ዘሌዋውያን 16 – NASV & CCB

New Amharic Standard Version

ዘሌዋውያን 16:1-34

የስርየት ቀን

16፥2-34 ተጓ ምብ – ዘሌ 23፥26-32ዘኍ 29፥7-11

1በእግዚአብሔር (ያህዌ) ፊት በቀረቡ ጊዜ ከሞቱት፣ ከሁለቱ የአሮን ልጆች ሞት በኋላ እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴን ተናገረው። 2እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴን እንዲህ አለው፤ “እኔ በስርየቱ መክደኛ ላይ በደመና ውስጥ እገለጣለሁና ወንድምህ አሮን በመጋረጃው ውስጥ ወዳለው ወደ ቅድስተ ቅዱሳን ማለት በታቦቱ ላይ ወዳለው ወደ ስርየቱ መክደኛ ፊት፣ በፈለገ ጊዜ ሁሉ እንዳይገባና እንዳይሞት ንገረው። 3ወደ ተቀደሰው ስፍራ በሚገባበት ጊዜ፣ አሮን እንዲህ ያድርግ፤ ለኀጢአት መሥዋዕት አንድ ወይፈን፣ ለሚቃጠል መሥዋዕት አንድ አውራ በግ ይዞ ይምጣ፤ 4የተቀደሰውን የበፍታ ቀሚስ ይልበስ፤ በሰውነቱ ላይ የሚያርፈውን ከበፍታ የተሠራውን የውስጥ ሱሪ ያጥልቅ፤ የበፍታውን መታጠቂያ ይታጠቅ፤ የበፍታውን መጠምጠሚያ ይጠምጥም፤ ልብሶቹ የተቀደሱ በመሆናቸው እነዚህን ከመልበሱ በፊት ሰውነቱን በውሃ ይታጠብ። 5ከእስራኤል ማኅበረ ሰብ ለኀጢአት መሥዋዕት ሁለት ተባዕት ፍየሎች፣ ለሚቃጠል መሥዋዕት አንድ አውራ በግ ይውሰድ።

6“አሮን ለራሱና ለቤተ ሰቡ ማስተስረያ ይሆን ዘንድ፣ ወይፈኑን የኀጢአት መሥዋዕት አድርጎ ስለ ራሱ ያቅርብ፤ 7ሁለቱንም አውራ ፍየሎች ወስዶ በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ በእግዚአብሔር (ያህዌ) ፊት ያቁማቸው። 8አሮንም አንዱን ዕጣ ለእግዚአብሔር (ያህዌ)፣ ሌላውን ለሚለቀቀው ፍየል16፥8 የሚወገደው ፍየል ማለት ነው፤ ዕብራይሰጡ ዐዛዜል ይላል፤ እንዲሁም 10፡26 ይመ ለማድረግ በሁለቱ ፍየሎች ላይ ዕጣ ይጣል። 9በዕጣ ለእግዚአብሔር (ያህዌ) የደረሰውንም ፍየል አምጥቶ ለኀጢአት መሥዋዕት በማድረግ ይሠዋ። 10ወደ ምድረ በዳ ተለቅቆ ማስተስረያ ይሆን ዘንድ፣ እንዲለቀቅ ዕጣ የወጣበትን ፍየል ከነሕይወቱ በእግዚአብሔር (ያህዌ) ፊት ያቅርብ።

11“አሮን ለራሱና ለቤተ ሰቡ ማስተስረያ ይሆን ዘንድ ወይፈኑን የኀጢአት መሥዋዕት አድርጎ ስለ ራሱ ያቅርብ፤ ወይፈኑንም ስለ ራሱ የኀጢአት መሥዋዕት አድርጎ ይረድ። 12በእግዚአብሔር (ያህዌ) ፊት ካለው መሠዊያ ፍም ተወስዶ የተሞላበትን ጥና ይያዝ፤ ሁለት እጅ ሙሉ መልካም መዐዛ ያለው ዕጣን ይውሰድ፤ እነዚህንም ወደ መጋረጃው ውስጥ ይዞ ይግባ። 13እንዳይሞትም የዕጣኑ ጢስ በምስክሩ ላይ ያለውን ስርየት መክደኛ ይሸፍነው ዘንድ፣ በእግዚአብሔር (ያህዌ) ፊት ዕጣኑን በእሳቱ ላይ ይጨምረው። 14ከወይፈኑም ደም ወስዶ በስርየቱ መክደኛ ፊተኛው ወገን ላይ በጣቱ ይርጭ፤ ደግሞም በስርየቱ መክደኛ ትይዩ በጣቱ ሰባት ጊዜ ይርጭ።

