New Amharic Standard Version

ዕብራውያን 3:1-19

ኢየሱስ ከሙሴ በላይ ነው

1እንግዲህ የሰማያዊው ጥሪ ተካፋዮች የሆናችሁ ቅዱሳን ወንድሞች ሆይ፤ የእምነታችን ሐዋርያና ሊቀ ካህናት የሆነውን ኢየሱስን አስቡ። 2ሙሴ በእግዚአብሔር ቤት ሁሉ ላይ ታማኝ እንደ ነበር፣ እርሱም ለሾመው ታማኝ ነበር። 3ቤትን የሚሠራ ከቤቱ ይልቅ የሚበልጥ ክብር እንዳለው፣ ኢየሱስም ከሙሴ የሚበልጥ ክብር የተገባው ሆኖ ተገኝቶአል፤ 4እያንዳንዱ ቤት የራሱ ሠሪ አለው፤ ነገር ግን ሁሉን የሠራ እግዚአብሔር ነው። 5ሙሴ ወደ ፊት ስለሚነገረው ነገር እየመሰከረ፣ በእግዚአብሔር ቤት ሁሉ ላይ እንደ አንድ ታማኝ አገልጋይ ነበር፤ 6ክርስቶስ ግን በእግዚአብሔር ቤት ላይ እንደ ታማኝ ልጅ ነው። እኛም የምንተማመንበትንና የምንመካበትን ተስፋ አጥብቀን ብንይዝ ቤቱ ነን።

ስለ አለማመን የተሰጠ ማስጠንቀቂያ

7ስለዚህ መንፈስ ቅዱስ እንደሚል፣

“ዛሬ ድምፁን ብትሰሙ፣

8በምድረ በዳ በፈተና ቀን፣

በዐመፅ እንዳደረጋችሁት፣

ልባችሁን አታደንድኑ።

9አባቶቻችሁ በዚያ ተፈታተኑኝ፤

መረመሩኝ፤ ያደረግሁትንም ሁሉ ለአርባ ዓመት አዩ።

10በዚያም ትውልድ ላይ የተቈጣሁት ለዚህ ነበር፤

እንዲህም አልሁ፤ ‘ልባቸው ሁል ጊዜ ይስታል፤

መንገዴንም አላወቁም፤’

11ስለዚህ በቍጣዬ እንዲህ ብዬ ማልሁ፤

“ወደ ዕረፍቴ ከቶ አይገቡም።”

12ወንድሞች ሆይ፤ ከእናንተ ማንም ከሕያው እግዚአብሔር የሚያስኰበልል፣ ኀጢአተኛና የማያምን ልብ እንዳይኖረው ተጠንቀቁ። 13ነገር ግን ከመካከላችሁ ማንም በኀጢአት ተታሎ ልቡ እንዳይደነድን፣ “ዛሬ” እየተባለ ሳለ በየቀኑ እርስ በርሳችሁ ተጽናኑ። 14በመጀመሪያ የነበረንን እምነት እስከ መጨረሻው አጽንተን ብንይዝ ከክርስቶስ ጋር ተካፋዮች እንሆናለን፤ 15ይኸውም፣

“ዛሬ ድምጹን ብትሰሙ፣

በዐመፅ እንዳደረጋችሁት፣

አሁንም ልባችሁን አታደንድኑ” እንደ ተባለው ነው።

16ሰምተው ያመፁት እነማን ነበሩ? ሙሴ ከግብፅ መርቶ ያወጣቸው ሁሉ አይደሉምን? 17አርባ ዓመት የተቈጣውስ እነማንን ነበር? ኀጢአት ሠርተው ሬሳቸው በምድረ በዳ ወድቆ የቀረውን አይደለምን? 18ያልታዘዙትን3፥18 ወይም ያላመኑትን ካልሆነ በቀር ወደ ዕረፍቱ እንዳይገቡ የማለባቸው እነማን ነበሩ? 19እንግዲህ ሊገቡ ያልቻሉት ካለማመናቸው የተነሣ እንደሆነ እንረዳለን።

Chinese Contemporary Bible (Simplified)

希伯来书 3:1-19

耶稣超越摩西

1因此,同蒙天召的圣洁的弟兄姊妹,你们应当仔细思想那位我们公认为特使和大祭司的耶稣。 2祂向委任祂的上帝尽忠,就好像摩西向上帝的全家尽忠一样。 3然而祂却比摩西配得更大的荣耀,因为建造房子的人当然比房子更尊贵。 4所有的房子都有建造者,但建造万物的是上帝。 5摩西以仆人的身份向上帝的全家尽忠,为将来要宣告的事做见证。 6但基督是以儿子的身份忠心治理上帝的家。我们若坚强勇敢,持定引以为荣的盼望,我们就是祂的家了。

不可存刚硬的心

7因此,正如圣灵说:

“你们今天若听见祂的声音,

8不可心里顽固,

像从前在旷野试探祂、悖逆祂一样。

9当时,你们的祖先试我、探我,

观看我的作为达四十年之久。

10所以,我向那世代的人发怒,

说,‘他们总是执迷不悟,

不认识我的道路。’

11我就在愤怒中起誓说,

‘他们绝不可进入我的安息。’”

12弟兄姊妹,要谨慎,免得你们当中有人心存恶念,不肯相信,背弃了永活的上帝。 13趁着还有今日,要天天互相劝勉,免得有人被罪迷惑,心里变得刚硬。 14如果我们将起初的信念坚持到底,便在基督里有份了。

15圣经上说:

“你们今日若听见祂的声音,

不可像从前那样硬着心悖逆祂。”

16听见祂的声音却又悖逆祂的是谁呢?不就是摩西埃及领出来的那些人吗? 17四十年之久惹上帝发怒的是谁呢?不就是那些犯罪作恶并倒毙在旷野的人吗? 18上帝起誓不准谁进入祂的安息呢?不就是那些不肯信从的人吗? 19可见,他们不能进入上帝的安息是因为不信的缘故。