New Amharic Standard Version

ዘፍጥረት 26:1-35

ይስሐቅና አቢሜሌክ

26፥1-11 ተጓ ምብ – ዘፍ 12፥10-20፤ 20፥1-18

1ቀድሞ በአብርሃም ዘመን ከደረሰው ራብ ሌላ፣ በአገሩ ላይ ራብ ሆነ። ይስሐቅም የፍልስጥኤም ንጉሥ አቢሜሌክ ወደሚኖርበት ወደ ጌራራ ሄደ። 2በዚያም እግዚአብሔር (ያህዌ) ለይስሐቅ ተገልጦ እንዲህ አለው፤ “እኔ በምነግርህ ምድር ተቀመጥ እንጂ፣ ወደ ግብፅ አትውረድ፤ 3ለጥቂት ጊዜ እዚሁ አገር ተቀመጥ፤ እኔም ካንተ ጋር እሆናለሁ፤ እባርክሃለሁም፤ ይህን ምድር በሙሉ ለአንተና ለዘርህ በመስጠት ለአባትህ ለአብርሃም በመሐላ የገባሁለትን ቃል አጸናለሁ። 4ዘርህን እንደ ሰማይ ከዋክብት አበዛለሁ፤ ይህን ምድር በሙሉ ለዘርህ እሰጣለሁ፤ የምድር ሕዝቦችም ሁሉ በዘርህ አማካይነት ይባረካሉ፤ 5ይኸውም አብርሃም ቃሌን ሰምቶ፣ ድንጋጌዬን፣ ትእዛዜን፣ ሥርዐቴንና ሕጌን በመጠበቁ ነው።” 6ስለዚህ ይስሐቅ በጌራራ ተቀመጠ።

7የዚያም አገር ሰዎች ስለ ሚስቱ በጠየቁት ጊዜ፣ “እኅቴ ናት” አለ፤ ምክንያቱም፣ “ሚስቴ ናት ብል ርብቃ ቈንጆ ስለሆነች፣ ያገሬው ሰዎች በእርሷ ምክንያት ይገድሉኛል” በማለት ፈርቶ ነበር።

8ይስሐቅ ብዙ ጊዜ በዚያ ከኖረ በኋላ፣ የፍልስጥኤም ንጉሥ አቢሜሌክ አንድ ቀን ወደ ውጭ ሲመለከት፣ ይስሐቅ ሚስቱን ርብቃን ሲዳራት አየ። 9አቢሜሌክም ይስሐቅን ጠርቶ፣ “እርሷ ሚስትህ ሆና ሳለች፣ እንዴት እኅቴ ናት ትላለህ?” አለው።

ይስሐቅም፣ “በእርሷ ሰበብ፣ ሕይወቴን እንዳላጣ ብዬ ነው” አለው። 10አቢሜሌክም መልሶ፣ “እንዲህ ያለ ነገር ያደረግህብን ለምንድን ነው? ከሰዎቻችን አንዱ ሚስትህን ቢደፍራት ኖሮ በእኛ ላይ በደል አስከትለህብን ነበር እኮ!” አለው።

11አቢሜሌክም፣ “ይህን ሰው ወይም ሚስቱን የነካ በሞት ይቀጣል” የሚል ትእዛዝ ለሕዝቡ ሁሉ አወጣ።

12ይስሐቅም በዚያች ምድር ዘር ዘራ፣ እግዚአብሔርም (ያህዌ) ባረከለትና በዚያኑ ዓመት መቶ ዕጥፍ አመረተ። 13ሰውየውም እጅግ ባለጠጋ እስኪሆን ድረስ ሀብት በሀብት ላይ እየተጨመረለት ሄደ። 14ብዙ የበግና የፍየል መንጋ፣ ብዙ ከብት፣ ብዙ አገልጋዮችም ስለ ነበሩት፣ ፍልስጥኤማውያን ተመቀኙት። 15ከዚህ የተነሣ ፍልስጥኤማውያን፣ አባቱ አብርሃም በሕይወት በነበረበት ጊዜ፣ የአብርሃም አገልጋዮች የቈፈሩአቸውን የውሃ ጒድጓዶች በሙሉ ዐፈር ሞልተው ደፈኑዋቸው።