15“ፍየሉንም ለሕዝቡ የኀጢአት መሥዋዕት አድርጎ ይረደው፤ ደሙንም ወደ መጋረጃው ውስጥ ወስዶ በወይፈኑ ደም እንዳደረገው በዚህኛው ያድርግ፤ ደሙን በስርየቱ መክደኛ ላይ፣ እንዲሁም በመክደኛው ትይዩ ይርጭ። 16ከእስራኤላውያን ርኩሰትና ዐመፅ፣ ከየትኛውም ኀጢአታቸው ይነጻ ዘንድ በዚህ ሁኔታ ለቅድስተ ቅዱሳኑ ያስተሰርይለታል፤ በርኩሰታቸው መካከል በእነርሱ ዘንድ ላለችውም የመገናኛዋ ድንኳን እንደዚሁ ያደርጋል። 17አሮን ለማስተስረይ ወደ ቅድስተ ቅዱሳን ከገባበት ጊዜ ጀምሮ ለራሱ፣ ለቤተ ሰቡና ለእስራኤል ማኅበረ ሰብ ሁሉ አስተስርዮ እስኪወጣ ድረስ ማንም ሰው በመገናኛው ድንኳን ውስጥ አይገኝ።

18“ከዚያም መጥቶ በእግዚአብሔር (ያህዌ) ፊት ወዳለው መሠዊያ ይምጣ፤ ለመሠዊያውም ያስተስርይለት፤ ከወይፈኑና ከፍየሉ ደም ወስዶ የመሠዊያውን ቀንዶች ሁሉ ያስነካ፤ 19ከእስራኤላውያንም ርኩሰት መሠዊያውን ለማንጻትና ለመቀደስ ከደሙ ወስዶ በጣቱ ሰባት ጊዜ ይርጭበት።

20“አሮን ለቅድስተ ቅዱሳኑ፣ ለመገናኛው ድንኳንና ለመሠዊያው የሚያደርገውን ስርየት ከፈጸመ በኋላ፣ በሕይወት ያለውን ፍየል ወደ ፊት ያቅርበው። 21ሁለት እጆቹን በሕይወት ባለው ፍየል ራስ ላይ ይጫን፤ በላዩም የእስራኤላውያንን ክፋትና ዐመፅ፣ ኀጢአታቸውንም ሁሉ ይናዘዝበት፤ እነዚህንም በፍየሉ ራስ ላይ ይጫን፤ ፍየሉንም ለዚሁ ተግባር በተመደበ ሰው እጅ ወደ ምድረ በዳ ይስደደው። 22ፍየሉም ኀጢአታቸውን ሁሉ ተሸክሞ ወደ ምድረ በዳ ይሄዳል፤ ሰውየውም ፍየሉን ሰው ሊኖርበት በማይችል ስፍራ ይልቀቀው።

23“ከዚህ በኋላ አሮን ወደ መገናኛው ድንኳን ሄዶ፣ ወደ ቅድስተ ቅዱሳን ሊገባ ሲል የለበሳቸውን የበፍታ ልብሶች አውልቆ በዚያው ይተዋቸው። 24በተቀደሰውም ስፍራ ሰውነቱን በውሃ ይታጠብ፤ የዘወትር ልብሱንም ይልበስ፤ ከዚያም ወጥቶ ለራሱ ማስተስረያ የሚቃጠል መሥዋዕት ያቅርብ፤ ለሕዝቡም ማስተስረያ የሚቃጠል መሥዋዕት ያቅርብ። 25የኀጢአት መሥዋዕቱንም በመሠዊያው ላይ ያቃጥል።

26“የሚለቀቀውን ፍየል የወሰደው ሰው ልብሱን ይጠብ፤ ሰውነቱንም በውሃ ይታጠብ፤ ከዚህ በኋላ ወደ ሰፈር መግባት ይችላል። 27ደማቸው ለማስተስረያነት ወደ ቅድስተ ቅዱሳን የገባው፣ ለኀጢአት መሥዋዕት የቀረቡት ወይፈንና ፍየል ከሰፈር ውጭ ተወስደው ቈዳቸው፣ ሥጋቸውና ፈርሳቸው ይቃጠል። 28እነዚህንም የሚያቃጥል ሰው ልብሱን ይጠብ፤ ሰውነቱንም በውሃ ይታጠብ፤ ከዚህ በኋላ ወደ ሰፈር መግባት ይችላል።

29“ለእናንተ የተሰጣችሁ የዘላለም ሥርዐት ይህ ነው፦ ሰባተኛው ወር በገባ በዐሥረኛው ቀን ሰውነታችሁን አድክሙ፤16፥29 ወይም ጹሙ፤ እንዲሁም 31 ይመ የአገሩ ተወላጅም ሆነ በመካከላችሁ የሚኖር መጻተኛ ምንም ሥራ አይሥራ፤ 30የምትነጹበት ስርየት በዚህች ዕለት ይደረግላችኋልና፤ በእግዚአብሔርም (ያህዌ) ፊት ከኀጢአታችሁ ሁሉ ትነጻላችሁ። 31ይህች የፍጹም ዕረፍት ሰንበት ናት፤ ሰውነታችሁን አድክሙባት፤ የዘላለም ሥርዐት ናት። 32ሊቀ ካህናት ለመሆን አባቱን በመተካት የተቀባና የተሾመ ካህን ያስተስርይ፤ የተቀደሰውንም የበፍታ ልብስ ይልበስ፤ 33ለቅድስተ ቅዱሳኑ፣ ለመገናኛው ድንኳንና ለመሠዊያው፣ ለካህናቱና ለማኅበረ ሰቡ ሁሉ ያስተስርይ።

