New Amharic Standard Version

ዕብራውያን 2:1-18

ትኵረት የሚያስፈልጋቸው ነገሮች

1ስለዚህ ከሰማነው ነገር ስተን እንዳንወድቅ፣ ለሰማነው ነገር አብልጠን ልንጠነቀቅ ይገባናል። 2ምክንያቱም በመላእክት በኩል የተነገረው ቃል ጽኑ ከሆነና ማንኛውም መተላለፍና አለመታዘዝ ተገቢውን ቅጣት ከተቀበለ፣ 3እኛስ እንዲህ ያለውን ታላቅ ድነት ቸል ብንል እንዴት ልናመልጥ እንችላለን? ይህ ድነት በመጀመሪያ በጌታ ተነገረ፤ ከእርሱ የሰሙትም ለእኛ አረጋገጡልን። 4እግዚአብሔርም በምልክት፣ በድንቅና በልዩ ልዩ ታምራት እንዲሁም እንደ ፈቃዱ በታደሉት የመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎች ስለ ዚሁ ነገር መስክሮአል።

ኢየሱስ ወንድሞቹን መሰለ

5ይህን የምንናገርለትን መጪውን ዓለም ለመላእክት አላስገዛም፤ 6ነገር ግን አንዱ በሌላ ስፍራ እንዲህ ብሎ መስክሮአል፤

“ታስታውሰው ዘንድ ሰው ምንድን ነው?

ታስብለትስ ዘንድ የሰው ልጅ ምንድን ነው”

7ከመላእክት ጥቂት2፥7 ወይም ለጥቂት ጊዜ አሳነስኸው፤

የክብርና የምስጋና ዘውድ ጫንህለት፤

8ሁሉንም ከእግሮቹ በታች አስገዛህለት።

እግዚአብሔር ሁሉን ከበታቹ ሲያስገዛለት፣ ያላ ስገዛለት ምንም ነገር የለም፤ ይሁን እንጂ በአሁኑ ጊዜ ሁሉም ነገር ተገዝቶለት አናይም። 9ነገር ግን በእግዚአብሔር ጸጋ ስለ ሰው ሁሉ ሞትን ይቀምስ ዘንድ ከመላእክት ጥቂት እንዲያንስ ተደርጎ የነበረው ኢየሱስ፣ የሞትን መከራ በመቀበሉ አሁን የክብርና የምስጋና ዘውድ ተጭኖለት እናየዋለን።

10ሁሉ ነገር ለእርሱና በእርሱ የሚኖር እግዚአብሔር፣ ብዙ ልጆችን ወደ ክብር ለማምጣት፣ የድነታቸውን መሥራች በመከራ ፍጹም ሊያደርገው የተገባ ነበር። 11ሰዎችን የሚቀድሰውና የሚቀደሱት ሰዎች ከአንድ ቤተ ሰብ ናቸው፤ ስለዚህ ኢየሱስ ወንድሞች ብሎ ሊጠራቸው ዐያፍርም፤ 12እንዲህም ይላል፤

“ስምህን ለወንድሞቼ እነግራቸዋለሁ፤

በጒባኤም መካከል ምስጋናህን እዘምራለሁ።”

13እንዲሁም፣

“እኔ በእርሱ እታመናለሁ።”

ደግሞም እንዲህ ይላል፤

“እነሆ፤ እኔና እግዚአብሔር የሰጠኝ ልጆች።”

14ልጆቹ በሥጋና በደም እንደሚካፈሉ እርሱ ራሱ ደግሞ ያንኑ ተካፈለ፤ ይኸውም በሞት ላይ ኀይል ያለውን ዲያቢሎስን በሞቱ ኀይል እንዲደመስስ ነው፤ 15እንዲሁም በሕይወት ዘመናቸው ሁሉ በሞት ፍርሀት ባርነት የታሰሩትን ነጻ እንዲያወጣ ነው። 16እርሱ የመጣው መላእክትን ለመርዳት ሳይሆን፣ የአብርሃምን ዘር ለመርዳት እንደሆነ ግልጽ ነው። 17ስለዚህ በሁሉም ነገር ወንድሞቹን መምሰል ተገባው፤ ይህንም ያደረገው መሓሪና ታማኝ ሊቀ ካህናት ሆኖ እግዚአብሔርን ለማገልገልና ለሕዝቡ የኀጢአትን ስርየት2፥17 ወይም ቍጣ ለመመለስ ለማስገኘት ነው። 18እርሱ ራሱ በተፈተነ ጊዜ መከራን ስለ ተቀበለ፣ የሚፈተኑትን ሊረዳቸው ይችላልና።

Chinese Contemporary Bible (Simplified)

希伯来书 2:1-18

持守真道

1因此,我们必须更加重视所听的道,以免随流漂去。 2既然借天使传下来的话正确无误,凡干犯、违背的人都受到了应有的报应, 3我们若忽略了这么大的救恩,怎能逃避惩罚呢?这救恩首先由主亲口宣讲出来,后来由听见的人向我们证实了。 4同时,上帝按自己的旨意,用神迹、奇事、各样的异能、圣灵的恩赐和他们一同做见证。

救恩的元帅

5上帝并没有把我们所谈论的未来世界交给天使掌管。 6相反,有人在圣经中做见证说:

“人算什么,你竟顾念他?

世人算什么,你竟眷顾他?

7你使他暂时比天使低微一点,

赐他荣耀和尊贵作冠冕,

派他管理你所造的一切,

8使万物降服在他脚下。”

既说叫万物都降服在人的管理之下,就没有一样例外。不过,我们到现在还没有看到万物都降服在人的管理之下, 9只看见耶稣暂时比天使低微一点,好靠着上帝的恩典为全人类亲尝死亡的滋味。祂因为经历死亡的痛苦而得到了尊贵和荣耀作冠冕。

10作为万物的归宿和根源的上帝,叫救恩的元帅耶稣经历苦难而得以纯全,以便带领许多的儿女进入荣耀,这样的安排是恰当的。 11因为使人圣洁的耶稣和那些得以圣洁的人都出自同一位父亲,所以耶稣不以称呼他们弟兄姊妹为耻。 12祂说:

“我要向众弟兄传扬你的名,

在会众中歌颂你。”

13又说:

“我要倚靠祂。”

还说:

“看啊,我和上帝赐给我的儿女都在这里。”

14因为众儿女都是血肉之躯,所以祂也同样取了血肉之躯,为要亲身经历死亡,借此摧毁掌握死亡权势的魔鬼, 15释放那些因怕死而一生做奴隶的人。 16很明显,祂要救助的不是天使,而是亚伯拉罕的后裔。 17所以祂必须在每一方面都与祂的弟兄姊妹相同,以便在事奉上帝的事上成为一位仁慈忠信的大祭司,替众人献上赎罪祭。 18祂经历过受试炼的痛苦,所以能帮助受试炼的人。