New Amharic Standard Version

ዘፍጥረት 18:1-33

ሦስቱ እንግዶች

1ቀትር ላይ አብርሃም በመምሬ ትልልቅ ዛፎች አቅራቢያ በምትገኘው ድንኳኑ ደጃፍ ተቀምጦ ሳለ እግዚአብሔር (ያህዌ) ተገለጠለት፤ 2ቀና ብሎም ሲመለከት፣ ሦስት ሰዎች ቆመው አየ፤ ወዲያውም ከድንኳኑ ደጃፍ ተነሥቶ፣ ፈጥኖ ወደ ሰዎቹ ሄደ፤ ወደ መሬት ዝቅ ብሎም እጅ ነሣ።

3አብርሃምም እንዲህ አለ፤ “ጌታዬ፤18፥3 ወይም ጌታ ሆይ በፊትህ ሞገስ አግኝቼ እንደሆነ፣ ባሪያህን አልፈህ አትሂድ፤ 4ጥቂት ውሃ ይምጣላችሁና እግራችሁን ታጠቡ፤ እዚህም ከዛፉ ሥር ዐረፍ በሉ። 5ወደ እኔ ወደ አገልጋያችሁ ከመጣችሁ፣ እህል ቀምሳችሁ ትበረቱ ዘንድ ምግብ ላቅርብላችሁና ጒዞአችሁን ትቀጥላላችሁ።”

እነርሱም፣ “መልካም፤ እንዳልኸው አድርግ” አሉት።

6አብርሃም በፍጥነት ሣራ ወዳለችበት ወደ ድንኳኑ ገብቶ፣ “ቶሎ ብለሽ ሦስት መስፈሪያ18፥6 22 ሊትር ገደማ ይሆናል ስልቅ ዱቄት አቡኪና ቂጣ ጋግሪ” አላት።

7ከዚያም ወደ መንጋው በጥድፊያ ሄዶ፣ አንድ ፍርጥም ያለ ሥጋው ገር የሆነ ጥጃ መርጦ ለአገልጋዩ ሰጠው፤ አገልጋዩም ጥጃውን ዐርዶ አዘጋጀው። 8አብርሃምም እርጎ፣ ወተትና የተዘጋጀውን የጥጃ ሥጋ አቀረበላቸው፤ ሲበሉም ዛፉሥር አጠገባቸው ቆሞ ነበር።

9እነርሱም አብርሃምን፣ “ሚስትህ ሣራ የት አለች?” ብለው ጠየቁት።

እርሱም፣ “ድንኳን ውስጥ ናት” አላቸው።

10እግዚአብሔርም (ያህዌ)18፥10 ዕብራይስጡ ከዚያም እርሱ ይለዋል “የዛሬ ዓመት በዚሁ ጊዜ በእርግጥ ተመልሼ እመጣለሁ፤ ሚስትህ ሣራ ወንድ ልጅ ትወልዳለች” አለው።

ሣራም በዚህ ጊዜ ከበስተ ጀርባው ካለው ከድንኳኑ ደጃፍ ሆና ትሰማ ነበር። 11በዚያን ጊዜ አብርሃምና ሣራ አርጅተው፣ ዕድሜአቸው ገፍቶ ነበር፤ ሣራም ልጅ የመውለጃዋ ዕድሜ ዐልፎ ነበር። 12ሣራ በልቧ፣ “ካረጀሁና ጌታዬም18፥12 ወይም ባሌ ከደከመ በኋላ በዚህ ነገር መደሰት ይሆንልኛል?” ብላ ሣቀች።

13እግዚአብሔርም (ያህዌ) አብርሃምን እንዲህ አለው፤ “ሣራ፣ ‘ካረጀሁ በኋላ ልጅ እንዴት አድርጌ እወልዳለሁ’ ስትል ለምን ሣቀች? 14ለእግዚአብሔር (ያህዌ) የሚሳነው ነገር አለን? የዛሬ ዓመት በተባለው ጊዜ ተመልሼ እመጣለሁ፤ ሣራም ልጅ ይኖራታል።”

