ሕዝቅኤል 45 – NASV & NIRV

New Amharic Standard Version

ሕዝቅኤል 45:1-25

የምድሪቱ አከፋፈል

1“ ‘ምድሪቱን ርስት አድርጋችሁ በዕጣ በምትከፋፈሉበት ጊዜ፣ ርዝመቱ ሃያ አምስት ሺሕ45፥1 ሰብዓ ሊቃናትም (በተጨማሪ 3፣ 5 እና 48፥9 ይመ) እንዲሁ ሲሆን፣ ዕብራይስጡ ግን ዐሥር ሺሕ ይላል። ክንድ፣ ወርዱ ሃያ ሺሕ ክንድ የሆነውን አንዱን ክፍል፣ ለእግዚአብሔር የተቀደሰ ስፍራ አድርጋችሁ ስጡ፤ ስፍራውም በሙሉ ቅዱስ ይሆናል፤ 2ከዚሁም አምስት መቶ ክንድ በአምስት መቶ ክንድ፣ ዙሪያው አምሳ ክንድ ባዶ ቦታ ቀርቶ፣ ለመቅደሱ ይሁን። 3ከተቀደሰውም ስፍራ ላይ ርዝመቱ ሃያ አምስት ሺሕ ክንድ፣ ወርዱም ዐሥር ሺሕ ክንድ ለካ፤ በዚህም ውስጥ መቅደሱ፣ ይኸውም ቅድስተ ቅዱሳኑ ይሆናል። 4ይህም በቤተ መቅደሱ ውስጥ ለሚያገለግሉና፣ በእግዚአብሔር ፊት ለአገልግሎት ለሚቀርቡ ካህናት፣ ቅዱስ የሆነ የምድሪቱ ክፍል ይሆናል። 5ርዝመቱ ሃያ አምስት ሺሕ ክንድ፣ ወርዱ ዐሥር ሺሕ ክንድ ስፋት ያለው ስፍራ መኖሪያ ከተሞቻቸውን እንዲከትሙ45፥5 ሰብዐ ሊቃናትም እንዲሁ ሲሆን፣ ዕብራይስጡ ግን በቤተ መቅደስ… ሃያ ክፍሎች በንብረትነት ይኖራቸዋል በቤተ መቅደስ ለሚያገለግሉ ሌዋውያን ርስት ይሆናል።

6“ ‘ከተቀደሰው ስፍራ ጋር የተያያዘ ወርዱ አምስት ሺሕ ክንድ፣ ርዝመቱ ሃያ አምስት ሺሕ ክንድ የሆነ ቦታ ለከተማዪቱ ርስት አድርገህ ስጥ፤ ይህም ለመላው የእስራኤል ቤት ይሆናል።

7“ ‘ገዥው ከቅዱሱ ስፍራና ከከተማው ወሰን ግራና ቀኝ ርስት ይኖረዋል፤ ይህም ከምዕራብ በኩል ወደ ምዕራብ አቅጣጫ ምሥራቅ በመዝለቅ፣ ከምዕራብ እስከ ምሥራቅ ያለውን ወሰን ርዝመት ተከትሎ ለአንዱ ነገድ ከተሰጠው ርስት ጋር ጐን ለጐን ይሄዳል። 8ይህም መሬት በእስራኤል ምድር የገዥው ርስት ይሆናል። ከእንግዲህ ገዥዎቼ ሕዝቤን አይጨቍኑም፤ ነገር ግን የእስራኤል ቤት በየነገዳቸው ርስት እንዲይዙ ይፈቅዱላቸዋል።

9“ ‘ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ የእስራኤል ገዦች ሆይ! ከልክ ዐልፋችኋል፤ ይብቃችሁ፤ ዐመፅንና ጭቈናን ተዉ፤ ቀናና ትክክል የሆነውን ነገር አድርጉ። የሕዝቤን ርስት መቀማት ይቅርባችሁ፤ ይላል ጌታ እግዚአብሔር10ትክክለኛ ሚዛን ትክክለኛ ኢፍና45፥10 ኢፍ የደረቅ ነገር መስፈሪያ ነው። ትክክለኛ ባዶስ45፥10 ባዶስ የፈሳሽ ነገር መለኪያ ነው። ይኑራችሁ። 11የኢፍና የባዶሱ መመዘኛ ተመሳሳይ ይሁን፤ አንድ ባዶስ የሆመር45፥11 ሆመር የደረቅ ነገር መስፈሪያ ነው። አንድ ዐሥረኛ እንዲሁም አንድ ኢፍ የሆመር አንድ ዐሥረኛ ይሆናል፤ ሆመር ለሁለቱም ሚዛኖች መደበኛ መለኪያ ነው። 12አንድ ሰቅል ሃያ ጌራህ የሚይዝ ይሆናል፤ በሃያ ሰቅል ላይ ሃያ አምስት ሰቅልና ዐሥራ አምስት ሰቅል ሲጨመር አንድ ምናን ይሆናል።

