New Amharic Standard Version

ዕዝራ 5:1-17

ለዳርዮስ የተላከ የተንትናይ ደብዳቤ

1በዚያን ጊዜ ነቢዩ ሐጌና የአዶ ልጅ ነቢዩ ዘካርያስ፣ በይሁዳና በኢየሩሳሌም ለሚኖሩ አይሁድ ከእነርሱ በላይ በሆነው በእስራኤል አምላክ ስም ትንቢት ተናገሩላቸው። 2ከዚያም የሰላትያል ልጅ ዘሩባቤልና የኢዮሴዴቅ ልጅ ኢያሱ በኢየሩሳሌም ያለውን የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ እንደ ገና ለመሥራት ተነሡ፤ የሚያግዟቸውም የእግዚአብሔር ነቢያት አብረዋቸው ነበሩ።

3በዚህ ጊዜ በኤፍራጥስ ማዶ ገዥ የነበረው ተንትናይ፣ ሰተርቡዝናይና ተባባሪዎቻቸው ሄደው፣ “ይህን ቤተ መቅደስ እንደ ገና ለመሥራትና ውቅሩንም ለመጠገን የፈቀደላችሁ ማን ነው?” ሲሉ ጠየቋቸው። 4ደግሞም፣ “ይህን ሕንጻ የሚገነቡት ሰዎች ስም ማን ይባላል?” በማለት ጠየቋቸው5፥4 የሰብዓ ሊቃናት ትርጒም ይመ፤ የአረማይስጡ ትርጒም እንዲህ ይላል፣ ይህን ሕንጻ የሚገነቡትን ሰዎች ስም ነገርናቸው5የአምላካቸው ዐይን ግን በአይሁድ መሪዎች ላይ ነበረ፤ ነገሩ ወደ ዳርዮስ ደርሶ የጽሑፍ መልስ እስኪያገኙ ድረስ አልተከለከሉም።

6በኤፍራጥስ ማዶ ገዥ የነበረው ተንትናይ፣ ሰተርቡዝናይ፣ ተባባሪዎቻቸውና በኤፍራጥስ ማዶ የነበሩ ሹማምት ለንጉሥ ዳርዮስ የላኩት ደብዳቤ ቅጅ ይህ ነው፤ 7የላኩትም ደብዳቤ እንዲህ የሚል ነበር፤

ለንጉሥ ዳርዮስ፣

የከበረ ሰላምታ እናቀርባለን።

8የታላቁ አምላክ ቤተ መቅደስ ወደሚገኝበት ወደ ይሁዳ አውራጃ ሄደን እንደ ነበር በንጉሡ ዘንድ የታወቀ ይሁን። ሕዝቡ ቤተ መቅደሱን በታላላቅ ድንጋዮች እየገነቡና ቅጥሩንም በወፍራም ምሰሶዎች እየሠሩ ነው፤ ሥራው በትጋት በመከናወንና በእነርሱም አመራር በመፋጠን ላይ ይገኛል።

9እኛም መሪዎቹን፣ “ይህን ቤተ መቅደስ እንደ ገና ለመሥራትና ይህንም ውቅር ለመጠገን የፈቀደላችሁ ማን ነው?” ብለን ጠየቅናቸው። 10የመሪዎቻቸውን ስም በጽሑፍ እናሳውቅህ ዘንድ ስማቸውን ደግሞ ጠየቅን።

11የሰጡን መልስ ይህ ነው፤

“እኛ የሰማይና የምድር አምላክ አገልጋዮች ነን፤ አሁንም እንደ ገና የምንሠራው ቤተ መቅደስ፣ ከብዙ ዘመናት በፊት ታላቁ የእስራኤል ንጉሥ ሠርቶ የጨረሰውን ነው። 12ነገር ግን አባቶቻችን የሰማይን አምላክ አስቈጥተውት ስለ ነበር፣ ለባቢሎኑ ንጉሥ ለከለዳዊው ናቡከደነፆር አሳልፎ ሰጣቸው፤ እርሱም ይህን ቤተ መቅደስ አፈራርሶ ሕዝቡን ወደ ባቢሎን አፈለሰ። 13“ይሁንና ቂሮስ፣ የባቢሎን ንጉሥ በሆነ በመጀመሪያው ዓመት ይህን የእግዚአብሔር ቤት እንደ ገና እንዲሠሩ ንጉሥ ቂሮስ ትእዛዝ ሰጠ። 14ናቡከደነፆር ከኢየሩሳሌም ቤተ መቅደስ አውጥቶ ባቢሎን በሚገኘው ቤተ መቅደስ5፥14 ወይም፣ ቤተ መንግሥት ውስጥ ያኖራቸውን የእግዚአብሔርን ቤት የወርቅና የብር ዕቃዎች ከባቢሎን ቤተ መቅደስ አስመጣ።