15ሣራ ስለ ፈራች፣ “ኧረ አልሣቅሁም” ብላ ዋሸች።

እርሱ ግን፣ “ሣቅሽ እንጂ” አላት።

አብርሃም ስለ ሰዶም ማለደ

16ሰዎቹም ለመሄድ ሲነሡ፣ ቊልቊል ወደ ሰዶም ተመለከቱ፤ አብርሃምም ሊሸኛቸው አብሮአቸው ወጣ። 17እግዚአብሔርም (ያህዌ) እንዲህ አለ፤ “እኔ የማደርገውን ነገር ከአብርሃም እሰውራለሁን? 18አብርሃም በእውነት ታላቅና ብርቱ ሕዝብ ይሆናል፤ የምድር ሕዝቦችም ሁሉ በእርሱ ይባረካሉ። 19ትክክለኛና ቀና የሆነውን በማድረግ የእግዚአብሔርን (ያህዌ) መንገድ ይጠብቁ ዘንድ ልጆቹንና ከእርሱ በኋላ ቤተ ሰቦቹን እንዲያዝ መርጬዋለሁ፤ ይኸውም እግዚአብሔር (ያህዌ) ለአብርሃም የሰጠው ተስፋ ሁሉ እንዲፈጸም ነው።”

20ደግሞም እግዚአብሔር (ያህዌ) እንዲህ አለ፤ “በሰዶምና በገሞራ ላይ የሚሰማው ጩኸት እጅግ በዝቶአል፤ ኀጢአታቸውም እጅግ ከፍቶአል፤ 21አድራጎታቸው እኔ ዘንድ እንደ ደረሰው ጩኸት መሆኑን ለማየት ወደዚያው እወርዳለሁ፤ እንደዚያ ካልሆነም ዐውቃለሁ።”

22ሰዎቹም ፊታቸውን ወደ ሰዶም አቅንተው ሄዱ፤ አብርሃም ግን በእግዚአብሔር (ያህዌ) ፊት እንደ ቆመ ነበር።18፥22 ከማሶሬቲኩ ጽሑፍ ጋር ተመሳሳይ ሲሆን የጥንት ዕብራውያን የጻፉት ትውፊት ግን እግዚአብሔር ግን በአብርሃም ፊት እንደ ቆመ ነበር ይላል 23አብርሃምም ወደ እርሱ ቀረብ ብሎ እንዲህ አለ፤ “በእርግጥ ጻድቁን ከኀጢአተኛው ጋር አብረህ ታጠፋለህን? 24አምሳ ጻድቃን በከተማዪቱ ቢገኙ፣ በውኑ ነዋሪዎቹን ሁሉ ታጠፋለህን? በውስጧ ለሚገኙ አምሳ ጻድቃን ስትል ከተማዪቱን አትምርምን?18፥24 ወይም ይቅርታ ማድረግ ሊሆን ይችላል፤ ይህም በቍ 26 ላይ ያለውንም ጨምሮ ነው። 25እንዲህስ አይሁን፤ ጻድቁን ከኀጢአተኛው ጋር እንዴት ትገድለዋለህ? ይህን የመሰለው አድራጎት ከአንተ ይራቅ፤ የምድር ሁሉ ዳኛ18፥25 ወይም ገዥ በቅን አይፈርድምን?”

26እግዚአብሔርም (ያህዌ)፣ “በሰዶም ከተማ አምሳ ጻድቃን ባገኝ ለእነርሱ ስል አገሪቱን በሞላ እምራለሁ” አለ።

27ደግሞም አብርሃም እንዲህ አለ፤ “እኔ ከንቱ፣ ትቢያና ዐመድ ሆኜ ሳለሁ ከጌታ (አዶናይ) ጋር ለመናገር አንዴ ደፍሬአለሁ፤ 28ለመሆኑ ከአምሳው ጻድቃን አምስት ቢጐድሉ በአምስቱ ሰዎች ምክንያት መላ ከተማዋን ታጠፋለህን?”

