New Amharic Standard Version

ዘሌዋውያን 18:1-30

1እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴን እንዲህ አለው፤ 2“ለእስራኤላውያን እንዲህ ብለህ ንገራቸው፤ ‘እኔ እግዚአብሔር (ያህዌ) አምላካችሁ (ኤሎሂም) ነኝ፤ 3በኖራችሁበት በግብፅ እነርሱ እንደሚያደርጉት አታድርጉ፤ እኔ በማስገባችሁ በከነዓን እንደሚያደርጉትም አታድርጉ፤ ልማዳቸውንም አትከተሉ። 4ሕጌን ታዘዙ፤ ሥርዐቴንም በጥንቃቄ ጠብቁ፤ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ (ያህዌ ኤሎሂም) ነኝ። 5ሥርዐቴንና ሕጌን ጠብቁ፤ እነዚህን የሚጠብቅ በሕይወት ይኖርባቸዋልና፤ እኔ እግዚአብሔር (ያህዌ) ነኝ።

6“ ‘ማንም ሰው ግብረ ሥጋ ለመፈጸም ወደ ማንኛውም የሥጋ ዘመዱ አይቅረብ፤ እኔ እግዚአብሔር (ያህዌ) ነኝ።

7“ ‘ከእናትህ ጋር ግብረ ሥጋ በመፈጸም አባትህን አታዋርድ፤ እናትህ ናት፤ ከእርሷ ጋር በግብረ ሥጋ አትገናኝ።

8“ ‘ከአባትህ ሚስት ጋር ግብረ ሥጋ አትፈጽም፤ ይህ አባትህን ያዋርዳል።

9“ ‘ከእኅትህ ጋር ግብረ ሥጋ አትፈጽም፤ በቤት ወይም በውጭ የተወለደች ብትሆን ከአባትህ ወይም ከእናትህ ሴት ልጅ ጋር በግብረ ሥጋ አትገናኝ።

10“ ‘ከወንድ ልጅህ ሴት ልጅ ወይም ከሴት ልጅህ ሴት ልጅ ጋር ግብረ ሥጋ አትፈጽም፤ ይህ አንተን ያዋርዳል።

11“ ‘የአባትህ ሚስት፣ ለአባትህ ከወለደቻት ሴት ልጅ ጋር ግብረ ሥጋ አትፈጽም፤ እኅትህ ናት።

12“ ‘ከአባትህ እኅት ጋር ግብረ ሥጋ አትፈጽም፤ እርሷ የአባትህ የሥጋ ዘመድ ናት።

13“ ‘ከእናትህ እኅት ጋር ግብረ ሥጋ አትፈጽም፤ እርሷ የእናትህ የሥጋ ዘመድ ናትና።

14“ ‘ከአባትህ ወንድም ሚስት ጋር ግብረ ሥጋ በመፈጸም፣ የአባትህን ወንድም አታዋርድ፤ እርሷ አክስትህ ናት።

15“ ‘ከምራትህ ጋር ግብረ ሥጋ አትፈጽም፤ የልጅህ ሚስት ናት፤ ከእርሷም ጋር በግብረ ሥጋ አትገናኝ።

16“ ‘ከወንድምህ ሚስት ጋር ግብረ ሥጋ አትፈጽም፤ ይህ ወንድምህን ያዋርዳል።

17“ ‘ከእናቲቱና ከሴት ልጇ ጋር ግብረ ሥጋ አትፈጽም፤ ከወንድ ልጇ ሴት ልጅ ወይም ከሴት ልጇ ሴት ልጅ ጋር ግብረ ሥጋ አትፈጽም፤ እነርሱ የሥጋ ዘመዶቿ ናቸው፤ ይህም ጸያፍ ነው።

18“ ‘ሚስትህ በሕይወት እያለች እኅቷን ጣውንት አድርገህ አታግባት፤ ከእርሷም ጋር ግብረ ሥጋ አትፈጽም።

19“ ‘በወር አበባዋ ርኵሰት ጊዜ ግብረ ሥጋ ለመፈጸም ወደ ሴት አትቅረብ።

20“ ‘ከባልንጀራህ ሚስት ጋር ግብረ ሥጋ በመፈጸም፣ ራስህን በእርሷ አታርክስ።

21“ ‘ከልጆችህ ማንኛውንም ለሞሎክ እንዲሠዋ18፥21 ወይም በእሳት ውስጥ እንዲያልፍ አሳልፈህ አትስጥ፤ የአምላክህንም (ኤሎሂም) ስም አታርክስ፤ እኔ እግዚአብሔር (ያህዌ) ነኝ።