ልዩ ልዩ መሥዋዕትና በዓላት

13“ ‘የምታቀርቡት ልዩ መባ ይህ ነው፤ ከአንድ ሆመር መስፈሪያ ስንዴ አንድ ስድስተኛ ኢፍ እንዲሁም ከእያንዳንዱ ሆመር ገብስ አንድ ስድስተኛ ኢፍ ነው። 14ዘይቱ በባዶስ ሲለካ፣ የተወሰነው መስፈሪያ ከእያንዳንዱ ሆመር አንድ ዐሥረኛ ባዶስ ይሆናል፤ ይኸውም ዐሥር ባዶስ ወይም አንድ ሆመር ነው፤ ዐሥር ባዶስ ከአንድ ሆመር ጋር እኩል ነውና። 15እንዲሁም ውሃ ከጠገበው ከእስራኤል መሰማሪያ፣ ሁለት መቶ በግ ካለው ከእያንዳንዱ መንጋ አንድ በግ ይውሰድ። ይህ ሁሉ ለሕዝቡ ማስተስረያ ለሚሆነው ለእህል ቍርባን፣ ለሚቃጠል መሥዋዕትና ለኅብረት መሥዋዕት45፥15 በትውፊት የድነት መሥዋዕት ይባላል። ይውላል፤ ይላል ጌታ እግዚአብሔር16የምድሪቱ ሕዝብ ሁሉ ይህን ልዩ መባ ለእስራኤል ገዥ ይሰጣሉ። 17በበዓላት፣ በወር መባቻና በሰንበታት፣ ለእስራኤል ቤት በተወሰኑት በዓላት ሁሉ የሚቃጠል መሥዋዕት፣ የእህል ቍርባንና የመጠጥ ቍርባን ማቅረብ የገዥው ኀላፊነት ነው፤ ለእስራኤል ቤት ማስተስረያ እንዲሆንም የኀጢአት መሥዋዕት፣ የእህል ቍርባን፣ የሚቃጠል መሥዋዕትና የኅብረት መሥዋዕት ያቀርባል።’

18“ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘በመጀመሪያው ወር፣ በመጀመሪያው ቀን ነውር የሌለበትን ወይፈን ውሰድ፤ መቅደሱንም አንጻው። 19ካህኑም ከኀጢአቱ መሥዋዕት ደም በመውሰድ በቤተ መቅደሱ በር መቃኖች፣ በመሠዊያው ላይኛው ዕርከን አራት ማእዘንና በውስጠኛው አደባባይ በር መቃኖች ላይ ይርጨው። 20አንድ ሰው ሳያስብ ወይም ባለማወቅ ኀጢአት ቢሠራ፤ ወር በገባ በሰባተኛው ቀን ይህን ታደርጋለህ፤ በዚህ ዐይነት ለቤተ መቅደሱ ታስተሰርያላችሁ።

21“ ‘በመጀመሪያው ወር በዐሥራ አራተኛው ቀን የፋሲካን በዓል ታከብራላችሁ፤ ይህም እርሾ የሌለበትን እንጀራ የምትበሉበት ሰባት ቀን የሚከበር በዓል ነው። 22በዚያም ቀን ገዥው ስለ ራሱና ስለ ምድሪቱ ሕዝብ ሁሉ አንድ ወይፈን የኀጢአት መሥዋዕት አድርጎ ያቀርባል። 23በዓሉ በሚከበርበት በሰባቱ ቀን ገዥው በየዕለቱ እንከን የሌለባቸውን ሰባት ወይፈኖችና ሰባት አውራ በጎች የሚቃጠል መሥዋዕት አድርጎ ለእግዚአብሔር ያቅርብ፤ በየዕለቱም ለኀጢአት መሥዋዕት አውራ ፍየል ያቅርብ። 24ለአንዱ ወይፈን አንድ የኢፍ መስፈሪያ፣ ለአንድ አውራ በግ አንድ የኢፍ መስፈሪያ የእህል ቍርባን አድርጎ፣ ለእያንዳንዱም ኢፍ አንድ የኢን መስፈሪያ ዘይት አብሮ ያቅርብ።

