New Amharic Standard Version

ገላትያ 6:1-18

ለሰው ሁሉ በጎ ማድረግ

1ወንድሞች ሆይ፤ አንድ ሰው በኀጢአት ውስጥ ገብቶ ቢገኝ፣ መንፈሳውያን የሆናችሁ እናንተ በገርነት ልትመልሱት ይገባል። ነገር ግን አንተም እንዳትፈተን ራስህን ጠብቅ። 2አንዱ የሌላውን ከባድ ሸክም ይሸከም፤ በዚህም ሁኔታ የክርስቶስን ሕግ ትፈጽማላችሁ። 3አንድ ሰው ምንም ሳይሆን ትልቅ የሆነ ቢመስለው ራሱን ያታልላል። 4እያንዳንዱ የራሱን ተግባር ይመርምር፤ ከዚያም በኋላ፣ ከሌላ ሰው ጋር ራሱን ሳያወዳድር፣ ስለ ራሱ የሚመካበትን ያገኛል፤ 5እያንዳንዱ የራሱን ሸክም ሊሸከም ይገባዋልና።

6ማንም ቃሉን የሚማር፣ መልካም የሆነውን ነገር ሁሉ ከመምህሩ ጋር ይካፈል።

7አትታለሉ፤ እግዚአብሔር አይዘበትበትም። ሰው የሚዘራውን ያንኑ ያጭዳል። 8ሥጋዊ ምኞቱን ለማርካት የሚዘራ፣ ከሥጋ6፥8 ወይም ኀጢአተኛ ተፈጥሮ ለማርካት የሚዘራ፣ ከዚሁ ተፈጥሮ ጥፋትን ያጭዳል፤ መንፈስን ለማስደሰት የሚዘራ ግን ከመንፈስ የዘላለምን ሕይወት ያጭዳል። 9በጎ ነገር ከማድረግ አንታክት፤ ተስፋ ካልቈረጥን ጊዜው ሲደርስ መከሩን እናጭዳለን። 10ስለዚህ ዕድሉ ካለን ለሰው ሁሉ፣ በተለይም ለእምነት ቤተ ሰቦች መልካም እናድርግ።

አዲስ ፍጥረት መሆን

11እንዴት ባሉ ታላላቅ ፊደላት በእጄ እንደ ጻፍሁላችሁ ተመልከቱ።

12ውጫዊ በሆነ ነገር ለመታየት የሚፈልጉ ሰዎች ትገረዙ ዘንድ ሊያስገድዷችሁ ይጥራሉ፤ ይህንም የሚያደርጉት ስለ ክርስቶስ መስቀል እንዳይሰደዱ ነው። 13እነርሱ በሥጋችሁ ለመመካት ሲሉ እንድትገረዙ ፈለጉ እንጂ፣ የተገረዙት ራሳቸው እንኳ ሕግን የሚጠብቁ አይደሉም። 14ነገር ግን ዓለም ለእኔ ከተሰቀለበት፣ እኔም ለዓለም ከተሰቀልሁበት ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል በቀር፣ ሌላው ትምክሕት ከእኔ የራቀ ይሁን። 15መገረዝም ሆነ አለመገረዝ አይጠቅምም፤ የሚጠቅመው አዲስ ፍጥረት መሆን ነው። 16ይህን ትእዛዝ በሚከተሉ ሁሉ፣ የእግዚአብሔር በሆነው እስራኤልም ላይ ሰላምና ምሕረት ይሁን።

17እኔ የኢየሱስን ምልክት በሥጋዬ ተሸክሜአለሁና፣ ከእንግዲህ ወዲህ ማንም አያስቸግረኝ። 18ወንድሞች ሆይ፤ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ከመንፈሳችሁ ጋር ይሁን፤ አሜን።

