New Amharic Standard Version

ዘፍጥረት 22:1-24

አብርሃም ተፈተነ

1ከዚህ ሁሉ በኋላ እግዚአብሔር (ኤሎሂም) አብርሃምን ፈተነው፤ “አብርሃም!” አለው። እርሱም “አቤቱ አለሁ” አለ።

2እግዚአብሔርም (ኤሎሂም)፣ “የምትወደውን አንዱን ልጅህን፣ ይስሐቅን ይዘህ ወደ ሞሪያ ምድር ሂድ፤ እኔ በማመለክትህ በአንዱ ተራራ ላይ የሚቃጠል መሥዋዕት አድርገህ ሠዋው” አለው።

3በማግስቱ ጠዋት አብርሃም ማልዶ ተነሣ፤ አህያውን ጭኖ፣ ሁለት አገልጋዮቹንና ልጁን ይስሐቅን ይዞ፣ ለመሥዋዕት የሚበቃውን ዕንጨት ከቈረጠ በኋላ እግዚአብሔር (ኤሎሂም) ወዳመለከተው ቦታ ለመሄድ ጒዞውን ጀመረ፤ 4በሦስተኛው ቀን አብርሃም ቀና ብሎ ቦታውን ከሩቅ ተመለከተ፤ 5አገልጋዮቹንም “እናንተ አህያውን ይዛችሁ እዚህ ቈዩን፤ እኔና ልጄ ግን ወደዚያ ሄደን ለእግዚአብሔር ሰግደን እንመለሳለን” አላቸው።

6አብርሃም ለሚቃጠል መሥዋዕት የሚሆነውን ዕንጨት ወስዶ፣ ልጁን ይስሐቅን አሸከመው፤ እሳቱንና ቢላዋውንም ራሱ ያዘ። ሁለቱም አብረው ሄዱ። 7ይስሐቅም አባቱን አብርሃምን፣ “አባቴ ሆይ” አለው።

አብርሃምም፣ “እነሆኝ፤ አለሁ ልጄ” አለው።

ይስሐቅም፣ “እሳቱና ዕንጨቱ ይኸው፤ ነገር ግን የሚቃጠለው መሥዋዕት የት አለ?” ብሎ ጠየቀ።

8አብርሃምም፣ “ልጄ ሆይ፤ ለሚቃጠለው መሥዋዕት የሚሆነውን በግእግዚአብሔር ራሱ ያዘጋጃል (ኤሎሂም ይሬህሎ)” አለው። ሁለቱም አብረው ጒዞአቸውን ቀጠሉ።

9እግዚአብሔር (ኤሎሂም) ወዳመለከተው ቦታ እንደ ደረሱ፣ አብርሃም መሠዊያ ሠራ፤ በላዩም ላይ ዕንጨት ረበረበ፤ ልጁን ይስሐቅንም አስሮ በመሠዊያው ዕንጨት ላይ አጋደመው። 10ከዚያም ልጁን ለማረድ እጁን ዘርግቶ ቢላዋውን አነሣ። 11የእግዚአብሔር (ያህዌ) መልአክ ግን ከሰማይ፣ “አብርሃም፤ አብርሃም፤” ብሎ ጠራው፤

አብርሃምም፣ “እነሆ፤ አለሁ” አለ።

12እርሱም፣ “እጅህን በብላቴናው ላይ አታሳርፍ፤ ምንም ጒዳት አታድርስበት፤ እነሆ፤ እግዚአብሔርን (ኤሎሂም) እንደምትፈራ ተረድቻለሁ፤ ልጅህን፣ ያውም አንዱን ልጅህን ለእኔ ለመስጠት አልሳሳህምና” አለው።

13አብርሃም ቀና ብሎ ሲመለከት በቊጥቋጦ መካከል ቀንዶቹ የተጠላለፉ አንድ አውራ በግ ከበስተ ኋላው አየ፤ ወደዚያው ሄዶ በጉን አመጣና የሚቃጠል መሥዋዕት አድርጎ ሠዋው። 14ከዚህም የተነሣ አብርሃም የዚያን ስፍራ ስም፣ “እግዚአብሔር ያዘጋጃል (ያህዌ ይርኤ)” ብሎ ጠራው፤ እስከ ዛሬም ድረስ፣ “በእግዚአብሔር (ያህዌ) ተራራ ላይ ይዘጋጃል” ይባላል።

