New Amharic Standard Version

ዕዝራ 10:1-44

ሕዝቡ ኀጢአቱን ተናዘዘ

1ዕዝራ በእግዚአብሔር ቤት ፊት ወድቆ በሚጸልይበት፣ በሚናዘዝበትና በሚያለቅስበት ጊዜ ወንዶች፣ ሴቶችና ልጆች የሚገኙበት እጅግ ብዙ የእስራኤል ማኅበር በዙሪያው ተሰበሰበ፤ እነርሱም እንደዚሁ አምርረው አለቀሱ። 2ከዚያም ከኤላም ዘሮች አንዱ የሆነው የይሒኤል ልጅ ሴኬንያ ዕዝራን እንዲህ አለው፤ “በዙሪያችን ካሉት አሕዛብ፣ ባዕዳን ሴቶችን በማግባታችን ለአምላካችን ታማኞች ሆነን አልተገኘንም፤ ይህም ሆኖ አሁንም ለእስራኤል ተስፋ አለ። 3አሁንም እንደ ጌታዬ ምክርና የአምላካችንን ትእዛዝ እንደሚፈሩ ሰዎች እነዚህን ሴቶችና ልጆቻቸውን ለመስደድ በአምላካችን ፊት ቃል ኪዳን እንግባ፤ በሕጉም መሠረት ይፈጸም። 4ዕዝራ፣ ነገሩ በእጅህ ነው፤ ተነሥ! እኛም እንደግፍሃለን፤ በርትተህም፤ አድርገው።”

5ዕዝራም ተነሥቶ ዋና ዋናዎቹ ካህናት፣ ሌዋውያንና እስራኤል ሁሉ የቀረበውን ሐሳብ እንዲፈጽሙ አስማላቸው፤ እነርሱም ማሉ። 6ከዚያም ዕዝራ ከእግዚአብሔር ቤት ፊት ተነሥቶ ወደ ኤልያሴብ ልጅ ወደ ዮሐናን ክፍል ገባ፤ ምርኮኞቹ ታማኞች ሆነው ባለ መገኘታቸው ያለቅስ ነበር፤ በዚያም ምግብ አልቀመሰም፤ ውሃም አልጠጣም።

7ከዚያም ምርኮኞቹ ሁሉ በኢየሩሳሌም እንዲሰበሰቡ በይሁዳና በኢየሩሳሌም ዐዋጅ ተነገረ፤ 8ዐዋጁም በሦስት ቀን ውስጥ ያልመጣ ማንም ሰው በሹማምቱና በሽማግሌዎቹ ውሳኔ መሠረት ንብረቱ ሁሉ እንዲወረስ፣ ራሱም ከምርኮኞቹ ጉባኤ እንዲወገድ የሚያዝ ነበር።

9ስለዚህ በሦስት ቀን ውስጥ የይሁዳና የብንያም ሰዎች ሁሉ በኢየሩሳሌም ተሰበሰቡ፤ በዘጠነኛው ወር በሃያኛውም ቀን ሕዝቡ ሁሉ ስለ ወቅቱ ጒዳይና ስለ ከባዱ ዝናብ በመጨነቅ በእግዚአብሔር ቤት ፊት ባለው አደባባይ ተቀምጠው ነበር። 10ከዚያም ካህኑ ዕዝራ ተነሥቶ እንዲህ አላቸው፤ “እናንተ ታማኞች አልነበራችሁም፤ በእስራኤል በደል ላይ በደል በመጨመር ባዕዳን ሴቶችን አገባችሁ። 11አሁንም ለአባቶቻችሁ አምላክ ለእግዚአብሔር ተናዘዙ፤ ፈቃዱን ፈጽሙ፤ በዙሪያችሁ ካሉት አሕዛብና ከባዕዳን ሚስቶቻችሁ ተለዩ።”

