ሕዝቅኤል 13 – NASV & CCBT

New Amharic Standard Version

ሕዝቅኤል 13:1-23

የሐሰተኛ ነቢያት መወገዝ

1የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፤ 2“የሰው ልጅ ሆይ፤ ትንቢት በሚናገሩት በእስራኤል ነቢያት ላይ ትንቢት ተናገር፤ ከገዛ ራሳቸው ትንቢት የሚናገሩትን እንዲህ በላቸው፤ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ፤ 3ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘አንዳች ነገር ሳያዩ የራሳቸውን መንፈስ ለሚከተሉ ሞኞች13፥3 ወይም ክፉዎች ነቢያት ወዮላቸው! 4እስራኤል ሆይ፤ ነቢያትሽ በፍርስራሽ መካከል እንደሚኖሩ ቀበሮዎች ናቸው። 5በእግዚአብሔር ቀን በሚሆነው ጦርነት ጸንቶ መቆም እንዲችል፣ የተሰነጠቀውን ቅጥር ለእስራኤል ቤት ለመጠገን ወደዚያ አልወጣችሁም። 6ራእያቸው ሐሰት፣ ትንቢታቸው ውሸት ነው፤ እግዚአብሔር ሳይልካቸው፣ “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል” ይላሉ፤ ይህም ሆኖ የተናገሩት ይፈጸማል ብለው ይጠብቃሉ። 7እኔ ሳልናገር፣ “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል” ስትሉ ሐሰተኛ ራእይ ማየታችሁ፣ ውሸተኛስ ትንቢት መናገራችሁ አይደለምን?

8“ ‘ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ቃላችሁ ሐሰት፣ ራእያችሁም ውሸት ስለሆነ እኔ በእናንተ ላይ ተነሥቻለሁ፤ ይላል ጌታ እግዚአብሔር9እጄ የሐሰት ራእይ በሚያዩና በሚያሟርቱ ነቢያት ላይ ተነሥቷል። የሕዝቤ ጉባኤ ተካፋይ አይሆኑም፤ በእስራኤል ቤት መዝገብ አይጻፉም፤ ወደ እስራኤልም ምድር አይገቡም። በዚያ ጊዜ እኔ ጌታ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ።”

10“ ‘ሰላም ሳይኖር፣ “ሰላም አለ” እያሉ ሕዝቤን ያስታሉ፤ ሕዝቡ ካብ ሲሠራ እነርሱ በኖራ ይለስናሉ፤ 11ስለዚህ በኖራ ለሚለስኑት ካቡ እንደሚወድቅ ንገራቸው። ዶፍ ይወርዳል፤ ታላቅ የበረዶ ድንጋይ እሰድዳለሁ፤ ዐውሎ ነፋስም ይነሣል። 12እነሆ ካቡ ሲፈርስ ሕዝቡ “የለሰናችሁበት ኖራው ወዴት ሄደ?” ብለው አይጠይቋችሁምን?

13“ ‘ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ በመዓቴ ዐውሎ ነፋስ እሰድዳለሁ፣ በቍጣዬ የበረዶ ድንጋይ እልካለሁ፤ ዶፍም ከታላቅ ጥፋት ጋር ይወርዳል። 14በኖራ የለሰናችሁትን ካብ አፈርሳለሁ፤ መሠረቱም ተገልጦ እስኪታይ ድረስ ከምድር ጋር አደባልቀዋለሁ። ቅጥሩ13፥14 ወይም ከተማው በሚወድቅበት ጊዜ፣ እናንተም በውስጡ ታልቃላችሁ። በዚያን ጊዜ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ። 15መዓቴንም በቅጥሩና ኖራ በለሰኑት ሰዎች ላይ እሰድዳለሁ፤ እናንተንም እንዲህ እላችኋለሁ፤ “ቅጥሩና ቅጥሩን በኖራ የለሰኑት የሉም፤ 16ኢየሩሳሌም ትንቢት የተናገሩላትና ሰላም ሳይኖር የሰላም ራእይ ያዩላት የእስራኤል ነቢያት ጠፍተዋል”፤ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።’

17“አሁንም የሰው ልጅ ሆይ፤ ከራሳቸው አመንጭተው ትንቢት ወደሚናገሩ ወደ ሕዝብህ ሴቶች ልጆች ፊትህን መልስ፤ ትንቢትም ተናገርባቸው፤ 18እንዲህም በል፤ ‘ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “የሕዝብን ነፍስ ለማጥመድ፣ ለአስማታቸው ለእጃቸው አንጓ ሁሉ አሸንክታብ ለሚያሰፉና፣ የተለያየ መጠን ያለውን የራስ መሸፈኛ ለሚያበጁ ሴቶች ወዮላቸው! በውኑ የሕዝቤን ነፍስ እያጠመዳችሁ የራሳችሁን ነፍስ ታድናላችሁን? 19ዕፍኝ ለማይሞላ ገብስና ለቍራሽ እንጀራ ስትሉ ሐሰትን የሚያደምጥ ሕዝቤን እየዋሻችሁ መሞት የማይገባውን በመግደል፣ መኖር የማይገባውንም በማትረፍ በሕዝቤ መካከል አርክሳችሁኛል።”