16አቢሜሌክም ይስሐቅን፣ “ከእኛ ይልቅ ኀያል ሆነሃልና አገራችንን ልቀቅልን” አለው።

17ይስሐቅም ያን ቦታ ትቶ ሄደ፤ በጌራራ ሸለቆም ተቀመጠ። 18ይስሐቅም በአባቱ በአብርሃም ጊዜ ተቈፍረው የነበሩትን፣ አባቱ ከሞተ በኋላ ፍልስጥኤማውያን የደፈኑአቸውን የውሃ ጒድጓዶች እንደ ገና እንዲከፈቱ አደረገ፤ አባቱ ቀድሞ ባወጣላቸው ስምም መልሶ ጠራቸው።

19የይስሐቅ አገልጋዮች በሸለቆው ውስጥ ሲቈፍሩ፣ ከጒድጓዱ የሚፈልቅ ውሃ አገኙ።

20የጌራራ እረኞች ግን፣ “ውሃው የእኛ ነው” በማለት ከይስሐቅ እረኞች ጋር ጠብ አነሡ፤ ከዚህ የተነሣ ይስሐቅ ያን የውሃ ጒድጓድ ኤሴቅ26፥20 ኤሴቅ ማለት ክርክር ማለት ነው ብሎ ጠራው፤ በጒድጓዱ ምክንያት ተጣልተውታልና። 21አሁንም እንደ ገና ሌላ የውሃ ጒድጓድ ቈፈሩ፤ አሁንም ሌላ ግጭት ተፈጠረ፤ ስለዚህ የውሃ ጒድጓዱን ስጥና26፥21 ስጥና ማለት ተቃውሞ ማለት ነው ብሎ ጠራው። 22ይስሐቅም ያን ቦታ ትቶ ሌላ ስፍራ ላይ የውሃ ጒድጓድ አስቈፈረ፤ በዚህ ጊዜ ግን አንድም ሰው ጠብ አላነሣበትም፤ ስለዚህ ያን የውሃ ጒድጓድ፣ “አሁን እግዚአብሔር (ያህዌ) ሰፊ ቦታ ሰጥቶናል፤ እኛም በምድር ላይ እንበዛለን” ሲል ርኆቦት26፥22 ርኆቦት ማለት ክፍል (የቤት) ማለት ነው ብሎ ጠራው።

23ከዚያም ይስሐቅ ወደ ቤርሳቤህ ወጣ። 24በዚያም ሌሊት እግዚአብሔር (ያህዌ) ተገለጠለትና፣ “እኔ የአባትህ የአብርሃም አምላክ (ኤሎሂም) ነኝ፤ ከአንተ ጋር ነኝና አትፍራ፤ እባርክሃለሁ፤ ስለ አገልጋዬም ስለ አብርሃም ስል ዘርህን አበዛለሁ” አለው።

25ይስሐቅም በዚያ ስፍራ መሠዊያ ሠርቶ፣ የእግዚአብሔርን (ያህዌ) ስም ጠራ፤ ድንኳንም ተከለ፤ አገልጋዮቹም በዚያ የውሃ ጒድጓድ ቈፈሩ።

26አቢሜሌክም ከአማካሪው ከአዘኮትና ከሰራዊቱ አዛዥ ከፊኮል ጋር ከጌራራ ተነሥቶ ይስሐቅ ወዳለበት ስፍራ መጣ። 27ይስሐቅም፣ “ጠልታችሁኝ ካባረራችሁኝ በኋላ፣ አሁን ደግሞ ለምን መጣችሁ?” ብሎ ጠየቃቸው።

