New Amharic Standard Version

ዘሌዋውያን 9:1-24

ካህናቱ አገልግሎታቸውን ጀመሩ

1በስምንተኛውም ቀን ሙሴ አሮንንና ልጆቹን እንዲሁም የእስራኤልን ሽማግሌዎች ጠራቸው፤ 2አሮንንም እንዲህ አለው፤ “የኀጢአት መሥዋዕት እንዲሆንልህ አንድ እንቦሳ እንዲሁም የሚቃጠል መሥዋዕት እንዲሆንልህ አንድ አውራ በግ፣ ወስደህ፣ በእግዚአብሔር (ያህዌ) ፊት አቅርባቸው፤ ሁለቱም እንከን የሌለባቸው ይሁኑ። 3እስራኤላውያንንም እንዲህ በላቸው፤ ‘ለኀጢአት መሥዋዕት አንድ አውራ ፍየል፣ ለሚቃጠል መሥዋዕት እንከን የሌለባቸውን የአንድ ዓመት እምቦሳና የአንድ ዓመት ጠቦት፣ 4ለኅብረት መሥዋዕት9፥4 በትውፊት የሰላም መሥዋዕት ይባላል፤ እንዲሁም ቍ 18፥22 ይመ። አንድ በሬና9፥4 የዕብራይስጥ ቃል ተባዕትና እንስትን ሊያጠቃልል ይችላል፤ እንዲሁም ቍ 18፡19 ይመ አንድ አውራ በግ በዘይት ከተለወሰ የእህል ቊርባን ጋር በእግዚአብሔር (ያህዌ) ፊት ለመሠዋት አቅርቡ፤ እግዚአብሔር (ያህዌ) ዛሬ ይገለጥላችኋልና።’ ”

5እነርሱም ሙሴ ያዘዛቸውን ሁሉ ወደ መገናኛው ድንኳን ደጃፍ አመጡ፤ ሕዝቡም በሙሉ ቀርበው በእግዚአብሔር (ያህዌ) ፊት ቆሙ። 6ሙሴም፣ “የእግዚአብሔር (ያህዌ) ክብር ይገለጥላችሁ ዘንድ፣ እንድታደርጉት እግዚአብሔር (ያህዌ) ያዘዛችሁ ይህ ነው” አለ።

7ሙሴ አሮንን፣ ወደ መሠዊያው ቀርበህ የኀጢአት መሥዋዕትህንና የሚቃጠለውን መሥዋዕትህን ሠዋ፤ ለራስህና ለሕዝቡም አስተሰርይ፤ እግዚአብሔርም (ያህዌ) ባዘዘው መሠረት የሕዝቡን መሥዋዕት አቅርብ፤ አስተሰርይላቸውም” አለው።

8አሮንም ወደ መሠዊያው መጥቶ ስለ ራሱ የኀጢአት መሥዋዕት የቀረበውን እምቦሳ ዐረደው። 9ልጆቹም ደሙን አመጡለት፤ እርሱም ጣቱን በደሙ ውስጥ ነክሮ የመሠዊያውን ቀንዶች ቀባ፤ የተረፈውንም ደም በመሠዊያው ግርጌ አፈሰሰው። 10እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴን ባዘዘው መሠረት የኀጢአት መሥዋዕቱን ሥብ፣ ኵላሊቶቹንና የጒበቱን ሽፋን በመሠዊያው ላይ አቃጠለው፤ 11ሥጋውንና ቊርበቱንም ከሰፈሩ ውጭ በእሳት አቃጠለው።

12ከዚህ በኋላ አሮን የሚቃጠለውን መሥዋዕት ዐረደ፤ ልጆቹ ደሙን አቀበሉት፤ እርሱም ደሙን በመሠዊያው ላይ ዙሪያውን ረጨ። 13ልጆቹም የሚቃጠለውን መሥዋዕት ብልት አንድ በአንድ፣ ጭንቅላቱን ሳይቀር አምጥተው ሰጡት፤ እርሱም በመሠዊያው ላይ አቃጠለው። 14የሆድ ዕቃውንና እግሮቹን አጥቦ በመሠዊያው ላይ ካለው ከሚቃጠለው መሥዋዕት በላይ አቃጠለ። 15አሮንም የሕዝቡን መሥዋዕት አቀረበ፤ ስለ ሕዝቡ የኀጢአት መሥዋዕት የሆነውን ፍየል ወስዶ ዐረደው፤ እንደ ፊተኛው ሁሉ ይህንም በኀጢአት መሥዋዕትነት ሠዋው።

16የሚቃጠለውንም መሥዋዕት አምጥቶ በሥርዐቱ መሠረት አቀረበው። 17የእህል ቊርባኑን አመጣ፤ ከላዩም እፍኝ ሙሉ ወስዶ ጧት ጧት ከሚቀርበው የሚቃጠል መሥዋዕት በተጨማሪ በመሠዊያው ላይ አቃጠለ።