15የእግዚአብሔርም (ያህዌ) መልአክ አብርሃምን ከሰማይ ዳግመኛ ጠራው፤ 16እንዲህም አለው፤ “እግዚአብሔርም (ያህዌ) በራሴ ማልሁ አለ፤ አንዱን ልጅህን ለእኔ ለመስጠት አልሳሳህምና፣ 17በእርግጥ እባርክሃለሁ፤ ዘርህን እንደ ሰማይ ከዋክብት፣ እንደ ባሕር ዳር አሸዋም አበዛዋለሁ። ዘሮችህም የጠላቶቻቸውን ደጆች ይወርሳሉ፤ 18ቃሌን ስለ ሰማህ የምድር ሕዝቦች ሁሉ በዘርህ ይባረካሉ።”

19ከዚያም አብርሃም ወደ አገልጋዮቹ ተመለሰ፤ ተያይዘውም ወደ ቤርሳቤህ ሄዱ፤ አብርሃምም በቤርሳቤህ ኖረ።

የናኮር ልጆች

20ከዚህ በኋላ እንዲህ ተብሎ ለአብርሃም ተነገረው፤ “ሚልካም ደግሞ የልጆች እናት ሆናለች፤ ለወንድምህም ለናኮር ወንዶች ልጆችን ወልዳለች። 21እነርሱም የበኵር ልጁ ዑፅና ወንድሙ ቡዝ፣ የአራም አባት ቀሙኤል፣ 22ኮዛት፣ ሐዞ፣ ፊልዳሥ፣ የድላፍና ባቱኤል ናቸው።” 23ባቱኤልም ርብቃን ወለደ። ሚልካ ለአብርሃም ወንድም ለናኮር የወለደችለት እነዚህ ስምንት ወንዶች ልጆች ናቸው። 24ከእነዚህም ሌላ የናኮር ቁባት ሬናሕ ደግሞ ጥባሕ፣ ገአም፣ ተሐሽና ሞክሳ የተባሉ ወንዶች ልጆች ወለደችለት።

Thai New Contemporary Bible

ปฐมกาล 22:1-24

พระเจ้าทรงทดสอบอับราฮัม

1ต่อมาพระเจ้าทรงทดสอบอับราฮัม พระองค์ตรัสกับเขาว่า “อับราฮัมเอ๋ย!”

เขาทูลตอบว่า “ข้าพระองค์อยู่ที่นี่”

2แล้วพระเจ้าตรัสว่า “ขอเจ้าจงพาลูกชายของเจ้า ลูกชายเพียงคนเดียวของเจ้า ผู้ที่เจ้ารัก คืออิสอัค ไปยังแคว้นโมริยาห์ จงถวายเขาเป็นเครื่องเผาบูชาบนภูเขาแห่งหนึ่งซึ่งเราจะสำแดงแก่เจ้า”

3เช้าตรู่วันรุ่งขึ้น อับราฮัมลุกขึ้นและผูกอานลาของเขา เขาพาคนรับใช้สองคนกับอิสอัคบุตรชายไปด้วย เมื่อเขาได้ตัดฟืนพอสำหรับเครื่องเผาบูชาแล้วจึงมุ่งหน้าไปยังที่ซึ่งพระเจ้าตรัสบอกเขาไว้ 4เมื่อถึงวันที่สาม อับราฮัมเงยหน้าขึ้นและเห็นสถานที่นั้นแต่ไกล 5เขาพูดกับคนรับใช้ว่า “จงอยู่กับลาที่นี่ ขณะที่เรากับเด็กคนนี้ไปที่โน่น พวกเราจะนมัสการพระเจ้า แล้วพวกเราจะกลับมาหาเจ้า”

6อับราฮัมจึงเอาฟืนสำหรับเครื่องเผาบูชาใส่บ่าอิสอัค ตัวเขาเองถือมีดและไฟ ขณะที่ทั้งสองกำลังเดินไปด้วยกันนั้น 7อิสอัคพูดกับอับราฮัมบิดาของเขาขึ้นมาว่า “พ่อ”

อับราฮัมตอบว่า “อะไรหรือลูก?”

อิสอัคกล่าวว่า “ไฟกับฟืนก็มีอยู่ที่นี่แล้ว แต่ลูกแกะสำหรับเผาบูชาอยู่ที่ไหนเล่า?”

