New Amharic Standard Version

ዕብራውያን 11:1-40

የእምነት ቋሚ ምስክሮች

1እምነት ተስፋ ያደረግነው ነገር እንደሚፈጸም ርግጠኛ የምንሆንበት፣ የማናየውም ነገር እውን መሆኑን የምንረዳበት ነው። 2አባቶችም የተመሰከረላቸው በዚሁ ነው።

3ዓለማት በእግዚአብሔር ቃል እንደ ተፈጠሩ በእምነት እንረዳለን፤ ስለዚህ የሚታየው ነገር የተፈጠረው ከሚታየው እንዳልሆነ እንገነዘባለን።

4አቤል ከቃየል ይልቅ የበለጠ መሥዋዕት ለእግዚአብሔር በእምነት አቀረበ። እግዚአብሔር ስለ ስጦታው በተናገረለት ጊዜ፣ እርሱ በእምነት ጻድቅ እንደሆነ ተመሰከረለት፤ ቢሞትም እንኳ እስከ አሁን በእምነቱ ይናገራል።

5ሄኖክ ሞትን እንዳያይ ከዚህ ዓለም በእምነት ተወሰደ፤ እግዚአብሔርም ስለ ወሰደው አልተገኘም፤ ከመወሰዱም በፊት እግዚአብሔርን ደስ እንዳሰኘ ተመስክሮለታልና። 6ደግሞም ያለ እምነት እግዚአብሔርን ደስ ማሰኘት አይቻልም፤ ምክንያቱም ወደ እግዚአብሔር የሚቀርብ ሁሉ እግዚአብሔር መኖሩንና ከልብ ለሚሹትም ዋጋ እንደሚሰጥ ማመን አለበት።

7ኖኅ ገና ስለማይታየው ነገር እግዚአብሔር ባስጠነቀቀው ጊዜ፣ እግዚአብሔርን ፈርቶ ቤተ ሰዎቹን ለማዳን መርከብን በእምነት ሠራ፤ በእምነቱ ዓለምን ኰነነ፤ በእምነትም የሚገኘውን ጽድቅ ወራሽ ሆነ።

8አብርሃም ርስት አድርጎ ወደሚቀበለው ስፍራ እንዲሄድ በተጠራ ጊዜ በእምነት ታዘዘ፤ ወዴት እንደሚሄድ ባያውቅም፣ እሺ ብሎ ሄደ። 9በባዕድ አገር እንዳለ መጻተኛ በተስፋዪቱ ምድር በእምነት ተቀመጠ፤ የተስፋውን ቃል አብረውት እንደሚወርሱት እንደ ይስሐቅና እንደ ያዕቆብ በድንኳን ኖረ፤ 10ምክንያቱም መሠረት ያላትን፣ እግዚአብሔር የሠራትንና የፈጠራትን ከተማ ይጠባበቅ ነበር።

11አብርሃም11፥11 ወይም ሣራ … አብርሃምም … ስለቈጠረች ሦስት ወር ሸሸጉት፤ የንጉሡንም ዐዋጅ አልፈሩም። ምንም እንኳ ዕድሜው ቢገፋም፣ ሣራምወይም ሣራ … አብርሃምም … ስለቈጠረች ሦስት ወር ሸሸጉት፤ የንጉሡንም ዐዋጅ አልፈሩም። ራሷ መካን ብትሆንም፣ ተስፋን የሰጠውን ታማኝ አድርጎ ስለ ቈጠረወይም ሣራ … አብርሃምም … ስለቈጠረች ሦስት ወር ሸሸጉት፤ የንጉሡንም ዐዋጅ አልፈሩም። በእምነት የልጅ አባት ለመሆን በቃ። 12ስለዚህ እንደ ሞተ ሰው ከሚቈጠር ከዚህ ከአንድ ሰው፣ እንደ ሰማይ ከዋክብት የበዛና እንደ ባሕር ዳር አሸዋ ተቈጥሮ የማያልቅ ዘር ተገኘ።