እርሱም፣ “አርባ አምስት ጻድቃን ባገኝ አላጠፋትም” አለ።

29አብርሃምም እንደ ገና፣ “ምናልባት አርባ ጻድቃን ቢገኙስ?” አለ እርሱም፣ “ለአርባው ስል እምራታለሁ” አለ።

30ደግሞም አብርሃም፣ “ጌታዬ (አዶናይ) አይቈጣ፤ እባክህ ልናገር፤ ሠላሳ ጻድቃን ብቻ ቢገኙስ?”

እርሱም፣ “ሠላሳ ባገኝ አላጠፋትም” ብሎ መለሰ።

31አብርሃምም፣ “ከጌታ (አዶናይ) ጋር እናገር ዘንድ መቼም አንዴ ደፍሬአለሁና ምናልባት ሃያ ብቻ ቢገኙስ?” አለ።

እርሱም፣ “ሃያ ቢገኙ፣ ለእነርሱ ስል እምራታለሁ” አለ።

32አብርሃምም፣ “ጌታዬ (አዶናይ) አይቈጣ፤ አንድ ጊዜ ብቻ ልናገር፤ ምናልባት ዐሥር ብቻ ቢገኙስ?” አለ።

እርሱም “ስለ ዐሥሩ ስል አላጠፋትም” ብሎ መለሰ።

33እግዚአብሔር (ያህዌ) ከአብርሃም ጋር ንግግሩን ከጨረሰ በኋላ ሄደ፤ አብርሃምም ወደ ቤቱ ተመለሰ።

Thai New Contemporary Bible

ปฐมกาล 18:1-33

ผู้มาเยือนทั้งสาม

1องค์พระผู้เป็นเจ้าทรงปรากฏแก่อับราฮัมใกล้หมู่ต้นไม้ใหญ่ของมัมเร ขณะเขานั่งอยู่ที่ประตูเต็นท์ช่วงแดดร้อนจัด 2อับราฮัมเงยหน้าขึ้นและมองเห็นชายสามคนยืนอยู่ใกล้ๆ จึงรีบลุกออกไปต้อนรับและก้มคำนับจนถึงพื้น

3เขากล่าวว่า “ท่านเจ้าข้า18:3 หรือข้าแต่องค์พระผู้เป็นเจ้า หากท่านจะกรุณา โปรดอย่าผ่านผู้รับใช้ของท่านไป 4ให้ข้าพเจ้าเอาน้ำมาสักหน่อยเพื่อพวกท่านจะได้ล้างเท้าและพักใต้ร่มไม้นี้ 5ข้าพเจ้าจะได้หาอะไรมาให้พวกท่านรับประทาน เพื่อพวกท่านจะได้สดชื่นขึ้น แล้วค่อยเดินทางต่อไป ในเมื่อพวกท่านได้มาหาผู้รับใช้ของพวกท่านแล้ว”

พวกเขาตอบว่า “ดีแล้ว จงไปทำอย่างที่ท่านพูดเถิด”

6ดังนั้นอับราฮัมจึงรีบกลับเข้าไปในเต็นท์ ไปหาซาราห์และกล่าวว่า “เร็วเข้า เอาแป้งละเอียด 3 ถัง18:6 ภาษาฮีบรูว่า3 ซีห์คือประมาณ 16 กิโลกรัมมานวดและทำขนมปัง”

7จากนั้นเขาวิ่งไปที่ฝูงสัตว์ คัดเลือกลูกวัวเนื้อนุ่มรสดีมาตัวหนึ่ง และบอกให้คนใช้รีบจัดแจงปรุงเป็นอาหาร 8แล้วเขาก็ยกนมเนย กับเนื้อวัวที่ปรุงแล้วมาตั้งต่อหน้าพวกเขา ขณะที่พวกเขารับประทานอาหาร อับราฮัมยืนอยู่ใกล้พวกเขาใต้ต้นไม้นั้น

9พวกเขาถามว่า “ซาราห์ภรรยาของเจ้าอยู่ที่ไหน?”