12ጉባኤውም ሁሉ እንዲህ ሲሉ በታላቅ ድምፅ መለሱ፤ “እውነት ብለሃል፤ ያልኸውን መፈጸም ይገባናል። 13ይሁን እንጂ በዚህ የተሰበሰበው ሕዝብ ብዙ ነው፤ ወቅቱም ክረምት ነው፤ ስለዚህ ውጭ መቆም አንችልም፤ ከዚህም በላይ በዚህ ነገር ብዙ ኀጢአት ስለ ሠራን፣ ይህ ጒዳይ በአንድና በሁለት ቀን የሚያልቅ አይደለም። 14ስለዚህ ሹሞቻችን በማኅበሩ ሁሉ ምትክ መደረግ ያለበትን ያድርጉ። ከዚያም በዚህ የተነሣ የመጣው የአምላካችን ብርቱ ቊጣ ከእኛ እስኪመለስ ድረስ፣ በየከተሞቻችን ያሉ ባዕዳን ሴቶችን ያገቡ ሁሉ በየከተማው ካሉት ሽማግሌዎችና ዳኞች ጋር በተወሰነው ቀን ይምጡ።” 15ይህንንም ነገር የተቃወሙት ከሜሱላምና ከሌዋዊው ከሳባታይ ድጋፍ ያገኙት የአሣሄል ልጅ ዮናታንና የቴቁዋ ልጅ የሕዝያ ብቻ ናቸው።

16ስለዚህ ምርኮኞቹ እንደ ተባለው አደረጉ፤ ካህኑ ዕዝራም ከእያንዳንዱ የቤተ ሰብ ምድብ አንዳንድ የቤተ ሰብ ኀላፊ የሆነ ሰው መረጠ፤ ሁሉም በየስማቸው ተመዘገቡ። ከዚያም በዐሥረኛው ወር በመጀመሪያው ቀን ጒዳዩን ለመመርመር ተቀመጡ፤ 17በመጀመሪያው ወር በመጀመሪያው ቀን ባዕዳን ሴቶችን ያገቡትን ወንዶች ሁሉ አጣርተው ጨረሱ።

ከባዕዳን ሴቶች ጋር የተጋቡት ሰዎች

18ከካህናት ዘሮች መካከል ባዕዳን ሴቶችን ያገቡት ከዚህ የሚከተሉት ናቸው፤

ከኢዮሴዴቅ ልጅ ከኢያሱ ዘሮችና ከወንድሞቹ መካከል፤ መዕሤያ፣ አልዓዛር፣ ያሪብና ጎዶልያስ። 19እነዚህ ሁሉ ሚስቶቻቸውን ለመፍታት ቃል በመግባት እጃቸውን ሰጡ፤ ስለ በደላቸውም እያንዳንዳቸው ከመንጋው አንዳንድ አውራ በግ ለበደል መሥዋዕት አቀረቡ።