18አሮንም ስለ ሕዝቡ የኅብረት መሥዋዕት የቀረቡትን በሬውንና አውራ በጉን ዐረደ፤ ልጆቹም ደሙን አመጡለት፤ እርሱም ደሙን በመሠዊያው ላይ ዙሪያውን ረጨ። 19የበሬውንና የአውራ በጉን ሥብ፦ ላቱን፣ የሆድ ዕቃውን የሚሸፍነውን ሥብ፤ ኵላሊቶቹንና የጒበቱን ሽፋን፣ 20በፍር ምባዎቹ ላይ አስቀመጡ፤ አሮንም ሥቡን በመሠዊያው ላይ አቃጠለ፤ 21ፍርምባዎቹንና የቀኝ ወርቹንም ሙሴ ባዘዘው መሠረት፣ የመወዝወዝ መሥዋዕት አድርጎ በእግዚአብሔር (ያህዌ) ፊት ወዘወዘው።

22አሮንም እጆቹን ወደ ሕዝቡ ዘርግቶ ባረካቸው፤ የኀጢአት መሥዋዕቱን፣ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የኅብረቱን መሥዋዕት ካቀረበ በኋላ ወረደ።

23ከዚህ በኋላ፣ ሙሴና አሮን ወደ መገናኛው ድንኳን ገቡ፤ ከዚያ ሲወጡም ሕዝቡን ባረኩ፤ የእግዚአብሔርም (ያህዌ) ክብር ለሕዝቡ ሁሉ ተገለጠ። 24እሳት ከእግዚአብሔር (ያህዌ) ዘንድ ወጥቶ፣ በመሠዊያው ላይ የነበረውን በላ፤ ሕዝቡም ሁሉ ይህን ባዩ ጊዜ እልል አሉ፤ በግምባራቸውም ተደፉ።

Korean Living Bible

레위기 9:1-24

제사장의 직무가 시작되다

1위임식이 끝난 다음날 모세는 아론과 그의 아들들과 이스라엘 장로들을 불 러 놓고

2아론에게 말하였다. “속죄제물로 흠 없는 수송아지 한 마리와 번제물로 흠 없는 숫양 한 마리를 끌어다가 여호와께 바친 다음

3이스라엘 백성에게 이렇게 말하십시오. ‘여러분은 속죄제물로 숫염소 한 마리와 번제물로 흠이 없고 일 년 된 송아지와 어린 양 한 마리씩,

4그리고 화목제물로 여호와 앞에 드릴 수소 한 마리와 숫양 한 마리를 끌어오고 기름 섞은 곡식 예물을 가져오십시오. 오늘 여호와께서 여러분에게 나타나실 것입니다.’ ”

5백성들이 모세가 명령한 대로 이 모든 것을 성막 입구로 가져오고 전체 백성이 여호와 앞에 나와 서자

6모세는 그들에게 “이것은 여호와께서 여러분에게 명령하신 일이므로 여호와의 영광이 여러분에게 나타날 것입니다” 하고

7또 아론에게 이렇게 말하였다. “형님은 제단으로 나아가 여호와께서 명령하신 대로 먼저 형님 자신의 죄를 위해 속죄제와 번제를 드린 다음 백성의 죄를 위해서도 그렇게 하십시오.”

8그래서 아론이 제단으로 나아가 자기 죄를 속할 속죄제물로 수송아지를 잡자

9그의 아들들이 피를 받아 그에게 주었다. 그래서 그는 손가락으로 그 피를 찍어 단 네 뿔에 바르고 나머지 피는 단 밑에 쏟았다.

10그리고 아론은 여호와께서 명령하신 대로 그 제물의 기름과 콩팥과 간 꺼풀을 단에서 불로 태워 바치고

11그 고기와 가죽은 야영지 밖으로 가지고 가서 불에 태웠다.

12그런 다음 아론은 번제물을 잡았는데 그의 아들들이 피를 받아 그에게 주자 아론은 그것을 단 사면에 뿌렸다.

13또 아론은 그들에게서 그 제물의 각 뜬 고기와 머리를 받아 그것들을 단 위에서 불태우고

14내장과 다리는 씻어서 이것도 번제물 위에 올려놓고 불로 태웠다.

15그 후에 아론은 속죄제의 염소를 잡아 자기 죄를 위해 속죄제를 드릴 때와 마찬가지로 백성의 죄를 위해 드리고

16번제물도 여호와께서 지시하신 규정대로 드렸으며

17또 곡식으로 드리는 소제물을 가져다가 그 중에 한 움큼을 집어서 아침마다 정규적으로 드리는 번제물에 더하여 단에서 불태웠다.

18그런 다음 아론은 백성을 위해 화목제의 수소와 숫양을 잡았다. 그의 아들들이 그 피를 받아오자 그는 그것을 단 사면에 뿌렸다.

19그리고 그는 수소와 숫양의 기름과 기름진 꼬리와 내장에 덮인 기름과 콩팥과 간 꺼풀을 떼어다가

20그 제물들의 가슴 위에 얹어 단으로 가지고 가서 그 기름은 단에서 불태우고

21가슴과 뒷다리는 모세가 지시한 대로 여호와께 흔들어 바쳤다.

22아론은 속죄제와 번제와 화목제를 다 드리고 나서 백성을 향해 손을 들고 축복한 다음 단에서 내려왔다.

23모세와 아론이 성막에 들어갔다가 나와서 백성들을 축복하자 여호와의 영광의 광채가 모든 백성에게 나타났다.

24바로 그때 여호와 앞에서 불이 나와 단 위의 번제물과 기름을 완전히 태워 버렸다. 그러자 백성들이 이 광경을 보고 모두 놀라 소리를 지르며 땅에 엎드렸다.