает облаков.

6Выше небес будь превознесён, о Всевышний;

над всей землёй да будет слава Твоя!

7Сохрани нас Своей правой рукой и ответь нам,

чтобы спаслись возлюбленные Тобой.

8Всевышний обещал в Своём святилище:

«Я разделю, торжествуя, город Шехем

и долину Суккот размерю для Своего народа107:8 Шехем здесь представляет всю территорию на западе от реки Иордан, а долина Суккот – на востоке..

9Мой Галаад и Мой Манасса,

Ефраим – Мой шлем,

Иуда – Мой скипетр107:9 Галаад – земля на востоке от Иордана. Роду Манассы принадлежали земли как на востоке, так и на западе от реки, а родам Ефраима и Иуды – северная и южная части земли на западе от Иордана. Ефраим и Иуда были наиболее влиятельными родами в Исраиле, а шлем и скипетр символизируют их военную мощь и царскую власть (царь Давуд и его потомки были из рода Иуды)..

10Моав служит Мне умывальной чашей для ног,

Я предъявлю Свои права на Эдом107:10 Букв.: «Я брошу Свою сандалию на Эдом».,

над землёй филистимлян торжествующе воскликну».

11Кто приведёт меня в укреплённый город?

Кто доведёт меня до Эдома?

12Не Ты ли, Всевышний, Который нас отринул

и теперь не выходишь с войсками нашими?

13Окажи нам помощь в борьбе с врагом,

потому что людская помощь бесполезна.

14Со Всевышним мы одержим победу;

Он низвергнет наших врагов.