New Amharic Standard Version

ዘፍጥረት 21:1-34

የይስሐቅ መወለድ

1እግዚአብሔር (ያህዌ) በተናገረው መሠረት ሣራን አሰባት፤ የገባውንም ተስፋ ፈጸመላት። 2ሣራ ፀነሰች፤ ልክ እግዚአብሔር (ኤሎሂም) ባለው ጊዜ ለአብርሃም ወንድ ልጅ ወለደችለት። 3አብርሃም፣ ሣራ የወለደችለትን ልጅ ስሙን ይስሐቅ21፥3 ይስሐቅ ማለት ይሥቃል ማለት ነው አለው። 4አብርሃም፣ እግዚአብሔር (ኤሎሂም) ባዘዘው መሠረት ልጁን ይስሐቅን በተወለደ በስምንተኛው ቀን ገረዘው። 5አብርሃም፣ ልጁ ይስሐቅ ሲወለድለት፣ ዕድሜው መቶ ዓመት ነበረ።

6ሣራም፣ “እግዚአብሔር (ኤሎሂም) ሣቅ አድሎኛል፤ ስለዚህ፣ ይህን የሚሰማ ሁሉ ከእኔ ጋር ይሥቃል” አለች። 7ደግሞም፣ “ለመሆኑ፣ ‘ሣራ ልጆች ታጠባለች’ ብሎ ለአብርሃም ማን ተናግሮት ያውቅ ነበር? ይኸው በስተርጅናው ወንድ ልጅ ወለድሁለት” አለች።

የአጋርና የእስማኤል መባረር

8ሕፃኑ አደገ፤ ጡት መጥባቱንም ተወ። አብርሃምም ይስሐቅ ጡት በጣለባት ዕለት ታላቅ ድግስ ደገሰ። 9በሌላ በኩል ደግሞ፣ ግብፃዊቷ አጋር ለአብርሃም የወለደችለት እስማኤል፣ በይስሐቅ ሲያሾፍበት ሣራ አየች፤ 10አብርሃምንም፣ “ይህችን ባሪያ ከነልጇ አባርልኝ፤ ምንም ቢሆን የዚህች ባሪያ ልጅ፣ ከልጄ ከይስሐቅ ጋር ውርስ አይካፈልም አለች።”

11እስማኤል ልጁ ስለ ሆነ ነገሩ አብርሃምን እጅግ አስጨነቀው። 12እግዚአብሔርም (ኤሎሂም) አብርሃምን እንዲህ አለው፤ “ስለ ልጁም ሆነ ስለ አገልጋይህ አሳብ አይግባህ፤ ዘር የሚጠራልህ በይስሐቅ በኩል ስለ ሆነ፣ ሣራ የምትልህን ሁሉ ስማ። 13የአገልጋይህም ልጅ የራስህ ልጅ ስለ ሆነ፣ እርሱንም ታላቅ ሕዝብ አደርገዋለሁ።”

14በማግስቱ አብርሃም ማልዶ ተነሣ። ጥቂት ምግብ ወስዶ፣ ውሃ በእርኮት አድርጎ ለአጋር ሰጣት፤ በትከሻዋም አሸክሞአት ከነልጇ አሰናበታት። እርሷም ሄደች፤ በቤርሳቤህም ምድረ በዳ ትንከራተት ጀመር።

15በእርኮት የነበረው ውሃ ባለቀ ጊዜ፣ ልጁን ከአንድ ቊጥቋጦ ሥር አስቀመጠችው። 16ከዚያም፣ “ልጁ ሲሞት ዐይኔ አያይም” ብላ፣ የቀስት ውርወራ ያህል ርቃ ዐረፍ አለች፤ እርሷም21፥16 ዕብራይስጡና ሰብዐ ሊቃናት ልጁ ይላሉ። እየተንሰቀሰቀች ታለቅስ ጀመር።