“ከዚያም ንጉሥ ቂሮስ፣ አገረ ገዥ አድርጎ ለሾመውና ሰሳብሳር ተብሎ ለሚጠራው ሰው ሰጠው፤ 15ቀጥሎም፣ ‘እነዚህን ዕቃዎች ይዘህ ሂድና በኢየሩሳሌም ቤተ መቅደስ ውስጥ አኑራቸው፤ የእግዚአሔር ቤት ቀድሞ በነበረበት ቦታ እንደ ገና ይሠራ’ አለው። 16ስለዚህ ይህ ሰሳብሳር መጥቶ በኢየሩሳሌም የሚገኘውን የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ መሠረት ጣለ፤ ከዚያን ቀን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ እነሆ በመሠራት ላይ ነው፤ ሆኖም ገና አላለቀም።

17“አሁንም ንጉሡን ደስ የሚያሰኘው ቢሆን፣ ይህ የእግዚአብሔር ቤት በኢየሩሳሌም እንዲሠራ ንጉሥ ቂሮስ በርግጥ ትእዛዝ ሰጥቶ እንደሆነ በባቢሎን ቤተ መንግሥት ግምጃ ቤት የተቀመጡት መዛግብት እንዲመረመሩ ያድርግ፤ ከዚያም ንጉሡ ስለዚህ ጒዳይ የወሰነውን ይላክልን።”

Korean Living Bible

에스라 5:1-17

다시 시작된 성전 재건 공사

1이때 두 예언자 곧 학개와 잇도의 손자 스가랴가 이스라엘 하나님의 이름으로 유다와 예루살렘에 사는 유대인들에게 예언하자

2스알디엘의 아들 스룹바벨과 요사닥의 아들 예수아가 그 말을 듣고 예루살렘에서 하나님의 성전을 건축하기 시작하였다. 그래서 그 예언자들도 그들을 도왔다.

3그때 유프라테스강 서쪽 지방의 총독 닷드내와 그리고 스달 – 보스내와 그들의 동료들이 예루살렘에 와서 “너희는 누구 허락으로 이 성전과 성곽을 짓고 있느냐?” 하고 물으며

4그 성전을 짓고 있는 사람들의 명단을 요구하였다.

5그러나 여호와께서 유다 지도자들을 지켜 주셨기 때문에 그들은 그 공사를 중단시키지 못하고 다리우스황제에게 그 사실을 보고하여 회답이 올 때까지 기다렸다.

6그들이 다리우스황제에게 보낸 보고서 내용은 다음과 같다.

7“다리우스황제 폐하께 문안드립니다.

8우리가 황제 폐하께 알려 드릴 말씀이 있습니다. 우리가 유다도에 가서 크신 하나님의 성전 작업 현장에 가 보니 사람들이 큰 돌을 쌓아 성전을 세우는데 벽에 들보를 얹고 부지런히 일을 하여 공사가 신속하게 진행되고 있었습니다.

9그래서 우리가 그들의 지도자들에게 ‘누구 허락으로 이 성전과 성곽을 짓고 있느냐?’ 고 묻고

10또 폐하께 보고하려고 그 지도자들의 이름을 묻자

11그들은 우리에게 이렇게 대답하였습니다. ‘우리는 하늘과 땅의 주인이신 하나님의 종들인데 오래 전에 이스라엘의 한 위대한 왕이 건축한 성전을 재건하고 있습니다.

12그러나 우리 조상들이 하늘의 하나님을 노하게 하였으므로 그가 우리 조상들을 갈대아 사람인 바빌로니아의 느부갓네살왕에게 넘겨 주셨습니다. 그래서 그가 이 성전을 헐고 백성들을 바빌로니아로 잡아갔습니다.

13그런데 바빌로니아의 키루스황제 원년에 그가 성전을 재건하라는 조서를 내리고

14느부갓네살왕이 예루살렘 성전에서 가져가 바빌론 신전에 두었던 모든 금은 그릇을 끄집어내어 그가 유다 총독으로 임명한 세스바살에게 그 모든 것을 주면서

15그것을 가지고 예루살렘으로 돌아가 옛터에 성전을 재건하라고 했습니다.

16그래서 세스바살은 돌아와 예루살렘에 성전 기초를 놓았고 그때부터 지금까지 공사가 진행중이지만 아직 완성하지 못하였습니다.’

17“이제 황제 폐하께서 기쁘게 여기신다면 바빌론의 궁중 문헌을 조사하셔서 정말 키루스황제가 예루살렘에 이 성전을 재건하라고 명령했는지 알아보시고 이 문제에 대하여 황제 폐하의 뜻을 우리에게 알려 주십시오.”