New Amharic Standard Version

ዘፍጥረት 49:1-33

ያዕቆብ ልጆቹን ባረከ

49፥1-28 ተጓ ምብ – ዘዳ 33፥1-29

1ከዚህ በኋላ ያዕቆብ ልጆቹን ሁሉ አስጠርቶ እንዲህ አላቸው፤ “በኋለኛው ዘመን ምን እንደሚደርስባችሁ እነግራችሁ ዘንድ ተሰብሰቡ።

2“እናንተ የያዕቆብ ልጆች ሆይ፤

ተሰብሰቡና ስሙ፤

አባታችሁ እስራኤልንም አድምጡ፤

3“ሮቤል፣ አንተ የበኵር ልጄ ነህ፤

ኀይሌና የጒብዝናዬም መጀመሪያ፤

በክብር ትልቃለህ በኀይልም

ትበልጣለህ።

4እንደ ውሃ የዋለልህ ነህና እልቅና

አይኖርህም፤

የአባትህን መኝታ ደፍረሃል፤

ምንጣፌንም አርክሰሃል።

5ስምዖንና ሌዊ ወንድማማቾች፣

ሰይፎቻቸው49፥5 በዕብራይስጥ የዚህ ቃል ትርጒም አይታወቅም የዐመፅ መሣሪያዎች ናቸው።

6ወደ ሸንጎአቸው አልግባ፤

ጉባኤያቸው ውስጥ አልገኝ፤

በቍጣ ተነሣሥተው ሰዎችን ገድለዋል፤

የበሬዎችንም ቋንጃ እንዳሻቸው ቈራርጠዋል።

7እጅግ አስፈሪ የሆነ ቍጣቸው፣

ጭከና የተሞላ ንዴታቸው የተረገመ ይሁን፤

በያዕቆብ እበትናቸዋለሁ፤

በመላው እስራኤልም አሠራጫቸዋለሁ።

8“ይሁዳ፣49፥8 ይሁዳ የሚለው ቃል ውዳሴ የሚል ትርጒም ካለው የዕብራይስጥ ቃል የመጣ ሲሆን፣ ከዚሁ ቃል ጋር አንድ ዐይነት ድምፅ አለው ወንድሞችህ ይወድሱሃል፤

እጅህም የጠላቶችህን ዐንገት ዐንቆ ይይዛል፤

የአባትህ ልጆች በፊትህ ተደፍተው ይሰግዱልሃል።

9“አንተ የአንበሳ ደቦል ይሁዳ፤

ከዐደንህ የምትመለስ ልጄ፣

እንደ አንበሳ ያደፍጣል፤ በምድርም ላይ ይተኛል፤

እንደ እንስት አንበሳም ያደባል፤

ታዲያ ማን ሊቀሰቅሰው ይደፍራል?

