New Amharic Standard Version

ዕብራውያን 7:1-28

ካህኑ መልከጼዴቅ

1ይህ መልከጼዴቅ የሳሌም ንጉሥና የልዑል እግዚአብሔር ካህን ነበር፤ እርሱም አብርሃም ነገሥታትን ድል አድርጎ ሲመለስ አግኝቶት ባረከው፤ 2አብርሃምም ከሁሉ ነገር ዓሥራት አውጥቶ ሰጠው። በመጀመሪያ ስሙ “የጽድቅ ንጉሥ” ማለት ነው፤ ኋላም ደግሞ “የሳሌም ንጉሥ” ማለትም “የሰላም ንጉሥ ማለት” ነው። 3አባትና እናት ወይም የትውልድ ሐረግ የለውም፤ ለዘመኑ መጀመሪያ፣ ለሕይወቱም ፍጻሜ የለውም፤ ነገር ግን እንደ እግዚአብሔር ልጅ ለዘላለም ካህን ሆኖ ይኖራል።

4እስቲ እርሱ የቱን ያህል ታላቅ እንደሆነ ዐስቡ፤ ርእሰ አበው የሆነው አብርሃም እንኳ ካገኘው ምርኮ ዓሥራት አውጥቶ ሰጠው። 5ክህነት የተሰጣቸው የሌዊ ልጆች ምንም እንኳ ወንድሞቻቸው የአብርሃም ዘሮች ቢሆኑም፣ ከሕዝቡ ማለት ከገዛ ወንድሞቻቸው ዓሥራት እንዲቀበሉ ሕጉ ያዛል። 6ይህ ግን ትውልዱ ከሌዊ ወገን አይደለም፤ ይሁን እንጂ ከአብርሃም ዓሥራት ተቀበለ፤ የተስፋ ቃል የተቀበለውንም ባረከው። 7ትንሹ በትልቁ እንደሚባረክ ጥርጥር የለውም። 8በአንድ በኩል ዓሥራት የሚቀበሉት ሟች ሰዎች ናቸው፤ በሌላ በኩል ግን ሕያው ሆኖ እንደሚኖር የተመሰከረለት ይቀበላል። 9እንዲያውም ዓሥራት የሚቀበለው ሌዊ፣ ራሱ በአብርሃም በኩል ዓሥራት ከፍሎአል ማለት ይቻላል፤ 10ምክንያቱም መልከጼዴቅ አብርሃምን ባገኘው ጊዜ፣ ሌዊ ገና በአባቱ በአብርሃም አብራክ ነበር።

ኢየሱስ እንደ መልከጼዴቅ

11ፍጹምነት የተገኘውና ሕጉ ለሕዝቡ የተሰጠው በሌዊ ክህነት መሠረት ቢሆን ኖሮ፣ እንደ አሮን ሳይሆን እንደ መልከጼዴቅ ሹመት ያለው ሌላ ካህን መምጣቱ ለምን አስፈለገ? 12የክህነት ለውጥ ካለ ሕጉም ሊለወጥ ግድ ነውና። 13ይህ ሁሉ የተነገረለት እርሱ ከሌላ ነገድ ነው፤ ከዚያም ነገድ በመሠዊያ ያገለገለ ማንም የለም። 14ጌታችን ከይሁዳ ነገድ እንደ መጣ ግልጽ ነውና፤ ሙሴ ስለ ካህናት ሲናገር ይህን ነገድ አስመልክቶ የተናገረው ምንም ነገር የለም። 15እንደ መልከጼዴቅ ያለ ሌላ ካህን ቢነሣ ግን እኛ የተናገርነው ይበልጥ ግልጽ ይሆናል፤ 16እርሱ ካህን የሆነው በማይጠፋ የሕይወት ኀይል መሠረት እንጂ፣ እንደ ትውልዱ የሕግ ሥርዐት አይደለም፤ 17እንዲህ ተብሎ ተመስክሮለታል፤

“እንደ መልከጼዴቅ ሹመት፣

አንተ ለዘላለም ካህን ነህ።”

18የቀድሞው ትእዛዝ ደካማና የማይጠቅም በመሆኑ ተሽሮአል፤ 19ሕጉ ማንንም ፍጹም ሊያደርግ ስለማይችል ወደ እግዚአብሔር የምንቀርብበት የተሻለ ተስፋ መጥቶአል።

20ይህ ያለ መሐላ አልሆነም፤ ሌሎች ካህናት የሆኑት ያለ መሐላ ነው፤ 21እርሱ ግን ካህን የሆነው በመሐላ ነው፤ ምክንያቱም እግዚአብሔር እንዲህ ብሎ ተናግሮለታል፤

“ጌታ ማለ፤

ዐሳቡንም አይለውጥም፤

‘አንተ ለዘላለም ካህን ነህ።’ ”

