New Amharic Standard Version

ዘፍጥረት 17:1-27

የግዝረት ኪዳን

1አብራም ዕድሜው 99 ዓመት በሆነ ጊዜ፣ እግዚአብሔር (ያህዌ) ተገልጦለት እንዲህ አለው፤ “እኔ ኤልሻዳይ”17፥1 ሁሉን የሚገዛ ማለት ነው ነኝ፤ በፊቴ ተመላለስ፤ ነቀፋም አይኑርብህ፤ 2በእኔና በአንተ መካከል የተመሠረተውን ኪዳን አጸናለሁ፤ ዘርህንም እጅግ አበዛለሁ።”

3አብራም በግንባሩ መሬት ላይ ተደፋ፤ እግዚአብሔርም (ኤሎሂም) እንዲህ አለው፤ 4“እነሆ፤ የምገባልህ ኪዳን ይህ ነው፤ የብዙ ሕዝቦች አባት ትሆናለህ። 5ከእንግዲህ ወዲያ ስምህ አብራም17፥5 አብራም ማለት የከበረ አባት ማለት ነው መባሉ ቀርቶ አብርሃም ይሆናል፤ የብዙ ሕዝቦች አባት አድርጌሃለሁና። 6ዘርህን እጅግ አበዛለሁ፤ ብዙ ሕዝብም አደርግሃለሁ፤ ነገሥታትም ከአንተ ይወጣሉ። 7በእኔና በአንተ፣ ከአንተም በኋላ ከዘርህ ጋር ከትውልድ እስከ ትውልድ የዘላለም ኪዳኔን እመሠርታለሁ፤ በዚህም የአንተና ከአንተም በኋላ የዘርህ አምላክ (ኤሎሂም) እሆናለሁ። 8ይህችን አሁን በእንግድነት የምትኖርባትን የከነዓንን ምድር በሙሉ ለአንተና ከአንተም በኋላ ለዘርህ ለዘላለም ርስት አድርጌ እሰጣለሁ፤ አምላካቸውም (ኤሎሂም) እሆናለሁ።”

9ከዚያም እግዚአብሔር (ኤሎሂም) አብርሃምን እንዲህ አለው፤ “በአንተም በኩል፣ አንተና ከአንተ በኋላ የሚመጣው ዘርህ ከትውልድ እስከ ትውልድ ኪዳኔን ትጠብቃላችሁ። 10አንተና ከአንተም በኋላ የሚመጣው ዘርህ የምትጠብቁት ኪዳን ይህ ነው፤ በመካከላችሁ ያለ ወንድ ሁሉ ይገረዝ። 11ስለዚህ ሁላችሁም ሸለፈታችሁን ትገረዛላችሁ፤ ይህም በእኔና በእናንተ መካከል ላለው ኪዳን ምልክት ይሆናል። 12የሚመጣውም ትውልድ ሁሉ፣ ማንኛውም ወንድ ልጅ፣ ስምንት ቀን ሲሞላው ይገረዝ፤ እንደዚሁም በቤትህ የተወለደውና ከውጭ በገንዘብ የተገዛ ባዕድ ሁሉ ይገረዝ። 13በቤትህ የተወለደም ሆነ በገንዘብህ የተገዛ ሁሉ መገረዝ አለበት፤ በሥጋችሁ የሚፈጸመው ይህ ኪዳኔ የዘላለም ኪዳን ይሆናል። 14የሥጋ ሸለፈቱን ያልተገረዘ ማንኛውም ወንድ ኪዳኔን በማፍረሱ ከወገኖቹ ይወገድ።”

15እግዚአብሔር (ኤሎሂም) አብርሃምን እንዲህ አለው፤ “ሦራን ከእንግዲህ ሦራ ብለህ አትጠራትም፤ ስሟ ከዛሬ ጀምሮ ሣራ ይሁን። 16እኔ እባርካታለሁ ከእርሷም ወንድ ልጅ እሰጥሃለሁ፤ የብዙም ሕዝቦች እናት ትሆን ዘንድ እባርካታለሁ፤ የሕዝቦችም ነገሥታት ከእርሷ ይወጣሉ።”

17አብርሃምም በግንባሩ መሬት ላይ ተደፋ፤ ሣቀና በልቡ፣ “እንዲያው ምንስ ቢሆን የመቶ ዓመት ሽማግሌ የልጅ አባት መሆን ይችላልን? ሣራስ በዘጠና ዓመቷ ልጅ መውለድ ትችላለችን?” አለ። 18አብርሃም እግዚአብሔርን (ኤሎሂም)፣ “እስማኤልን ብቻ ባርከህ ባኖርህልኝ” አለው።

