New Amharic Standard Version

ዘፍጥረት 10:1-32

የኖኅ ልጆች ትውልድ

1የኖኅ ልጆች የሴም፣ የካምና የያፌት ትውልድ ይህ ነው፤ እነርሱም ራሳቸው ከጥፋት ውሃ በኋላ ወንዶች ልጆችን ወለዱ።

የያፌት ዝርያዎች

10፥2-5 ተጓ ምብ – 1ዜና 1፥5-7

2የያፌት ልጆች፦10፥2 ልጆች ማለት ዘርዐ ትውልዶች ወይም ወራሾች ወይም ሕዝቦች ማለት ሊሆን ይችላል፤ በቍ 3፡4፡6፡7፡20-23፡29 እና 31 እንዲሁ

ጋሜር፣ ማጎግ፣ ማዴ፣ ያዋን፣ ቶቤል፣ ሞሳሕ፣ ቴራስ ናቸው።

3የጋሜር ልጆች፦

አስከናዝ፣ ራፋት፣ ቴርጋማ ናቸው።

4የያዋን ልጆች፦

ኤሊሳ፣ ተርሴስ፣ ኪቲም፣ ሮዲኢ10፥4 ጥቂት የማሶሬቲክ የጥንት ጽሑፎች፣ ከኦሪተ ሳምራውያን፣ ሰብዐ ሊቃናትና አብዛኞቹ የማሶሬቲክ የጥናት ጽሑፎች የሚሉት ዶዳኒም ነው ናቸው። 5ከእነዚህም በየነገዳቸው፣ በየጐሣቸውና በየቋንቋቸው ተከፋፍለው በባሕር ዳርና በደሴቶች፣ በየምድራቸው የሚኖሩ ሕዝቦች ወጡ።

የካም ዝርያዎች

10፥6-20 ተጓ ምብ – 1ዜና 1፥8-16

6የካም ልጆች፦

ኩሽ፣ ምጽራይም፣ 10፥6 ቍ 13ትንም ጨምሮ ግብፅን ያመለክታልፉጥ፣ ከነዓን ናቸው።

7የኩሽ ልጆች፦

ሳባ፣ ኤውላጥ፣ ሰብታ፣ ራዕማ፣ ሰበቅታ ናቸው።

የራዕማ ልጆች፦

ሳባ፣ ድዳን ናቸው።

8ኩሽ የናምሩድ አባት10፥8 ቍ 13፡15፡24 እና 26ትን ጨምሮ አባት ማለት ቅድመ አያት ወይም ተተኪ ወይም መሥራች ማለት ሊሆን ይችላል። ነበረ፤ ናምሩድም በምድር ላይ ኀያል ሰው እየሆነ ሄደ። 9በእግዚአብሔር (ያህዌ) ፊት ብርቱ አዳኝ ነበረ፤ ስለዚህም፣ “በእግዚአብሔር (ያህዌ) ፊት እንደ ናምሩድ ብርቱ አዳኝ” ይባል ነበር። 10የግዛቱም የመጀመሪያ ከተሞች፦ ባቢሎን፣ ኦሬክ፣ አርካድና ካልኔ ናቸው፤ እነዚህ በ10፥10 ወይም ኦሬክና አርካድ፣ ሁሉም በ … ሰናዖር10፥10 ባቢሎን ነው ምድር ነበሩ። 11ከዚያም ምድር ወደ አሦር ወጥቶ ነነዌን፣ ረሆቦትን፣10፥11 ወይም ነነዌ ከነከተማዋ አደባባዮች ካለህን 12እንዲሁም በነነዌና በካለህ መካከል ሬስን ቈረቈረ፤ ታላቁንም ከተማ መሠረተ።

13ምጽራይም፦

የሉዳማውያን፣ የዕሚማውያን፣ ላህቢያውያን፣ የነፍታሌማውያን፣ 14የፈትሩሲማውያን፣ ፍልስጥኤማውያን የተገኙባቸው የኮስሉሂማውያን፣ የቀፍቶሪማውያን አባት ነበረ።

15ከነዓንም፦

የበኵር ልጁ10፥15 ወይም ከሲዶናውያን የመጀመሪያው የሲዶን፣ የኬጢያውያን፣ 16የኢያቡሳውያን፣ የአሞራውያን፣ የጌርሳው ያን አባት ነበረ፤ 17እንዲሁም የኤዊያውያን፣ የዑር ኬዋናውያን፣ የሲኒያውያን፣ 18የአራዴዎ ናውያን፣ የሰማሪናውያን፣ የአማቲያውያን አባት ነበረ።

ከጊዜ በኋላ የከነዓን ጐሣዎች በየስፍራው ተሠራጩ፤ 19የከነዓን ወሰን ከሲዶና አንሥቶ በጌራራ በኩል እስከ ጋዛ ይደርሳል፤ ከዚያም በሰዶም በኩል ገሞራን፣ አዳማንና ሰቦይን ይዞ እስከ ላሣ ይዘልቃል።

20እነዚህም በየጐሣቸውና በየቋንቋቸው፣ በየምድራቸውና በየነገዳቸው ይኖሩ የነበሩ የካም ዝርያዎች ናቸው።

የሴም ዝርያዎች

10፥21-31 ተጓ ምብ – ዘፍ 11፥10-27፤ 1ዜና 1፥17-27

21ለያፌት ታላቅ ወንድም10፥21 ወይም ሴም፣ የ … ታላቅ ወንድም ለሴም ደግሞ ወንዶች ልጆች ተወለዱለት፤ እርሱም የዔ ቦር ልጆች ሁሉ ቅደመ አያት ነው።