22“ ‘ከሴት ጋር እንደሚደረገው ሁሉ ከወንድ ጋር አትተኛ፤ ይህ አስጸያፊ ነው።

23“ ‘ከእንስሳ ጋር ግብረ ሥጋ በመፈጸም ራስህን አታርክስ። ሴትም ከእንስሳ ጋር ግብረ ሥጋ ለመፈጸም ራስዋን አታቅርብ፤ ይህ አስጸያፊ ምግባር ነው።

24“ ‘ከእነዚህ በአንዱ እንኳን ራሳችሁን አታርክሱ፤ ከፊታችሁ የማሳድዳቸው አሕዛብ በእነዚህ ሁሉ ረክሰዋልና። 25ምድሪቱም ሳትቀር ረከሰች፤ እኔም ስለ ኀጢአቷ ቀጣኋት፤ ስለዚህ የሚኖሩባትን ሰዎች ተፋቻቸው። 26እናንተ ግን ሥርዐቴንና ሕጌን ጠብቁ፤ እናንተ የአገር ተወላጆችና በመካከላችሁ የሚኖሩ መጻተኞች ከእነዚህ አስጸያፊ ድርጊቶች ማንኛውንም አትፈጽሙ። 27ከእናንተ በፊት በምድሪቱ የኖሩ ሰዎች እነዚህን አስጸያፊ ነገሮች ሁሉ ስለ ፈጸሙ፣ ምድሪቱ ረክሳለች። 28እናንተም ምድሪቱን ብታረክሷት፣ ከእናንተ በፊት የነበረውን ሕዝብ እንደ ተፋች እንዲሁ እናንተንም ትተፋችኋለች። 29“ ‘ከእነዚህ አስጸያፊ ድርጊቶች ማንኛውንም የሚፈጽም ሰው ሁሉ ከወገኑ ተለይቶ ይጥፋ። 30ትእዛዜን ጠብቁ፤ ከእናንተ በፊት በምድሪቱ የኖሩ ሰዎች ካደረጓቸው አስጸያፊ ድርጊቶች አንዱንም አትፈጽሙ፤ በእነዚህም ራሳችሁን አታርክሱ፤ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ (ያህዌ ኤሎሂም) ነኝ።

Chinese Contemporary Bible (Traditional)

利未記 18:1-30

禁止淫亂的條例

1耶和華對摩西說: 2「你把以下條例告訴以色列人。

「我是你們的上帝耶和華。 3你們曾經住在埃及,但不可效法埃及人的行為。我要把你們帶到迦南,但你們不可效法迦南人的行為,不可隨從他們的風俗。 4你們必須遵行我的典章,持守我的律例。我是你們的上帝耶和華。 5你們要遵守我的典章和律例。遵行的人必存活。我是耶和華。

6「你們任何人不可與近親亂倫。我是耶和華。 7不可與你母親亂倫而羞辱你父親。她是你的母親,不可與她亂倫。 8不可與你父親的妻妾亂倫,那會羞辱你的父親。 9不可與你的姊妹亂倫。不論是同父異母的,還是同母異父的,成長在同一家庭,還是不同家庭,都不可與她亂倫。 10不可與孫女或外孫女亂倫,那會自取羞辱。 11不可與你父親妻妾的女兒亂倫。她是你的姊妹,不可與她亂倫。 12不可與姑母亂倫,她是你父親的親人。 13不可與姨母亂倫,她是你母親的親人。 14不可與伯母或嬸母亂倫而羞辱你伯父或叔父。 15不可與兒媳亂倫。她是你兒子的妻子,不可與她亂倫。 16不可與兄嫂或弟媳亂倫,她是你兄弟的妻子。

17「不可與一個女人性交,又與她女兒性交,也不可與她孫女或外孫女性交。她們是她的近親。這都是邪惡行為。 18妻子還在世時,不可娶她的姊妹,與她的姊妹性交,使她們彼此作對。 19女人在月經期間不潔淨,不可與她性交。 20不可與鄰居的妻子性交,那會玷污自己。 21不可把兒女當作祭物獻給假神摩洛,不可褻瀆你上帝的名。我是耶和華。 22男人不可與男人性交,像和女人一樣,這是可憎的。 23不可與獸類交合,玷污自己。女人也不可與獸類交合。這是變態行為。

24「你們不可做這些事玷污自己。因為我要在你們面前趕走的各國正是因為這些行為而玷污了自己。 25他們居住的土地也都被玷污了,所以我因他們的罪惡而懲罰那片土地,我要使那片土地吐出他們。 26你們必須遵守我的律例和典章。不論你們還是寄居在你們中間的外族人,都不可做這些可憎之事。 27因為在你們之前居住在那裡的人做了這些可憎之事,玷污了那片土地。 28如果你們玷污了那片土地,它也會像吐出從前的居民一樣把你們吐出去。 29凡做這些可憎之事的,要將他從民中剷除。 30你們要遵守我的命令,不要效法那片土地上居民的惡俗,以致玷污自己。我是你們的上帝耶和華。」