New Amharic Standard Version

ዕዝራ 4:1-24

ቤተ መቅደሱ እንዳይሠራ የተነሣ ተቃውሞ

1የይሁዳና የብንያም ጠላቶች ከምርኮ የተመለሱት ሰዎች የእስራኤልን አምላክ የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ በመሥራት ላይ መሆናቸውን ሲሰሙ፣ 2ወደ ዘሩባቤልና ወደ ቤተ ሰቡ አለቆች መጥተው፣ “እኛም እንደ እናንተ አምላካችሁን የምንፈልግ ነን፤ የአሦር ንጉሥ አስራዶን ወደዚህ ካመጣን ጊዜ ጀምሮ ለእርሱ ስንሠዋለት ቈይተናል፤ ስለዚህ አብረን ከእናንተ ጋር እንሥራ” አሏቸው።

3ዘሩባቤል፣ ኢያሱና ሌሎቹ የእስራኤል ቤተ ሰቦች አለቆች ግን፣ “ለአምላካችን ቤተ መቅደስ እንድትሠሩ ከእኛ ጋር የሚያገናኛችሁ ምንም ነገር የለም። የፋርስ ንጉሥ ቂሮስ ባዘዘን መሠረት ለእስራኤል አምላክ ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ የምንሠራው እኛ ብቻ ነን” ሲሉ መለሱላቸው።

4ከዚያም የምድሪቱ ነዋሪዎች የይሁዳን ሕዝብ ተስፋ ማስቈረጥና ሥራውንም እንዳይቀጥሉ ማስፈራራት ጀመሩ4፥4 ወይም፣ ቤተ መቅድሱን ለመሥራት ሲነሡ አወኳቸው።5ከፋርስ ንጉሥ ከቂሮስ ዘመነ መንግሥት ጀምሮ እስከ ፋርስ ንጉሥ እስከ ዳርዮስ ዘመነ መንግሥት ድረስ ዕቅዶቻቸውን የሚያሰናክሉ መካሪዎችን በገንዘብ ገዙባቸው።

በጠረክሲስና በአርጤክስስ ዘመን የተደረገ ሌላው ተቃውሞ

6በጠረክሲስ ዘመነ መንግሥት መጀመሪያ በይሁዳና በኢየሩሳሌም ነዋሪዎች ላይ የጽሑፍ ክስ መሠረቱባቸው።

7በፋርስ ንጉሥ በአርጤክስስ ዘመን ቢሽላም፣ ሚትሪዳጡ፣ ጣብኤልና ተባባሪዎቹ ወደ አርጤክስስ ደብዳቤ ጻፉ። ደብዳቤው የተጻፈው በአረማይስጥ ፊደል፣ በአረማይስጥ ቋንቋ ነበረ4፥7 ወይም፣ በአረማይስጥ ቋንቋ ተጽፎ በዚያው ቋንቋ የተተረጐመ። ዕዝ 4፥8–6፥18 ያለው ክፍል የተጻፈው በአረማይስጥ ቋንቋ ነው።

8አገረ ገዡ ሬሁምና ጸሓፊው ሲምሳይ በኢየሩሳሌም ላይ ለንጉሡ ለአርጤክስስ እንዲህ የሚል ደብዳቤ ጻፉ፤

9ደብዳቤው የተጻፈው፣ ከአገረ ገዡ ሬሁም፣ ከጸሓፊው ሲምሳይ በትሪፖሊስ፣ በፋርስ፣ በአርክ፣ በባቢሎን፣ እንዲሁም በሱሳ ማለትም በኤላማውያን ላይ ዳኞችና ገዦች ከሆኑት ከተባባሪዎቻቸው፣ 10ደግሞም ታላቁና ኀያሉ አስናፈር4፥10 በአረማይስጥ ቋንቋ “አሹርባኒጳል” ማለት ነው። አፍልሶ በሰማርያ ከተማና ከኤፍራጥስ ወንዝ ማዶ እንዲሰፍሩ ካደረጋቸው ሌሎች ሕዝቦች ነው።