28እነርሱም እንዲህ አሉ፤ “እግዚአብሔር (ያህዌ) ከአንተ ጋር መሆኑን በግልጽ ተረድተናል፤ ስለዚህም፣ ‘በመሐላ የጸና ውል በመካከላችን መኖር አለበት’ አልን፤ ይህም በእኛና በአንተ መካካል የሚጸናውል ነው፤ አሁንም ከአንተ ጋር ስምምነት እናድርግ፤ 29አንተን እንዳልጐዳንህ፣ ነገር ግን በጎነትን እንዳሳየንህና በሰላም እንደ ሸኘንህ ሁሉ፣ አንተም ክፉ እንዳታደርግብን በመካከላችን ውል ይደረግ፤ አንተን እንደሆን መቼም እግዚአብሔር (ያህዌ) ባርኮሃል።” 30ይስሐቅም ድግስ ደግሶ፣ አበላቸው፤ አጠጣቸው። 31በማግስቱም በማለዳ ተነሥተው፣ በመካከላቸው መሐላ ፈጸሙ። ይስሐቅም አሰናበታቸው፤ እነርሱም በሰላም ሄዱ።

32በዚያኑ ዕለት፣ የይስሐቅ አገልጋዮች መጥተው ስለ ቈፈሩት የውሃ ጒድጓድ ነገሩት፤ “ውሃ እኮ አገኘን!” አሉት። 33እርሱም የውሃውን ጒድጓድ ሳቤህ26፥33 ሳቤህ ማለት መሐላ ወይም ሰባት ማለት ሊሆን ይችላል አለው፤ ከዚያም የተነሣ የከተማዪቱ ስም እስከ ዛሬ ድረስ ቤርሳቤህ ተብሎ ይጠራል።

34ዔሳው አርባ ዓመት በሆነው ጊዜ፣ የኬጢያዊውን የብኤሪን ልጅ ዮዲትን እንዲሁም የኬጢያዊውን የኤሎንን ልጅ ቤሴሞትን አገባ፤ 35በእነዚህም ሴቶች ምክንያት የይስሐቅና የርብቃ ልብ ያዝን ነበር።

Thai New Contemporary Bible

ปฐมกาล 26:1-35

อิสอัคและอาบีเมเลค

(ปฐก.12:10-20; 20:1-18)

1ต่อมาเกิดการกันดารอาหารในดินแดนนั้นอีกครั้งหนึ่งนอกเหนือจากการกันดารอาหารที่เคยเกิดขึ้นในสมัยอับราฮัม อิสอัคจึงไปหากษัตริย์อาบีเมเลคชาวฟีลิสเตียที่เมืองเกราร์ 2องค์พระผู้เป็นเจ้าทรงปรากฏแก่อิสอัคและตรัสว่า “อย่าลงไปอียิปต์ จงอยู่ในแผ่นดินนี้อย่างที่เราบอกเจ้า 3จงอาศัยในแผ่นดินนี้สักระยะหนึ่ง เพื่อเราจะอยู่ช่วยเจ้าและอวยพรเจ้า เพราะเราจะยกดินแดนทั้งหมดนี้ให้แก่เจ้ากับลูกหลานของเจ้า และจะทำให้คำปฏิญาณที่เราได้สาบานไว้กับอับราฮัมบิดาของเจ้าสำเร็จ 4เราจะทำให้ลูกหลานของเจ้ามีจำนวนมากมายเหมือนดวงดาวในท้องฟ้า และจะยกดินแดนทั้งหมดนี้ให้แก่พวกเขา และประชาชาติทั่วโลกจะได้รับพรผ่านทางวงศ์วาน26:4 หรือเมล็ดพันธุ์ของเจ้า 5ทั้งนี้เพราะอับราฮัมได้เชื่อฟังเราและรักษาข้อกำหนด คำบัญชา กฎหมาย และบทบัญญัติของเรา” 6ฉะนั้นอิสอัคยังคงอยู่ที่เมืองเกราร์

7เมื่อผู้คนที่นั่นถามเรื่องภรรยาของเขา เขาก็ตอบว่า “นางเป็นน้องสาวของข้าพเจ้า” เพราะเขาไม่กล้าบอกว่า “นางเป็นภรรยาของข้าพเจ้า” เขาคิดว่า “ผู้ชายถิ่นนี้อาจจะฆ่าฉันเพราะเรเบคาห์เป็นเหตุ เนื่องจากนางเป็นคนสวย”

