New Amharic Standard Version

ዘሌዋውያን 5:1-19

1“ ‘አንድ ሰው ስላየውና ስለሚያውቀው ነገር ሕጋዊ ምስክርነቱን እንዲሰጥ ተጠይቆ ቃሉን ለመስጠት ፈቃደኛ ባይሆን፣ ይህ ሰው ኀጢአት ሠርቶአልና ይጠየቅበታል።

2“ ‘ማንኛውም ሰው ሳያውቅ በሥርዐቱ መሠረት የተከለከለውን ርኩስ ነገር ቢነካ፣ ይኸውም፦ የረከሰ የአውሬ በድን ወይም የረከሰ የቤት እንስሳ በድን ወይም በደረቱ እየተሳበ የሚንቀሳቀሰውን የረከሰ ፍጥረት በድን ቢነካ ይህ ሰው ረክሶአል፤ በደለኛም ነው።

3“ ‘ወይም የሰውን ርኵሰት ይኸውም ርኵስ የሚያደርገውን ማናቸውንም ነገር ሳያውቅ ቢነካ፣ ነገሩን ባወቀ ጊዜ በደለኛ ይሆናል።

4“ ‘ሰዎች በሚምሉበት በማናቸውም ነገር፣ በጎ ወይም ክፉ ለማድረግ ሳያስብ በግዴለሽነት ቢምል በኋላ ግን ነገሩን ባወቀ ጊዜ በደለኛ ይሆናል።

5“ ‘ማንኛውም ሰው ከእነዚህ በአንዱ በደለኛ ሆኖ ቢገኝ፣ የትኛውን ኀጢአት እንደሠራ ገልጾ መናዘዝ አለበት፤ 6ስለ ኀጢአቱም ቅጣት የኀጢአት መሥዋዕት እንድትሆነው ከመንጋው አንዲት የበግ ወይም የፍየል እንስት ለእግዚአብሔር (ያህዌ) ያቅርብ፤ ካህኑም ስለ ኀጢአቱ ያስተሰረይለታል።

7“ ‘ሰውየው ስለ ሠራው ኀጢአት በግ ለማቅረብ ዐቅሙ ካልፈቀደ ሁለት ዋኖሶች ወይም ሁለት የዋኖስ ጫጩቶች የመጀመሪያውን ለኀጢአት መሥዋዕት፣ ሁለተኛውን ለሚቃጠል መሥዋዕት ለእግዚአብሔር (ያህዌ) ያቅርብ። 8ወደ ካህኑም ያምጣቸው፤ እርሱም ለኀጢአት መሥዋዕት የምትሆነውን አስቀድሞ ያቅርብ፤ ራሷን ዐንገቷ ላይ ይቈልምም፤ ነገር ግን ቈርጦ አይጣል፤ 9ከኀጢአት መሥዋዕቱም ጥቂት ደም ወስዶ በመሠዊያው ዙሪያ ላይ ይርጨው፤ የተረፈውም ደም ሁሉ በመሠዊያው ግርጌ ይፍሰስ፤ ይህም የኀጢአት መሥዋዕት ነው። 10ካህኑም ቀደም ሲል በታዘዘው መሠረት ሁለተኛዋን የሚቃጠል መሥዋዕት አድርጎ ያቅርብ፤ ካህኑም የሰውየውን ኀጢአት ያስተሰርይለታል፤ ሰውየውም ይቅር ይባላል።

11“ ‘ሰውየው ሁለት ርግቦች ወይም ሁለት የዋኖስ ጫጩቶች ለማቅረብ ዐቅሙ ካልፈቀደ፣ ስለ ሠራው ኀጢአት የኢፍ መስፈሪያ5፥11 ሁለት ሊትር ገደማ ይሆናል አንድ ዐሥረኛ የላመ ዱቄት ለኀጢአት መሥዋዕት ያቅርብ፤ ነገር ግን የኀጢአት መሥዋዕት ስለ ሆነ ዘይት አያፍስበት፤ ዕጣንም አይጨምርበት፤ 12ከዚያም ለካህኑ ያቅርብ፤ ካህኑም ለመታሰቢያ እንዲሆን ዕፍኝ ሙሉ ይዝገንለት፤ በእሳት ከሚቀርበውም ቊርባን በላይ አድርጎ ለእግዚአብሔር (ያህዌ) በመሠዊያው ላይ በእሳት ያቃጥለው፤ ይህም የኀጢአት መሥዋዕት ነው። 13ሰውየው ከእነዚህ በአንዱ ኀጢአት ቢሠራ፣ ካህኑ በዚህ ሁኔታ ያስተሰርይለታል፤ ሰውየውም ይቅር ይባላል። ከመሥዋዕቱ የተረፈውም እንደ እህል ቊርባን ሁሉ ለካህኑ ይሆናል።’ ”

