New Amharic Standard Version

ዘሌዋውያን 16:1-34

የስርየት ቀን

16፥2-34 ተጓ ምብ – ዘሌ 23፥26-32፤ ዘኁ 29፥7-11

1በእግዚአብሔር (ያህዌ) ፊት በቀረቡ ጊዜ ከሞቱት፣ ከሁለቱ የአሮን ልጆች ሞት በኋላ እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴን ተናገረው። 2እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴን እንዲህ አለው “እኔ በስርየቱ መክደኛ ላይ በደመና ውስጥ እገለጣለሁና፣ ወንድምህ አሮን በመጋረጃው ውስጥ ወዳለው ወደ ቅድስተ ቅዱሳን ማለት በታቦቱ ላይ ወዳለው ወደ ስርየቱ መክደኛ ፊት፣ በፈለገ ጊዜ ሁሉ እንዳይገባና እንዳይሞት ንገረው። 3ወደ ተቀደሰው ስፍራ በሚገባበት ጊዜ፣ አሮን እንዲህ ያድርግ፦ ለኀጢአት መሥዋዕት አንድ ወይፈን፣ ለሚቃጠል መሥዋዕት አንድ አውራ በግ ይዞ ይምጣ፤ 4የተቀደሰውን የበፍታ ቀሚስ ይልበስ፤ በሰውነቱ ላይ የሚያርፈውን ከበፍታ የተሠራውን የውስጥ ሱሪ ያጥልቅ፤ የበፍታውን መታጠቂያ ይታጠቅ፤ የበፍታውን መጠምጠሚያ ይጠምጥም፤ ልብሶቹ የተቀደሱ በመሆናቸው እነዚህን ከመልበሱ በፊት ሰውነቱን በውሃ ይታጠብ። 5ከእስራኤል ማኅበረሰብ ለኀጢአት መሥዋዕት ሁለት ተባዕት ፍየሎች፣ ለሚቃጠል መሥዋዕት አንድ አውራ በግ ይውሰድ።

6“አሮን ለራሱና ለቤተ ሰቡ ማስተሰረያ ይሆን ዘንድ፣ ወይፈኑን የኀጢአት መሥዋዕት አድርጎ ስለ ራሱ ያቅርብ፤ 7ሁለቱንም አውራ ፍየሎች ወስዶ በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ በእግዚአብሔር (ያህዌ) ፊት ያቁማቸው። 8አሮንም አንዱን ዕጣ ለእግዚአብሔር (ያህዌ)፣ ሌላውን ለሚለቀቀው ፍየል16፥8 የሚወገደው ፍየል ማለት ነው፤ ዕብራይሰጡ ዐዛዜል ይላል፤ እንዲሁም ቍ 10፡26 ይመ ለማድረግ በሁለቱ ፍየሎች ላይ ዕጣ ይጣል። 9በዕጣ ለእግዚአብሔር (ያህዌ) የደረሰውንም ፍየል አምጥቶ ለኀጢአት መሥዋዕት በማድረግ ይሠዋ። 10ወደ ምድረ በዳ ተለቅቆ ማስተሰረያ ይሆን ዘንድ፣ እንዲለቀቅ ዕጣ የወጣበትን ፍየል ከነሕይወቱ በእግዚአብሔር (ያህዌ) ፊት ያቅርብ።

11“አሮን ለራሱና ለቤተ ሰቡ ማስተሰረያ ይሆን ዘንድ ወይፈኑን የኀጢአት መሥዋዕት አድርጎ ስለ ራሱ ያቅርብ፤ ወይፈኑንም ስለ ራሱ የኀጢአት መሥዋዕት አድርጎ ይረድ። 12በእግዚአብሔር (ያህዌ) ፊት ካለው መሠዊያ ፍም ተወስዶ የተሞላበትን ጥና ይያዝ፤ ሁለት እጅ ሙሉ መልካም መዐዛ ያለው ዕጣን ይውሰድ፤ እነዚህንም ወደ መጋረጃው ውስጥ ይዞ ይግባ። 13እንዳይሞትም የዕጣኑ ጢስ በምስክሩ ላይ ያለውን ስርየት መክደኛ ይሸፍነው ዘንድ፣ በእግዚአብሔር (ያህዌ) ፊት ዕጣኑን በእሳቱ ላይ ይጨምረው። 14ከወይፈኑም ደም ወስዶ በስርየቱ መክደኛ ፊተኛው ወገን ላይ በጣቱ ይርጭ፤ ደግሞም በስርየቱ መክደኛ ትይዩ በጣቱ ሰባት ጊዜ ይርጭ።

