New Amharic Standard Version

ዘፍጥረት 33:1-20

የያዕቆብና የዔሳው መገናኘት

1ያዕቆብ አሻግሮ ተመለከተ፤ እነሆ ዔሳው አራት መቶ ሰዎች አስከትሎ እየመጣ ነበር። ስለዚህ ልጆቹን ለልያ፣ ለራሔልና ለሁለቱ አገልጋዮች አከፋፈላቸው። 2ከዚያም ሁለቱን አገልጋዮች ከነልጆቻቸው አስቀደመ፤ ልያንና ልጆቿንም አስከተለ፤ ራሔልንና ዮሴፍን ግን ከሁሉ ኋላ እንዲሆኑ አደረገ። 3እርሱ ራሱም ቀድሞአቸው ሄደ፤ ወንድሙም ዘንድ እስኪደርስ ድረስ ሰባት ጊዜ ወደ መሬት ለጥ ብሎ እጅ ነሣ።

4ዔሳው ግን ሊገናኘው ወደ እርሱ ሮጦ ሄዶ ዐቀፈው፤ በዐንገቱም ላይ ተጠምጥሞ ሳመው፤ ሁለቱም ተላቀሱ። 5ከዚያም ዔሳው ቀና ብሎ ሲመለከት ሴቶቹንና ልጆቹን አየ፤ እርሱም፣ “እነዚህ አብረውህ ያሉት እነማን ናቸው?” ብሎ ጠየቀው።

ያዕቆብም መልሶ፣ “እነዚህማ እግዚአብሔር (ኤሎሂም) በቸርነቱ ለእኔ ለአገልጋይህ የሰጠኝ ልጆች ናቸው” አለው።

6በዚህ ጊዜ ሁለቱ ሴት አገልጋዮችና ልጆቻቸው ቀርበው እጅ ነሡ፤ 7ከዚያም ልያና ልጆቿ መጥተው እጅ ነሡ፤ በመጨረሻም ዮሴፍና ራሔል መጡ፤ እነርሱም ቀርበው እጅ ነሡ።

8ዔሳውም፣ “ወደ እኔ ተነድቶ የመጣው ይህ ሁሉ መንጋ ምንድን ነው?” አለው።

እርሱም፣ “ጌታዬ ሆይ፤ በአንተ ዘንድ ሞገስ ባገኝ ብዬ ነው” አለው።

9ዔሳው ግን፣ “ወንድሜ ሆይ፤ እኔ በቂ አለኝ፤ የራስህን ለራስህ አድርገው አለው።

10ያዕቆብም፣ “የለም፣ እንዲህ አይደለም፤ በአንተ ዘንድ ሞገስ አግኝቼ እንደሆነ፣ እጅ መንሻዬን ተቀበል፤ በመልካም ሁኔታ ተቀብለኸኝ ፊትህን ማየት መቻሌ ራሱ፣ የእግዚአብሔርን (ኤሎሂም) ፊት የማየት ያህል እቈጥረዋለሁ። 11እግዚአብሔር (ኤሎሂም) በቸርነቱ አሟልቶ ስለ ሰጠኝ የሚያስፈልገኝ ሁሉ አለኝና ያቀረብኹልህን እጅ መንሻ እባክህ ተቀበለኝ” አለው። ያዕቆብ አጥብቆ ስለ ለመነው፣ ዔሳው እጅ መንሻውን ተቀበለ።

12ዔሳውም “በል ተነሥና ጒዟችንን እንቀጥል፤ እኔም እሄዳለሁ” አለው።

13ያዕቆብ ግን እንዲህ አለው፤ “ጌታዬ፣ እንደምታየው ልጆቹ ይህን ያህል የጠኑ አይደሉም፣ ለሚያጠቡት በጎችና ጥገቶች እንክብካቤ ማድረግ አለብኝ፤ እንስሳቱ ለአንዲት ቀን እንኳ በጥድፊያ ቢነዱ በሙሉ ያልቃሉ። 14ስለዚህ ጌታዬ፣ አንተ ቀድመኸኝ ሂድ፤ እኔም በምነዳቸው እንስሳትና በልጆቹ ጒዞ ዐቅም ልክ እያዘገምሁ ሴይር ላይ እንገናኛለን።”

15ዔሳው፣ “እንግዲያስ ከሰዎቼ ጥቂቶቹን ልተውልህ” አለው።

ያዕቆብ ግን፣ “ለምን ብለህ? በአንተ ዘንድ ሞገስ ማግኘቴ ብቻ ይበቃኛል” አለው።

16ስለዚህ ዔሳው በዚሁ ዕለት ወደ ሴይር ለመመለስ ተነሣ። 17ያዕቆብ ግን ወደ ሱኮት33፥17 ሱኮት ማለት መጠለያዎች ማለት ነው። ሄደ፤ እዚያም ለራሱ መጠለያ፣ ለከብቶቹም በረት ሠራ፤ ከዚህም የተነሣ የቦታው ስም ሱኮት ተባለ።