11የላኩለት ደብዳቤ ቅጅ ይህ ነው፤

ለንጉሥ አርጤክስስ፣

በኤፍራጥስ ወንዝ ማዶ ከሚኖሩት አገልጋዮችህ የተላከ፤

12ከአንተ ዘንድ ወደ እኛ የመጡት አይሁዳውያን ወደ ኢየሩሳሌም በመሄድ ዐመፀኛና ርኵስ ከተማ እንደ ገና በመሥራት ላይ ናቸው፤ ቅጥሮቿንም እንደ ገና በመሥራትና መሠረቶቿንም በመጠገን ላይ መሆናቸው በንጉሡ ዘንድ የታወቀ ይሁን።

13ከዚህም በላይ ይህች ከተማ ከተሠራች፣ ቅጥሮቿም እንደ ገና ከተገነቡ፣ ቀረጥና እጅ መንሻ ወይም ግብር እንደማይከፍሉ፣ የቤተ መንግሥቱም ገቢ እንደሚቀንስ በንጉሡ ዘንድ የታወቀ ይሁን። 14አሁንም እኛ ስለ ቤተ መንግሥቱ ስለሚገደን፣ የንጉሡም ክብር ሲነካ ዝም ብሎ ማየት ተገቢ ሆኖ ስላላገኘነው፣ ይህ ነገር በንጉሡ ዘንድ የታወቀ እንዲሆን ይህን መልእክት ልከናል፤ 15ስለዚህ በአባቶችህ ቤተ መዛግብት ምርመራ ይደረግ፤ በእነዚህ መዛግብት ውስጥ ይህች ከተማ ዐመፀኛ ከተማ እንደሆነች፣ ነገሥታትንና አውራጃዎችን የጐዳችና ከጥንት ጀምሮ የዐመፅ ጐሬ ስለ መሆኗ ማስረጃ ታገኛለህ፤ እንግዲህ ከተማዪቱ የተደመሰሰችው በዚህ ምክንያት ነው። 16ይህች ከተማ ተመልሳ የምትሠራና ቅጥሮቿም እንደ ገና የሚገነቡ ከሆነ፣ ከኤፍራጥስ ማዶ ምንም ነገር እንደማ ይኖርህ ንጉሥ ታውቅ ዘንድ እንወዳለን።

17ንጉሡም ይህን መልስ ላከ፤

ለአገረ ገዡ ሬሁም፣ ለጸሓፊው ሲምሳይ፣ በሰማርያና በኤፍራጥስ ማዶ ለሚኖሩ ተባባሪዎቻቸው፤

ሰላም ለእናንተ ይሁን፤

18የላካችሁልኝ ደብዳቤ በፊቴ ተተርጒሞ ተነቧል። 19እኔም ትእዛዝ ሰጥቼ ምርመራ ተደርጎአል፤ በምርመራውም መሠረት ይህች ከተማ ከጥንት ጀምሮ በነገሥታት ላይ ስታምፅ የኖረች የዐመፅና የወንጀል መናኸሪያ እንደሆነች ማስረጃ ተገኝቶአል። 20ኢየሩሳሌም ከኤፍራጥስ ማዶ ያለውን አገር ሁሉ የገዙ፣ ቀረጥ፣ ግብርና እጅ መንሻም ይቀበሉ የነበሩ ኀያላን ነገሥታት ነበሯት። 21አሁንም እኔ ትእዛዝ እስከምሰጥበት ድረስ ይህች ከተማ እንደ ገና እንዳትሠራ ሥራውን ያቆሙ ዘንድ ለእነዚህ ሰዎች ትእዛዝ አስተላልፉ።

22ይህን ነገር ቸል እንዳትሉ ተጠንቀቁ፤ በነገሥታቱ ላይ የሚደርሰው ኪሣራ ለምን እየበዛ ይሄዳል?

