New Amharic Standard Version

ዘፍጥረት 40:1-23

የመጠጥ አሳላፊውና የእንጀራ ቤቱ

1ከዚህም በኋላ የግብፅ ንጉሥ የመጠጥ አሳላፊና እንጀራ ቤቱ ጌታቸውን የግብፅን ንጉሥ በደሉት። 2ፈርዖንም በመጠጥ አሳላፊዎቹ አለቃና በእንጀራ ቤቱ አዛዥ፣ በሁለቱም ሹማምቱ ላይ ክፉኛ ተቈጣ፤ 3በዘበኞቹ አለቃ ቤት ወዳለው ዮሴፍ ወደ ተጋዘበትም እስር ቤት አስገባቸው።

4የዘበኞቹም አለቃ እስረኞቹን ለዮሴፍ አስረከባቸው፤ ዮሴፍም በሚያስፈልጋቸው ይረዳቸው ነበር።

እስር ቤት ገብተው ጥቂት እንደ ቈዩም፣ 5ታስረው የነበሩት የግብፅ የንጉሥ የመጠጥ አሳላፊዎች አለቃና የእንጀራ ቤቱ አዛዥ፣ በአንድ ሌሊት የየራሳቸውን ሕልም አዩ፤ የሁለቱም ሕልም ለየራሱ የተለየ ፍቺ ነበረው።

6በማግስቱ ጧት ዮሴፍ ወደ እነርሱ ሲገባ ተክዘው አገኛቸው። 7ስለዚህም፣ “ምነው ዛሬስ ፊታችሁ ላይ ሐዘን ይነበባል?” በማለት አብረውት በጌታው ግቢ የታሰሩትን የፈርዖን ሹማምት ጠየቃቸው።

8እነርሱም “ሁለታችንም ሕልም አየን፤ ነገር ግን የሚተረጒምልን ሰው አጣን” ሲሉ መለሱለት።

ዮሴፍም፣ “ሁልጊዜስ ቢሆን የሕልም ትርጓሜ ከእግዚአብሔር (ኤሎሂም) የሚገኝ አይደለምን? እስቲ ያያችሁትን ሕልም ንገሩኝ” አላቸው።

9ስለዚህ የመጠጥ አሳላፊዎቹ አለቃ እዲህ ሲል ሕልሙን ለዮሴፍ ነገረው፤ ከፊት ለፊቴ አንዲት የወይን ተክል አየሁ፤ 10ተክሏም ሦስት ሐረጎች ነበሯት፤ ወዲያው አቈቊጣ አበበች፤ ዘለላዎቿም ተንዠርግገው በሰሉ። 11የፈርዖንንም ጽዋ ይዤ ነበረ፤ የወይኑን ፍሬ ለቅሜ በጽዋው ውስጥ ጨምቄ ጽዋውን በእጁ ሰጠሁት።”

12ዮሴፍም እንዲህ አለው፤ “እንግዲህ የሕልሙ ትርጓሜ ይህ ነው፤ ሦስቱ ሐረግ ሦስት ቀን ነው፤ 13በሦስት ቀን ውስጥ ፈርዖን ከእስር ቤት ያወጣሃል፣ ወደ ቀድሞ ሹመትህም ይመልስሃል፤ በፊት የመጠጥ አሳላፊ በነበርህበት ጊዜ ታደርግ እንደነረው ሁሉ የፈርዖንን ጽዋ በእጁ ትሰጠለህ። 14እንግዲህ፣ በጎ ነገር በገጠመህ ጊዜ፣ እኔን አስበህ ቸርነት አድርግልኝ፤ ስለ እኔም ለፈርዖን ንገርልኝ፤ ከዚህም እስር ቤት አስወጣኝ፤ 15ከዕብራውያን ምድር ወደዚህ የመጣሁት በአፈና ነው፤ አሁንም ቢሆን እዚህ እስር ቤት የተጣልሁት አንዳች ጥፋት ኖሮብኝ አይደለም።”

16የእንጀራ ቤት አዛዡም፣ ለመጠጥ አላፊዎቹ አለቃ ሕልም፣ የተሰጠው ፍቺ ደስ የሚያሰኝ መሆኑን ሲሰማ፣ የራሱን ሕልም ለዮሴፍ እንዲህ ሲል ነገረው፤ “እኔም ደግሞ ሕልም አይቻለሁ፤ ሦስት መሶቦች40፥16 ወይም ሦስት የሸንበቆ ቅርጫቶች በራሴ ላይ ተሸክሜ ነበር፤ 17በላይኛው መሶብ ውስጥ ለፈርዖን የተዘጋጀ የተለያየ ምግብ ነበረበት፤ ወፎችም ራሴ ላይ ካለው መሶብ ይበሉ ነበር።”