13እነዚህ ሁሉ የተሰጣቸውን የተስፋ ቃል ሳያገኙ እምነታቸውን እንደ ጠበቁ ሞቱ፤ ሆኖም ከሩቅ አይተው ሰላም አሉት፤ በዚህ ምድር ሲኖሩ መጻተኞችና እንግዶች መሆናቸውን ተገንዝበው ነበርና። 14እንደዚህ የሚሉት ሰዎች የራሳቸው የሆነውን አገር እንደሚጠባበቁ ያሳያሉ። 15ትተውት የወጡትን አገር ቢያስቡ ኖሮ፣ ወደዚያ የመመለስ ዕድል ነበራቸው። 16አሁን ግን ከዚህ የሚበልጠውን ሰማያዊ አገር ይናፍቃሉ፤ ስለዚህ እግዚአብሔር አምላካቸው ተብሎ ሊጠራ አላፈረም፤ ከተማን አዘጋጅቶላቸዋልና።

17አብርሃም እግዚአብሔር በፈተነው ጊዜ፣ ይስሐቅን መሥዋዕት አድርጎ በእምነት አቀረበ፤ የተስፋን ቃል የተቀበለው እርሱ፣ አንድ ልጁን ሊሠዋ ዝግጁ ነበር፤ 18ይህም እግዚአብሔር፣ “ዘርህ በይስሐቅ ይጠራል” ያለለት ነበር። 19አብርሃም እግዚአብሔር ሙታንን ሊያስነሣ እንደሚችል ተገንዝቦ ነበር፤ ይስሐቅንም ከሞት የመነሣት አምሳያ ሆኖ አገኘው።

20ይስሐቅ ወደ ፊት የሚሆነውን ዐስቦ ያዕቆብንና ዔሳውን በእምነት ባረካቸው።

21ያዕቆብ በሚሞትበት ጊዜ እያንዳንዳቸውን የዮሴፍን ልጆች በእምነት ባረካቸው፤ በበትሩም ጫፍ ዘንበል ብሎ ሰገደ።

22ዮሴፍ ሊሞት በተቃረበ ጊዜ፣ ስለ እስራኤል ሕዝብ ከግብፅ መውጣት በእምነት ተናገረ፤ ስለ ዐጽሙም ትእዛዝ ሰጠ።

23ሙሴ ከተወለደ በኋላ፣ ወላጆቹ መልከ መልካም ሕፃን መሆኑን ስላዩ በእምነት ሦስት ወር ሸሸጉት፤ የንጉሡንም ዐዋጅ አልፈሩም።

24ሙሴ ካደገ በኋላ፣ የፈርዖን የልጅ ልጅ መባልን በእምነት እምቢ አለ። 25ለጥቂት ጊዜ በኀጢአት ከሚገኝ ደስታ ይልቅ፣ ከእግዚአብሔር ሕዝብ ጋር መከራን መቀበል መረጠ። 26ከግብፅ ሀብት ይልቅ ስለ ክርስቶስ መከራን መቀበል እጅግ የሚበልጥ ሀብት መሆኑን ተገነዘበ፤ ወደ ፊት የሚቀበለውን ብድራት ከሩቅ ተመልክቶአልና። 27የንጉሡን ቊጣ ሳይፈራ ግብፅን ለቆ በእምነት ወጣ፤ የማይታየውንም እንዳየው አድርጎ በመቍጠር በሐሳቡ ጸና። 28በኵሮች የሆኑትን የሚገድለው ቀሣፊ የእስራኤልን በኵር ልጆች እንዳይ ገድል ፋሲካን በእምነት አደረገ፤ ደምንም ረጨ።

29ሕዝቡ በደረቅ መሬት እንደሚኬድ ቀይ ባሕርን በእምነት ተሻገሩ፤ ግብፃውያን ግን እንደዚሁ ለማድረግ ሲሞክሩ ሰጠሙ።

30ሕዝቡ የኢያሪኮን ግንብ ሰባት ቀን ከዞሩት በኋላ፣ በእምነት ወደቀ።

31ዝሙት አዳሪዋ ረዓብ፣ ሰላዮቹን በሰላም ስለ ተቀበለቻቸው ከማይታዘዙት11፥31 ወይም ከማያመኑት ጋር ያልጠፋችው በእምነት ነው።

