New Amharic Standard Version

ዘፍጥረት 41:1-57

የፈርዖን ሕልም

1ድፍን ሁለት ዓመት ካለፈ በኋላ ፈርዖን ሕልም ዐለመ፤ በሕልሙም፣ በዐባይ ወንዝ ዳር ቆሞ ነበር፤ 2እነሆ መልቸው ያማረ፣ ሥጋቸው የወፈረ ሰባት ላሞች ከወንዙ ወጥተው በወንዙ ዳር የበቀለውን ሣር ይበሉ ጀመር። 3ቀጥሎም መልካቸው የከፋ ዐጥንታቸው የወጣ፣ ሌሎች ሰባት ላሞች ከወንዙ ወጥተው አስቀድመው ከወጡት ላሞች አጠገብ ቆሙ። 4እነዚህ መልካቸው የከፋና ዐጥንታቸው የወጣ ላሞች፣ እነዚያን ያማሩና የወፈሩ ላሞች ሲውጡአቸው አየ፤ ከዚያም ፈርዖን ከእንቅልፉ ነቃ።

5ፈርዖንም እንደ ገና እንቅልፍ ወስዶት ሳለ፣ ሌላ ሕልም አየ። በሕልሙም በአንድ የእህል አገዳ ላይ፣ ፍሬያቸው የተንዠረገገና ያማረ ሰባት የእሸት ዛላዎች ሲወጡ አየ። 6ከዚያም የቀጨጩና በምሥራቅ ነፋስ ተመትተው የደረቁ ሰባት የእሸት ዛላዎች ወጡ። 7የቀጨጩት የእሸት ዛላዎች፣ ፍሬያቸው የተንዠረገገውን ሰባቱን ያማሩ ዛላዎች ዋጡአቸው። በዚህ ጊዜ ፈርዖን ከእንቅልፉ ነቃ፤ ነገሩ ሕልም ነበር።

8በነጋታውም ፈርዖን መንፈሱ ታወከበት፤ ስለዚህ በግብፅ አገር ያሉትን አስማተኞችና ጥበበኞች በሙሉ አስጠርቶ ሕልሞቹን ነገራቸው፣ ይሁን እንጂ ሕልሞቹን ሊተረጒምለት የቻለ አንድም ሰው አልተገኘም።

9በዚያን ጊዜ የመጠጥ አሳላፊዎች አለቃ ፈርዖንን እንዲህ አለው፤ “የሠራሁት በደል ዛሬ ታወሰኝ። 10በአንድ ወቅት ፈርዖን እኔንና የእንጀራ ቤት አዛዡን ተቈጥቶ በዘበኞቹ አለቃ ግቢ አስሮን ነበር። 11ሁለታችንም በአንዲት ሌሊት የተለያየ ሕልም አየን፤ የእያንዳንዳችንም ሕልም የየራሱ ትርጒም ነበረው። 12በዚያን ጊዜ የዘበኞች አለቃ አገልጋይ የሆነ አንድ ዕብራዊ ወጣት ከእኛ ጋር እስር ቤት ነበር። ሕልማችንን በነገርነው ጊዜ፣ ፍቺውን ነገረን፤ ለእያንዳንዳችንም እንደ ሕልማችን ተረጐመልን፤ 13ነገሩም ልክ እርሱ እንደ ተረጐመልን ሆነ፤ እኔ ወደ ቀድሞ ሹመቴ ተመለስሁ፤ የእንጀራ ቤት አዛዡም ተሰቀለ41፥13 ወይም ተወጋ

14ፈርዖን ዮሴፍን እንዲያመጡት ትእዛዝ ሰጠ፤ ከእስር ቤትም በጥድፊያ ይዘውት መጡ፤ ጠጒሩንም ከተላጨና ልብሱን ከለወጠ በኋላ ፈርዖን ፊት ቀረበ።

15ፈርዖንም ዮሴፍን፣ “ሕልም አይቼ ነበር፤ ሕልሜን ሊተረጒምልኝ የቻለ አንድም ሰው አልተገኘም፤ አንተ ግን ሕልም ሲነገርህ የመተርጐም ችሎታ እንዳለህ ሰማሁ” አለው።