23የንጉሡ የአርጤክስስ ደብዳቤ ቅጅ በሬሁም፣ በጸሓፊው በሲምሳይና በተባባሪዎቻቸው ፊት እንደ ተነበበ፣ ወዲያውኑ በኢየሩሳሌም ወደሚገኙት አይሁድ ሄደው ሥራውን እንዲያቆሙ አስገደዷቸው።

24ስለዚህም በኢየሩሳሌም የሚሠራው የእግዚአብሔር ቤት ሥራ እስከ ፋርስ ንጉሥ እስከ ዳርዮስ ዘመነ መንግሥት ሁለተኛ ዓመት ድረስ ተቋረጠ።

Thai New Contemporary Bible

เอสรา 4:1-24

ศัตรูพยายามขัดขวาง

1เมื่อบรรดาศัตรูของยูดาห์และเบนยามินได้ยินว่า เชลยทั้งหลายกำลังสร้างพระวิหารเพื่อพระยาห์เวห์พระเจ้าแห่งอิสราเอล 2พวกเขาก็มาพบเศรุบบาเบลและหัวหน้าครอบครัวต่างๆ และกล่าวว่า “ขอให้พวกเราช่วยท่านสร้างเถิด เพราะเราก็แสวงหาพระเจ้าของท่านเช่นเดียวกับท่าน เราได้ถวายเครื่องบูชาแด่พระองค์นับตั้งแต่กษัตริย์เอสารฮัดโดนแห่งอัสซีเรียนำเรามาที่นี่”

3แต่เศรุบบาเบล เยชูอา และหัวหน้าครอบครัวต่างๆ ของอิสราเอลตอบว่า “ท่านไม่มีส่วนร่วมกับเราในการสร้างพระวิหารถวายแด่พระเจ้าของเรา เราเท่านั้นที่จะสร้างถวายพระยาห์เวห์พระเจ้าแห่งอิสราเอลตามที่กษัตริย์ไซรัสแห่งเปอร์เซียทรงบัญชาเราไว้”

4บรรดาคนที่อาศัยอยู่ในถิ่นนั้นจึงพยายามทำลายขวัญของชาวยูดาห์ และทำให้เขาไม่กล้าสร้างต่อ4:4 หรือและสร้างปัญหาให้แก่พวกเขาขณะที่พวกเขาสร้างพระวิหาร 5คนเหล่านั้นว่าจ้างที่ปรึกษาไว้คอยก่อกวนขัดขวางงานของพวกเขาตลอดรัชกาลกษัตริย์ไซรัสแห่งเปอร์เซียจวบจนรัชกาลกษัตริย์ดาริอัสแห่งเปอร์เซีย

การขัดขวางในรัชกาลเซอร์ซีสและอารทาเซอร์ซีส

6ต้นรัชกาลกษัตริย์เซอร์ซีส4:6 ภาษาฮีบรูว่าอาหะสุเอรัสเป็นอีกรูปหนึ่งของเซอร์ซีสซึ่งเป็นชื่อภาษาเปอร์เซีย พวกเขาตั้งข้อหาฟ้องร้องประชาชนยูดาห์และเยรูซาเล็ม

7และในรัชกาลของกษัตริย์อารทาเซอร์ซีสแห่งเปอร์เซีย บิชลาม มิทเรดาท และทาเบเอลกับพรรคพวกเขียนจดหมายราบทูลพระองค์เป็นภาษาอารเมค4:7 อสร.4:8—6:18 เขียนเป็นภาษาอารเมคและมีผู้แปลถวาย

8ผู้บัญชาการเรฮูมและเลขานุการชิมชัยเขียนจดหมายฟ้องร้องเยรูซาเล็ม กราบทูลกษัตริย์อารทาเซอร์ซีสดังนี้ว่า

9ผู้บัญชาการเรฮูมและเลขานุการชิมชัยพร้อมคณะ อันได้แก่ เหล่าตุลาการ และเจ้าหน้าที่ปกครองคนจากทริโปลิส เปอร์เซีย4:9 หรือเจ้าหน้าที่ ตุลาการและผู้ว่าการที่ปกครองคนจาก เอเรก และบาบิโลน พวกเอลามแห่งสุสา 10และชนชาติอื่นซึ่งอาชูร์บานิปาล4:10 ภาษาอารเมคว่าโอสนัปปาร์เป็นอีกรูปหนึ่งของอาชูร์บานิปาลผู้ยิ่งใหญ่และสูงศักดิ์นำตัวมาและให้ตั้งถิ่นฐานในเยรูซาเล็ม สะมาเรีย และทั่วดินแดนใกล้เคียงที่อีกฟากหนึ่งของแม่น้ำยูเฟรติส

