ሕዝቅኤል 11 – NASV & CCBT

New Amharic Standard Version

ሕዝቅኤል 11:1-25

በእስራኤል መሪዎች ላይ የተላለፈ ፍርድ

1መንፈስም ወደ ላይ አነሣኝ፤ ከዚያም በምሥራቅ በኩል ወዳለው ወደ እግዚአብሔር ቤት በር አመጣኝ። በበሩም መግቢያ ላይ ሃያ አምስት ሰዎች ነበሩ፤ በእነርሱም መካከል የሕዝቡን መሪዎች የዓዙርን ልጅ ያእዛንያንና የበናያስን ልጅ ፈላጥያንን አየሁ። 2እግዚአብሔርም እንዲህ አለኝ፤ “የሰው ልጅ ሆይ፤ እነዚህ ሰዎች ክፋትን የሚያቅዱና በዚህችም ከተማ ላይ ተንኰልን የሚመክሩ ናቸው። 3እነርሱም፣ ‘ቤቶች የሚሠሩበት ጊዜ ቅርብ አይደለምን?11፥3 ወይም ቤቶችን ለመሥራት ጊዜው አሁን አይደለም ይህች ከተማ ድስት ናት፤ እኛም ሥጋ ነን’ ብለዋል። 4ስለዚህ ትንቢት ተናገርባቸው፤ የሰው ልጅ ሆይ፤ ትንቢት ተናገር።”

5የእግዚአብሔርም መንፈስ በላዬ ወረደ፤ እንዲህም አለኝ፤ “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘የእስራኤል ቤት ሆይ፤ እናንተ እንዲህ ብላችኋል፤ እኔ ግን የልባችሁን ሐሳብ ዐውቃለሁ። 6በዚህች ከተማ ብዙ ሰው ገድላችኋል፤ መንገዶቿንም ሬሳ በሬሳ አድርጋችኋል።’

7“ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ በዚያ የጣላችኋቸው ሬሳዎች እነርሱ ሥጋ ናቸው፤ ይህችም ከተማ ድስት ናት፤ እናንተን ግን ከውስጧ አወጣችኋለሁ። 8ሰይፍን ፈርታችኋል፤ እኔም ሰይፍ እልክባችኋለሁ፤ ይላል ጌታ እግዚአብሔር9ከከተማዪቱ አውጥቼ ለባዕዳን አሳልፌ እሰጣችኋለሁ፤ ፍርድንም አመጣባችኋለሁ። 10በሰይፍ ትወድቃላችሁ፤ በእስራኤል ድንበር ላይ እፈርድባችኋለሁ፤ በዚያ ጊዜም እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ። 11ይህች ከተማ ድስት አትሆንላችሁም፤ እናንተም በውስጧ ሥጋ አትሆኑም፤ በእስራኤልም ድንበር ላይ እፈርድባችኋለሁ፤ 12በዚያ ጊዜ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ፤ እናንተ በዙሪያችሁ ያሉትን አሕዛብ ሥርዐት ተከተላችሁ እንጂ ትእዛዜን አልፈጸማችሁም ሕጌንም አልጠበቃችሁምና።”

13ትንቢት እየተናገርሁ ሳለ፣ የበናያስ ልጅ ፈላጥያ ሞተ፤ እኔም በግንባሬ ተደፍቼ፣ “ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፣ ወዮ! የእስራኤልን ቅሬታ ፈጽመህ ታጠፋለህን?” በማለት በታላቅ ድምፅ ጮኽሁ።

14የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፤ 15“የሰው ልጅ ሆይ፤ ወንድሞችህ፣ የራስህ ዘመዶችና11፥15 ወይም በምርኮ ከአንተ ጋር የነበሩና (ሰብዐ ሊቃናትና ሱርስትን ይመ) የእስራኤል ቤት ሁሉ፤ ‘ከእግዚአብሔር ርቀዋል፤ ይህች ምድር ርስት ሆና ለእኛ ተሰጥታናለች’ ብለው የኢየሩሳሌም ነዋሪዎች የተናገሩባቸው ናቸው።11፥15 ወይም የኢየሩሳሌም ሰዎች የተናገሩባቸው፣ ከእግዚአብሔር ራቁ

የእስራኤል የመመለስ ተስፋ

16“ስለዚህ እንዲህ በል፤ ‘ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ በአሕዛብ መካከል ብሰድዳቸውም፤ በአገሮች መካከል ብበታትናቸውም፣ በሄዱባቸው አገሮች ሁሉ ለጥቂት ጊዜ መቅደስ ሆኜአቸዋለሁ’ ”።

17“ስለዚህ እንዲህ በል፤ ‘ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ከአሕዛብ መካከል እሰበስባችኋለሁ፤ ከተበተናችሁባቸው አገሮች እመልሳችኋለሁ፤ የእስራኤልንም ምድር እንደ ገና እሰጣችኋለሁ።’