16ዮሴፍም ፈርዖንን፣ “እኔ የመተርጐም ችሎታ የለኝም፤ ነገር ግን እግዚአብሔር (ኤሎሂም) ለፈርዖን የሚሻውን ትርጒም ይሰጠዋል” አለው።

17ከዚህ በኋላ ፈርዖን ዮሴፍን እንዲህ አለው፤ “በሕልሜ በአባይ ወንዝ ዳር ቆሜ ነበር። 18ሥጋቸው የወፈረና መልካቸው ያማረ ሰባት ላሞች ከወንዙ ወጥተው በወንዙ ዳር የበቀለውን ሣር ሲበሉ አየሁ። 19ከእነርሱም በኋላ፣ ዐቅመ ደካማ፣ መልካቸው እጅግ የከፋና ዐጥንታቸው የወጣ ሌሎች ሰባት ላሞች ወጡ፤ እነዚያን የመሰሉ የሚያስከፋ መልክ ያላቸው ላሞች በግብፅ ምድር ከቶ አይቼ አላውቅም። 20ዐጥንታቸው የወጣና አስከፊ መልክ ያላቸው ላሞች መጀመሪያ የወጡትን፣ ሥጋቸው የወፈረውን ሰባቱን ላሞች ዋጧቸው። 21ከዋጧቸውም በኋላ፣ ያው የበፊቱ መልካቸው ስላልተለወጠ እንደ ዋጧቸው ማንም ሊያውቅ አይችልም ነበር፤ ከዚያም ከእንቅልፌ ነቃሁ።

22እንደዚሁም፣ በሕልሜ በአንድ የእህል አገዳ ላይ ፍሬያቸው የፋፋና ያማሩ ሰባት እሸት ዛላዎች ወጥተው አየሁ። 23ቀጥሎም በምሥራቅ ነፋስ ተመተው የቀጨጩና የደረቁ ሌሎች ሰባት ዛላዎች ወጡ። 24የቀጨጩት የእሸት ዛላዎችም ሰባቱን ያማሩ የእሸት ዛላዎች ዋጧቸው፤ ይህንኑም ለአስማተኞች ነገርሁ፤ ነገር ግን ማንም ሊፈታው አልቻለም።”

25ዮሴፍም ለፈርዖን እንዲህ አለው፤ “ሁለቱም የፈርዖን ሕልሞች ተመሳሳይና አንድ ዐይነት ናቸው፤ እግዚአብሔር (ኤሎሂም) ወደ ፊት የሚያደርገውን ለፈርዖን ገልጦለታል። 26ሰባቱ የሚያማምሩ ላሞች፣ ሰባት ዓመታት ናቸው፣ ሰባቱም የሚያማምሩ የእሸት ዛላዎች ሰባት ዓመታት ናቸው፤ ሕልሙም አንድና ተመሳሳይ ነው። 27ከእነርሱም በኋላ ዐጥንታቸው የወጣ አስከፊ መልክ ያላቸው ሰባት ላሞች፣ ሰባት ዓመታት ናቸው፤ እንደዚሁም ፍሬ አልባ የሆኑትና በምሥራቅ ነፋስ ተመትተው የደረቁት ሰባት የእሸት ዛላዎች ሰባት የራብ ዓመታት ናቸው።