11(สำเนาจดหมายที่พวกเขานำขึ้นกราบทูลกษัตริย์ ความว่า)

กราบทูล กษัตริย์อารทาเซอร์ซีส

จากบรรดาข้าราชบริพารของพระองค์ที่อีกฟากหนึ่งของแม่น้ำยูเฟรติส

12ขอกราบทูลให้ทรงทราบว่าชาวยิวซึ่งถูกส่งตัวจากบาบิโลนไปยังเยรูซาเล็มกำลังสร้างนครจอมกบฏและชั่วร้ายนั้นขึ้นใหม่ พวกเขากำลังซ่อมแซมกำแพงเมืองและฐานราก

13ยิ่งกว่านั้นฝ่าพระบาทควรจะได้ทราบว่า หากเมืองนี้สร้างเสร็จและซ่อมแซมกำแพงเมืองเรียบร้อยแล้ว พวกเขาจะไม่ส่งบรรณาการ ค่าธรรมเนียม และค่าภาษี ทำให้เงินรายได้ของหลวงขาดหายไป 14เนื่องจากเหล่าข้าพระบาทจงรักภักดีต่อฝ่าพระบาท ไม่ประสงค์จะเห็นฝ่าพระบาทถูกหมิ่นพระเกียรติ จึงนำความขึ้นกราบทูล 15เพื่อขอทรงสั่งให้ค้นดูจดหมายเหตุของกษัตริย์องค์ก่อนๆ ในบันทึกเหล่านี้ฝ่าพระบาทจะพบว่านครแห่งนี้ชอบกบฏและสร้างความเดือดร้อนแก่เหล่ากษัตริย์และแว่นแคว้นต่างๆ เป็นนครที่ชอบกบฏแข็งเมืองมาตั้งแต่ครั้งโบราณ ด้วยเหตุนี้จึงถูกทำลายไป 16ข้าพระบาททั้งหลาย ขอกราบทูลว่าหากเมืองนี้สร้างสำเร็จและกำแพงเมืองสร้างขึ้นได้ ฝ่าพระบาทอาจจะสูญเสียจักรวรรดิที่อีกฟากหนึ่งของแม่น้ำยูเฟรติสนี้ไป

17กษัตริย์ทรงส่งพระราชสาส์นตอบว่า

ถึงผู้บัญชาการเรฮูม เลขานุการชิมชัย และพวกพ้องซึ่งอาศัยในสะมาเรียและอาศัยอยู่ที่อีกฟากหนึ่งของแม่น้ำยูเฟรติส

สวัสดี

18จดหมายที่ท่านส่งมามีการอ่านและแปลให้เราฟังแล้ว 19เราสั่งให้สืบค้นเรื่องราวก็พบว่าเมืองนี้มีประวัติยาวนานว่าได้กบฏแข็งเมืองต่อกษัตริย์ต่างๆ และมักก่อการจลาจลและความวุ่นวายต่างๆ 20ในเยรูซาเล็มยังเคยมีกษัตริย์ที่ยิ่งใหญ่ซึ่งปกครองดินแดนทั้งหมดเหนือแม่น้ำยูเฟรติส และเรียกเก็บภาษี เครื่องบรรณาการ และค่าธรรมเนียมมากมาย 21ฉะนั้นจงสั่งให้คนเหล่านี้หยุดงานจะได้ไม่มีการสร้างเมืองนี้ขึ้นใหม่จนกว่าเราจะสั่ง 22จงใส่ใจ อย่าละเลยเรื่องนี้ เราจะปล่อยให้สถานการณ์นี้บานปลายจนเสียหายกระทบกระเทือนต่อผลประโยชน์ของหลวงทำไม?

23เมื่อเรฮูมและเลขานุการชิมชัยกับพรรคพวกได้ฟังความในพระราชสาส์นของกษัตริย์อารทาเซอร์ซีสแล้ว ก็รีบมายังเยรูซาเล็ม และใช้กำลังบังคับให้ชาวยิวหยุดการก่อสร้าง

24ฉะนั้นงานก่อสร้างพระวิหารของพระเจ้าในเยรูซาเล็มจึงหยุดชะงักลงจนถึงปีที่สองของรัชกาลกษัตริย์ดาริอัสแห่งเปอร์เซีย