19እግዚአብሔርም (ኤሎሂም) እንዲህ አለ፤ “ይሁን እሺ፤ ነገር ግን ሚስትህ ሣራ ወንድ ልጅ ትወልድልሃለች፤ ስሙንም ይስሐቅ17፥19 ይስሐቅ ማለት ይሥቃል ማለት ነው ብለህ ትጠራዋለህ፤ እኔም ከእርሱ በኋላ ለዘሩ ሁሉ የሚሆን የዘላለም ኪዳን ከእርሱ ጋር እገባለሁ። 20ስለ እስማኤልም ቢሆን ልመናህን ሰምቼሃለሁ፤ እርሱንም እባርከዋለሁ፤ ፍሬያማም አደርገዋለሁ፤ እጅግም አበዛዋለሁ፤ የዐሥራ ሁለት አለቆች አባት ይሆናል፤ ታላቅም ሕዝብ አደርገዋለሁ። 21ኪዳኔን ግን የዛሬ ዓመት በዚሁ ጊዜ ሣራ ከምትወልድልህ ልጅ፣ ከይስሐቅ ጋር አደርጋለሁ።” 22እግዚአብሔር (ኤሎሂም) ከአብርሃም ጋር መነጋገሩን ከፈጸመ በኋላ ወደ ላይ ወጣ።

23በዚያችም ዕለት አብርሃም እግዚአብሔር (ያህዌ) ባዘዘው መሠረት ልጁን እስማኤልን፣ በቤቱ ውስጥ የተወለዱትንና ከውጭ በገንዘቡ የገዛቸውን ወንዶች በሙሉ ገረዛቸው። 24አብርሃም ሲገረዝ ዕድሜው 99 ዓመት ነበር። 25ልጁም እስማኤል ሲገረዝ 13 ዓመቱ ነበር። 26አብርሃምና ልጁ እስማኤል፣ ሁለቱም በዚያኑ ቀን ተገረዙ። 27በአብርሃም ቤት ያሉ ወንዶች ሁሉ፣ በቤቱ የተወለዱትም ሆኑ ከውጭ በገንዘብ የተገዙ ከእርሱ ጋር ተገረዙ።

Thai New Contemporary Bible

ปฐมกาล 17:1-27

พันธสัญญาแห่งการเข้าสุหนัต

1เมื่ออับรามอายุ 99 ปี องค์พระผู้เป็นเจ้าทรงปรากฏแก่เขาและตรัสว่า “เราคือพระเจ้าผู้ทรงฤทธิ์ จงดำเนินชีวิตอยู่ในทางของเราและเป็นคนดีพร้อม 2เราจะทำพันธสัญญาระหว่างเรากับเจ้า และจะทวีจำนวนพงศ์พันธุ์ของเจ้าอย่างมากมาย”

3อับรามจึงหมอบกราบซบหน้าลงและพระเจ้าตรัสกับเขาว่า 4“สำหรับเรา นี่คือพันธสัญญาของเรากับเจ้า คือเจ้าจะเป็นบิดาของชนชาติต่างๆ 5เขาจะไม่เรียกเจ้าว่าอับราม17:5 แปลว่าบิดาผู้ได้รับการยกย่องอีกต่อไป เจ้าจะมีชื่อว่าอับราฮัม17:5 แปลว่าบิดาของคนมากมาย เพราะเราได้ให้เจ้าเป็นบิดาของชนชาติต่างๆ 6เราจะให้เจ้ามีลูกมีหลานมากมาย เราจะให้หลายชนชาติเกิดขึ้นมาจากเจ้า และกษัตริย์หลายองค์จะสืบเชื้อสายจากเจ้า 7เราจะสถาปนาพันธสัญญาของเราไว้ เป็นพันธสัญญานิรันดร์ระหว่างเรากับเจ้า และกับลูกหลานของเจ้าทุกชั่วอายุที่จะตามมา เป็นพันธสัญญาว่าเราจะเป็นพระเจ้าของเจ้า และจะเป็นพระเจ้าของลูกหลานของเจ้าที่จะเกิดมาภายหลัง 8เราจะยกดินแดนคานาอันทั้งหมด คือที่เจ้าอาศัยอยู่อย่างคนต่างด้าวในขณะนี้ ให้เป็นกรรมสิทธิ์นิรันดร์ของเจ้ากับลูกหลานสืบไป และเราจะเป็นพระเจ้าของพวกเขา”