17እግዚአብሔርም (ኤሎሂም) የልጁን ጩኸት ሰማ። የእግዚአብሔር (ኤሎሂም) መልአክ ከሰማይ አጋርን እንዲህ አላት፤ “አጋር ሆይ፤ ምን ሆነሻል? ልጅሽ ከተኛበት ሲያለቅስ እግዚአብሔር (ኤሎሂም) ሰምቶታል፤ ስለዚህ አትፍሪ። 18ተነሥተሽ ልጁን አንሺው፤ ያዢውም፤ ታላቅ ሕዝብ አደርገዋለሁና።”

19እግዚአብሔርም (ኤሎሂም) ዐይኖቿን ከፈተላት፤ የውሃ ጒድጓድም አየች፤ ሄዳም በእርኮቱ ውሃ ሞልታ ልጇን አጠጣች።

20እግዚአብሔር (ኤሎሂም) ከልጁ ጋር ነበር፤ ልጁም እያደገ ሄደ፤ መኖሪያውንም በምድረ በዳ ውስጥ አደረገ፤ ጐበዝ ቀስተኛም ሆነ። 21በፋራን ምድረ በዳ ሳለም፣ እናቱ ከግብፅ አንዲት ሴት አምጥታ አጋባችው።

በቤርሳቤህ የተደረገው ስምምነት

22በዚያን ጊዜ አቢሜሊክ ከሰራዊቱ አለቃ ከፊኮል ጋር ሆኖ አብርሃምን እንዲህ አለው፤ “በምታደርገው ነገር ሁሉ እግዚአብሔር (ኤሎሂም) ከአንተ ጋር ነው። 23እንግዲህ እኔንና ልጆቼን፣ ዘሬንም በመሸንገል አንዳች ክፉ ነገር እንዳታደርስብን በእግዚአብሔር (ኤሎሂም) ፊት ማልልኝ። እኔ ለአንተ ቸርነት እንዳደረግሁ፣ አንተም ለእኔና በእንግድነት ለተቀመጥህባት ለዚች ምድር ቸርነት አድርግ።”

24አብርሃምም፣ “እሺ፤ እምላለሁ” አለ።

25ከዚያም አብርሃም፣ የአቢሜሌክ አገልጋዮቹ ነጥቀው ስለያዙበት የውሃ ጒድጓድ መከፋቱን ለአቢሜሌክ ገለጠለት። 26አቢሜሌክም፣ “መቼም ይህን ድርጊት ማን እንደ ፈጸመ በበኩሌ አላውቅም፤ አንተም አልነገርኸኝም፤ ነገሩንም ገና አሁን መስማቴ ነው” አለው።

27ስለዚህ አብርሃም፣ በጎችና ከብቶች አምጥቶ ለአቢሜሌክ ሰጠው፤ ሁለቱም በመካከላቸው የስምምነት ውል አደረጉ። 28አብርሃም ከመንጋው ሰባት እንስት በጎች ለየ፤ 29አቢሜሌክም፣ “እነዚህን ሰባት እንስት በጎች ለይተህ ለብቻ ያቆምሃቸው ለምንድ ነው?” ሲል አብርሃምን ጠየቀው።

30አብርሃምም፣ “ይህን የውሃ ጒድጓድ የቈፈርሁ እኔ ለመሆኔ ምስክር እንዲሆን እነዚህን ሰባት እንስት በጎች እንካ ተቀበለኝ” አለው።

31ስለዚህ ቦታው፣ ሁለቱ ተማምለው የተስማሙበት ስፍራ በመሆኑ ቤርሳቤህ21፥31 ቤርሳቤህ ማለት ሰባት የውሃ ጒድጓድ ወይም የመሐላ የውሃ ጒድጓድ ማለት ሊሆን ይችላል። ተባለ።

32በቤርሳቤህ የስምምነት ውል ካደረጉ በኋላ፣ አቢሜሌክና የሰራዊቱ አለቃ ፊኮል ወደ ፍልስጥኤማውያን ምድር ተመለሱ። 33አብርሃምም በቤርሳቤህ የተምር ዛፍ ተከለ፤ በዚያም የዘላለም አምላክን (ኤል ኦላም) ስም ጠራ። 34አብርሃምም በፍልስጥኤማውያን ምድር ለረጅም ጊዜ በእንግድነት ኖረ።