34“ይህ የዘላለም ሥርዐት ይሁናችሁ፤ በዚህም ሥርዐት መሠረት ለእስራኤላውያን ኀጢአት ሁሉ በዓመት አንድ ጊዜ ስርየት ይደረግ።” እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴን እንዳዘዘ እንዲሁ ተደረገ።

Chinese Contemporary Bible (Simplified)

利未记 16:1-34

赎罪日的条例

1亚伦的两个儿子死在耶和华面前以后, 2耶和华对摩西说:“告诉你哥哥亚伦,他不可随意进入幔子里面的至圣所,走到约柜上的施恩座前,免得死亡,因为我要在施恩座之上的云彩中显现。 3亚伦进入圣所时,要带一只作赎罪祭的公牛犊和一只作燔祭的公绵羊。 4他要穿上圣洁的细麻内袍、细麻裤子,束上细麻腰带,戴上细麻礼冠。这些是圣洁的衣物,他必须沐浴后才可穿戴。 5他要从以色列会众那里取两只公山羊作赎罪祭、一只公绵羊作燔祭。 6亚伦要先献上那头公牛犊作赎罪祭,为自己和全家赎罪。 7然后,他要把两只公山羊带到会幕门口,放在耶和华面前, 8抽签决定哪只归耶和华、哪只归阿撒泻勒16:8 阿撒泻勒”是希伯来文的音译,意义不确定。9亚伦要献上那只归耶和华的公山羊作赎罪祭, 10要将那只归阿撒泻勒的公山羊活着献给耶和华,然后把它放到旷野归阿撒泻勒,用来赎罪。

11亚伦要把那只为他作赎罪祭的公牛犊牵来宰杀,为自己和全家赎罪, 12然后拿一个香炉,盛满从耶和华面前的祭坛上取的火炭,再拿两把磨细的香带进幔子里。 13他要在耶和华面前烧香,使香的烟笼罩约柜上的施恩座,免得他死亡。 14他要取一些牛血,用手指弹洒在施恩座的东面,也要在施恩座前用手指弹洒七次。 15然后,亚伦要出去宰杀那只为民众作赎罪祭的公山羊,把羊血带进幔子里,像洒牛血一样洒在施恩座的上面和前面。 16以色列人的污秽、叛逆和罪恶,他要这样为至圣所赎罪。他也要同样为会幕赎罪,因为会幕座落在以色列人中间,处在他们的污秽中。 17从他进入圣所为自己全家和以色列全体会众赎罪开始,直到他赎完罪出来为止,任何人都不可待在会幕里。 18之后,他要来到耶和华面前的祭坛那里,为祭坛赎罪。他要取一些牛血和羊血,抹在祭坛的四角上, 19用手指向祭坛洒血七次,除掉以色列人的污秽,使祭坛圣洁。

20“他为至圣所、会幕和祭坛赎罪后,要牵来那只活山羊, 21把双手放在羊头上,承认以色列人的过犯、叛逆和罪恶,将这一切罪归到公山羊的头上,然后派人把它送到旷野。 22这只公山羊担当他们的一切罪,将这一切罪带到荒无人烟的地方。

23亚伦要走进会幕,脱下他进至圣所时穿的细麻衣服,放在会幕里。 24他要在圣洁之处沐浴,穿上平时的衣服出去为自己和民众献燔祭,为自己和民众赎罪。 25他要将赎罪祭牲的脂肪焚烧在坛上。 26把羊送交阿撒泻勒的人要洗衣、沐浴,然后才可回到营里。 27作赎罪祭的公牛和公山羊的血被带进圣所用来赎罪,要把公牛和公山羊带到营外,用火焚烧它们的皮、肉和粪。 28负责焚烧的人要洗衣、沐浴,然后才可回到营里。

29“每年七月十日,不论是你们,还是寄居在你们中间的外族人,都要禁食,停止所有工作。这是你们要永远遵守的律例。 30因为在这一天要为你们赎罪,使你们在耶和华面前洁净。 31这天是你们的安息日,你们要禁食。这是一条永远不变的律例。 32那受膏、承受圣职、替代父亲做大祭司的要献祭赎罪。他要穿上圣洁的细麻衣, 33为至圣所、会幕和祭坛赎罪,也要为祭司和全体会众赎罪。 34这是你们要永远遵守的律例——每年一次为以色列人赎罪。”

于是,摩西遵行了耶和华的吩咐。