New Amharic Standard Version

ዘፍጥረት 2:1-25

1የሰማያትና የምድር፣ በውስጣቸውም ያሉት ሁሉ አፈጣጠር በዚህ ሁኔታ ተከናወነ።

2እግዚአብሔር (ኤሎሂም) ይሠራ የነበረውን ሥራ በሰባተኛው ቀን ላይ ፈጽሞ ነበር፤ ስለዚህ ከሠራው ሥራ ሁሉ በሰባተኛው ቀን ዐረፈ።2፥2 ወይም አቈመ፤ በቍ 3 ላይም እንዲሁ 3እግዚአብሔር (ኤሎሂም) ሰባተኛውን ቀን ባረከው፤ ቀደሰውም፤ ካከናወነው የመፍጠር ሥራው ሁሉ ያረፈው በሰባተኛው ቀን ነውና።

አዳምና ሔዋን

4እግዚአብሔር አምላክ (ያህዌ ኤሎሂም) ሰማያትንና ምድርን በፈጠረ ጊዜ የተከናወኑት እንደዚህ ነበረ፤

እግዚአብሔር አምላክ (ያህዌ ኤሎሂም) ሰማያትንና ምድርን ሲፈጥር 5የሜዳ ቡቃያ ገና በምድር2፥5 ወይም መሬት፤ በቍ 6 ላይም እንዲሁ ላይ አልታየም፤ የሜዳ ተክልም ገና አልበቀለም፤ ምክንያቱም እግዚአብሔር አምላክ (ያህዌ ኤሎሂም) በመሬት ላይ ገና ዝናብ አላዘነበም ነበር፤ ምድርንም የሚያለማ ሰው አልነበረም። 6ነገር ግን ውሃ2፥6 ወይም ጭጋግ ከመሬት እየመነጨ የምድርን ገጽ ያረሰርስ ነበር። 7እግዚአብሔር አምላክ (ያህዌ ኤሎሂም) ከምድር ዐፈር ወስዶ ሰውን2፥7 በዕብራይስጥ ሰው (አዳም) የሚለው ቃል፣ መሬት (አዳማኽ) ከሚለው ቃል ጋር በድምፅ ይመሳሰላል፤ በፍቺም ሳይዛመድ አይቀርም፤ አዳም የመጀመሪያው ሰው ስምም ነው (ዘፍ 2፥20 ይመ) አበጀው፤ በአፍንጫውም የሕይወት እስትንፋስ እፍ አለበት፤ ሰውም ሕያው ነፍስ ሆነ።

8እግዚአብሔር አምላክ (ያህዌ ኤሎሂም) በምሥራቅ፣ በዔድን የአትክልት ስፍራ አዘጋጀ፤ ያበጀውንም ሰው በዚያ አኖረው። 9እግዚአብሔር አምላክም (ያህዌ ኤሎሂም) ለዐይን የሚያስደስት ለመብልም መልካም የሆነውን ዛፍ ሁሉ ከምድር አበቀለ፤ በአትክልቱ ቦታ መካከልም የሕይወት ዛፍ ነበረ፤ እንዲሁም መልካምና ክፉን መለየት የሚያስችለው የዕውቀት ዛፍ ነበረ።

10የአትክልት ስፍራውን የሚያጠጣ ወንዝ ከዔድን ይፈስ ነበር፤ ከዚያም በአራት ተከፍሎ ይወጣ ነበር። 11የመጀመሪያው፣ ወርቅ በሚገኝበት በሐዊላ ምድር ዙሪያ ሁሉ የሚፈሰው የፊሶን ወንዝ ነው። 12ኤውላጥ ምርጥ የሆነ ወርቅ፣ መልካም መዐዛ2፥12 ወይም መልካም ዕንቁ ያለው ከርቤና የከበረ ድንጋይ የሚገኙበት ምድር ነው። 13ሁለተኛው፣ በኢትዮጵያ2፥13 ደቡብ ምሥራቅ መስጴጦምያ ሊሆን ይችላል ምድር ዙሪያ ሁሉ የሚፈሰው የግዮን ወንዝ ነው። 14ሦስተኛው፣ ከአሦር በስተ ምሥራቅ የሚፈሰው የጤግሮስ ወንዝ ሲሆን፣ አራተኛው የኤፍራጥስ ወንዝ ነው።

15እግዚአብሔር አምላክ (ያህዌ ኤሎሂም) ሰውን ወስዶ እንዲያለማትና እየተንከባከበ እንዲጠብቃት በዔድን የአትክልት ስፍራ አስቀመጠው። 16እግዚአብሔር አምላክ (ያህዌ ኤሎሂም) ሰውን እንዲህ በማለት አዘዘው፤ “በአትክልት ስፍራው ውስጥ ከሚገኝ ከማንኛውም ዛፍ ፍሬ ትበላለህ። 17ነገር ግን መልካምና ክፉን ከሚያሳውቀው ዛፍ አትብላ፤ ምክንያቱም ከእርሱ በበላህ ቀን በርግጥ ትሞታለህ።”

18ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር አምላክ (ያህዌ ኤሎሂም)፣ “ሰው ብቻውን መሆኑ መልካም አይደለምና የሚስማማውን ረዳት አበጅለታለሁ” አለ።

19እግዚአብሔር አምላክ (ያህዌ ኤሎሂም) የዱር አራዊትንና የሰማይ ወፎችን ከምድር ሠርቶ ነበር፤ ለእያንዳንዳቸውም ምን ስም እንደሚያወጣላቸው ለማየት ወደ አዳም አመጣቸው። አዳም ሕይወት ላላቸው ፍጡራን ሁሉ ያወጣላቸው ስም መጠሪያቸው ሆነ። 20ስለዚህ አዳም2፥20 ወይም ሰው ለከብቶች፣ ለሰማይ ወፎች፣ ለዱር አራዊት ሁሉ ስም አወጣላቸው።

ይሁን እንጂ ለአዳም ተስማሚ ረዳት አልተገኘለትም ነበር። 21እግዚአብሔር አምላክም (ያህዌ ኤሎሂም) በአዳም ላይ ከባድ እንቅልፍ ጣለበት፤ አንቀላፍቶም ሳለ ከጐድኑ አንዲት ዐጥንት2፥21 ወይም ከሰው የጐን ክፍል ወስዶ ወስዶ፣ ስፍራውን በሥጋ ሞላው። 22እግዚአብሔር አምላክ (ያህዌ ኤሎሂም) ከአዳም የወሰዳትን ዐጥንት2፥22 ወይም ክፍል ሴት አድርጎ ሠራት፤ ወደ አዳምም አመጣት።

23አዳምም እንዲህ አለ፤

“እነሆ፤ ይህች ዐጥንት ከዐጥንቴ፣

ሥጋም ከሥጋዬ ናት።

ከወንድ ተገኝታለችና ሴት2፥23 ሰው የሚል ትርጒም ያለው የዕብራይስጥ ቃል ሴት የሚል ትርጒም ካለው የዕብራይስጥ ቃል ጋር ተመሳሳይ ድምፅ አለው ትባል።”

24ስለዚህ ሰው ከአባቱና ከእናቱ ተለይቶ ከሚስቱ ጋር ይጣመራል፤ ሁለቱም አንድ ሥጋ ይሆናሉ።

25አዳምና ሚስቱ፣ ሁለቱም ዕራቍታቸውን ነበሩ፤ ይሁን እንጂ አይተፋፈሩም ነበር።

Thai New Contemporary Bible

ปฐมกาล 2:1-25

1ดังนั้นสวรรค์และโลกพร้อมกับสรรพสิ่งทั้งปวงจึงถูกสร้างขึ้นสำเร็จครบถ้วน

2เมื่อถึงวันที่เจ็ดพระเจ้าก็ทรงเสร็จสิ้นจากพระราชกิจที่ทรงกระทำ ดังนั้นในวันที่เจ็ดพระองค์ทรงหยุดพักจากพระราชกิจทั้งปวงของพระองค์ 3และพระเจ้าทรงอวยพรวันที่เจ็ดและทรงตั้งขึ้นเป็นวันบริสุทธิ์ศักดิ์สิทธิ์ เพราะในวันนั้นพระองค์ทรงหยุดพักจากพระราชกิจในการทรงสร้างที่พระองค์ทรงกระทำ

อาดัมและเอวา

4นี่คือเรื่องราวการทรงสร้างสวรรค์และโลก เมื่อพระเจ้าพระยาห์เวห์ทรงสร้างโลกและสวรรค์

5ขณะนี้ยังไม่มีต้นไม้และพืชพันธุ์ในท้องทุ่งปรากฏขึ้นในโลก2:5 หรือแผ่นดินเช่นเดียวกับข้อ 6เลย เพราะว่าพระเจ้าพระยาห์เวห์ยังไม่ได้ประทานฝนลงมา ทั้งยังไม่มีมนุษย์ที่จะไถพรวนดิน 6แต่ก็มีน้ำ2:6 หรือหมอกพลุ่งขึ้นจากพื้นโลกและให้ความชุ่มชื้นแก่ผิวดินทั้งหมด 7แล้วพระเจ้าพระยาห์เวห์ทรงปั้นมนุษย์2:7 ในภาษาฮีบรูคำที่มีความหมายว่ามนุษย์หรือชาย(อดัม) มีเสียงคล้ายและอาจเกี่ยวข้องกับคำที่มีความหมายว่าพื้นดิน(อดามาห์) คำนี้เป็นชื่อของอาดัมด้วย (ดู 2:20)จากธุลีดินและทรงระบายลมหายใจแห่งชีวิตเข้าไปทางจมูกของเขา มนุษย์จึงมีชีวิต

