ወደ አገራቸው የተመለሱ ምርኮኞች ዝርዝር
2፥1-70 ተጓ ምብ – ነህ 7፥6-73
1የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ወደ ባቢሎን ማርኮ ከወሰዳቸው መካከል ከምርኮ ተመልሰው ወደ የራሳቸው ከተሞች፣ ወደ ይሁዳና ወደ ኢየሩሳሌም የመጡት የአገሩ ልጆች እነዚህ ናቸው፤ 2የመጡትም ከዘሩባቤል፣ ከኢያሱ፣ ከነህምያ፣ ከሠራያ፣ ከረዕላያ፣ ከመርዶክዮስ፣ ከበላሳን፣ ከመሴፋር፣ ከበጉዋይ፣ ከሬሁም፣ ከበዓና ጋር ነበር።
የተመለሱት የእስራኤል ሰዎች ዝርዝር የሚከተለው ነው፦
36ካህናቱ፦
40ሌዋውያኑ፦
41መዘምራኑ፦
42የቤተ መቅደሱ በረኞች፦
43የቤተ መቅደሱ አገልጋዮች፦
55የሰሎሞን አገልጋዮች ዘሮች፦
59ከዚህ የሚከተሉት ደግሞ ከቴልሜላ፣ ከቴላሬሳ፣ ከክሩብ፣ ከአዳንና ከኢሜር ከተሞች የመጡ ናቸው፤ ነገር ግን ቤተ ሰቦቻቸው የእስራኤል ዘር መሆናቸውን ማስረዳት አልቻሉም፦
61ከካህናቱ መካከል፦
የኤብያ፣ የአቆስና የቤርዜሊ ዘሮች፤ ቤርዜሊ በዚህ ስም ሊጠራ የቻለው የገለዓዳዊውን የቤርዜሊን ልጅ አግብቶ ስለ ነበር ነው።
62እነዚህ በትውልድ መዝገቡ ውስጥ የቤተ ሰባቸውን ዝርዝር ፈለጉ፤ ነገር ግን ማግኘት አልቻሉም፤ ስለዚህ እንዳልነጹ ተቈጥረው፣ ከክህነት አገልግሎት ተገለሉ። 63አገረ ገዥውም በኡሪምና በቱሚም እግዚአብሔርን የሚጠይቅ ካህን እስኪነሣ ድረስ፣ እጅግ ከተቀደሰው ምግብ እንዳይበሉ አዘዛቸው።
64ከምርኮ የተመለሱት ሰዎች ብዛት 42,360 ነበረ፤ 65ይህም 7,337 ከሚሆኑት ከወንዶችና ከሴቶች አገልጋዮቻቸው በተጨማሪ ነው፤ 200 ወንድና ሴት ዘማሪዎችም ነበሯቸው። 66736 ፈረሶች፣ 245 በቅሎዎች፣ 67435 ግመሎችና 6,720 አህዮች ነበሯቸው።
68በኢየሩሳሌም ወደሚገኘው ወደ እግዚአብሔር ቤት በደረሱ ጊዜ፣ አንዳንድ የቤተ ሰብ መሪዎች በቀድሞው ቦታ እንደ ገና ለሚሠራው የእግዚአብሔር ቤት በበጎ ፈቃድ ስጦታ አደረጉ። 69እንደየችሎታቸውም 61,000 የወርቅ ዳሪክ2፥69 500 ኪሎ ግራም ያህል ነው።፣ 5,000 ምናን2፥69 2.9 ሜትሪክ ቶን ያህል ነው። ብር፣ 100 ልብሰ ተክህኖ ለግምጃ ቤቱ ሰጡ።
70ካህናቱ፣ ሌዋውያኑ፣ መዘምራኑ፣ በር ጠባቂዎቹና የቤተ መቅደስ አገልጋዮቹ፣ ከሌሎች ሰዎች ጋር በየራሳቸው ከተሞች ሰፈሩ፤ የቀሩት እስራኤላውያንም በየከተሞቻቸው ተቀመጡ።