9แล้วพระเจ้าตรัสกับอับราฮัมว่า “สำหรับเจ้า เจ้าต้องรักษาพันธสัญญาของเรา คือทั้งตัวเจ้าและลูกหลานตลอดทุกชั่วอายุสืบไป 10นี่คือพันธสัญญาของเรากับเจ้าและกับลูกหลานที่จะมาภายหลังเจ้า เป็นพันธสัญญาที่เจ้าต้องรักษา คือชายทุกคนในพวกเจ้าจะต้องเข้าสุหนัต 11เจ้าต้องเข้าสุหนัต นี่จะเป็นเครื่องหมายแห่งพันธสัญญาระหว่างเรากับเจ้า 12ผู้ชายทุกคนในพวกเจ้าทุกชั่วอายุที่มีอายุแปดวันจะต้องเข้าสุหนัต รวมทั้งคนที่เกิดในครัวเรือนของเจ้าหรือซื้อมาจากคนต่างชาติซึ่งไม่ใช่วงศ์วานของเจ้า 13ไม่ว่าจะเป็นคนที่เกิดในครัวเรือนของเจ้าหรือเจ้าซื้อตัวมาก็ต้องเข้าสุหนัต พันธสัญญาของเราที่กายของเจ้าจะเป็นพันธสัญญานิรันดร์ 14ชายใดที่ไม่เข้าสุหนัต คือผู้ที่ไม่ได้เข้าสุหนัตฝ่ายกาย จะถูกตัดออกจากชนชาติของตน เพราะเขาได้ละเมิดพันธสัญญาของเรา”

15พระเจ้าตรัสกับอับราฮัมด้วยว่า “ส่วนซารายภรรยาของเจ้า เจ้าจะไม่เรียกนางว่าซารายอีกต่อไป นางจะชื่อว่าซาราห์ 16เราจะอวยพรนางและจะให้นางกำเนิดลูกชายคนหนึ่งแก่เจ้าอย่างแน่นอน เราจะอวยพรให้นางเป็นมารดาของชาติต่างๆ กษัตริย์ของชนชาติต่างๆ จะมาจากนาง”

17อับราฮัมหมอบกราบซบหน้าลง เขาหัวเราะและพูดกับตนเองว่า “ชายอายุร้อยปีจะมีลูกได้หรือ? และซาราห์จะให้กำเนิดลูกเมื่ออายุเก้าสิบหรือ?” 18และอับราฮัมทูลพระเจ้าว่า “ขอเพียงแต่พระองค์ทรงอวยพรชีวิตของอิชมาเอล!”

19แล้วพระเจ้าตรัสว่า “แต่ซาราห์จะคลอดลูกชายคนหนึ่งให้เจ้า และเจ้าจะเรียกเขาว่าอิสอัค17:19 แปลว่าเขาหัวเราะ เราจะสถาปนาพันธสัญญาของเรากับเขา เป็นพันธสัญญานิรันดร์แก่ลูกหลานของเขาที่จะมาภายหลัง 20สำหรับอิชมาเอล เราได้ฟังเจ้า เราจะอวยพรเขาอย่างแน่นอน เราจะทำให้เขามีลูกมีหลานและจะให้เขาทวีจำนวนขึ้นมากมาย เขาจะเป็นบิดาของเจ้านายสิบสองคน และเราจะทำให้เขาเป็นชนชาติยิ่งใหญ่ 21แต่พันธสัญญาของเรานั้น เราจะทำกับอิสอัคซึ่งซาราห์จะคลอดให้เจ้าปีหน้าในช่วงเวลานี้” 22เมื่อตรัสกับอับราฮัมจบแล้ว พระเจ้าก็เสด็จขึ้นไปจากเขา

23วันเดียวกันนั้นเอง อับราฮัมก็นำอิชมาเอลและชายทุกคนทั้งที่เกิดในครัวเรือนหรือซื้อมาด้วยเงินของเขามาเข้าสุหนัตตามที่พระเจ้าตรัสสั่งไว้ 24เวลานั้นอับราฮัมอายุ 99 ปีเมื่อเข้าสุหนัต 25และอิชมาเอลบุตรชายของเขาอายุ 13 ปี 26อับราฮัมกับอิชมาเอลบุตรชายของเขาเข้าสุหนัตในวันเดียวกัน 27และผู้ชายทุกคนในครัวเรือนของอับราฮัม ทั้งคนที่เกิดมาในครัวเรือนหรือซื้อมาจากคนต่างชาติได้เข้าสุหนัตด้วยกันกับเขา