25“ ‘በሰባተኛው ወር በዐሥራ አምስተኛው ቀን በሚጀመረው በሰባቱ ቀን በዓል፣ ለኀጢአት መሥዋዕት፣ ለሚቃጠል መሥዋዕት፣ ለእህል ቍርባንና ለዘይቱም እንዲሁ ያቅርብ።

New International Reader’s Version

Ezekiel 45:1-25

The Lord Establishes Israel Again

1“People of Israel, you will divide up the land you will receive. When you do, give me my share of it. It will be a sacred area. It will be eight miles long and six and a half miles wide. The entire area will be holy. 2The temple area in it will be 875 feet long and 875 feet wide. An 88-foot strip around it will be open land. 3In the sacred area, measure off a large strip of land. It will be eight miles long and three and a third miles wide. The temple will be in it. It will be the most holy place of all. 4The large strip will be the sacred share of land for the priests. There they will serve in the temple. And they will approach me to serve me there. Their houses will be built on that land. The holy temple will also be located there. 5So the Levites will serve in the temple. They will have an area eight miles long and three and a third miles wide. The towns they live in will be located there.

6“Give the city an area one and two-thirds miles wide and eight miles long. It will be right next to the sacred area. It will belong to all the people of Israel.

7“The prince will have land on both sides of the sacred area and the city. Its border will run east and west along the land of one of the tribes. 8The prince will own this land in Israel. And my princes will not crush my people anymore. Instead, they will allow the people of Israel to receive their own share of land. It will be divided up based on their tribes.”

9The Lord and King says, “Princes of Israel, you have gone far enough! Stop hurting others. Do not crush them. Do what is fair and right. Stop taking my people’s land away from them,” announces the Lord and King. 10“Use weights and measures that are honest and exact. 11Use the same standard to measure dry and liquid products. Use a 6-bushel measure for dry products. And use a 60-gallon measure for liquids. 12Every amount of money must be weighed out in keeping with the standard weights.

13“You must offer a special gift. It must be six pounds out of every six bushels of grain. 14Give two and a half quarts out of every 60 gallons of olive oil. 15Also give one sheep from every flock of 200 sheep. Get them from the grasslands of Israel that receive plenty of water. Use them for grain offerings, burnt offerings and friendship offerings. They will be used to pay for the sin of the people,” announces the Lord and King. 16“All the people in the land will be required to give this special gift. They must give it to the prince in Israel. 17He must provide the burnt offerings, grain offerings and drink offerings. They will be for the yearly feasts, New Moon feasts and Sabbath days. So they will be for all the appointed feasts of the people of Israel. The prince will provide the sin offerings, grain offerings, burnt offerings and friendship offerings. They will be used to pay for the sin of the Israelites.”

18The Lord and King says, “Get a young bull. It must not have any flaws. Use it to make the temple pure and ‘clean.’ Do this on the first day of the first month. 19The priest must get some of the blood from the sin offering. He must put some on the doorposts of the temple. He must apply some to the four corners of the upper ledge of the altar. He must put the rest on the gateposts of the inner courtyard. 20Do the same thing on the seventh day of the month. Do this for those who sin without meaning to. And do this for those who sin without realizing what they are doing. So you will make the temple pure and ‘clean.’

21“Keep the Passover Feast on the 14th day of the first month. It will last for seven days. During that time you must eat bread made without yeast. 22The prince must provide a bull as a sin offering. It will be for him and all the people of the land. 23For each of the seven days of the feast he must provide seven bulls and seven rams. They must not have any flaws. They will be a burnt offering to me. The prince must also provide a male goat for a sin offering. 24He must bring 35 pounds for each bull or ram. He must also provide four quarts of olive oil for each of them.

25“The seven days of the feast begin on the 15th day of the seventh month. During those days the prince must provide the same sin offerings, burnt offerings, grain offerings and olive oil.”