28“አስቀድሜ ለፈርዖን እንደተናገርኩት፣ እግዚአብሔር (ኤሎሂም) ወደ ፊት የሚያደርገውን ነገር ለፈርዖን ገልጦለታል። 29በመላው የግብፅ ምድር እጅግ የተትረፈረፈ ጥጋብ የሚሆንባቸው ሰባት ዓመታት ይመጣሉ። 30ከዚህ በኋላ ግን በተከታታይ ሰባት የራብ ዓመታት ይሆናሉ። የራቡ ዘመን አገሪቱን እጅግ ስለሚጐዳት፣ በግብፅ የነበረው ያለፈው የጥጋብ ዘመን ሁሉ ጨርሶ አይታወስም። 31ከጥጋቡ ዓመታት በኋላ የሚመጣው የራብ ዘመን እጅግ ጽኑ ከመሆኑ የተነሣ፣ ቀደም ሲል የነበረው የጥጋብ ዘመን ፈጽሞ ይረሳል። 32ሕልሙ ለፈርዖን በሁለት መልክ በድጋሚ መታየቱ፣ ነገሩ ከእግዚአብሔር (ኤሎሂም) ዘንድ የተቈረጠ ስለ ሆነ ነው፤ ይህንንም እግዚአብሔር (ኤሎሂም) በቅርብ ጊዜ ይፈጽመዋል።

33እንግዲህ ፈርዖን ብልኅና አስተዋይ ሰው ፈልጎ፣ በመላው የግብፅ ምድር ላይ አሁኑኑ ይሹም። 34እንደዚሁም በሰባቱ የጥጋብ ዓመታት ከሚገኘው ምርት፣ አንድ አምስተኛው እንዲሰበሰብ የሚያደርጉ ኀላፊዎችን ይሹም። 35እነርሱም በሚመጡት የጥጋብ ዓመታት ከሚገኘው ምርት ሁሉ ይሰብስቡ፤ በፈርዖንም ሥልጣን ሥር ያከማቹ፤ ለምግብ እንዲሆኑም በየከተማው ይጠበቁ። 36የሚከማቸው እህል፣ ወደ ፊት በግብፅ አገር ላይ ለሚመጣው የሰባት ዓመት ራብ መጠባበቂያ ይሁን፤ በዚህም ሁኔታ አገሪቱ በራብ አትጠፋም።”

37ዕቅዱንም ፈርዖንና ሹማምቱ ሁሉ መልካም ሆኖ አገኙት። 38ፈርዖንም፣ “የእግዚአብሔር (ኤሎሂም) መንፈስ41፥38 ወይም የአማልክት መንፈስ ያለበት እንደዚህ ያለ ሰው ማንን ልናገኝ እንችላለን?” ብሎ ጠየቃቸው።

39ፈርዖን ዮሴፍን እንዲህ አለው፤ “እግዚአብሔር (ኤሎሂም) ይህን ሁሉ ስለ ገለጠልህ፣ እንዳንተ ያለ አስተዋይና ብልኅ ሰው የለም። 40አንተ በቤተ መንግሥቴ የበላይ ትሆናለህ፤ ሕዝቤም ሁሉ ለሥልጣንህ ይገዛል፤ እኔ ከአንተ የምበልጠው በዙፋኔ ብቻ ይሆናል።”

ዮሴፍ በግብፅ ተሾመ

41ከዚያም፣ ፈርዖን ዮሴፍን “በመላዪቱ የግብፅ ምድር ላይ ኀላፊ አድርጌሃለሁ” አለው። 42ፈርዖንም ባለማኅተሙን ቀለበት ከጣቱ አውልቆ በዮሴፍ ጣት ላይ አደረገው፤ እንዲሁም ከጥሩ የተልባ እግር የተሠራ ልብስ አለበሰው፤ በዐንገቱም የወርቅ ሐብል አጠለቀለት። 43በማዕረግ ከእርሱ ሁለተኛ ሰው አድርጎ፣ በሠረገላ ላይ አስቀመጠው።41፥43 ወይም በማዕረግ ሁለተኛ በሆነው የእርሱ ሠረገላ ላይ፤ ወይም በሁለተኛ ሠረገላው ላይ ሰዎችም በፊቱ፣ “እጅ ንሡ41፥43 ወይም ስገዱ” እያሉ ይጮኹ ነበር፤ በዚህ ሁኔታም በግብፅ ምድር ሁሉ ላይ ሾመው።