15“ፍየሉንም ለሕዝቡ የኀጢአት መሥዋዕት አድርጎ ይረደው፤ ደሙንም ወደ መጋረጃው ውስጥ ወስዶ በወይፈኑ ደም እንዳደረገው በዚህኛው ያድርግ፤ ደሙን በስርየቱ መክደኛ ላይ፣ እንዲሁም በመክደኛው ትይዩ ይርጭ። 16ከእስራኤላውያን ርኵሰትና ዐመፅ፣ ከየትኛውም ኀጢአታቸው ይነጻ ዘንድ በዚህ ሁኔታ ለቅድስተ ቅዱሳኑ ያስተሰርይለታል፤ በርኵሰታቸው መካከል በእነርሱ ዘንድ ላለችውም የመገናኛዋ ድንኳን እንደዚሁ ያደርጋል። 17አሮን ለማስተሰረይ ወደ ቅድስተ ቅዱሳን ከገባበት ጊዜ ጀምሮ ለራሱ፣ ለቤተሰቡና ለእስራኤል ማኅበረሰብ ሁሉ አስተሰርዮ እስኪወጣ ድረስ ማንም ሰው በመገናኛው ድንኳን ውስጥ አይገኝ።

18“ከዚያም መጥቶ በእግዚአብሔር (ያህዌ) ፊት ወዳለው መሠዊያ ይምጣ፤ ለመሠዊያውም ያስተሰርይለት፤ ከወይፈኑና ከፍየሉ ደም ወስዶ የመሠዊያውን ቀንዶች ሁሉ ያስነካ፤ 19ከእስራኤላውያንም ርኵሰት መሠዊያውን ለማንጻትና ለመቀደስ ከደሙ ወስዶ በጣቱ ሰባት ጊዜ ይርጭበት።

20“አሮን ለቅድስተ ቅዱሳኑ፣ ለመገናኛው ድንኳንና ለመሠዊያው የሚያደርገውን ስርየት ከፈጸመ በኋላ በሕይወት ያለውን ፍየል ወደ ፊት ያቅርበው፤ 21ሁለት እጆቹን በሕይወት ባለው ፍየል ራስ ላይ ይጫን፤ በላዩም የእስራኤላውያንን ክፋትና ዐመፅ፣ ኀጢአታቸውን ሁሉ በሙሉ ይናዘዝበት፤ እነዚህንም በፍየሉ ራስ ላይ ይጫን፤ ፍየሉንም ለዚሁ ተግባር በተመደበ ሰው እጅ ወደ ምድረ በዳ ይስደደው። 22ፍየሉም ኀጢአታቸውን ሁሉ ተሸክሞ ወደ ምድረ በዳ ይሄዳል፤ ሰውየውም ፍየሉን ሰው ሊኖርበት በማይችል ስፍራ ይልቀቀው።

23“ከዚህ በኋላ አሮን ወደ መገናኛው ድንኳን ሄዶ፣ ወደ ቅድስተ ቅዱሳን ሊገባ ሲል የለበሳቸውን የበፍታ ልብሶች አውልቆ፣ በዚያው ይተዋቸው። 24በተቀደሰውም ስፍራ ሰውነቱን በውሃ ይታጠብ፤ የዘወትር ልብሱንም ይልበስ፤ ከዚያም ወጥቶ ለራሱ ማስተሰረያ የሚቃጠል መሥዋዕት ያቅርብ፣ ለሕዝቡም ማስተሰረያ የሚቃጠል መሥዋዕት ያቅርብ። 25የኀጢአት መሥዋዕቱንም በመሠዊያው ላይ ያቃጥል።

