New Amharic Standard Version

ዮናስ 1:1-17

ዮናስ ከእግዚአብሔር ኰበለለ

1የእግዚአብሔር ቃል ወደ አማቴ ልጅ ወደ ዮናስ እንዲህ ሲል መጣ፤ 2“ወደ ታላቂቱ ከተማ ወደ ነነዌ ሄደህ፣ በእርሷ ላይ ስበክ፤ ክፋቷ በእኔ ፊት ወጥቶአልና።”

3ዮናስ ግን ከእግዚአብሔር ፊት ኰበለለ፤ ወደ ተርሴስም ለመሄድ ተነሣ። ወደ ኢዮጴ ወረደ፣ ወደዚያው ወደ ተርሴስ የምትሄድ መርከብም አገኘ። የጒዞውንም ዋጋ ከከፈለ በኋላ፣ ከእግዚአብሔር ፊት ወደ ተርሴስ ለመኰብለል በመርከቢቱ ተሳፈረ። 4እግዚአብሔርም በባሕሩ ላይ ታላቅ ነፋስን ላከ፤ ከባድ ማዕበልም ተነሥቶ መርከቢቱን አንገላታት፤ ልትሰበርም ተቃረበች። 5መርከበኞቹ ሁሉ ፈሩ፤ እያንዳንዱም ሰው ወደ አምላኩ ጮኸ፤ የመርከቢቱም ክብደት እንዲቀል፣ በውስጧ የነበረውን ዕቃ ወደ ባሕሩ ጣሉት።

ዮናስ ግን ወደ መርከቢቱ ታችኛ ክፍል ወርዶ ተኛ፤ በከባድም እንቅልፍ ላይ ነበር። 6የመርከቢቱም አዛዥ ወደ እርሱ ሄዶ፣ “እንዴት ትተኛለህ? ተነሥና አምላክህን ጥራ እንጂ፤ ምናልባትም ያስበንና ከጥፋት ያድነን ይሆናል” አለው።

7ከዚያም መርከበኞቹ እርስ በርሳቸው፣ “ይህ ክፉ ነገር በማን ምክንያት እንደ መጣብን ለማወቅ፣ ኑ፣ ዕጣ እንጣጣል” ተባባሉ። ዕጣም ተጣጣሉ፤ ዕጣውም በዮናስ ላይ ወደቀ።

8ከዚያም፣ “ይህ ሁሉ አስጨናቂ ነገር በማን ምክንያት እንደ መጣብን ንገረን፤ ሥራህ ምንድን ነው? ከወዴትስ መጣህ? አገርህስ የት ነው? ከየትኛውስ ሕዝብ ነህ?” አሉት።

9እርሱም፣ “እኔ ዕብራዊ ነኝ፤ የብስንና ባሕርን የፈጠረውን፣ የሰማይን አምላክ እግዚአብሔርን አመልካለሁ” አለ።

10እርሱ አስቀድሞ ነግሮአቸው ስለ ነበር፣ ከእግዚአብሔር እንደ ኰበለለ ዐወቁ፣ ስለዚህም በሁኔታው በመደንገጥ፣ “ይህ ያደረግኸው ምንድን ነው?” አሉት።

11የባሕሩም ማዕበል እጅግ እየበረታ ስለሄደ፣ “ባሕሩ ጸጥ እንዲልልን በአንተ ላይ ምን ብናደርግ ይሻላል?” አሉት።

12እርሱም፣ “ይህ ታላቅ ማዕበል በእኔ ምክንያት እንደ መጣባችሁ ዐውቃለሁ፤ አንሥታችሁ ወደ ባሕሩ ጣሉኝ፤ ባሕሩም ጸጥ ይላል” አላቸው።

13ሰዎቹ ግን ባላቸው ኀይል እየቀዘፉ ወደ የብስ ለመጠጋት ሞከሩ፤ ይሁን እንጂ አልቻሉም፤ ባሕሩ የባሰ ይናወጥ ነበርና። 14እግዚአብሔር ሆይ፤ እባክህ በዚህ ሰው ነፍስ ምክንያት አታጥፋን፤ የዚህ ንጹሕ ሰው ደምም በእኛ ላይ አይሁን፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ የወደድኸውን አድርገሃልና” ብለው ወደ እግዚአብሔር ጮኹ። 15ከዚያም ዮናስን ይዘው ወደ ባሕሩ ጣሉት፤ ባሕሩም ከመናወጥ ጸጥ አለ። 16ሰዎቹም እግዚአብሔርን እጅግ ፈሩ፤ ለእግዚአብሔር መሥዋዕትም አቀረቡ፤ ለእርሱም ስእለትን ተሳሉ።

17እግዚአብሔር ግን ዮናስን የሚውጥ ትልቅ ዓሣ አዘጋጀ፤ ዮናስም በዓሣው ሆድ ውስጥ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት አደረ።