8อับราฮัมตอบว่า “ลูกเอ๋ย พระเจ้าจะจัดเตรียมลูกแกะสำหรับเผาบูชาไว้เอง” แล้วทั้งสองก็เดินต่อไปด้วยกัน

9เมื่อพวกเขามาถึงสถานที่ที่พระเจ้าทรงบอกไว้ อับราฮัมก็สร้างแท่นบูชาขึ้นและจัดฟืนไว้บนแท่นนั้น เขามัดอิสอัคลูกของเขา แล้ววางบนฟืนเหนือแท่นบูชา 10จากนั้นเขาเอื้อมมือหยิบมีดจะฆ่าลูกชายของตน 11แต่ทูตขององค์พระผู้เป็นเจ้าเรียกอับราฮัมจากฟ้าสวรรค์ว่า “อับราฮัม! อับราฮัม!”

เขาตอบว่า “ข้าพระองค์อยู่ที่นี่”

12ทูตสวรรค์กล่าวว่า “อย่าแตะต้องเด็กคนนั้น อย่าทำอะไรเขาเลย บัดนี้เรารู้แล้วว่าเจ้ายำเกรงพระเจ้า เพราะเจ้าไม่ได้หวงลูกชายของเจ้าจากเรา แม้เป็นลูกชายเพียงคนเดียวของเจ้า”

13อับราฮัมเงยหน้าขึ้นเห็นแกะผู้ตัวหนึ่ง22:13 สำเนา MT. ส่วนใหญ่ว่าแกะผู้ตัวหนึ่งข้างหลังเขา เขาของมันเกี่ยวติดอยู่กับพุ่มไม้ จึงไปจับแกะนั้นมาถวายเป็นเครื่องเผาบูชาแทนลูกชายของเขา 14ดังนั้นอับราฮัมจึงเรียกสถานที่นั้นว่า “พระยาห์เวห์จะทรงจัดเตรียมไว้” อย่างที่พูดกันทุกวันนี้ว่า “จะจัดเตรียมไว้บนภูเขาของพระยาห์เวห์”

15แล้วทูตขององค์พระผู้เป็นเจ้าร้องเรียกอับราฮัมจากฟ้าสวรรค์เป็นครั้งที่สอง 16และกล่าวว่า “องค์พระผู้เป็นเจ้าทรงประกาศว่า เราปฏิญาณโดยตัวของเราเองว่า ด้วยเหตุที่เจ้าทำเช่นนี้และไม่ได้หวงแม้กระทั่งลูกชายของเจ้า คือลูกชายเพียงคนเดียวของเจ้า 17เราจะอวยพรเจ้าแน่นอนและจะทำให้ลูกหลานของเจ้ามีจำนวนมากมายเหมือนดวงดาวในท้องฟ้า เหมือนเม็ดทรายที่ชายทะเล ลูกหลานของเจ้าจะครอบครองเมืองต่างๆ ของเหล่าศัตรูของพวกเขา 18และทุกประชาชาติทั่วโลกจะได้รับพรผ่านทางเชื้อสาย22:18 หรือเมล็ดพันธุ์ของเจ้า เพราะเจ้าได้เชื่อฟังเรา”

19แล้วอับราฮัมก็กลับมาหาคนรับใช้ และพากันกลับไปยังเมืองเบเออร์เชบา อับราฮัมอาศัยอยู่ที่เมืองเบเออร์เชบา

บรรดาบุตรของนาโฮร์

20ต่อมามีผู้แจ้งอับราฮัมว่า “มิลคาห์ได้เป็นแม่แล้ว นางได้คลอดลูกชายหลายคนให้แก่นาโฮร์น้องชายของท่าน คือ 21อูสบุตรหัวปี บูสน้องชายของเขา เคมูเอล (บิดาของอารัม) 22เคเสด ฮาโซ ปิลดาช ยิดลาฟ และเบธูเอล” 23เบธูเอลเป็นบิดาของนางเรเบคาห์ มิลคาห์ให้กำเนิดบุตรชายแปดคนนี้แก่นาโฮร์น้องชายของอับราฮัม 24นอกจากนี้นาโฮร์ยังมีบุตรชายอีกสี่คนซึ่งเกิดจากเรอูมาห์ภรรยาน้อย ได้แก่เทบาห์ กาฮัม ทาหาช และมาอาคาห์