20ከኢሜር ዘሮች፤

አናኒና ዝባድያ።

21ከካሪም ዘሮች፤

መዕሤያ፣ ኤልያስ፣ ሸማያ፣ ይሒኤልና ዖዝያ።

22ከፋስኩር ዘሮች፤

ኤልዮዔናይ፣ መዕሤያ፣ ይስማኤል፣ ናትናኤል፣ ዮዛባትና ኤልዓሣ።

23ከሌዋውያኑም መካከል፤

ዮዛባት፣ ሰሜኢ፣ ቆሊጣስ የሚባል ቆልያ፣ ፈታያ፣ ይሁዳ፣ አልዓዛር።

24ከመዘምራኑም መካከል፤

ኤልያሴብ።

ከበር ጠባቂቹም፣

ሰሎም፣ ጤሌም፣ ኡሪ።

25ከሌሎቹ እስራኤላውያን መካከል፤

ከፋሮስ ዘሮች፤ ራምያ፣ ይዝያ፣ መልክያ፣

ሚያሚን፣ አልዓዛር፣ መልክያና በናያስ።

26ከኤላም ዘሮች፤

መታንያ፣ ዘካርያስ፣ ይሒኤል፣ አብዲ፣ ይሬሞትና ኤልያ።

27ከዛቱዕ ዘሮች፤

ዒሊዮዔናይ፣ ኢልያሴብ፣ መታንያ፣ ይሬሞት፣ ዛባድና ዓዚዛ።

28ከቤባይ ዘሮች፤

ይሆሐናን፣ ሐናንያ፣ ዛባይና አጥላይ።

29ከባኒ ዘሮች፤

ሜሱላም፣ መሉክ፣ ዓዳያ፣ ያሱብ፣ ሸዓልና ራሞት።

30ከፈሐት ሞዓብ ዘሮች፤

ዓድና፣ ክላል፣ በናያስ፣ መዕሤያ፣ መታንያ፣ ባስልኤል፣ ቢንዊና ምናሴ።

31ከካሪም ዘሮች፤

አልዓዛር፣ ይሺያ፣ መልክያ፣ ሸማያ፣ ስምዖን፣ 32ብንያም፣ መሉክና ሰማራያ።

33ከሐሱም ዘሮች፤

መትናይ፣ መተታ፣ ዛባድ፣ ኤሊፋላት፣ ይሬማይ፣ ምናሴና ሰሜኢ።

34ከባኒ ዘሮች፤

መዕዳይ፣ ዓምራም፣ ኡኤል፣ 35በናያስ፣ ቤድያ፣ ኬልቅያ፣ 36ወንያ፣ ሜሪሞት፣ ኤልያሴብ፣ 37መታንያ፣ መትናይና የዕሡ።

38ከቢንዊ ዘሮች፤

ሰሜኢ10፥37-38 የሰብዓ ሊቃናት ትርጒም (እንዲሁም መጽሐፈ ዕዝራ ሱቱኤል 9፥34) ይመ፤ ዕብራይስጡ ግን፣ የዕሡ፣ ባኒና ቤኑዊ ይላል።39ሰሌምያ፣ ናታን፣ ዓዳያ፣

40መክነድባይ፣ ሴሴይ፣ ሸራይ፣ 41ኤዝርኤል፣

ሰሌምያ፣ ሰማራያ፣ 42ሰሎም፣ አማርያና ዮሴፍ።

43ከናባው ዘሮች፤

ይዒኤል፣ መቲትያ፣ ዛባድ፣ ዘቢና፣ ያዳይ፣ ኢዮኤልና በናያስ።

44እነዚህ ሁሉ ባዕዳን ሴቶችን ያገቡ ናቸው፤ ከእነርሱም ጥቂቶቹ ከእነዚህ ሴቶች ልጆችን ወልደው ነበር።10፥44 ወይም ከልጆቻቸው ጋር ላኩአቸው

Thai New Contemporary Bible

เอสรา 10:1-44

ประชาชนสารภาพบาป

1ขณะที่เอสราอธิษฐานและสารภาพบาป ร่ำไห้และทิ้งกายลงหน้าพระนิเวศของพระเจ้า ฝูงชนอิสราเอลหมู่ใหญ่ทั้งผู้ชายผู้หญิงและเด็กมาห้อมล้อมเขา พวกเขาร้องไห้อย่างรันทดเช่นกัน 2แล้วเชคานิยาห์บุตรเยฮีเอลวงศ์วานเอลามกล่าวกับเอสราว่า “พวกข้าพเจ้าไม่ซื่อสัตย์ต่อพระเจ้าของเราที่ไปแต่งงานกับผู้หญิงจากชนชาติต่างๆ ที่แวดล้อมเรา แต่ถึงกระนั้นก็ยังมีความหวังเหลืออยู่สำหรับอิสราเอล 3บัดนี้ให้เราทำพันธสัญญาต่อหน้าพระเจ้าของเราว่าจะทิ้งภรรยาเหล่านี้กับลูกๆ ตามคำแนะนำของเจ้านายของข้าพเจ้ากับบรรดาผู้ที่เกรงกลัวพระบัญชาของพระเจ้าของเรา ขอให้เป็นไปตามบทบัญญัติเถิด 4ลุกขึ้นเถิด เรื่องนี้สุดแท้แต่ท่าน เราจะสนับสนุนท่าน ขอให้กล้าหาญและลงมือทำเถิด”