20“ ‘ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “እነሆ የሕዝብን ነፍስ እንደ ወፍ በምታጠምዱበት አሸንክታብ ላይ ተነሥቻለሁ፤ ከክንዳችሁ ላይ እቀዳድደዋለሁ፤ እንደ ወፍ የምታጠምዱትንም ሕዝብ ነጻ አወጣዋለሁ። 21መሸፈኛችሁን ቀድጄ ሕዝቤን ከእጃችሁ አድናለሁ፤ ከእንግዲህም ወዲህ በቍጥጥራችሁ ሥር አይሆኑም፤ በዚያ ጊዜ፣ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ። 22እኔ ያላሳዘንሁትን ጻድቅ በውሸት ስላሳዘናችሁ፣ ኀጢአተኛም ከክፉ መንገዱ ተመልሶ ሕይወቱን እንዳያድን በኀጢአቱ ስላበረታታችሁት፣ 23ከእንግዲህ የሐሰት ራእይ አታዩም፣ ሟርትም አታሟርቱም፤ ሕዝቤን ከእጃችሁ አድናለሁ፤ በዚያ ጊዜ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ።” ’ ”

Chinese Contemporary Bible (Traditional)

以西結書 13:1-23

斥責假先知

1耶和華對我說: 2「人子啊,你要說預言斥責以色列那些說預言的先知,告訴那些私自發預言的人,『你們要聽耶和華的話。 3主耶和華說,愚頑的先知有禍了!他們沒有看到異象,卻私自發預言。 4以色列人啊,你們的先知像廢墟中的狐狸, 5沒有上去堵住缺口,也沒有重建以色列的圍牆,使以色列在耶和華的日子來臨時的爭戰中堅立。 6他們的異象虛假不實,他們的預言謊話連篇。他們口口聲聲說是傳達耶和華的話,其實耶和華並沒有差遣他們。他們竟然指望自己的謊言能夠應驗。 7難道你們不是見了虛假的異象,說了虛謊的預言嗎?你們說這是耶和華說的,其實我並沒有說。』」

8所以主耶和華說:「因為你們的假異象和謊言,我要攻擊你們。這是主耶和華說的。 9我必動手攻擊那些見假異象、說假預言的先知。他們必從我的子民當中被剔除,不被收錄在以色列人的名冊上,也不能進入以色列的土地。這樣,你們就知道我是主耶和華。 10因為他們欺騙我的子民說,『平安!』其實並沒有平安,就像有人築了一道薄牆,用白灰加以粉飾。 11所以,你要警告那些粉刷白灰的人,說,『牆必倒塌,暴雨要來臨,冰雹勢必降下,狂風也必大作。』 12牆倒塌之後,一定會有人問,『你們粉飾的白灰在哪裡呢?』 13主耶和華說,『我必在烈怒中用狂風暴雨和冰雹來摧毀這牆, 14我必把你們粉飾的牆夷為平地,使其露出根基。牆倒塌的時候,你們必葬身其中。這樣,你們就知道我是耶和華。 15我要向這牆和粉飾這牆的人發怒,懲罰他們。我告訴你們,這牆完了!粉飾這牆的人也完了!』 16他們就是那些向耶路撒冷說假預言,在沒有平安的時候宣稱看到了平安異象的以色列先知。這是主耶和華說的。」

17「人子啊,你要說預言斥責你同胞中私自發預言的女子, 18告訴她們主耶和華這樣說,『你們這些婦女有禍了!你們為了獵取人命,給人縫製戴在手腕上的符咒和各種尺寸的頭巾。你們獵取我子民的性命,還想保住自己的性命嗎? 19你們為了幾把大麥和幾塊餅,在我的子民中褻瀆我,向那些肯聽謊言的說謊,殺死那些不該死的,救活那些不該活的。』

20「所以主耶和華說,『你們用符咒獵取人命如同捕鳥,我要除去你們的符咒,從你們手臂上扯掉它們,釋放你們所獵取的人。 21我還要撕去你們的頭巾,把我的子民從你們手中拯救出來,使他們不再做你們手中的獵物。這樣,你們就知道我是耶和華。 22我沒有使義人憂傷,你們卻以謊言叫他們灰心。你們慫恿惡人不要改邪歸正,以致他們喪命。 23因此,你們必不再見假異象,也不再占卜。我必從你們手中拯救我的子民。這樣,你們就知道我是耶和華。』」