18ዮሴፍም እንዲህ ሲል መለሰለት፤ “የሕልሙ ፍቺ ይህ ነው፤ ሦስቱ መሶብ ሦስት ቀን ነው፤ 19በሦስት ቀን ውስጥ ፈርዖን ከእስር ቤት ያወጣሃል፤ በዕንጨትም ላይ ይሰቅልሃል፤40፥19 ወይም በእንጨትም ላይ ይወጋሃል ወፎችም ሥጋህን ይበሉታል።”

20በሦስተኛውም ቀን የፈርዖን የልደት በዓል ነበረ፤ ለሹማምቱም ሁሉ ግብር አበላ። በዚያኑ ዕለትም የመጠጥ አሳላፊዎችን አለቃና የእንጀራ ቤት አዛዡን ሹማምቱ ካሉበት ከእስር ቤት አወጣቸው።

21የመጠጥ አሳላፊዎቹን አለቃ ወደ ቀድሞ ሹመቱ መለሰው፤ እርሱም እንደ ቀድሞው ጽዋውን ለፈርዖን በእጁ ይሰጠው ጀመር፤ 22የእንጀራ ቤት አዛዡን ግን ልክ ዮሴፍ እንደ ተረጐመላቸው ሰቀለው።40፥22 ወይም ወጋው

23የሆነው ሆኖ፣ የመጠጥ አሳላፊዎቹ አለቃ ዮሴፍን አላስታወሰውም፤ ረሳው።

Korean Living Bible

창세기 40:1-23

두 신하의 꿈을 해석하는 요셉

1얼마 후에 이집트 왕의 술을 따르는 신하와 빵 굽는 신하가 자기 주 인인 이집트 왕에게 범죄하였다.

2그래서 바로는 그 두 신하에게 분노하여

3그들을 경호대장의 집 안에 있는 감옥에 가두었는데 그 곳은 요셉이 갇혀 있는 곳이었다.

4그리고 경호대장은 그들을 요셉에게 맡겨 요셉이 그들을 보살피도록 하였다. 그들이 갇힌 지 상당한 시간이 지난 어느 날

5이집트 왕의 술을 따르는 신하와 빵 굽는 신하가 같은 날 밤에 서로 다른 꿈을 꾸었다.

6다음날 아침 요셉이 들어가 보니 그들이 수심에 잠겨 있었다.

7그래서 요셉이 그들에게 물었다. “오늘은 어째서 그처럼 수심에 잠겨 있습니까?”

8“우리가 꿈을 꾸었으나 해몽해 줄 사람이 없구나.” “해몽은 하나님이 하시지 않습니까? 당신들의 꿈을 나에게 말씀해 주십시오.”

9그러자 왕의 술을 따르던 신하가 이렇게 말하였다. “내가 꿈에 보니 내 앞에 포도나무가 있는데

10그 나무에 세 가지가 있고 그것이 싹이 나자마자 꽃이 피고 포도송이가 달려 곧 익었다.

11그리고 나는 이때 왕의 술잔을 들고 있었다. 그래서 내가 그 포도를 따서 포도즙을 만들어 왕의 술잔에 붓고 그것을 왕에게 갖다 드렸다.”

12그때 요셉은 그 꿈을 이렇게 해석하였다. “세 개의 그 포도나무 가지는 3일을 뜻합니다.

13지금부터 3일 안에 왕이 당신을 석방하여 당신의 전직을 회복시켜 주실 것입니다. 당신은 전에 하던 것처럼 왕에게 다시 술을 따르게 될 것입니다.

14당신의 모든 일이 잘 되거든 나를 기억하셔서, 나에게 은혜를 베풀어 내 사정을 왕에게 말씀드리고 나를 이 감옥에서 나가도록 해 주십시오.

15나는 히브리 땅에서 강제로 끌려왔으며 여기서도 감옥에 갇힐 만한 일은 하지 않았습니다.”

16빵 굽던 신하가 요셉이 그 꿈을 좋게 해석하는 것을 보고 그에게 말하였다. “나도 꿈을 꾸었는데 빵을 담은 광주리 세 개가 내 머리 위에 있고

17제일 윗 광주리에는 왕을 위해 만든 여러 가지 구운 음식이 있었으나 새들이 그것을 먹고 있었다.”

18그러자 요셉이 그 꿈을 이렇게 해석하였다. “그 세 광주리는 3일을 뜻합니다.

19지금부터 3일 안에 왕이 당신을 감옥에서 끌어내어 당신을 나무에 매달 것입니다. 그리고 새들이 당신의 시체를 뜯어먹을 것입니다.”

20그로부터 3일째가 되던 날은 바로의 생일이었다. 그래서 그는 모든 신하들을 위해 잔치를 베풀고 술을 따르던 신하와 빵 굽던 신하를 감옥에서 풀어내어 신하들 앞에 세웠다.

21그러고서 왕은 술 따르던 신하의 전직을 회복시켜 다시 술을 따르게 하고

22빵 굽던 신하는 나무에 매달아 처형시켰다. 이와 같이 모든 일이 요셉의 말대로 되었으나

23술 따르는 신하는 요셉을 까마득하게 잊어버리고 기억하지 않았다.