26“የሚለቀቀውን ፍየል የወሰደው ሰው ልብሱን ይጠብ፤ ሰውነቱንም በውሃ ይታጠብ፤ ከዚህ በኋላ ወደ ሰፈር መግባት ይችላል። 27ደማቸው ለማስተሰረያነት ወደ ቅድስተ ቅዱሳን የገባው፣ ለኀጢአት መሥዋዕት የቀረቡት ወይፈንና ፍየል ከሰፈር ውጭ ተወስደው ቈዳቸው፣ ሥጋቸውና ፈርሳቸው ይቃጠል። 28እነዚህንም የሚያቃጥል ሰው ልብሱን ይጠብ፤ ሰውነቱንም በውሃ ይታጠብ፤ ከዚህ በኋላ ወደ ሰፈር መግባት ይችላል።

29“ለእናንተ የተሰጣችሁ የዘላለም ሥርዐት ይህ ነው፦ ሰባተኛው ወር በገባ በዐሥረኛው ቀን ሰውነታችሁን አድክሙ፤16፥29 ወይም ጹሙ፤ እንዲሁም ቍ 31 ይመ የአገሩ ተወላጅም ሆነ በመካከላችሁ የሚኖር መጻተኛ ምንም ሥራ አይሥራ፤ 30የምትነጹበት ስርየት በዚች ዕለት ይደረግላችኋልና በእግዚአብሔርም (ያህዌ) ፊት ከኀጢአታችሁ ሁሉ ትነጻላችሁ። 31ይህች የፍጹም ዕረፍት ሰንበት ናት፤ ሰውነታችሁን አድክሙባት፤ የዘላለም ሥርዐት ናት። 32ሊቀ ካህናት ለመሆን አባቱን በመተካት የተቀባና የተሾመ ካህን ያስተሰርይ፤ የተቀደሰውንም የበፍታ ልብስ ይልበስ፤ 33ለቅድስተ ቅዱሳኑ፣ ለመገናኛው ድንኳንና ለመሠዊያው፣ ለካህናቱና ለማኅበረ ሰቡ ሁሉ ያስተሰርይ።

34“ይህ የዘላለም ሥርዐት ይሁናችሁ፤ በዚህም ሥርዐት መሠረት ለእስራኤላውያን ኀጢአት ሁሉ በዓመት አንድ ጊዜ ስርየት ይደረግ።” እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴን እንዳዘዘ እንዲሁ ተደረገ።

Thai New Contemporary Bible

เลวีนิติ 16:1-34

วันลบบาป

(ลนต.23:26-32; กดว.29:7-11)

1องค์พระผู้เป็นเจ้าตรัสกับโมเสสหลังจากที่บุตรชายสองคนของอาโรนสิ้นชีวิตเมื่อพวกเขาเข้ามาหาองค์พระผู้เป็นเจ้า 2องค์พระผู้เป็นเจ้าตรัสกับโมเสสว่า “จงเตือนอาโรนพี่ชายของเจ้าไม่ให้เข้าไปในอภิสุทธิสถานหลังม่านซึ่งอยู่เบื้องหน้าพระที่นั่งกรุณาที่อยู่บนหีบพันธสัญญาตามอำเภอใจ มิฉะนั้นเขาจะต้องตาย เพราะเราจะปรากฏในกลุ่มเมฆเหนือพระที่นั่งกรุณา

3“ต่อไปนี้เป็นข้อปฏิบัติในการที่อาโรนจะเข้าไปยังบริเวณสถานนมัสการ เขาจะต้องนำวัวหนุ่มสำหรับเป็นเครื่องบูชาไถ่บาปและแกะผู้สำหรับเป็นเครื่องเผาบูชาไป 4เขาต้องสวมเสื้อตัวในอันบริสุทธิ์ที่ทำด้วยผ้าลินินกับเครื่องแต่งกายชั้นในผ้าลินินที่ติดกับร่างกายของเขา คาดสายคาดเอวลินิน และโพกศีรษะด้วยผ้าลินิน นี่เป็นเครื่องแต่งกายอันบริสุทธิ์ ดังนั้นเขาต้องอาบน้ำก่อนที่จะสวมใส่ 5ให้เขารับแพะผู้สองตัวสำหรับเป็นเครื่องบูชาไถ่บาป และแกะผู้หนึ่งตัวสำหรับเป็นเครื่องเผาบูชาจากชุมชนอิสราเอล

