መሳፍንት 17 – NASV & CCB

New Amharic Standard Version

መሳፍንት 17:1-13

ሚካ ያሠራቸው ጣዖታት

1ሚካ የተባለ በኰረብታማው በኤፍሬም አገር የሚኖር ሰው ነበር። 2እናቱን፣ “አንድ ሺሕ አንድ መቶ ሰቅል17፥2 13 ኪሎ ግራም ያህል ነው። ብር ተሰርቆብሽ፣ የሰረቀውን ሰው ስትራገሚ ሰምቼሽ ነበር፤ ብሩ ከእኔ ዘንድ ይገኛል፤ የወሰድሁት እኔ ነኝ” አላት።

ከዚያም እናቱ፣ “ልጄ፤ እግዚአብሔር ይባርክህ” አለችው።

3አንድ ሺሕ አንድ መቶውን ሰቅል ብር በመለሰላት ጊዜ እናቱ፣ “ብሬን የተቀረጸ ምስልና ቀልጦ የተሠራ ጣዖት ለማበጀት ስለ ልጄ ለእግዚአብሔር እቀድሰዋለሁ፤ አሁንም ለአንተው መልሼ እሰጥሃለሁ” አለችው።

4ስለዚህ ብሩን ለእናቱ መለሰላት፤ እናቱም ከላዩ ሁለት መቶ ጥሬ17፥4 17፥4 2.3 ኪሎ ግራም ያህል ነው። ብር ወስዳ ለብር አንጥረኛ ሰጠች፤ አንጥረኛውም የተቀረጸ ምስልና ቀልጦ የተሠራ ጣዖት አደረገው፤ ምስሎቹም በሚካ ቤት ተቀመጡ።

5ሚካ የተባለው ይህ ሰው የአምልኮ ስፍራ ነበረው፤ አንድ ኤፉድና ተራፊም ሠርቶ ከልጆቹ አንዱን ካህን ሆኖ እንዲያገለግለው አደረገ። 6በዚያን ዘመን በእስራኤል ንጉሥ አልነበረም፤ እያንዳንዱ ሰው ለራሱ መልካም መስሎ የታየውን ያደርግ ነበር። 7በይሁዳ ምድር፣ በይሁዳ ነገድ መካከል በቤተ ልሔም የሚኖር አንድ ሌዋዊ ወጣት ነበር። 8ይህም ሰው ሌላ መኖሪያ ስፍራ ለመፈለግ ከተማዪቱን ለቆ ሄደ። በሚጓዝበትም17፥8 ወይም የዕለት ምግባሩን እያከናወነ ሳለ ጊዜ በኰረብታማው በኤፍሬም አገር ወዳለው ወደ ሚካ ቤት መጣ።

9ሚካም፣ “የየት አገር ሰው ነህ?” ሲል ጠየቀው።

እርሱም፣ “እኔ በይሁዳ ምድር ከምትገኝ ከቤተ ልሔም የመጣሁ ሌዋዊ ነኝ፤ መኖሪያ ስፍራ እፈልጋለሁ” አለው።

10ሚካም፣ “እንግዲያውስ አብረኸኝ ተቀመጥ፤ አባትም ካህንም ሁነኝ፤ እኔም በዓመት ዐሥር ሰቅል17፥10 110 ግራም ያህል ነው። ብር እንዲሁም ልብስና ምግብ እሰጥሃለሁ” አለው። 11ስለዚህ ሌዋዊው አብሮት ለመኖር ተስማማ፤ ወጣቱም ለሚካ ከልጆቹ እንደ አንዱ ሆነለት። 12ሚካም ሌዋዊውን ካህን አድርጎ አስቀመጠው፤ ወጣቱም ካህኑ ሆነ፤ በቤቱም ኖረ። 13ሚካም፤ “ይህ ሌዋዊ ካህን ለሆነልኝ፣ እግዚአብሔር በጎ ነገር እንደሚያደርግልኝ አሁን ተረዳሁ” አለ።

Chinese Contemporary Bible (Simplified)

士师记 17:1-13

米迦的神像

1以法莲山区住了一个名叫米迦的人。 2他对母亲说:“你那一千一百块银子丢了,我还听见你咒诅小偷。看啊,银子在我这里,是我拿去的。”他母亲说:“我儿啊,愿耶和华赐福给你!” 3米迦把一千一百块银子还给母亲。他母亲说:“我要为你把这些银子献给耶和华,用来雕刻、铸造神像。现在这银子还是你的。” 4米迦把银子还给母亲后,他母亲拿出二百块银子交给银匠雕刻、铸造神像,放在米迦的房子里。 5米迦有一个神庙,他制造了一件以弗得和一些家庭神像,并指派他的一个儿子做祭司。 6那时,以色列没有王,人人各行其是。

7犹大伯利恒住着一个年轻的利未人。 8他离开伯利恒想到别的地方居住,一路走到以法莲山区米迦的家。 9米迦问他:“你从哪里来?”他回答说:“我是从犹大伯利恒来的利未人,我要找一个住的地方。” 10米迦说:“你就住在我这里吧,做我的师父和祭司。我每年给你十块银子,还为你提供衣服和膳食。”利未人就进了米迦的家, 11住了下来。米迦待他就像待自己的儿子一样。 12这样,米迦派他做祭司,让他住在自己家里。 13米迦说:“现在我有一个利未人做我的祭司,耶和华一定会赐福给我。”