8เมื่ออิสอัคอยู่ที่นั่นเป็นเวลานานแล้ว กษัตริย์อาบีเมเลคของชาวฟีลิสเตียมองลงมาจากหน้าต่างและเห็นอิสอัคคลอเคลียอยู่กับเรเบคาห์ภรรยาของเขา 9อาบีเมเลคจึงบัญชาให้นำตัวอิสอัคมาและกล่าวว่า “แท้จริงนางเป็นภรรยาของท่าน! ทำไมท่านจึงบอกว่า ‘นางเป็นน้องสาว’?”

อิสอัคตอบว่า “เพราะข้าพเจ้าคิดว่าตนเองอาจจะต้องตายเพราะนาง”

10อาบีเมเลคจึงกล่าวว่า “ทำไมท่านทำกับเราอย่างนี้? ถ้าหากว่ามีชายใดไปนอนกับภรรยาของท่าน ท่านก็จะนำความผิดมาตกอยู่กับพวกเรา”

11ดังนั้นอาบีเมเลคจึงออกคำสั่งถึงคนทั้งปวงว่า “ผู้ใดก็ตามที่ล่วงเกินชายคนนี้หรือภรรยาของเขา จะถูกประหารชีวิตอย่างแน่นอน”

12อิสอัคปลูกพืชผลในดินแดนนั้น และในปีเดียวกันก็เก็บเกี่ยวได้ร้อยเท่า เพราะองค์พระผู้เป็นเจ้าทรงอวยพรเขา 13เขาก็มั่งมีขึ้น ความมั่งคั่งของเขาก็เพิ่มพูนขึ้นทุกทีจนเขากลายเป็นคนใหญ่คนโต 14เขามีฝูงแพะแกะ วัว และคนรับใช้มากมายจนชาวฟีลิสเตียอิจฉา 15ดังนั้นพวกฟีลิสเตียจึงเอาดินถมบ่อน้ำทั้งหมดที่คนรับใช้ของอับราฮัมบิดาของเขาได้ขุดไว้ตั้งแต่สมัยที่อับราฮัมยังมีชีวิตอยู่

16แล้วอาบีเมเลคกล่าวกับอิสอัคว่า “ย้ายไปอยู่ที่อื่นเถิด ตอนนี้ท่านมีกำลังมากกว่าพวกเราแล้ว”

17อิสอัคจึงย้ายไปจากที่นั่นและตั้งถิ่นฐานในหุบเขาเกราร์ 18อิสอัคขุดบ่อน้ำต่างๆ ที่ขุดในสมัยอับราฮัมบิดาของเขาขึ้นมาใหม่ พวกฟีลิสเตียได้ถมบ่อน้ำเหล่านี้หลังจากที่อับราฮัมตายไป แล้วอิสอัคก็ตั้งชื่อให้บ่อน้ำตามชื่อเดิมที่บิดาเคยตั้งไว้

19คนรับใช้ของอิสอัคขุดพบบ่อน้ำจืดแห่งหนึ่งในหุบเขานั้น 20แต่คนเลี้ยงสัตว์เมืองเกราร์ทะเลาะกับคนเลี้ยงสัตว์ของอิสอัคและกล่าวว่า “น้ำนี้เป็นของเรา!” อิสอัคจึงตั้งชื่อบ่อน้ำนั้นว่าเอเสก26:20 แปลว่าโต้เถียง เพราะพวกเขาโต้เถียงกัน 21คนของอิสอัคจึงขุดบ่อน้ำขึ้นอีกบ่อหนึ่ง แต่มีการทะเลาะกันเรื่องบ่อน้ำนั้นด้วย ดังนั้นเขาจึงตั้งชื่อว่าสิตนาห์26:21 แปลว่าการเป็นศัตรูกัน 22เขาย้ายไปจากที่นั่นแล้วขุดบ่อน้ำอีกบ่อหนึ่ง คราวนี้ไม่มีใครมาทะเลาะเรื่องบ่อน้ำนั้น เขาจึงตั้งชื่อว่าเรโหโบท26:22 แปลว่าที่ว่าง เขากล่าวว่า “บัดนี้องค์พระผู้เป็นเจ้าได้ประทานที่ให้เราและเราจะเจริญรุ่งเรืองขึ้นในดินแดนนี้”