Thai New Contemporary Bible

ปฐมกาล 21:1-34

กำเนิดอิสอัค

1องค์พระผู้เป็นเจ้าทรงเสด็จมาโปรดซาราห์ตามที่ตรัสไว้ และองค์พระผู้เป็นเจ้าทรงทำตามสัญญาที่ให้แก่ซาราห์ไว้ 2ซาราห์ตั้งครรภ์และให้กำเนิดบุตรชายแก่อับราฮัมเมื่อเขาชราแล้ว ตรงตามเวลาที่พระเจ้าได้ทรงสัญญาไว้กับเขา 3อับราฮัมตั้งชื่อบุตรที่ซาราห์คลอดให้ว่าอิสอัค21:3 แปลว่าเขาหัวเราะ 4เมื่ออิสอัคบุตรของเขาอายุครบแปดวัน อับราฮัมให้เขาเข้าสุหนัตตามที่พระเจ้าทรงบัญชาไว้ 5เมื่ออิสอัคบุตรของเขาเกิดมา อับราฮัมอายุได้หนึ่งร้อยปี

6ซาราห์กล่าวว่า “พระเจ้าทรงทำให้ฉันหัวเราะ ทุกคนที่ได้ยินเรื่องนี้จะพลอยหัวเราะไปกับฉันด้วย” 7และนางกล่าวอีกว่า “ใครจะคิดว่าซาราห์จะมีลูกให้กับอับราฮัม? แต่ฉันก็ได้คลอดลูกชายให้เขาเมื่อเขาชราแล้ว”

นางฮาการ์กับอิชมาเอลถูกขับไล่ออกจากบ้าน

8เด็กนั้นก็เติบโตขึ้นและหย่านม ในวันที่อิสอัคหย่านม อับราฮัมจัดงานเลี้ยงใหญ่ 9แต่ซาราห์เห็นบุตรของนางฮาการ์ชาวอียิปต์ที่เกิดแก่อับราฮัมกำลังหัวเราะเยาะ 10นางจึงพูดกับอับราฮัมว่า “จงไล่เมียทาสกับลูกของนางไปเถิด เพราะลูกของเมียทาสคนนั้นจะไม่มีวันมีส่วนร่วมในกองมรดกกับอิสอัคลูกชายของฉัน”

11เรื่องนี้ทำให้อับราฮัมทุกข์ใจมากเพราะเกี่ยวข้องกับบุตรชายของเขา 12แต่พระเจ้าตรัสกับเขาว่า “อย่าทุกข์ใจเรื่องเด็กคนนั้นกับเมียทาสของเจ้าเลย จงทำตามที่ซาราห์บอก เพราะเชื้อสาย21:12 หรือเมล็ดพันธุ์ของเจ้าจะนับทางอิสอัค 13และเราจะให้ชนชาติหนึ่งสืบเชื้อสายจากลูกของเมียทาสคนนี้ด้วย เพราะเขาก็เป็นเชื้อสายของเจ้าเหมือนกัน”

14เช้าตรู่วันรุ่งขึ้นอับราฮัมก็เอาอาหารและน้ำหนึ่งถุงหนังใส่บ่าของฮาการ์ แล้วส่งนางออกไปพร้อมกับบุตรชาย นางก็ระเหเร่ร่อนเข้าไปในถิ่นกันดารเบเออร์เชบา

15เมื่อน้ำในถุงหนังหมดแล้ว นางจึงทิ้งลูกชายไว้ใต้พุ่มไม้ 16แล้วเดินหนีไปนั่งอยู่ไม่ไกล ห่างออกไปประมาณระยะยิงธนูตก เพราะนางคิดว่า “ฉันไม่อาจทนดูลูกตายไป” และขณะนั่งอยู่ที่นั่น นาง21:16 ฉบับ LXX. ว่าเด็กหนุ่มคนนั้นก็เริ่มร้องไห้สะอึกสะอื้น