22የሴም ልጆች፦

ኤላም፣ አሦር፣ አርፋክስድ፣ ሉድ፣ አራም ናቸው።

23የአራም ልጆች፦

ዑፅ፣ ሁል፣ ጌቴር፣ ሞሶሕ10፥23 ሰብዐ ሊቃናትንና 1ዜና 1፥17 ይመ፤ በዕብራይስጡ ማሽ ይለዋል። ናቸው።

24አርፋክስድ ሳላን ወለደ፤10፥24 ከዕብራይስጡ ጋር ተመሳሳይ ሲሆን ሰብዐ ሊቃናት ግን የቃይናን አባት፣ ቃይናንም የ … አባት ነበረ ይላል

ሳላም ዔቦርን ወለደ።

25ለዔቦርም ሁለት ወንዶች ልጆች ተወለዱለት፤

አንደኛው ልጅ በዘመኑ ምድር ተከፍላ ስለ ነበር ፍሌቅ10፥25 ፍሌቅ ማለት ክፍፍል ማለት ነው ተባለ፤ ወንድሙም ዮቅጣን ተባለ።

26ዮቅጣንም፦ የኤልሞሳድ፣ የሣሌፍ፣ የሐስረ ሞት፣ የያራሕ፣ 27የሀደራም፣ የአውዛል፣ የደቅላ አባት ነበረ፤ 28እንዲሁም የዖባል፣ የአቢማኤል፣ የሳባ፣ 29የኦፊር፣ የኤውላጥ፣ የዮባል አባት ነበረ፤ እነዚህ ሁሉ የዮቅጣን ልጆች ናቸው።

30መኖሪያ ስፍራቸውም እስከ ሶፋር ድረስ ይዘልቃል።

31እነዚህም በየጐሣቸውና በየቋንቋቸው፣ በየምድራቸውና በየነገዳቸው ይኖሩ የነበሩ የሴም ዝርያዎች ናቸው።

32የኖኅ ወንዶች ልጆች ጐሣዎች እንደ ትውልዳቸው በየነገዳቸው እነዚህ ነበሩ። ከጥፋት ውሃ በኋላ ሕዝቦች በምድር ላይ የተሠራጩት ከእነዚሁ ነው።

Japanese Contemporary Bible

創世記 10:1-32

10

セム、ハム、ヤペテの子孫

1ノアの三人の息子セム、ハム、ヤペテの家系は次のとおりです。以下は、洪水のあと三人に生まれた子どもたちです。

2ヤペテの子孫はゴメル、マゴグ、マダイ、ヤワン、トバル、メシェク、ティラス。

3ゴメルの子孫はアシュケナズ、リファテ、トガルマ。

4ヤワンの子孫はエリシャ、タルシシュ、キティム、ドダニム。

5この人たちの子孫は各地に散らばり、海に沿ってそれぞれの言語を持つ国々をつくりました。

6ハムの子孫はクシュ、ミツライム、プテ、カナン。

7クシュの子孫はセバ、ハビラ、サブタ、ラマ、サブテカ。

ラマの子孫はシェバ、デダン。

8クシュの子孫の一人に、ニムロデという人がいました。地上で最初の王になった人です。 9彼は神に祝福された力ある狩猟家で、その名が知れ渡っていました。「神に祝福された力ある狩猟家ニムロデのような人」という称賛のことばもあったほどです。 10彼は帝国をシヌアルの地に建て、バベル、エレク、アカデ、カルネなどを中心に栄えました。 11-12領土はやがてアッシリヤまで広がりました。ニネベ、レホボテ・イル、ケラフ、ニネベとケラフの間にあるレセンなどは、みな彼が建てた大きな町です。特にレセンは、王国の中でも重要な町でした。

13-14ミツライムは、次の地域に住みついた人たちの先祖となりました。ルデ、アナミム、レハビム、ナフトヒム、パテロス、ペリシテ人が出たカスルヒム、カフトル。

15-19カナンの長男はシドンで、ヘテも彼の子です。カナンの子孫から次の氏族が分かれ出ました。エブス人、エモリ人、ギルガシ人、ヒビ人、アルキ人、シニ人、アルワデ人、ツェマリ人、ハマテ人。カナンの子孫はやがて、シドンからガザ地区のゲラルに至る一帯に進出し、さらにソドム、ゴモラ、アデマ、ツェボイム、そしてレシャの近くまで広がりました。

20以上がハムの子孫で、たくさんの国や地方に散らばり、多くの国語を話すようになりました。

21ヤペテの兄セムはエベルのすべての子孫の父祖となりました。 22セムの子孫は次のとおりです。エラム、アシュル、アルパクシャデ、ルデ、アラム。

23アラムの子孫はウツ、フル、ゲテル、マシュ。

24アルパクシャデの息子はシェラフで、シェラフの息子がエベルです。

25エベルには二人の息子が生まれました。ペレグ〔「分裂」の意〕とヨクタンです。ペレグという名の由来は、彼の時代に世界が分裂し、人々が散らされたからです。

26-30ヨクタンの子孫はアルモダデ、シェレフ、ハツァルマベテ、エラフ、ハドラム、ウザル、ディクラ、オバル、アビマエル、シェバ、オフィル、ハビラ、ヨバブ。ヨクタンの子孫はみな、メシャからセファルに至る東部の丘陵地帯に住みつきました。

31以上がセムの子孫です。それぞれを政治区分、国語、地理的な位置などによって分けると、このようになります。

32これらの人々はみなノアの子孫の家系で、洪水のあと何世代にもわたって、彼らからいろいろな国が興ってきたのです。