10በትረ መንግሥት ከይሁዳ እጅ አይወጣም፤

የገዥነት ምርኵዝም ከእግሮቹ መካከል።

ገዥነት የሚገባው እስኪመጣ ድረስ፣49፥10 ወይም ሴሎ እስኪመጣ ድረስ ወይም ክብር የሚገባው እስኪመጣ ድረስ

ሕዝቦች ሁሉ ይታዘዙታል።

11አህያውን በወይን ግንድ፣

ውርንጫውንም በምርጡ የወይን ሐረግ

ቅርንጫፍ ላይ ያስራል፤

ልብሱን በወይን ጠጅ፣

መጐናጸፊያውንም በወይን ጭማቂ ያጥባል።

12ዐይኖቹ ከወይን ጠጅ የቀሉ፣

ጥርሶቹም ከወተት ይልቅ የነጡ ይሆናሉ።

13“ዛብሎን፣ በባሕር ዳር ይኖራል፤

የመርከቦች መጠጊያም ይሆናል፤

ወሰኑም እስከ ሲዶና ይደርሳል።

14“ይሳኮር፣ ዐጥንተ ብርቱ አህያ፣

በጭነት49፥14 ወይም በሰፈር ሜዳ የሚነድ እሳት መካከል የሚተኛ፣

15ማረፊያ ቦታው መልካም፣

ምድሪቱም አስደሳች መሆኗን ሲያይ፣

ትከሻውን ለሸክም ያመቻቻል፤

ተገድዶም ያገለግላል።

16“ዳን፣49፥16 ዳን ማለት ፍትሕ ይሰጣል ማለት ነው ከእስራኤል ነገዶች እንደ አንዱ ሆኖ፣

በራሱ ሕዝብ ላይ ይፈርዳል።

17ዳን የመንገድ ዳር እባብ፣

የመተላለፊያም መንገድ እፉኝት ነው፤

ጋላቢው የኋሊት እንዲወድቅ፣

የፈረሱን ሰኮና ይነክሳል።

18እግዚአብሔር ሆይ (ያህዌ)፤ ማዳንህን እጠባበቃለሁ።

19“ጋድን49፥19 ጋድ ማለት ማጥቃት እንዲሁም ወራሪ ሰራዊት ማለት ነው ወራሪዎች አደጋ ይጥሉበታል፤

እርሱ ግን ዱካቸውን ተከታትሎ ብድሩን ይመልሳል።

20“አሴር ማእደ ሰፊ ይሆናል፤

ለነገሥታትም የሚስማማ ምግብ ያቀርባል።

21“ንፍታሌም ነጻ እንደ ተለቀቀች፣

የሚያማምሩም ግልገሎች49፥21 ወይም ነጻ፤ ውብ ቃሎችን የሚናገር

እንደምትወልድ ሚዳቋ ነው።

22ዮሴፍ፤ ፍሬያማ የወይን ተክል፣

በምንጭ ዳር የተተከለ ወይን ነው።

ሐረጎቹ ቅጥርን ያለብሳሉ።49፥22 ወይም ዮሴፍ የዱር የፈረስ ግልገል፣ በምንጭ ዳር ያለ የፈረስ ግልገል፣ በባለ ዕርከን ኰረብታ ላይ የዱር አህያ ነው

23ቀስተኞች በጭካኔ አጠቁት፤

በጥላቻም ነደፉት።

24ነገር ግን በያዕቆብ ኀያል አምላክ ክንድ፣49፥23-24 ወይም ቀስተኞች ያጠቃሉ … ያስፈነጥራሉ … ይኖራሉ … ይቈያሉ

እረኛው በሆነው በእስራኤል ዐለት፣ ቀስቱ ጸና፤

ጠንካራ ክንዱም ቀለጠፈ።

25አንተን በሚረዳህ በአባትህ አምላክ፣

በሚባርክህ፣ ሁሉን ማድረግ በሚችል አምላክ፣49፥25 ዕብራይስጡ ሻዳይ ይለዋል

ከላይ ከሰማይ በሚገኝ ረድኤት፣

ከምድር ጥልቅ በሚገኝ በረከት፣

ከማሕፀንና ከጡት በሚገኝ ምርቃት ይባርክሃል።

26ከጥንት ተራሮች በረከት፣

ከዘላለም ኰረብቶች ምርቃት ይልቅ፣

የአባትህ በረከት ይበልጣል፤49፥26 … ከአያት ቅድማያቶቼ … ታላቅ ነው

ይኸ ሁሉ በዮሴፍ ራስ ላይ ይውረድ፤

በወንድሞቹ መካከል አለቃ በሆነውም ግንባር ላይ ይረፍ።49፥26 ወይም ከ … የተለየ

27ብንያም፣ ነጣቂ ተኵላ ነው፤

ያደነውን ማለዳ ይበላል፤

የማረከውን ማታ ይከፋፈላል።

28እነዚህ ሁሉ ዐሥራ ሁለቱ የእስራኤል ነገዶች ናቸው። ይህም እያንዳንዳቸውን ተገቢ በሆነው በረከት አባታቸው ሲባርካቸው የተናገረው ቃል ነው።

የያዕቆብ መሞት

29ከዚህ በኋላ ያዕቆብ እንዲህ ሲል አዘዛቸው፤ “እነሆ፤ ወደ ወገኖቼ የምሰበሰብበት ጊዜ ደርሶአል፤ በኬጢያዊው በኤፍሮን ዕርሻ ውስጥ ባለችው ዋሻ ከአባቶቼ ዘንድ ቅበሩኝ፤ 30ይህ በከነዓን ምድር፣ በመምሬ አጠገብ፣ በማክፌላ ዕርሻ ውስጥ ያለው ዋሻ፣ የመቃብር ቦታ እንዲሆን አብርሃም ከኬጢያዊው ኤፍሮን ላይ ከነዕርሻ ቦታው የገዛው ነው። 31በዚያ አብርሃምና ሚስቱ ሣራ ተቀብረዋል፤ በዚያ ይስሐቅና ሚስቱ ርብቃ ተቀብረዋል፤ 32እኔም ልያን የቀበርኋት እዚያው ነው። ዕርሻውና ዋሻው የተገዙት ከኬጢያውያን49፥32 ወይም ከኬጢ ልጆች ላይ ነው።”

33ያዕቆብ እነዚህን ቃላት ለልጆቹ ተናግሮ እንዳበቃ፣ እግሮቹን በዐልጋው ላይ ሰብስቦ፣ የመጨረሻ ትንፋሹን ተነፈሰ፤ ወደ ወገኖቹም ተሰበሰበ።

Persian Contemporary Bible

پيدايش 49:1-33

آخرين سخنان يعقوب

1آنگاه يعقوب همهٔ پسرانش را نزد خود فرا خواند و به ايشان گفت: «دور من جمع شويد تا به شما بگويم كه در آينده بر شما چه خواهد گذشت. 2ای پسران يعقوب به سخنان پدر خود اسرائيل گوش دهيد.