Thai New Contemporary Bible

กาลาเทีย 6:1-18

ทำดีต่อคนทั้งปวง

1พี่น้องทั้งหลาย หากใครถูกจับได้ว่าทำบาป ท่านที่อยู่ฝ่ายจิตวิญญาณควรช่วยเขาอย่างสุภาพอ่อนโยนให้เขากลับตั้งตัวใหม่ แต่จงระวังตัวท่านเอง มิฉะนั้นท่านเองจะถูกล่อลวงให้ทำบาปไปด้วย 2จงช่วยรับภาระของกันและกัน ทำดังนี้แล้วท่านก็ได้ปฏิบัติตามบทบัญญัติของพระคริสต์ 3หากผู้ใดคิดว่าตนสำคัญทั้งๆ ที่ไม่สำคัญ ผู้นั้นก็หลอกตัวเอง 4แต่ละคนควรสำรวจการกระทำของตนเองจึงจะมีข้อภาคภูมิใจในตัวเอง โดยไม่ต้องเอาตัวไปเปรียบเทียบกับคนอื่น 5เพราะว่าแต่ละคนต้องแบกภาระของตัวเอง

6ผู้ที่รับคำสั่งสอนจงแบ่งสิ่งดีทั้งปวงแก่ผู้สอน

7อย่าหลงเลย ท่านไม่อาจหลอกลวงพระเจ้า ใครหว่านอะไรย่อมเก็บเกี่ยวสิ่งนั้น 8ผู้ที่หว่านเพื่อวิสัยบาปของเขาจะเก็บเกี่ยวความพินาศจากวิสัยนั้น6:8 หรือเพื่อเนื้อหนังของเขาจะเก็บเกี่ยวความพินาศจากเนื้อหนังของเขา ส่วนผู้ที่หว่านเพื่อพระวิญญาณจะเก็บเกี่ยวชีวิตนิรันดร์จากพระวิญญาณ 9อย่าให้เราอ่อนล้าในการทำดี เพราะถ้าเราไม่ย่อท้อ เราก็จะเก็บเกี่ยวในเวลาอันเหมาะสม 10เหตุฉะนั้นเมื่อมีโอกาส ให้เราทำดีต่อคนทั้งปวง โดยเฉพาะอย่างยิ่งต่อคนที่อยู่ในครอบครัวแห่งความเชื่อ

ไม่ใช่เข้าสุหนัตแต่รับการทรงสร้างใหม่

11ดูเถิด ข้าพเจ้าใช้ตัวอักษรขนาดใหญ่เพียงไร เมื่อเขียนถึงท่านด้วยมือของข้าพเจ้าเอง!

12บรรดาผู้ที่อยากสร้างความประทับใจแต่เพียงเปลือกนอกพยายามบังคับให้ท่านเข้าสุหนัต เพียงเพื่อหลีกเลี่ยงไม่ให้ตนเองถูกข่มเหงเพราะเรื่องไม้กางเขนของพระคริสต์ 13แม้แต่คนที่เข้าสุหนัตแล้วยังไม่เชื่อฟังบทบัญญัติ แต่พวกเขาต้องการให้ท่านเข้าสุหนัตจะได้อวดอ้างเนื้อหนังของท่าน 14ขออย่าให้ข้าพเจ้าอวดอะไรเว้นแต่ไม้กางเขนขององค์พระเยซูคริสต์เจ้าของเรา โดยไม้กางเขนนั้น6:14 หรือโดยผู้นั้น โลกถูกตรึงไว้จากข้าพเจ้าแล้วและข้าพเจ้าถูกตรึงไว้จากโลกแล้ว 15เข้าสุหนัตหรือไม่เข้าสุหนัตก็ไม่มีความหมาย ความสำคัญอยู่ที่การได้รับการทรงสร้างใหม่ 16สันติสุขและพระเมตตาคุณจงมีแก่คนทั้งปวงที่ทำตามกฎนี้ คือแก่ชนอิสราเอลของพระเจ้า

17สุดท้ายนี้อย่าให้ใครมาก่อความเดือดร้อนแก่ข้าพเจ้า เพราะข้าพเจ้ามีเครื่องหมายของพระเยซูอยู่บนกายของข้าพเจ้า

18พี่น้องทั้งหลาย ขอให้พระคุณขององค์พระเยซูคริสต์เจ้าของเราดำรงอยู่กับวิญญาณจิตของท่านทั้งหลายเถิด อาเมน