22ከዚህ መሐላ የተነሣ፣ ኢየሱስ ለተሻለ ኪዳን ዋስ ሆኖአል።

23በአገልግሎታቸው እንዳይቀጥሉ ሞት ስለ ከለከላቸው፣ የቀድሞዎቹ ካህናት ቍጥራቸው ብዙ ነበር፤ 24ኢየሱስ ግን ለዘላለም የሚኖር በመሆኑ፣ ክህነቱ የማይሻር ነው። 25ስለዚህ ስለ እነርሱ እየማለደ ሁል ጊዜ በሕይወት ስለሚኖር፣ በእርሱ በኩል ወደ እግዚአብሔር የሚመጡትን ፈጽሞ7፥25 ወይም ለዘላለም ሊያድናቸው ይችላል።

26እንግዲህ ለእኛ የሚያስፈልገን፣ ቅዱስ፣ ነቀፋ የሌለበት፣ ንጹሕ፣ ከኀጢአተኞች የተለየና ከሰማያት በላይ የከበረ እንደዚህ ያለ ሊቀ ካህናት ነው። 27እርሱም እንደ ሌሎቹ ሊቃነ ካህናት፣ መጀመሪያ ስለ ራሱ ኀጢአት ከዚያም ስለ ሕዝቡ ኀጢአት በየቀኑ መሥዋዕት ማቅረብ አያስፈልገውም፤ ራሱን በሰጠ ጊዜ፣ ስለ ኀጢአታቸው ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ መሥዋዕት አቅርቦአልና። 28ሕጉ ደካማ የሆኑትን ሰዎች ሊቃነ ካህናት አድርጎ ይሾማልና፤ ከሕግ በኋላ የመጣው መሐላ ግን ለዘላለም ፍጹም የሆነውን ልጅ ሾሞአል።

Chinese Contemporary Bible (Simplified)

希伯来书 7:1-28

大祭司麦基洗德

1这位麦基洗德撒冷王,也是至高上帝的祭司。当年亚伯拉罕杀败众王凯旋归来的时候,麦基洗德迎上去为他祝福, 2亚伯拉罕把战利品的十分之一给了他。麦基洗德这名字的原意是“公义之王”,后来他又被称为撒冷王,意思是“和平之王”。 3他的父母、族谱、生辰、寿数都不得而知,他跟上帝的儿子相似,永远担任祭司的职分。

4试想,连我们的祖先亚伯拉罕都将战利品的十分之一给了他,可见他是何等的尊贵! 5按照犹太人的律法,那些承袭做祭司的利未后裔可以照例向自己的同胞,就是亚伯拉罕的后裔,收取十分之一。 6但这位与犹太人没有血缘关系的麦基洗德,不单接受了亚伯拉罕给他的十分之一,还为承受应许的亚伯拉罕祝福。 7毫无疑问,那为人祝福的总比领受祝福的位分大。 8收取十分之一的利未祭司都是会死的人,但那位收取十分之一的麦基洗德被证明仍然活着。 9这样说来,连接受十分之一奉献的利未也透过亚伯拉罕麦基洗德纳了十分之一。 10因为亚伯拉罕遇见麦基洗德时,利未虽然还没有出生,却已经在他祖先的身体里面了。

大祭司耶稣

11犹太人在利未祭司制度的基础上承受了律法,如果通过这个祭司制度可以达到纯全,又何必照麦基洗德的模式而不是亚伦的模式,另外兴起一位祭司呢? 12既然这祭司制度更改了,律法也必须更改。 13因为这里所说的这位祭司属于别的支派,那支派里从来没有在祭坛前供职的祭司。 14显然,我们的主基督属于犹大支派,摩西从来没有说这个支派会出祭司。

15-16如果照麦基洗德的模式另外兴起一位祭司,祂做祭司不是照律法要求的血统关系,而是照不能朽坏之生命的大能,事情就更加清楚了。 17因为有一处经文为祂做见证说:“你照麦基洗德的模式永远做祭司。” 18以前的条例由于本身的弱点和无益被废除了, 19因为律法并没有使人变得纯全。但如今,我们可以借着一个更美好的盼望来到上帝面前。

20此外,耶稣做祭司并非没有誓言作保,其他人做祭司没有誓言作保。 21上帝只对耶稣说过:

“主起了誓,绝不反悔,

你永远做祭司。”

22这誓言使耶稣成了更美之约的保证人。 23以前做祭司的人数极多,但因为受死亡的限制,都不能长久担任圣职。 24然而,基督永远活着,祂的祭司职位也永不更改。 25所以祂能拯救那些靠着祂来到上帝面前的人,直到永远,因为祂永远活着,为他们祈求。

26我们所需要的,正是这样一位圣洁无瑕、良善纯全、远离罪恶、超越诸天的大祭司。 27祂无需像其他大祭司每天先为自己的罪献祭,然后为百姓的罪献祭,因为祂只一次献上自己的生命,便永远完成了赎罪的工作。 28根据律法所立的大祭司都有弱点,但律法之后凭誓言所立的大祭司——上帝的儿子永远纯全。