44ከዚህ በኋላ ፈርዖን ዮሴፍን፣ “እኔ ፈርዖን ነኝ፤ ሆኖም በመላዪቱ ግብፅ ያላንተ ትእዛዝ እጁንም ሆነ እግሩን ልውስ የሚያደርግ አይኖርም” አለው። 45ፈርዖንም ዮሴፍን ጸፍናት ፐዕናህ ብሎ ስም አወጣለት። እንዲሁም የሄልዮቱ41፥45 በቍ 50 ላይ ያለውንም ጨምሮ ሆልዮፓሊስን ያመለክታል ከተማ ካህን የጶጥፌራ ልጅ አስናትን አጋባው። ዮሴፍም በመላዪቱ የግብፅ ምድር ተዘዋወረ።

46ዮሴፍ የግብፅ ንጉሥ ፈርዖንን ማገልገል ሲጀምር፣ ዕድሜው ሠላሳ ዓመት ነበር። ዮሴፍም ከፈርዖን ፊት ወጥቶ የግብፅን ምድር በሙሉ ዞረ።

47በሰባቱም የጥጋብ ዓመታት ምድሪቱ የተትረፈረፈ ሰብል ሰጠች። 48በእነዚያ ሰባት የጥጋብ ዓመታት፣ ዮሴፍ በግብፅ አገር የተገኘውን ምርት ሰብስቦ በየከተሞቹ አከማቸ፤ በእያንዳንዱ ከተማ ከየአቅራቢያው የተመረተውን እህል እንዲከማች አደረገ። 49ዮሴፍ ብዛቱ እንደ ባሕር አሸዋ የሚሆን የእህል ሰብል አከማቸ፤ ሰብሉ እጅግ ከመብዛቱ የተነሣ ልኩን መስፈርና መመዝገብ አልቻለም ነበር።

50ሰባቱ የራብ ዓመታት ከመምጣቱ በፊት፣ የሄልዮቱ ካህን የጶጥፌራ ልጅ አስናት ለዮሴፍ ሁለት ወንዶች ልጆች ወለደችለት። 51ዮሴፍም፣ “እግዚአብሔር (ኤሎሂም) መከራዬን ሁሉ፣ የአባቴንም ቤት እንድረሳ አድርጎኛል” በማለት የመጀመሪያ ልጁን ስም ምናሴ41፥51 ምናሴ የሚለው ቃል መርሳት የሚል ትርጒም ካለው የዕብራይስጥ ቃል የወጣ ሲሆን ከዚሁ ቃል ጋር አንድ ዐይነት ድምፅ አለው አለው። 52እንደዚሁም፣ “መከራ በተቀበልኩበት ምድር እግዚአብሔር (ኤሎሂም) ፍሬያማ አደረገኝ” ሲል ሁለተኛ ልጁን ኤፍሬም41፥52 ኤፍሬም የሚለው ቃል በዕብራይስጥ ዕጥፍ ፍሬያማ የሚል ትርጒም ካለው ቃል ጋር አንድ ዐይነት ድምፅ አለው። አለው።

53በግብፅ ምድር የነበረው ሰባቱ የጥጋብ ዘመን ዐለፈና 54ዮሴፍ አስቀድሞ እንደ ተናገረው የሰባቱ ዓመት የራብ ዘመን ጀመረ። ሌሎች አገሮች ሁሉ ሲራቡ፣ በመላው የግብፅ ምድር ግን ምግብ ነበር። 55ራቡ በመላው የግብፅ ምድር መስፋፋት ሲጀምር፣ ሕዝቡ ምግብ ይሰጠን በማለት ወደ ፈርዖን ጮኸ። ፈርዖንም ግብፃውያኑን፣ “ወደ ዮሴፍ ሂዱና የሚላችሁን አድርጉ” አላቸው።

56ራቡ በአገሩ ላይ እየተስፋፋ ስለሄደ፣ ዮሴፍ ጐተራዎቹን ከፍቶ እህሉ ለግብፃውያን እንዲሸጥ አደረገ፤ ምክንያቱም ራቡ በመላዪቱ ግብፅ ጸንቶ ነበር። 57ራቡ በመላው ዓለም ጸንቶ ስለ ነበር፣ የየአገሩ ሰዎች ሁሉ ከዮሴፍ ዘንድ እህል ለመሸመት ወደ ግብፅ ምድር መጡ።

