New Amharic Standard Version

ዘሌዋውያን 21:1-24

ለካህናት የተሰጠ መመሪያ

1እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴን እንዲህ አለው፤ “ለካህናቱ ለአሮን ልጆች ንገራቸው፤ እንዲህም በላቸው፤ ‘ማንኛውም ሰው ከዘመዶቹ መካከል ስለ ሞተው ሰው ራሱን አያርክስ፤ 2ነገር ግን የቅርብ ዘመዶቹ ስለሆኑት እናቱ፣ አባቱ፣ ወንድ ልጁ፣ ሴት ልጁ፣ ወይም ወንድሙ፣ 3እንዲሁም ባለማግባቷ ከእርሱ ጋር ስለ ምትኖር እኅቱ ራሱን ሊያረክስ ይችላል። 4ከእርሱ ጋር በጋብቻ ለሚዛመዱት21፥4 ወይም እንደ መሪነቱ በሕዝቡ መካከል ራሱን አያርክስ። ግን ራሱን አያርክስ።

5“ ‘ካህናት ዐናታቸውን አይላጩ፤ የጢማቸውን ዙሪያ አይላጩ፤ ሰውነታቸውንም አይንጩ፤ 6ለአምላካቸው (ኤሎሂም) የተቀደሱ ይሁኑ፤ የአምላካቸውንም (ኤሎሂም) ስም አያርክሱ። ለእግዚአብሔር (ያህዌ) በእሳት የሚቀርበውን መሥዋዕት የአምላካቸውን (ኤሎሂም) ምግብ ስለሚያቀርቡ ቅዱሳን ይሁኑ።

7“ ‘ካህናት በዝሙት የረከሱትንም ሆነ ከባሎቻቸው የተፋቱትን ሴቶች አያግቡ፤ ለእግዚአብሔር (ያህዌ) የተቀደሱ ናቸውና። 8የአምላክህን (ኤሎሂም) ምግብ የሚያቀርብ ነውና ቀድሰው፤ እኔ የምቀድሳችሁ21፥8 ወይም ቅዱስ አድርጌ የምለያችሁ እኔ እግዚአብሔር እግዚአብሔር (ያህዌ) ቅዱስ ነኝና ቅዱስ ይሁንላችሁ።

9“ ‘የካህን ሴት ልጅ ዝሙት አዳሪ ሆና ራሷን ብታረክስ፣ አባቷን ታዋርዳለች፤ በእሳት ትቃጠል።

10“ ‘ከወንድሞቹ መካከል ተለይቶ በራሱ ላይ ዘይት የፈሰሰበትና የክህነት ልብስ እንዲለብስ የተቀባው ካህን የራስ ጠጒሩን አይንጭ፤21፥10 ወይም ጠጒሩን አይላጭ። ወይም ልብሱን አይቅደድ። 11አስከሬን ወዳለበት ስፍራ አይግባ፤ ስለ አባቱም ሆነ ስለ እናቱ ራሱን አያርክስ። 12የተቀደሰበት የአምላኩ (ኤሎሂም) የቅባት ዘይት በላዩ ስለ ሆነ የአምላኩን (ኤሎሂም) መቅደስ ትቶ በመሄድ መቅደሱን አያርክስ፤ እኔ እግዚአብሔር (ያህዌ) ነኝ።

13“ ‘ካህኑ የሚያገባት ሴት ድንግል ትሁን። 14ባል የሞተባትን፣ የተፋታችውን ወይም በዝሙት ዐዳሪነት የረከሰችውን ሴት አያግባ፤ ነገር ግን ከወገኖቹ መካከል ድንግሊቱን ያግባ። 15በወገኖቹ መካከል ዘሩን አያርክስ። እርሱን የምቀድሰው21፥15 ወይም ቅዱስ አድርጌ የምለየው እኔ እግዚአብሔር (ያህዌ) ነኝ።’ ”

16እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴን እንዲህ አለው፤ 17“አሮንን እንዲህ በለው፤ ‘በሚቀጥሉት ትውልዶች ከዘርህ እንከን ያለበት ማንኛውም ሰው የአምላኩን (ኤሎሂም) ምግብ ይሠዋ ዘንድ አይቅረብ። 18ዕውር ወይም አንካሳ፣ የፊቱ ገጽታ ወይም የሰውነቱ ቅርጽ የተበላሸ ማንኛውም የአካል ጒድለት ያለበት ሰው አይቅረብ። 19እንዲሁም እግሩ ወይም እጁ ሽባ የሆነ፣ 20ጐባጣ ወይም ድንክ፣ ማንኛውም ዐይነት የዐይን እንከን ያለበት፣ የሚያዥ ቊስል ወይም እከክ ያለበት ወይም ጃንደረባ አይቅረብ። 21ከካህኑ ከአሮን ዘር ማንኛውም ዐይነት የአካል ጒድለት ያለበት ሰው ለእግዚአብሔር (ያህዌ) በእሳት የሚቀርብ መሥዋዕት ሊያቀርብ አይምጣ፤ እንከን ያለበት ስለ ሆነ፣ የአምላኩን (ኤሎሂም) ምግብ ለማቅረብ አይምጣ። 22እርሱም የተቀደሰውንና እጅግ ቅዱስ የሆነውን የአምላኩን (ኤሎሂም) ምግብ ይብላ። 23ነገር ግን እንከን ያለበት ስለ ሆነ መቅደሴን እንዳያረክስ ወደ መጋረጃው አይቅረብ ወይም ወደ መሠዊያው አይጠጋ፤ የምቀድሳቸው21፥23 ወይም ቅዱስ አድርጌ የምለያቸው እኔ እግዚአብሔር (ያህዌ) ነኝ።’ ”

24ሙሴም ይህን ለአሮን፣ ለልጆቹና ለእስራኤላውያን ሁሉ ነገራቸው።

Japanese Contemporary Bible

レビ記 21:1-24

21

祭司の汚れ

1続いて、主はモーセに告げました。「縁者に不幸があった場合、遺体にさわって身を汚してはならないと祭司に命じなさい。 2-3ただし、両親、息子、娘、兄弟、同居している未婚の姉妹といった近親者の場合は例外である。 4祭司はすべての民の指導者だから、特に身をきよく保ちなさい。一般の人と同じにふるまって、身を汚してはならない。

5祭司は髪やひげをそってはならない。異教徒がするように体を傷つけてはならない。 6神の前に聖なる者となるように、神の名を冒瀆してはならない。さもないと、火で焼く食物の供え物を神にささげる資格はない。 7また、売春婦や離婚歴のある女と結婚することも許されない。祭司は神のもので、聖なる者だからだ。 8神へのいけにえをささげるために選ばれた祭司を、聖なる者としなさい。あなたがたを選び、きよい者とするわたしが聖なる者だからだ。 9祭司の娘でありながら売春婦になる者は、自分ばかりか父親のきよさまで汚すのだから、火あぶりの刑に処しなさい。

10大祭司として油を注がれ、そのための装束を身につける者は、どんなに悲しいときも、髪を乱したり衣服を引き裂いたりしてはならない。 11たとえ両親の遺体であっても、近づいてはならない。 12務めの間は聖所を離れてはならない。神聖な務めを果たす者として、神から任命されているからだ。 13-15大祭司は同族の、しかも処女を妻にしなければならない。未亡人や離婚歴のある女、売春婦と結婚してはならない。大祭司の家系に一般人の血が混じってはならない。わたしが彼を特別に選び、きよい者としたからである。」

16-17主はまた、モーセに語りました。「アロンに言いなさい。代々の子孫のうち、体に欠陥のある者は神にいけにえをささげてはならない。 18目や足の不自由な者、鼻に欠陥のある者や手足の不釣り合いな者、 19手足の折れた者、 20背中の曲がった者、小人、できものや疥癬のある者、睾丸のつぶれた者など。 21アロンの子孫のうち、以上のような体に欠陥のある者は、火で焼くいけにえを主にささげることはできない。 22ただし、いけにえのうち祭司の食物になる分は、聖なるものでも最も聖なるものでも食べてよい。 23しかし、垂れ幕や祭壇に近づいたりしてはならない。彼はわたしの聖所を汚してはならない。そこを神聖な所とするのは主だからである。」

24モーセはこれらのことをアロンとその子ら、およびイスラエルのすべての民に告げました。