6“ให้อาโรนถวายวัวหนุ่มหนึ่งตัวเป็นเครื่องบูชาไถ่บาป เพื่อลบบาปให้ตนเองและครอบครัว 7จากนั้นจะนำแพะสองตัวมาต่อหน้าองค์พระผู้เป็นเจ้าที่ทางเข้าเต็นท์นัดพบ 8เขาจะต้องจับฉลากสำหรับแพะทั้งสองนั้น ฉลากอันหนึ่งสำหรับองค์พระผู้เป็นเจ้า และอีกอันหนึ่งสำหรับแพะรับบาป16:8 คือแพะแห่งการขจัดออกภาษาฮีบรูว่าอาซาเซลเช่นเดียวกับข้อ 10 และ 26 9อาโรนจะถวายแพะตัวที่ใช้ถวายองค์พระผู้เป็นเจ้าเป็นเครื่องบูชาไถ่บาป 10แต่แพะที่ได้รับเลือกโดยฉลากให้เป็นแพะรับบาปจะถูกนำมาถวายทั้งที่ยังมีชีวิตต่อหน้าองค์พระผู้เป็นเจ้า เพื่อเป็นการลบบาป โดยส่งมันเข้าไปในถิ่นกันดารเป็นแพะรับบาป

11“อาโรนจะนำวัวหนุ่มมาฆ่าเป็นเครื่องบูชาไถ่บาปเพื่อลบบาปให้ตนเองและครอบครัว 12เขาจะเอากระถางไฟบรรจุถ่านคุโชนจากแท่นบูชาต่อหน้าองค์พระผู้เป็นเจ้าและกอบผงเครื่องหอมซึ่งบดละเอียดสองกำมือนำเข้าไปหลังม่าน 13เขาจะโรยเครื่องหอมบนไฟต่อหน้าองค์พระผู้เป็นเจ้าให้ควันเครื่องหอมปกคลุมทั่วพระที่นั่งกรุณาเหนือหีบพันธสัญญา เพื่อว่าเขาจะไม่ตาย 14เขาจะนำเลือดบางส่วนของวัวหนุ่มเข้าไปและใช้นิ้วพรมบนด้านหน้าของพระที่นั่งกรุณาเจ็ดครั้ง

15“แล้วอาโรนจะฆ่าแพะเป็นเครื่องบูชาไถ่บาปสำหรับประชากร และนำเลือดของมันเข้าไปหลังม่าน แล้วทำเช่นเดียวกับที่ทำกับเลือดวัวผู้คือ เขาจะพรมเลือดนั้นที่ข้างบนและข้างหน้าของพระที่นั่งกรุณา 16เขาจะลบบาปสำหรับอภิสุทธิสถานด้วยวิธีนี้เพราะมลทินและการกบฏของชาวอิสราเอล ไม่ว่าบาปของเขาจะเป็นอะไร เขาจะต้องทำอย่างเดียวกันนี้สำหรับเต็นท์นัดพบซึ่งอยู่ท่ามกลางพวกเขา ซึ่งแวดล้อมด้วยมลทินของพวกเขา 17ห้ามผู้ใดอยู่ในเต็นท์นัดพบขณะที่อาโรนเข้าไปทำการลบบาปในอภิสุทธิสถาน จนกว่าเขาจะออกมาอีกครั้งหลังจากลบบาปให้ตนเอง ให้ครอบครัวและชุมชนอิสราเอลทั้งหมดแล้ว

18“จากนั้นอาโรนจะไปยังแท่นบูชา คือต่อหน้าองค์พระผู้เป็นเจ้าและทำการลบบาปสำหรับแท่นนั้น เขาจะเอาเลือดวัวผู้และเลือดแพะบางส่วนทาที่เชิงงอนของแท่น 19แล้วเอานิ้วจุ่มเลือดพรมบนแท่นบูชาเจ็ดครั้ง เป็นการชำระแท่นนั้นให้บริสุทธิ์พ้นจากมลทินของชนอิสราเอล