18ያዕቆብ ከሰሜን ምዕራብ መስጴጦምያ ከተመለሰ በኋላ፣ በከነዓን ወዳለችው ወደ ሴኬም በደኅና ደረሰ፤33፥18 ወይም ሳሌም ደረሰ በከተማዪቱም ፊት ለፊት ሰፈረ። 19ድንኳኑን የተከለበትንም ቦታ ከኤሞር ልጆች በመቶ ጥሬ ብር ገዛ፤ ኤሞርም የሴኬም አባት ነበር። 20በዚያም መሠዊያ አቁሞ፣ ኤል ኤሎሄ እስራኤል33፥20 ኤል ኤሎሄ እስራኤል ማለት የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ወይም የእስራኤል አምላክ ኀያል ነው ማለት ነው። ብሎ ጠራው።

Persian Contemporary Bible

پيدايش 33:1-20

يعقوب با عيسو روبرو می‌شود

1آنگاه يعقوب از فاصلهٔ دور ديد كه عيسو با چهارصد نفر از افراد خود می‌آيد. 2او خانوادهٔ خود را در يک صف به سه دسته تقسيم كرد و آنها را پشت سر هم به راه انداخت. در دستهٔ اول دو كنيز او و فرزندانشان، در دستهٔ دوم ليه و فرزندانش و در دستهٔ سوم راحيل و يوسف قرار داشتند. 3خود يعقوب نيز در پيشاپيش آنها حركت می‌كرد. وقتی يعقوب به برادرش نزديک شد، هفت مرتبه او را تعظيم كرد. 4عيسو دوان‌دوان به استقبال او شتافت و او را در آغوش كشيده، بوسيد و هر دو گريستند. 5سپس عيسو نگاهی به زنان و كودكان انداخت و پرسيد: «اين همراهان تو كيستند؟»

يعقوب گفت: «فرزندانی هستند كه خدا به بنده‌ات عطا فرموده است.» 6آنگاه كنيزان با فرزندانشان جلو آمده، عيسو را تعظيم كردند، 7بعد ليه و فرزندانش و آخر همه راحيل و يوسف پيش آمدند و او را تعظيم نمودند.

8عيسو پرسيد: «آن حيواناتی كه در راه ديدم، برای چه بود؟» يعقوب گفت: «آنها را به تو پيشكش كردم تا مورد لطف تو قرار گيرم.»

9عيسو گفت: «برادر، من خود گله و رمه بسيار دارم. آنها را برای خودت نگاه دار.» 10يعقوب پاسخ داد: «اگر واقعاً مورد لطف تو واقع شده‌ام، التماس دارم هديهٔ مرا قبول كنی. ديدن روی تو برای من مانند ديدن روی خدا بود! حال كه تو با مهربانی مرا پذيرفتی، 11پس هدايايی را كه به تو پيشكش كرده‌ام قبول فرما. خدا نسبت به من بسيار بخشنده بوده و تمام احتياجاتم را رفع كرده است.» يعقوب آنقدر اصرار كرد تا عيسو آنها را پذيرفت.

12عيسو گفت: «آماده شو تا برويم. من و افرادم تو را همراهی خواهيم كرد.»

13يعقوب گفت: «چنانكه می‌بينی بعضی از بچه‌ها كوچكند و رمه‌ها و گله‌ها نوزادانی دارند كه اگر آنها را به سرعت برانيم همگی تلف خواهند شد. 14پس شما جلو برويد و ما هم همراه بچه‌ها و گله‌ها آهسته می‌آييم و در سعير به شما ملحق می‌شويم.»

15عيسو گفت: «لااقل بگذار چند نفر از افرادم همراه تو باشند.»

يعقوب پاسخ داد: «لزومی ندارد، ما خودمان می‌آييم. از لطف سَروَرم سپاسگزارم.»

16عيسو همان روز راه خود را پيش گرفته، به سعير مراجعت نمود، 17اما يعقوب با خانواده‌اش به سوكوت رفت و در آنجا برای خود خيمه و برای گله‌ها و رمه‌هايش سايبانها درست كرد. به همين دليل آن مكان را سوكوت (يعنی «سايبانها») ناميده‌اند. 18سپس از آنجا به سلامتی به شكيم واقع در كنعان كوچ كردند و خارج از شهر خيمه زدند. 19او زمينی را كه در آن خيمه زده بود از خانوادهٔ حمور، پدر شكيم به صد پاره نقره خريد. 20در آنجا يعقوب قربانگاهی ساخت و آن را ايل الوهی اسرائيل (يعنی «قربانگاه خدای اسرائيل») ناميد.