Thai New Contemporary Bible

ปฐมกาล 41:1-57

ความฝันของฟาโรห์

1เวลาผ่านไปสองปีเต็ม คืนหนึ่งฟาโรห์ทรงฝันว่าพระองค์ทรงยืนอยู่ที่ริมฝั่งแม่น้ำไนล์ 2มีวัวอ้วนพีแข็งแรงเจ็ดตัวขึ้นมาจากแม่น้ำไนล์ กินหญ้าอยู่ริมฝั่ง 3แล้วมีวัวอีกเจ็ดตัวขึ้นมาจากแม่น้ำไนล์ แต่พวกหลังนี้ตัวผอมแห้งจนน่าเกลียด พวกมันเดินมาหยุดยืนอยู่ข้างวัวอ้วนพีแข็งแรง 4วัวผอมโซน่าเกลียดเหล่านั้นก็กินวัวอ้วนพีแข็งแรงทั้งเจ็ดตัว แล้วฟาโรห์ทรงตื่นจากบรรทม

5พระองค์บรรทมหลับไปอีกและทรงฝันเป็นครั้งที่สอง คราวนี้ทรงเห็นข้าวต้นหนึ่งกำลังออกรวงเจ็ดรวงซึ่งมีเมล็ดเต่งงามดี 6หลังจากนั้นมีอีกเจ็ดรวงผลิออกมา แต่มีเมล็ดเหี่ยวแห้งเพราะลมตะวันออก 7แล้วรวงข้าวที่เหี่ยวแห้งก็กลืนกินรวงข้าวที่เต่งงามเจ็ดรวงนั้นจนหมด แล้วฟาโรห์ตื่นจากบรรทมและทรงทราบว่าเป็นความฝัน

8เช้าวันรุ่งขึ้นฟาโรห์ทรงกังวลพระทัยนักจึงรับสั่งให้บรรดานักเล่นอาคมและปราชญ์ของอียิปต์มาเข้าเฝ้า พระองค์ทรงเล่าความฝันให้ฟัง แต่ไม่มีใครบอกได้ว่าความฝันพวกนั้นหมายถึงอะไร

9แล้วหัวหน้าพนักงานเชิญจอกเสวยจึงกราบทูลว่า “วันนี้ข้าพระบาทระลึกถึงความผิดพลาดของตนได้แล้ว 10ครั้งหนึ่งฟาโรห์กริ้วข้าพระบาท และทรงให้จำคุกข้าพระบาทพร้อมกับหัวหน้าพนักงานทำขนมปังไว้ในบ้านของผู้บัญชาการทหารรักษาพระองค์ 11คืนหนึ่งข้าพระบาททั้งสองต่างฝันไป และความฝันของแต่ละคนนั้นก็มีความหมายแตกต่างกัน 12ขณะนั้นชายหนุ่มฮีบรูคนหนึ่งซึ่งเป็นทาสรับใช้ของท่านผู้บัญชาการทหารรักษาพระองค์ได้ถูกจำคุกอยู่กับข้าพระบาททั้งสอง ข้าพระบาทจึงเล่าความฝันให้เขาฟัง เขาก็บอกความหมายของความฝันให้กับข้าพระบาททั้งสอง 13ทุกสิ่งก็เป็นไปตามที่เขาได้ทำนายให้กับข้าพระบาททุกประการ คือข้าพระบาทได้กลับเข้ามาประจำหน้าที่ดังเดิม ส่วนอีกคนหนึ่งก็ถูกเสียบประหาร”

14ฟาโรห์จึงรับสั่งให้นำโยเซฟมาเข้าเฝ้า เขาจึงถูกนำตัวออกจากคุกอย่างเร่งด่วน เมื่อโกนหนวดเคราและเปลี่ยนเสื้อผ้าเสร็จแล้วก็เข้าเฝ้าฟาโรห์