17พระเจ้าทรงได้ยินเสียงร้องของเด็กหนุ่ม ทูตของพระเจ้าเรียกฮาการ์จากฟ้าสวรรค์และพูดกับนางว่า “ฮาการ์เอ๋ย มีเรื่องอะไรหรือ? อย่ากลัวเลย พระเจ้าทรงได้ยินเสียงร้องของเด็กที่นอนอยู่ตรงนั้นแล้ว 18จงไปประคองเขาขึ้นและจูงมือเขาไป เพราะเราจะทำให้เขาเป็นชาติใหญ่ชาติหนึ่ง”

19แล้วพระเจ้าทรงเบิกตาของนาง นางก็เห็นบ่อน้ำแห่งหนึ่ง จึงไปเติมน้ำเต็มถุงหนังและให้เด็กหนุ่มนั้นดื่ม

20พระเจ้าสถิตกับเด็กหนุ่มคนนั้น ขณะที่เขาเติบโตขึ้น เขาอาศัยในถิ่นกันดารและกลายเป็นนักยิงธนู 21ขณะเขาอาศัยในถิ่นกันดารแห่งปาราน มารดาได้หาหญิงสาวจากอียิปต์มาเป็นภรรยาของเขา

สนธิสัญญาที่เบเออร์เชบา

22ครั้งนั้น อาบีเมเลคกับแม่ทัพฟีโคล์กล่าวกับอับราฮัมว่า “พระเจ้าสถิตกับท่านในทุกสิ่งที่ท่านทำ 23บัดนี้ขอให้ท่านปฏิญาณต่อหน้าพระเจ้าเถิดว่าท่านจะไม่หลอกเรา ไม่หลอกลูกหลานหรือเชื้อสายของเรา ให้จงรักภักดีต่อเราและต่อบ้านเมืองซึ่งท่านมาอาศัยเป็นคนต่างด้าวอยู่นี้เหมือนที่เราจงรักภักดีต่อท่าน”

24อับราฮัมกล่าวว่า “ข้าพเจ้าขอปฏิญาณ”

25แล้วอับราฮัมจึงร้องทุกข์ต่ออาบีเมเลคเรื่องบ่อน้ำแห่งหนึ่งที่บริวารของอาบีเมเลคยึดไป 26แต่อาบีเมเลคตอบว่า “เราไม่รู้ว่าใครทำเช่นนั้น ท่านไม่ได้บอกเรา และเราเพิ่งได้ยินเรื่องนี้วันนี้เอง”

27อับราฮัมจึงยกแกะและวัวให้อาบีเมเลค และชายทั้งสองก็ทำสนธิสัญญากัน 28อับราฮัมคัดลูกแกะตัวเมียเจ็ดตัวออกจากฝูง 29และอาบีเมเลคก็ถามอับราฮัมว่า “ลูกแกะตัวเมียเจ็ดตัวที่ท่านคัดออกมานี้มีความหมายอะไร?”

30เขาตอบว่า “ขอจงรับลูกแกะเจ็ดตัวนี้จากมือข้าพเจ้าเพื่อเป็นพยานหลักฐานว่าข้าพเจ้าเป็นผู้ขุดบ่อน้ำนี้”

31ที่แห่งนั้นจึงได้ชื่อว่าเบเออร์เชบา21:31 แปลว่าบ่อน้ำแห่งเจ็ดหรือบ่อน้ำแห่งสัตยาบันก็ได้เพราะทั้งสองได้ปฏิญาณร่วมกันที่นั่น

32หลังจากทำสนธิสัญญาที่เบเออร์เชบาแล้ว อาบีเมเลคกับแม่ทัพฟีโคล์ก็กลับสู่ดินแดนฟีลิสเตีย 33อับราฮัมได้ปลูกต้นสนหมอกต้นหนึ่งในเบเออร์เชบาและนมัสการร้องออกพระนามพระยาห์เวห์ พระเจ้าองค์นิรันดร์ 34และอับราฮัมก็อาศัยอยู่ในดินแดนของชาวฟีลิสเตียเป็นเวลานาน