20“เมื่ออาโรนลบบาปสำหรับอภิสุทธิสถาน เต็นท์นัดพบ และแท่นบูชาเสร็จแล้ว เขาจะนำแพะที่มีชีวิตตัวนั้นมา 21วางมือทั้งสองบนหัวแพะ สารภาพความชั่วร้ายและการละเมิดฝ่าฝืนของชนอิสราเอล ปลดเปลื้องบาปทั้งหมดลงบนแพะ แล้วมอบหมายให้ชายคนหนึ่งจูงแพะเข้าไปในถิ่นกันดาร 22แพะตัวนั้นจะแบกรับบาปทั้งหมดของเหล่าประชากรเข้าสู่ที่เปลี่ยว ชายผู้นั้นจะปล่อยมันไว้ในถิ่นกันดาร

23“จากนั้นให้อาโรนเข้าไปในเต็นท์นัดพบ ถอดชุดผ้าลินินซึ่งใช้สวมเข้าไปในอภิสุทธิสถานนั้นวางไว้ในเต็นท์นัดพบ 24แล้วอาบน้ำชำระกายในที่บริสุทธิ์ สวมเสื้อผ้าชุดปกติ แล้วออกไปถวายเครื่องเผาบูชาสำหรับตนเองและเครื่องเผาบูชาสำหรับประชากร เพื่อลบบาปให้ตนเองและประชากร 25เขาจะเผาไขมันของเครื่องบูชาไถ่บาปบนแท่นบูชาด้วย

26“ชายคนที่จูงแพะเข้าไปปล่อยในถิ่นกันดารเสร็จแล้ว ต้องอาบน้ำ ซักเสื้อผ้า แล้วกลับเข้ามาในค่ายพัก 27วัวหนุ่มและแพะซึ่งใช้เป็นเครื่องบูชาไถ่บาป ซึ่งอาโรนนำเลือดของมันเข้าไปในอภิสุทธิสถานเพื่อทำการลบบาป จะถูกนำไปเผาให้หมดนอกค่ายพัก รวมทั้งหนัง เนื้อ และไส้ 28แล้วผู้ทำหน้าที่เผาต้องซักเสื้อผ้าและอาบน้ำ และค่อยกลับมาที่ค่ายพัก

29“ต่อไปนี้เป็นข้อปฏิบัติถาวรสำหรับเจ้าคือ ห้ามเจ้าทำกิจธุระในวันที่สิบเดือนที่เจ็ด แต่จงบังคับตน16:29 หรือต้องอดอาหารเช่นเดียวกับข้อ 31 ไม่ว่าจะเป็นคนอิสราเอลโดยกำเนิดหรือเป็นคนต่างด้าวซึ่งอาศัยอยู่ในหมู่พวกเจ้า 30เพราะในวันนี้จะมีการลบบาปสำหรับเจ้า เพื่อชำระเจ้าให้สะอาด แล้วเจ้าจะสะอาดพ้นจากบาปทั้งสิ้นต่อหน้าองค์พระผู้เป็นเจ้า 31เป็นสะบาโตแห่งการหยุดพัก เจ้าต้องบังคับตน ถือเป็นข้อปฏิบัติถาวรสืบไปทุกชั่วอายุ 32ปุโรหิตซึ่งได้รับการเจิมและสถาปนาให้เป็นมหาปุโรหิตสืบทอดจากบิดาจะเป็นผู้ลบบาป เขาจะต้องสวมชุดบริสุทธิ์ที่ทำจากผ้าลินิน 33และลบบาปสำหรับอภิสุทธิสถาน เต็นท์นัดพบ และแท่นบูชา สำหรับปุโรหิตและประชากรทั้งปวงในชุมชน

34“นี่เป็นข้อปฏิบัติถาวรสำหรับเจ้าทั้งหลายสืบไปคือ ให้ลบบาปทั้งสิ้นสำหรับประชากรอิสราเอลปีละครั้ง”

และเขาก็ทำตามที่องค์พระผู้เป็นเจ้าทรงบัญชาโมเสสไว้