የበደል መሥዋዕት

14እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴን እንዲህ አለው፤ 15“ማንኛውም ሰው በደል ቢፈጽም ለእግዚአብሔር (ያህዌ) ከተቀደሰ ከማናቸውም ነገር በማጒደል ኀጢአት ቢሠራ፣ ከመንጋው እንከን የሌለበትን አውራ በግ የበደል መሥዋዕት አድርጎ ለእግዚአብሔር (ያህዌ) ያቅርብ። የዋጋውም ግምት በቤተ መቅደሱ ሰቅል5፥15 11.5 ግራም ይሆናል። መሠረት ተመዝኖ በጥሬ ብር ይሁን፤ ይህም የበደል መሥዋዕት ነው። 16ከተቀደሱ ነገሮች ያጐደለውንም ይተካ፤ የዚህንም ተመን አንድ አምስተኛ በላዩ ጨምሮ ለካህኑ ይስጥ፤ ካህኑም ከበጉ ጋር የበደል መሥዋዕት አድርጎ በማቅረብ ያስተሰርይለታል፤ ሰውየውም ይቅር ይባላል።

17“ ‘ማንኛውም ሰው ኀጢአት ቢሠራ፣ እግዚአብሔር (ያህዌ) አታድርጉ ብሎ ከከለከላቸው ትእዛዛት ሳያውቅ አንዱን ተላልፎ ቢገኝ በደለኛ ነው፤ በኀጢአቱም ይጠየቅበታል። 18እርሱም ከመንጋው ለበደል መሥዋዕት የሚሆን እንከን የሌለበት አውራ በግ ወደ ካህኑ ያምጣ፤ ዋጋውም ተመጣጣኝ ይሁን። ካህኑም በዚህ ሁኔታ ሰውየው ሳያውቅ ስለ ፈጸመው ስሕተት ያስተሰርይለታል፤ ሰውየውም ይቅር ይባላል። 19ይህ የበደል መሥዋዕት ነው። ሰውየውም በእግዚአብሔር (ያህዌ) ፊት ጥፋት በመፈጸሙ በደለኛ5፥19 ወይም ለፈጸመው በደል ሙሉ የኀጢአቱ ማስተስረያ ነው። ነው።”

Japanese Contemporary Bible

レビ記 5:1-19

5

1ある犯罪について何かの事実を知っていながら、証言を拒否すれば、その人は罪に定められる。

2野生でも家畜でも、食用にすることを禁じられている動物や昆虫の死体など、礼拝規則で汚れているとみなされるものにさわったら、気づかずにした場合でもその人は汚れ、責めを負う。 3何であれ人体から生じる汚れにさわったら、たとえその時は気づかなくても、あとで気づいたときに責めを負う。 4良いことでも悪いことでも、軽々しく誓いを立て、あとで愚かなことをしたと気づいたときには、責めを負う。

5以上のどの場合も、罪を告白し、 6償いとして、雌の羊かやぎを罪の赦しのためのいけにえとしてささげなさい。祭司はその人の罪の償いをしなさい。

7貧しくて羊をささげる余裕がない場合は、山鳩か家鳩のひなを二羽ささげなさい。一羽を罪の赦しのためのいけにえに、もう一羽を焼き尽くすいけにえとする。 8祭司は、初めに手渡されたほうを、罪の赦しのためのいけにえとし、その首をひねって殺す。ただし、切り落としてはならない。 9次に、その血を祭壇の側面に振りかけ、残りは土台に絞り出す。これが罪の赦しのためのいけにえである。 10祭司はもう一羽も、定められたとおりに、焼き尽くすいけにえとしなさい。こうして、祭司はその人が犯した罪の償いをし、その者は赦される。

11もしその人が貧しくて、山鳩や家鳩のひなさえささげられないときは、細かくひいた小麦粉二・三リットルを持って来なさい。オリーブ油を混ぜたり、香料をかけたりしてはならない。罪の赦しのためのいけにえだからである。 12それを祭司のところへ持って行き、そのうちの一つかみを祭壇で焼いてもらう。火で焼く他のささげ物の場合と同じである。これが、罪の赦しのためのいけにえとなる。 13こうして、祭司はその人が犯した罪の償いをし、その者は赦される。残りの粉は穀物のささげ物と同じように、祭司のものとなる。」

罪過を償ういけにえ

14さらに、主はモーセに告げて言いました。 15「不実なことを行い、過って神聖なものを汚したときは、その罪を償うのに見合ういけにえとして、傷のない雄羊を一頭ささげなさい。 16そのほかに、自分が汚した神聖なものや、ささげるのを怠った十分の一のささげ物の償いをしなければならない。自分が与えた損害額に二割を加えた額を、祭司に納める。祭司は罪を償ういけにえの雄羊で償いをし、その者は赦される。

17-18主がしてはならないと定めたおきてのどれかに違反すれば、たとえ気づかずにしたことでも罪に定められる。そのときは、犯した罪に見合ういけにえをささげなければならない。これは自分の罪過を償ういけにえで、傷のない雄羊を一頭ささげる。祭司は雄羊一頭でその者の罪過の償いをする。過って犯した過失、知らずに犯した過失は、これで赦される。 19罪を犯し、主の前に責めを負った者は、このようにして罪過を償ういけにえをささげなければならない。」