15ฟาโรห์ตรัสกับโยเซฟว่า “เราฝันไป และไม่มีใครบอกความหมายของความฝันได้ แต่เราได้ยินมาว่าเมื่อใครเล่าความฝันให้เจ้าฟัง เจ้าก็สามารถบอกความหมายของความฝันนั้นได้”

16โยเซฟทูลฟาโรห์ว่า “ข้าพระบาททำไม่ได้ แต่พระเจ้าจะทรงแจ้งให้ฟาโรห์ทราบคำตอบตามที่ฟาโรห์ต้องการ”

17ฟาโรห์จึงตรัสกับโยเซฟว่า “ในฝันเรายืนอยู่ริมฝั่งแม่น้ำไนล์ 18มีวัวอ้วนพีแข็งแรงเจ็ดตัวขึ้นมาจากแม่น้ำและกินหญ้าอยู่ริมฝั่ง 19แล้วก็มีวัวอีกเจ็ดตัวขึ้นมาจากแม่น้ำ ตัวผอมแห้งน่าเกลียดมาก เราไม่เคยเห็นวัวตัวไหนน่าเกลียดขนาดนั้นมาก่อนเลยในแผ่นดินอียิปต์ 20แล้ววัวผอมแห้งน่าเกลียดเหล่านั้นก็กินวัวอ้วนพีทั้งเจ็ดตัวที่ขึ้นมาก่อนจนหมด 21แม้พวกมันจะกินวัวเหล่านั้นไปหมดแล้วก็ไม่มีใครรู้ได้ว่าพวกมันได้ทำเช่นนั้น เพราะพวกมันก็ยังผอมแห้งน่าเกลียดอยู่เหมือนเดิม แล้วเราก็ตื่น

22“เราฝันไปอีกว่าเห็นต้นข้าวต้นหนึ่งออกรวงเจ็ดรวงซึ่งมีเมล็ดเต่งงามดี 23แล้วมีรวงข้าวอีกเจ็ดรวงงอกขึ้นมาซึ่งมีเมล็ดเหี่ยวแห้งเพราะลมตะวันออก 24รวงข้าวที่เหี่ยวแห้งนั้นก็กลืนกินรวงข้าวที่เต่งงามทั้งเจ็ดรวงเสียหมด เราเล่าเรื่องนี้ให้บรรดานักเล่นอาคมฟัง แต่ไม่มีใครอธิบายให้เราเข้าใจได้”

25โยเซฟทูลฟาโรห์ว่า “ความฝันทั้งสองนี้หมายความถึงสิ่งเดียวกัน พระเจ้าทรงเปิดเผยแก่ฟาโรห์ถึงสิ่งที่พระองค์จะทรงกระทำ 26วัวอ้วนพีเจ็ดตัวหมายถึงเจ็ดปี และรวงข้าวเต่งงามเจ็ดรวงก็หมายถึงเจ็ดปี ความฝันทั้งสองนี้หมายความถึงสิ่งเดียวกัน 27ส่วนวัวผอมน่าเกลียดเจ็ดตัวที่ขึ้นจากแม่น้ำมาภายหลังหมายถึงเจ็ดปี และรวงข้าวไร้ค่าเจ็ดรวงที่เหี่ยวแห้งไปเพราะลมตะวันออกนั้นก็หมายถึงเจ็ดปีเช่นกัน เป็นเจ็ดปีแห่งการกันดารอาหาร

28“อย่างที่ข้าพระบาทได้ทูลฟาโรห์ไว้แล้วว่า พระเจ้าได้ทรงสำแดงแก่ฟาโรห์ถึงสิ่งที่พระองค์จะทรงกระทำ 29ตลอดเจ็ดปีต่อไปนี้จะเป็นช่วงอุดมสมบูรณ์ทั่วแผ่นดินอียิปต์ 30แต่เจ็ดปีแห่งการกันดารอาหารจะตามมา แล้วประชาชนจะลืมความอุดมสมบูรณ์ทั้งสิ้นของประเทศอียิปต์ และการกันดารอาหารจะทำลายแผ่นดินนี้ 31ความอุดมสมบูรณ์ของแผ่นดินถูกลบเลือนไปจากความทรงจำ เพราะการกันดารอาหารจะรุนแรงยิ่งนัก 32เหตุที่พระเจ้าทรงประทานความฝันถึงสองอย่างแก่ฟาโรห์นั้น เพราะว่าพระเจ้าทรงตัดสินพระทัยแน่วแน่แล้ว พระองค์จะทรงให้สิ่งนี้เกิดขึ้นในไม่ช้า