23จากที่นั่นเขาขึ้นไปยังเบเออร์เชบา 24องค์พระผู้เป็นเจ้าทรงปรากฏแก่เขาในคืนนั้นและตรัสว่า “เราคือพระเจ้าของอับราฮัมบิดาของเจ้า อย่ากลัวเลย เพราะเราอยู่กับเจ้า เราจะอวยพรเจ้า และจะให้ลูกหลานของเจ้าทวีจำนวนขึ้นเพราะเห็นแก่อับราฮัมผู้รับใช้ของเรา”

25อิสอัคจึงสร้างแท่นบูชาขึ้นที่นั่นและนมัสการออกพระนามของพระยาห์เวห์ เขาตั้งเต็นท์ที่นั่น และคนรับใช้ของเขาก็ขุดบ่อน้ำบ่อหนึ่งขึ้นที่นั่นด้วย

26ในระหว่างนั้น กษัตริย์อาบีเมเลคกับอาหุสซัทที่ปรึกษาส่วนพระองค์และแม่ทัพฟีโคล์ เดินทางจากเมืองเกราร์มาพบอิสอัค 27อิสอัคถามพวกเขาว่า “พวกท่านมาหาข้าพเจ้าทำไมในเมื่อพวกท่านเห็นว่าข้าพเจ้าเป็นศัตรูและขับไล่ข้าพเจ้าออกมา?”

28พวกเขาตอบว่า “พวกเราเห็นชัดว่าองค์พระผู้เป็นเจ้าสถิตอยู่กับท่าน ดังนั้นพวกเราจึงพูดว่า ‘ควรจะทำสัตย์สาบานตกลงกันระหว่างเรา’ คือระหว่างพวกเรากับท่าน ให้พวกเราทำสนธิสัญญากับท่าน 29ว่าท่านจะไม่ทำอันตรายพวกเราเหมือนที่พวกเราไม่ได้ทำร้ายท่าน แต่ได้ปฏิบัติต่อท่านอย่างดีเสมอมาและส่งท่านจากมาอย่างสันติ และบัดนี้ท่านได้รับพรจากองค์พระผู้เป็นเจ้า”

30อิสอัคจึงจัดงานเลี้ยงให้พวกเขา คนเหล่านั้นก็ได้กินดื่ม 31เช้าตรู่วันรุ่งขึ้น ต่างฝ่ายก็ให้สัตย์สาบานต่อกัน จากนั้นอิสอัคก็ส่งพวกเขาให้เดินทางต่อไป และพวกเขาก็จากไปอย่างสันติ

32ในวันนั้นเองคนรับใช้ของอิสอัคมาบอกเรื่องบ่อน้ำที่ขุดว่า “เราพบน้ำแล้ว!” 33เขาจึงตั้งชื่อบ่อนั้นว่าชิบาห์26:33 แปลว่าคำสัญญาหรือเจ็ดก็ได้ และเมืองนั้นจึงได้ชื่อว่าเบเออร์เชบา26:33 แปลว่าบ่อแห่งคำสัญญาหรือบ่อแห่งเจ็ดก็ได้ มาจนถึงทุกวันนี้

ยาโคบได้พรจากอิสอัค

34เมื่อเอซาวอายุได้สี่สิบปี เขาแต่งงานกับยูดิธ บุตรสาวของเบเออรีชาวฮิตไทต์ และกับบาเสมัท บุตรสาวของเอโลนชาวฮิตไทต์ 35พวกเขาทำให้อิสอัคกับเรเบคาห์ขมขื่นใจ