เขาตอบว่า “นางอยู่ในเต็นท์”

10แล้วองค์พระผู้เป็นเจ้าตรัสว่า18:10 ภาษาฮีบรูว่าแล้วเขากล่าวว่า “เราจะกลับมาหาเจ้าอีกอย่างแน่นอนในปีหน้าเวลาราวๆ นี้ และซาราห์ภรรยาของเจ้าจะให้กำเนิดบุตรชายคนหนึ่ง”

ส่วนซาราห์กำลังฟังอยู่ที่ทางเข้าประตูเต็นท์ข้างหลังเขา 11ทั้งอับราฮัมกับซาราห์มีอายุมากแล้ว และซาราห์ก็ไม่มีประจำเดือนอีกแล้ว 12ดังนั้นซาราห์จึงหัวเราะกับตนเองขณะคิดอยู่ในใจว่า “ฉันก็อายุปูนนี้แล้ว และนายของฉัน18:12 หรือสามีของฉันก็แก่เฒ่าแล้ว ฉันจะยังมีเรื่องยินดีเช่นนี้อีกหรือ?”

13แล้วองค์พระผู้เป็นเจ้าตรัสกับอับราฮัมว่า “ทำไมซาราห์จึงหัวเราะและพูดว่า ‘คนแก่อย่างฉันยังจะมีลูกได้จริงๆ หรือ?’ 14มีอะไรยากเกินไปสำหรับองค์พระผู้เป็นเจ้าหรือ? เราจะกลับมาหาเจ้าตามเวลาที่กำหนดในปีหน้า และซาราห์จะให้กำเนิดบุตรชาย”

15ซาราห์กลัวจึงโกหกว่า “ข้าพระองค์ไม่ได้หัวเราะ”

แต่พระองค์ตรัสว่า “เจ้าหัวเราะจริงๆ”

อับราฮัมวิงวอนเพื่อเมืองโสโดม

16แล้วคนเหล่านั้นก็ลุกขึ้นจะจากไป พวกเขามองลงไปทางเมืองโสโดม และอับราฮัมเดินตามไปส่งพวกเขา 17แล้วองค์พระผู้เป็นเจ้าตรัสว่า “ควรหรือที่เราจะปิดบังสิ่งที่เราจะกระทำไม่ให้อับราฮัมรู้? 18ในเมื่ออับราฮัมจะเป็นชนชาติที่ยิ่งใหญ่และทรงอำนาจอย่างแน่นอน และทุกประชาชาติทั่วโลกจะได้รับพรผ่านทางเขา 19เพราะว่าเราได้เลือกเขา เพื่อเขาจะสั่งสอนลูกหลานและครัวเรือนของเขาที่จะมีมาภายหลัง ให้รักษาวิถีทางขององค์พระผู้เป็นเจ้าด้วยการทำสิ่งที่ถูกต้องและยุติธรรม เพื่อว่าองค์พระผู้เป็นเจ้าจะทำให้สิ่งที่พระองค์ทรงสัญญาไว้กับอับราฮัมเป็นจริง”

20แล้วองค์พระผู้เป็นเจ้าตรัสว่า “เสียงฟ้องร้องเมืองโสโดมกับโกโมราห์ก็ดังสนั่น และพวกเขาทำบาปมหันต์ 21จนเราต้องลงไปดูว่าสิ่งที่พวกเขาทำนั้นเลวร้ายอย่างเสียงฟ้องร้องที่ขึ้นมาถึงเราหรือไม่ ถ้าไม่จริง เราก็จะได้รู้”