33“และบัดนี้ขอให้ฟาโรห์ทรงโปรดคัดเลือกคนที่ฉลาดหลักแหลมและมีสติปัญญา และตั้งให้เขาให้ดูแลแผ่นดินอียิปต์ 34ขอให้ฟาโรห์ทรงแต่งตั้งข้าราชการประจำเขตไว้ทั่วแผ่นดิน ทำหน้าที่เก็บพืชผลหนึ่งในห้าของผลผลิตที่ได้ในตลอดเจ็ดปีแห่งความอุดมสมบูรณ์ 35พวกเขาควรรวบรวมอาหารทั้งหมดที่ได้ในปีแห่งความอุดมสมบูรณ์ที่กำลังจะมาถึง และให้ฟาโรห์มอบอำนาจให้พวกเขาเก็บสะสมเมล็ดข้าวไว้เป็นคลังอาหารตามเมืองต่างๆ 36อาหารเหล่านี้ควรเก็บไว้เป็นเสบียงสำรองให้กับประเทศสำหรับช่วงเจ็ดปีแห่งการกันดารอาหารซึ่งจะเกิดขึ้นกับอียิปต์ เพื่อว่าประเทศชาติจะไม่ย่อยยับไปเพราะการกันดารอาหาร”

37ฟาโรห์และข้าราชการทั้งปวงล้วนเห็นชอบกับแผนงานนี้ 38ดังนั้นฟาโรห์จึงตรัสถามพวกเขาว่า “เราจะหาใครที่มีพระวิญญาณของพระเจ้า41:38 หรือของเทพเจ้าทั้งหลายอยู่ภายในเหมือนชายผู้นี้ได้หรือ?”

39แล้วฟาโรห์ตรัสกับโยเซฟว่า “เนื่องจากพระเจ้าทรงเปิดเผยความหมายของความฝันให้เจ้ารู้ จึงไม่มีผู้ใดฉลาดหลักแหลมและมีสติปัญญาเหมือนเจ้า 40เราจะแต่งตั้งเจ้าให้ดูแลราชสำนักของเรา และราษฎรทั้งหมดของเราจะทำตามคำสั่งของเจ้า เราจะเป็นผู้เดียวที่มีฐานะสูงกว่าเจ้าเพียงเพราะว่าเราเป็นผู้ครองราชบัลลังก์”

โยเซฟปกครองดูแลอียิปต์

41ดังนั้นฟาโรห์จึงตรัสแก่โยเซฟว่า “บัดนี้เราขอตั้งเจ้าให้ดูแลทั่วแผ่นดินอียิปต์” 42แล้วฟาโรห์ทรงถอดแหวนตราประจำพระองค์จากนิ้วมาสวมที่นิ้วของโยเซฟ พระองค์ทรงให้เขาสวมเสื้อคลุมผ้าลินินเนื้อดีและประทานสร้อยคอทองคำแก่เขา 43ฟาโรห์ให้โยเซฟนั่งรถม้าศึกในฐานะผู้มีอำนาจรองจากพระองค์41:43 หรือรถม้าศึกของผู้มีอำนาจรองจากพระองค์หรือรถม้าศึกคันที่สองของพระองค์ ไม่ว่าเขาจะไปที่ไหนก็มีคนคอยร้องประกาศว่า “จงเปิดทาง!41:43 หรือจงหมอบลง!” ดังนั้นฟาโรห์จึงทรงแต่งตั้งโยเซฟให้ดูแลทั่วแผ่นดินอียิปต์