18“ወደዚያ በተመለሱ ጊዜ የረከሱ ምስሎቿንና ጸያፍ ተግባሯን ያስወግዳሉ። 19የማያወላውል ልብ እሰጣቸዋለሁ፤ አዲስ መንፈስ በውስጣቸው አኖራለሁ፤ ድንጋዩን ልብ ከውስጣቸው አወጣለሁ፤ ሥጋ ልብም እሰጣቸዋለሁ። 20ስለዚህ ትእዛዜን ይፈጽማሉ፤ ሕጌን ይጠብቃሉ። እነርሱ ሕዝቤ ይሆናሉ፤ እኔም አምላካቸው እሆናለሁ። 21ነገር ግን ልባቸው ወደ ረከሱ ምስሎቻቸውና ወደ ጸያፍ ተግባራቸው ያዘነበለውን እንደ ሥራቸው እከፍላቸዋለሁ፤ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።”

22ኪሩቤልም ክንፎቻቸውን ዘረጉ፤ መንኰራኵሮቹም በአጠገባቸው ነበሩ፤ የእስራኤልም አምላክ ክብር በላያቸው ላይ ነበር። 23የእግዚአብሔርም ክብር ከከተማዪቱ ውስጥ ተነሥቶ ወጣ፤ ከከተማዪቱም በስተ ምሥራቅ ካለው ተራራ በላይ ቆም አለ። 24መንፈስም ወደ ላይ አነሣኝ፤ በእግዚአብሔርም መንፈስ በተሰጠው ራእይም በባቢሎን11፥24 ወይም ከለዳውያን ምድር ወደ ነበሩት ምርኮኞች አመጣኝ።

ከዚያም ያየሁት ራእይ ከእኔ ወጥቶ ሄደ፤ 25እኔም እግዚአብሔር ያሳየኝን ነገር ሁሉ ለምርኮኞቹ ተናገርሁ።

Chinese Contemporary Bible (Traditional)

以西結書 11:1-25

審判以色列的首領

1那時,靈將我舉起,帶我到耶和華殿的東門,我見那裡有二十五個人,當中有百姓的首領押朔的兒子雅撒尼亞比拿雅的兒子毗拉提2耶和華對我說:「人子啊,這些人在這城裡專給人出毒計,設惡謀。 3他們說,『建造房屋的時候不是到了嗎?我們的城像鐵鍋一樣堅固,我們像在鍋裡的肉一樣得到保護。』 4人子啊,你要說預言,說預言斥責他們。」

5耶和華的靈降在我身上,並吩咐我說:「耶和華這樣說,『以色列人啊,我知道你們口中在說什麼,心裡在想什麼。 6你們在城中殺人無數,大街小巷遍地屍體。 7所以,主耶和華說,你們在城中殺死的人就是肉,這城就是鍋,但我必把你們從鍋中拉出來。 8你們懼怕刀劍,我必使刀劍臨到你們。這是主耶和華說的。 9我必把你們從城中趕出去,交給外族人。我必懲罰你們, 10使你們死於刀下。我要審判整個以色列,這樣你們就知道我是耶和華。 11這城必不是你們的鍋,你們也必不是其中的肉,我必在全以色列施行審判。 12這樣你們就知道我是耶和華。因為你們沒有遵行我的律例,沒有順從我的典章,卻效法你們四鄰外族的規矩。』」

13我正在說預言的時候,比拿雅的兒子毗拉提就死了。我便俯伏在地大喊:「唉,主耶和華啊,你要滅絕以色列的餘民嗎?」

14耶和華對我說: 15「人子啊,留在耶路撒冷的居民會這樣談論你、你的親人和一切被擄的以色列人,說,『他們遠離了耶和華,這地方已經給了我們。』 16因此,你要說,『主耶和華這樣說,我雖然把以色列人趕到遠方各國,分散在列邦,卻要在他們所去的國家暫作他們的聖所。』

17「你要說,『主耶和華這樣說,我必從各國召集你們,從你們被驅散到的列邦中聚集你們,將以色列再賜給你們。』 18他們回來後,必除掉一切醜惡可憎的事。 19我必賜給他們一顆專一的心,將新靈放在他們裡面,除去他們的石心,賜給他們肉心, 20使他們恪守我的律例,謹遵我的典章。他們將做我的子民,我將做他們的上帝。 21至於那些心裡戀慕醜惡可憎之物的人,我必按他們所行的報應他們。這是主耶和華說的。」

22於是,基路伯天使展開翅膀,輪子跟在他們旁邊,在他們上面有以色列上帝的榮耀。 23耶和華的榮耀從城中升起,停在城東的山上。 24靈將我舉起,在異象中把我帶到迦勒底被擄的人那裡,我所見的異象從我面前上升消失了。 25我把耶和華讓我看到的一切都告訴了那些被擄的人。