3«رئوبين، تو پسر ارشد من و فرزند اوايل جوانی من هستی. تو از لحاظ مقام و قدرت از همه برتر می‌باشی، 4ولی چون امواج سركش دريا، خروشانی. پس از اين ديگر برتر از همه نخواهی بود، زيرا با يكی از زنان من نزديكی نموده، مرا بی‌حرمت كردی.

5«شمعون و لاوی، شما مثل هم هستيد، مردانی بی‌رحم و بی‌انصاف. 6من هرگز در نقشه‌های پليد شما شريک نخواهم شد، زيرا از روی خشم خود انسانها را كُشتيد و خودسرانه رگ پاهای گاوان را قطع كرديد. 7لعنت بر خشم شما كه اينچنين شديد و بی‌رحم بود. من نسل شما را در سراسر سرزمين اسرائيل پراكنده خواهم ساخت.

8«ای يهودا، برادرانت تو را ستايش خواهند كرد. تو دشمنانت را منهدم خواهی نمود. 9يهودا مانند شير بچه‌ای است كه از شكار برگشته و خوابيده است. كيست كه جرأت كند او را بيدار سازد؟ 10عصای سلطنت از يهودا دور نخواهد شد تا شيلو كه همهٔ قومها او را اطاعت می‌كنند، بيايد. 11الاغ خود را به بهترين درخت انگور خواهد بست و جامهٔ خود را در شراب خواهد شست. 12چشمان او تيره‌تر از شراب و دندانهايش سفيدتر از شير خواهد بود.

13«زبولون در سواحل دريا ساكن خواهد شد و بندری برای كشتيها خواهد بود و مرزهايش تا صيدون گسترش خواهد يافت.

14«يساكار حيوان باركش نيرومندی است كه زير بار خود خوابيده است. 15وقتی ببيند جايی كه خوابيده دلپسند است، تن به كار خواهد داد و چون برده‌ای به بيگاری كشيده خواهد شد.

16«دان قبيلهٔ خود را چون يكی از قبايل اسرائيل داوری خواهد كرد. 17او مثل مار بر سر راه قرار گرفته، پاشنه اسبان را نيش خواهد زد تا سوارانشان سرنگون شوند. 18خداوندا، منتظر نجات تو می‌باشم.

19«جاد مورد حملهٔ غارتگران واقع خواهد شد، اما او بر آنها هجوم خواهد آورد.

20«اشير سرزمينی حاصلخيز خواهد داشت و از محصول آن برای پادشاهان خوراک تهيه خواهد كرد.

21«نفتالی غزالی است آزاد كه بچه‌های زيبا به وجود می‌آورد.

22«يوسف درخت پرثمريست در كنار چشمهٔ آب كه شاخه‌هايش به اطراف سايه افكنده است. 23دشمنان بر او هجوم آوردند و با تيرهای خود به او صدمه زدند. 24ولی خدای قادر يعقوب يعنی شبان و پناهگاه اسرائيل بازو و كمان آنها را شكسته است. 25باشد كه خدای قادر مطلق، خدای پدرت، تو را ياری كند و از بركات آسمانی و زمينی بهره‌مند گرداند و فرزندان تو را زياد سازد. 26بركت پدر تو عظيم‌تر از وفور محصولات کوههای قديمی است. تمام اين بركات بر يوسف كه از ميان برادرانش برگزيده شد، قرار گيرد.

27«بنيامين گرگ درنده‌ای است كه صبحگاهان دشمنانش را می‌بلعد و شامگاهان آنچه را كه به غنيمت گرفته است، تقسيم می‌نمايد.»

28اين بود بركات يعقوب به پسران خود كه دوازده قبيلهٔ اسرائيل را به وجود آوردند.

مرگ يعقوب

29‏-30سپس يعقوب چنين وصيت كرد: «من بزودی می‌ميرم و به اجداد خود می‌پيوندم. شما جسد مرا به كنعان برده، در كنار پدرانم در غار مكفيله كه مقابل ممری است دفن كنيد. ابراهيم آن را با مزرعه‌اش از عفرون حيتّی خريداری نمود تا مقبره خانوادگی‌اش باشد. 31در آنجا ابراهيم و همسرش ساره، اسحاق و همسر وی ربكا دفن شده‌اند. ليه را هم در آنجا به خاک سپردم. 32پدربزرگم ابراهيم آن غار و مزرعه‌اش را برای همين منظور از حيتّی‌ها خريد.»

33پس از آنکه يعقوب اين وصيت را با پسرانش به پايان رساند، بر بستر خود دراز كشيده، جان سپرد و به اجداد خود پيوست.