5ดังนั้นเอสราจึงลุกขึ้นและให้บรรดาหัวหน้าปุโรหิต คนเลวี และชนอิสราเอลทั้งปวงปฏิญาณว่าจะทำตามที่เสนอมา พวกเขาก็ปฏิญาณ 6แล้วเอสราละจากหน้าพระนิเวศของพระเจ้าเข้าไปในห้องของเยโฮฮานันบุตรเอลียาชีบ ขณะอยู่ที่นั่นเขาไม่รับประทานอาหารหรือดื่มน้ำ เพราะทุกข์โศกเนื่องด้วยความไม่ซื่อสัตย์ของเชลยที่กลับมา

7จากนั้นมีการออกหมายประกาศทั่วยูดาห์และเยรูซาเล็มให้เชลยทุกคนมารวมกันที่เยรูซาเล็ม 8ผู้ใดไม่มาปรากฏตัวภายในสามวันจะถูกริบทรัพย์สินทั้งหมดตามมติของบรรดาเจ้าหน้าที่กับผู้อาวุโส และถูกขับออกจากชุมนุมของพวกเชลย

9ภายในสามวันคนยูดาห์และเบนยามินทั้งหมดก็มาชุมนุมกันในเยรูซาเล็ม และในวันที่ยี่สิบเดือนที่เก้าประชากรทั้งปวงมานั่งอยู่ในลานหน้าพระนิเวศของพระเจ้า เป็นทุกข์ยิ่งนักเพราะเรื่องนี้และเพราะฝนตก 10แล้วปุโรหิตเอสราจึงลุกขึ้นและกล่าวแก่พวกเขาว่า “ท่านทั้งหลายไม่ซื่อสัตย์ ไปแต่งงานกับหญิงต่างชาติ เพิ่มความผิดให้อิสราเอล 11บัดนี้จงสารภาพผิดต่อพระยาห์เวห์พระเจ้าของบรรพบุรุษของท่าน และทำตามพระประสงค์ของพระองค์ จงแยกตัวออกจากชนชาติทั้งหลายโดยรอบและจากภรรยาต่างชาติของท่าน”

12ทั้งชุมชนก็ตอบเสียงดังว่า “ท่านพูดถูก! เราต้องทำตามที่ท่านบอก 13แต่เรื่องนี้ไม่อาจจัดการให้เสร็จภายในวันสองวัน เพราะเราได้ทำบาปมากในเรื่องนี้ และที่นี่มีคนมากมาย ทั้งเป็นฤดูฝน เราจึงไม่อาจทนอยู่ข้างนอก 14ขอให้บรรดาเจ้าหน้าที่จัดการแทนทั้งชุมชน แล้วให้ทุกคนในเมืองของเราที่มีภรรยาเป็นชาวต่างชาติมาพบกับผู้อาวุโสและตุลาการในแต่ละเมืองตามเวลาที่กำหนด จนกว่าพระพิโรธอันรุนแรงของพระเจ้าของเราในเรื่องนี้จะหันเหไปจากเรา” 15มีแต่โยนาธานบุตรอาสาเฮลและยาไซอาห์บุตรทิกวาห์ที่ต่อต้านเรื่องนี้โดยได้รับการสนับสนุนจากเมชุลลามกับชับเบธัยคนเลวี

16เหล่าเชลยจึงทำตามที่เสนอมา ปุโรหิตเอสราเลือกหัวหน้าครอบครัวคนหนึ่งจากกลุ่มครอบครัวแต่ละกลุ่มที่ได้แบ่งไว้และระบุชื่อทุกคน หัวหน้าเหล่านี้นั่งลงเพื่อไต่สวนแต่ละกรณีในวันที่หนึ่งเดือนที่สิบ 17เมื่อถึงวันที่หนึ่งเดือนที่หนึ่ง พวกเขาก็จัดการกับทุกคนที่ได้แต่งงานกับหญิงต่างชาติเรียบร้อย