Thai New Contemporary Bible

โยนาห์ 1:1-17

โยนาห์หนีจากองค์พระผู้เป็นเจ้า

1พระดำรัสจากองค์พระผู้เป็นเจ้ามาถึงโยนาห์บุตรอามิททัยว่า 2“จงไปยังนีนะเวห์นครใหญ่ เทศนาตักเตือนกรุงนั้นเพราะความชั่วช้าของเขากระฉ่อนขึ้นมาต่อหน้าเรา”

3แต่โยนาห์หนีจากองค์พระผู้เป็นเจ้ามุ่งหน้าไปยังเมืองทารชิช เขาเดินทางไปที่ยัฟฟาและพบเรือที่จะไปเมืองนั้น จึงจ่ายค่าโดยสารแล้วขึ้นเรือจะไปทารชิช เพื่อหนีจากองค์พระผู้เป็นเจ้า

4แล้วองค์พระผู้เป็นเจ้าทรงบันดาลให้เกิดพายุใหญ่เหนือทะเล พายุโหมกระหน่ำจนเรือแทบจะอับปางอยู่รอมร่อ 5ลูกเรือทั้งหมดกลัวมาก ต่างก็ร้องเรียกให้เทพเจ้าของตนมาช่วย และโยนสินค้าทิ้งไปเพื่อให้เรือเบาลง

ส่วนโยนาห์นอนหลับสนิทอยู่ในห้องข้างในเรือ 6นายเรือไปหาเขาและพูดว่า “ท่านหลับอยู่ได้อย่างไร? จงลุกขึ้นมาอ้อนวอนให้พระเจ้าของท่านช่วย! เผื่อพระองค์จะทรงพระกรุณา เราจะได้รอดตาย”

7แล้วลูกเรือทั้งหลายพูดกันว่า “ให้เรามาจับสลากดูว่าใครเป็นตัวการทำให้เกิดภัยพิบัติครั้งนี้” เขาจึงจับสลากกันและสลากนั้นตกแก่โยนาห์

8เขาก็ถามโยนาห์ว่า “บอกเรามาเถิดว่าใครเป็นต้นเหตุสร้างความเดือดร้อนให้เราในครั้งนี้? ท่านทำอะไร? มาจากที่ไหน? อยู่ประเทศอะไร? เป็นคนชาติไหน?”

9โยนาห์ตอบว่า “ข้าพเจ้าเป็นชาวฮีบรู นับถือพระยาห์เวห์พระเจ้าแห่งฟ้าสวรรค์ผู้ทรงสร้างทะเลและแผ่นดิน”

10พวกเขาฟังแล้วตกใจมากและถามว่า “ท่านทำอะไรลงไป?” (พวกเขารู้ว่าโยนาห์หลบหนีองค์พระผู้เป็นเจ้ามา เพราะโยนาห์เล่าให้ฟังก่อนหน้านี้แล้ว)

11ทะเลยิ่งปั่นป่วนขึ้นทุกทีๆ พวกเขาจึงถามโยนาห์ว่า “เราควรทำอย่างไรกับท่านดีทะเลจึงจะสงบ?”

12โยนาห์ตอบว่า “จับข้าพเจ้าโยนลงทะเลเถิด แล้วทะเลก็จะสงบ ข้าพเจ้ารู้ว่าที่เกิดพายุรุนแรงครั้งนี้ก็เพราะข้าพเจ้าผิดเอง”

13คนเหล่านั้นพยายามกรรเชียงพาเรือเข้าฝั่ง แต่ทำไม่ได้ เพราะทะเลยิ่งปั่นป่วนมากขึ้นไปอีก 14พวกเขาจึงร้องทูลต่อองค์พระผู้เป็นเจ้าว่า “โอ องค์พระผู้เป็นเจ้าขออย่าให้พวกเราต้องตายเพราะเอาชีวิตชายผู้นี้เลย อย่าให้เราต้องรับโทษที่ฆ่าคนที่ไม่มีความผิดเลย ข้าแต่องค์พระผู้เป็นเจ้า เพราะพระองค์เองทรงกระทำไปตามที่ทรงเห็นชอบ” 15แล้วพวกเขาก็จับโยนาห์โยนลงจากเรือ ทะเลที่ปั่นป่วนก็สงบราบเรียบ 16คนทั้งหลายจึงยำเกรงองค์พระผู้เป็นเจ้ายิ่งนัก เขาถวายเครื่องบูชาแด่องค์พระผู้เป็นเจ้าและถวายปฏิญาณต่อพระองค์

17แต่องค์พระผู้เป็นเจ้าทรงใช้ปลาใหญ่มากลืนโยนาห์เข้าไป และโยนาห์อยู่ในท้องปลาสามวันสามคืน