8พระเจ้าพระยาห์เวห์ได้ทรงสร้างสวนแห่งหนึ่งไว้ในเอเดนทางทิศตะวันออก และให้ชายที่ทรงสร้างขึ้นอาศัยอยู่ในสวนนั้น 9พระเจ้าพระยาห์เวห์ทรงให้ต้นไม้ทุกชนิดทั้งที่งดงามน่าดูและที่เหมาะเป็นอาหารงอกขึ้นในสวน ที่กลางสวนนั้นมีต้นไม้แห่งชีวิตและต้นไม้แห่งการรู้ดีรู้ชั่ว

10มีแม่น้ำสายหนึ่งจากเอเดนไหลมาหล่อเลี้ยงสวนนั้นแล้วแยกออกเป็นต้นน้ำสี่สาย 11สายที่หนึ่งชื่อปิโชน ไหลผ่านดินแดนฮาวิลาห์ที่ซึ่งมีแร่ทองคำ 12(ดินแดนนี้มีแร่ทองคำคุณภาพดี ยางไม้หอม2:12 หรือไข่มุก และพลอยด้วย) 13สายที่สองชื่อกิโฮน ไหลผ่านทั่วดินแดนคูช 14สายที่สามคือไทกริส ซึ่งไหลไปทางทิศตะวันออกของอัสชูร์ และสายที่สี่คือยูเฟรติส

15พระเจ้าพระยาห์เวห์ทรงกำหนดให้ชายผู้นั้นอยู่ในสวนเอเดน ให้เขาทำงานและดูแลรักษาสวนแห่งนั้น 16และพระเจ้าพระยาห์เวห์ทรงบัญชาเขาไว้ว่า “เจ้ามีอิสระที่จะกินผลจากต้นใดๆ ในสวนก็ได้ 17แต่เจ้าต้องไม่กินผลจากต้นแห่งการรู้ดีรู้ชั่ว เพราะถ้าเจ้ากินผลของมันเมื่อใด เจ้าจะตายแน่นอน”

18แล้วพระเจ้าพระยาห์เวห์ตรัสว่า “ไม่ควรให้ชายผู้นี้อยู่คนเดียว เราจะสร้างผู้อุปถัมภ์ที่เหมาะสมเท่าเทียมกับเขา”

19พระเจ้าพระยาห์เวห์ได้ทรงปั้นสัตว์และนกทุกชนิดขึ้นจากดิน พระองค์ทรงนำมายังชายผู้นั้นเพื่อดูว่าเขาจะเรียกมันว่าอย่างไร สัตว์เหล่านั้นก็ได้ชื่อตามที่เขาเรียก 20ดังนั้นชายผู้นั้นจึงตั้งชื่อให้กับสัตว์เลี้ยงทั้งปวง นกในอากาศ และสัตว์ในท้องทุ่งทั้งสิ้น

แต่อาดัม2:20 หรือชายผู้นั้นยังไม่พบผู้อุปถัมภ์ที่เหมาะสมเท่าเทียมสำหรับเขา 21พระเจ้าพระยาห์เวห์จึงทรงบันดาลให้ชายนั้นหลับสนิท จากนั้นทรงชักกระดูกซี่โครงของเขาออกมาซี่หนึ่ง2:21 หรือทรงนำส่วนหนึ่งจากสีข้างของชายผู้นั้นมาและทรงปิดเนื้อให้สนิทเข้าดังเดิม 22แล้วพระเจ้าทรงสร้างผู้หญิงขึ้นจากกระดูกซี่โครง2:22 หรือส่วนนั้นที่พระองค์ทรงนำออกมาจากชายนั้น และพานางมาหาเขา

23ชายผู้นั้นกล่าวว่า

“นี่คือกระดูกจากกระดูกของเรา

และเนื้อจากเนื้อของเรา

นางจะได้ชื่อว่า ‘หญิง2:23 เป็นการเล่นคำในภาษาฮีบรู เพราะคำที่มีความหมายว่าหญิงมาจากคำว่าอิชชา ซึ่งมีเสียงคล้ายกับคำว่าอิชที่มีความหมายว่าชาย

เพราะนางมาจากชาย”

24เพราะเหตุนี้ผู้ชายจะละจากบิดามารดาของตนไปผูกพันกับภรรยา และพวกเขาจะเป็นเนื้อเดียวกัน

25ชายนั้นกับภรรยาต่างเปลือยกายอยู่ และพวกเขาไม่รู้สึกละอายเลย