รายชื่อผู้กระทำผิด

18คนที่ไปแต่งงานกับหญิงต่างชาติในหมู่วงศ์วานปุโรหิตได้แก่

จากวงศ์วานของเยชูอาบุตรโยซาดักและพี่น้องของเขาได้แก่ มาอาเสอาห์ เอลีเยเซอร์ ยารีบ และเกดาลิยาห์ 19(พวกเขาทั้งหมดยกมือปฏิญาณว่าจะทิ้งภรรยาและมอบแกะผู้จากฝูงคนละตัวเป็นเครื่องบูชาลบความผิด)

20จากวงศ์วานของอิมเมอร์ได้แก่ ฮานานี และเศบาดิยาห์

21จากวงศ์วานของฮาริมได้แก่ มาอาเสอาห์ เอลียาห์ เชไมอาห์ เยฮีเอล และอุสซียาห์

22จากวงศ์วานของปาชเฮอร์ได้แก่ เอลีโอเอนัย มาอาเสอาห์ อิชมาเอล เนธันเอล โยซาบาด และเอลาสาห์

23ในหมู่คนเลวีได้แก่ โยซาบาด ชิเมอี เคลายาห์ (คือเคลิทา) เปธาหิยาห์ ยูดาห์ และเอลีเยเซอร์

24จากพวกนักร้องได้แก่ เอลียาชีบ

จากพวกยามเฝ้าประตูได้แก่ ชัลลูม เทเลม และอูรี

25และในหมู่ชาวอิสราเอลอื่นๆ ได้แก่

จากวงศ์วานของปาโรชได้แก่ รามียาห์ อิสซียาห์ มัลคียาห์ มิยามิน เอเลอาซาร์ มัลคียาห์ และเบไนยาห์

26จากวงศ์วานของเอลามได้แก่ มัททานิยาห์ เศคาริยาห์ เยฮีเอล อับดี เยเรโมท และเอลียาห์

27จากวงศ์วานของศัทธูได้แก่ เอลีโอเอนัย เอลียาชีบ มัททานิยาห์ เยเรโมท ศาบาด และอาซีซา

28จากวงศ์วานของเบบัยได้แก่ เยโฮฮานัน ฮานันยาห์ ศับบัย และอัทลัย

29จากวงศ์วานของบานีได้แก่ เมชุลลาม มัลลุค อาดายาห์ ยาชูบ เชอัล และเยเรโมท

30จากวงศ์วานของปาหัทโมอับได้แก่ อัดนา เคลาล เบไนยาห์ มาอาเสอาห์ มัททานิยาห์ เบซาเลล บินนุย และมนัสเสห์

31จากวงศ์วานของฮาริมได้แก่ เอลีเยเซอร์ อิสชีอาห์ มัลคียาห์ เชไมอาห์ ชิเมโอน

32เบนยามิน มัลลุค และเชมาริยาห์

33จากวงศ์วานของฮาชูมได้แก่ มัทเทนัย มัททัตตาห์ ศาบาด เอลีเฟเลท เยเรมัย มนัสเสห์ และชิเมอี

34จากวงศ์วานของบานีได้แก่ มาอาดัย อัมราม อูเอล 35เบไนยาห์ เบไดยาห์ เคลุฮี 36วานิยาห์ เมเรโมท เอลียาชีบ 37มัททานิยาห์ มัทเทนัย และยาอาสุ

38จากวงศ์วานของบินนุย10:37-38 ภาษาฮีบรูว่ายาอาสุ 38และบานี และบินนุยได้แก่ ชิเมอี 39เชเลมิยาห์ นาธัน อาดายาห์ 40มัคนาเดบัย ชาชัย ชารัย 41อาซาเรล เชเลมิยาห์ เชมาริยาห์ 42ชัลลูม อามาริยาห์ และโยเซฟ

43จากวงศ์วานของเนโบได้แก่ เยอีเอล มัททีธิยาห์ ศาบาด เศบินา ยาดดัย โยเอล และเบไนยาห์

44คนทั้งหมดนี้ได้แต่งงานกับหญิงต่างชาติ และบางคนมีบุตรที่เกิดจากภรรยาเหล่านั้น10:44 หรือและพวกเขาส่งภรรยาเหล่านั้นไปพร้อมกับบุตร