44ฟาโรห์ตรัสกับโยเซฟว่า “แม้ว่าเราคือฟาโรห์ แต่ถ้าเจ้าไม่อนุญาตก็จะไม่มีผู้ใดในแผ่นดินอียิปต์ยกมือยกเท้าได้” 45ฟาโรห์ประทานนามแก่โยเซฟว่าศาเฟนาทปาเนอาห์ และประทานอาเสนัทบุตรีปุโรหิตโปทิเฟราแห่งเมืองโอนให้เป็นภรรยา และโยเซฟออกตรวจตราทั่วแผ่นดินอียิปต์

46โยเซฟมีอายุได้สามสิบปีเมื่อเข้ารับราชการกับฟาโรห์กษัตริย์แห่งอียิปต์ โยเซฟได้ทูลลาฟาโรห์และออกเดินทางไปปฏิบัติราชการทั่วแผ่นดินอียิปต์ 47ตลอดเจ็ดปีแห่งความอุดมสมบูรณ์ แผ่นดินก็ให้ผลผลิตมากมาย 48โยเซฟรวบรวมอาหารทั้งหมดที่ผลิตได้ในเจ็ดปีแห่งความอุดมสมบูรณ์ของอียิปต์ และเก็บสะสมไว้ตามเมืองต่างๆ ผลผลิตที่เก็บได้จากนารอบเมืองใด เขาก็ให้เก็บไว้ในเมืองนั้น 49โยเซฟเก็บสะสมเมล็ดข้าวได้มหาศาลเหมือนเม็ดทรายในทะเล จนเขาต้องเลิกทำบัญชี เพราะตรวจนับไม่ไหว

50ก่อนปีกันดารอาหารจะมาถึง โยเซฟได้บุตรชายสองคนซึ่งเกิดจากนางอาเสนัทบุตรีของปุโรหิตโปทิเฟราแห่งเมืองโอน 51โยเซฟตั้งชื่อบุตรหัวปีว่ามนัสเสห์41:51 คำว่ามนัสเสห์มีเสียงคล้ายและอาจมาจากคำภาษาฮีบรูที่มีความหมายว่าลืม เขากล่าวว่า “เพราะพระเจ้าทรงทำให้ข้าพเจ้าลืมความทุกข์ยากทั้งปวงและญาติพี่น้องทั้งหมดในครัวเรือนบิดาของข้าพเจ้า” 52เขาตั้งชื่อบุตรชายคนที่สองว่าเอฟราอิม41:52 คำว่าเอฟราอิมมีเสียงคล้ายคำภาษาฮีบรูที่มีความหมายว่าเกิดผลสองเท่า เขากล่าวว่า “เพราะพระเจ้าทรงกระทำให้ข้าพเจ้ามีลูกมีหลานมากมายในดินแดนที่ข้าพเจ้าตกทุกข์ได้ยาก”

53ในที่สุดเจ็ดปีแห่งความอุดมสมบูรณ์ก็สิ้นสุดลง 54และเจ็ดปีแห่งการกันดารอาหารก็เริ่มต้นขึ้นตามที่โยเซฟได้กล่าวไว้ เกิดการกันดารอาหารขึ้นทั่วทุกประเทศ แต่ทั่วแผ่นดินอียิปต์มีอาหาร 55เมื่อชาวอียิปต์เริ่มได้รับผลกระทบจากการกันดารอาหาร ผู้คนต่างก็มาทูลขออาหารจากฟาโรห์ ฟาโรห์จึงสั่งชาวอียิปต์ทุกคนว่า “จงไปหาโยเซฟและทำตามสิ่งที่เขาบอก”

56เมื่อการกันดารอาหารขยายไปทั่วประเทศ โยเซฟจึงเปิดคลังขายข้าวให้แก่ชาวอียิปต์ เพราะเกิดการกันดารอาหารอย่างรุนแรงทั่วทั้งอียิปต์ 57ทุกประเทศทั่วโลกพากันมายังอียิปต์เพื่อซื้อข้าวจากโยเซฟ เพราะการกันดารอาหารรุนแรงทั่วโลก