22คนเหล่านั้นจึงหันหน้าเดินไปยังเมืองโสโดม แต่อับราฮัมยังยืนอยู่ต่อหน้าองค์พระผู้เป็นเจ้า18:22 สำเนาต้นฉบับภาษาฮีบรูโบราณว่าแต่องค์พระผู้เป็นเจ้ายังคงยืนอยู่ตรงหน้าอับราฮัม 23แล้วอับราฮัมเข้าไปหาพระองค์และทูลว่า “พระองค์จะทรงกวาดล้างคนชอบธรรมไปพร้อมกับคนชั่วหรือ? 24พระองค์จะทำอย่างไรถ้าหากว่ามีคนชอบธรรมห้าสิบคนในเมืองนั้น? พระองค์จะทรงกวาดล้างเมืองนั้นจริงๆ หรือ พระองค์จะไม่ทรงละเว้น18:24 หรืออภัยเช่นเดียวกับข้อ 26ชาวเมืองนั้นเพื่อเห็นแก่คนชอบธรรมห้าสิบคนในนั้นหรือ? 25พระองค์จะไม่ทรงทำอย่างนั้นแน่ พระองค์จะไม่ทรงประหารคนชอบธรรมไปพร้อมกับคนชั่ว หรือปฏิบัติต่อคนชอบธรรมเช่นเดียวกับคนอธรรมเลย พระองค์จะไม่ทรงทำอย่างนั้นแน่ องค์ตุลาการแห่งสากลโลกจะไม่ธำรงความยุติธรรมไว้หรือ?”

26องค์พระผู้เป็นเจ้าตรัสว่า “หากเราพบคนชอบธรรมห้าสิบคนในเมืองโสโดม เราจะละเว้นคนทั้งเมืองนั้นเพราะเห็นแก่พวกเขา”

27อับราฮัมทูลอีกว่า “ข้าพระองค์ซึ่งเป็นเพียงผงธุลีและขี้เถ้าไม่ควรอาจเอื้อมทูลขอต่อองค์พระผู้เป็นเจ้า 28แต่หากคนชอบธรรมขาดไปห้าคนจากห้าสิบคนเล่า? พระองค์จะยังทรงทำลายเมืองนั้นทั้งเมืองเพราะคนห้าคนหรือ?”

พระองค์ตรัสว่า “หากเราพบสี่สิบห้าคนที่นั่น เราจะไม่ทำลายเมืองนั้น”

29อับราฮัมจึงทูลอีกว่า “หากพบเพียงสี่สิบคนเล่าพระเจ้าข้า?”

พระองค์ตรัสว่า “เพื่อเห็นแก่สี่สิบคนนั้น เราจะไม่ทำลายเมืองนั้น”

30แล้วอับราฮัมจึงทูลว่า “ขอองค์พระผู้เป็นเจ้าอย่าได้ทรงพระพิโรธเลย ข้าพระองค์ขอกราบทูลอีก หากพบเพียงสามสิบคนที่นั่นเล่า?”

พระองค์ตรัสตอบว่า “เราจะไม่ทำลาย หากเราพบสามสิบคนที่นั่น”

31อับราฮัมทูลว่า “ในเมื่อข้าพระองค์ก็กล้าอาจเอื้อมกราบทูลองค์พระผู้เป็นเจ้าไปแล้ว หากพบเพียงยี่สิบคนเท่านั้นเล่า?”

พระองค์ตรัสว่า “เพื่อเห็นแก่ยี่สิบคน เราจะไม่ทำลายเมืองนั้น”

32แล้วอับราฮัมทูลว่า “ขอองค์พระผู้เป็นเจ้าอย่าทรงพระพิโรธเลย ข้าพระองค์ขอกราบทูลอีกเพียงครั้งเดียว หากพบแต่เพียงสิบคนเท่านั้นเล่า?”

พระองค์ตรัสตอบว่า “เพื่อเห็นแก่สิบคน เราจะไม่ทำลายเมืองนั้น”

33เมื่อองค์พระผู้เป็นเจ้าตรัสกับอับราฮัมจบแล้วก็เสด็จจากไป ส่วนอับราฮัมก็กลับบ้าน