32እንግዲህ ከዚህ በላይ ምን ልበል? ስለ ጌዴዎን፣ ስለ ባርቅ፣ ስለ ሳምሶን፣ ስለ ዮፍታሔ፣ ስለ ዳዊት፣ ስለ ሳሙኤል፣ እንዲሁም ስለ ነቢያት እንዳልተርክ ጊዜ የለም። 33እነዚህ በእምነት መንግሥታትን ድል ነሡ፤ በቅን ፈረዱ፤ የተሰጠውን የተስፋ ቃል ተቀበሉ፤ የአንበሶችን አፍ ዘጉ፤ 34የእሳትን ኀይል አጠፉ፤ ከሰይፍ ስለት አመለጡ፤ ከድካማቸው በረቱ፤ በጦርነት ኀያል ሆኑ፤ ባዕዳን ወታደሮችን አባረሩ። 35ሴቶች ሙታናቸው ተነሡላቸው። ሌሎቹ ደግሞ የተሻለውን ትንሣኤ ለማግኘት ሲሉ፣ መትረፍን ንቀው ለሞት ለሚዳርግ ሥቃይ ራሳቸውን ሰጡ፤ ከዚህም ነጻ ለመውጣት አልፈለጉም። 36አንዳንዶቹ መዘባበቻ ሆኑ፤ ተገረፉ። ሌሎቹ ደግሞ ታስረው ወደ ወህኒ ተጣሉ፤ 37በድንጋይ ተወገሩ፤ በመጋዝ ለሁለት ተሰነጠቁ፤11፥37 አንዳንድ የጥንት ቅጆች በድንጋይ ተወገሩ፤ ለፈተና አልፈው ተሰጡ፤ በሰይፍ ተወግተው ሞቱ፤ እየተጐሳቈሉ፣ እየተሰደዱና እየተንገላቱ የበግና የፍየል ቈዳ ለብሰው ዞሩ፤ 38ዓለም ለእነርሱ አልተገባቻቸውምና። በየበረሓውና በየተራራው፣ በየዋሻውና በየጒድጓዱ ተንከራተቱ።

39እነዚህ ሁሉ ስለ እምነታቸው የተመሰከረላቸው ቢሆኑም ከእነርሱ ማንም የተስፋውን ቃል የተቀበለ የለም። 40እግዚአብሔር ለእኛ የሚበልጥ ነገር ስላዘጋጀ፣ ያለ እኛ ፍጹማን ሊሆኑ አልቻሉም።

Chinese Contemporary Bible (Simplified)

希伯来书 11:1-40

论信心

1信心是对盼望的事有把握,对还没看见的事很确定。 2古人因有这样的信心而得到了赞许。 3我们凭信心知道宇宙是借着上帝的话造成的,所以看得见的是从看不见的造出来的。

4亚伯凭信心向上帝献祭,比该隐所献的更美,蒙了上帝的悦纳,被称为义人。他虽然死了,却仍然借着信心说话。

5以诺因为信而被接到天上,没有经历死亡。世人找不到他,因为上帝已经把他接走了。其实他在被接之前,已经得到了肯定,是一个蒙上帝喜悦的人。 6没有信心的人不能得到上帝的喜悦,因为来到上帝面前的人必须相信上帝存在,并相信祂会赏赐一切寻求祂的人。

7挪亚因为有信心,在上帝指示他未来要发生的事之后,就怀着敬畏的心建造方舟,来救全家的人。他借着信心定了那个世代的罪,并承受了因信而来的义。

8亚伯拉罕因为有信心,听到上帝的呼召后,就遵命前往他将要承受为产业的地方,但他出发的时候还不知道自己要去哪里。 9他凭信心像异乡人一样寄居在上帝应许给他的地方。他住在帐篷里,与同受一个应许的以撒雅各一样。 10因为他盼望的是一座有根基的城,是由上帝设计、建造的。

11撒拉过了生育年龄后凭信心仍然得到了孕育后代的能力,因为她认定赐她应许的上帝言出必行。 12所以,从一个垂暮之年的人生出许多子孙,好像天上的星、海边的沙那么多。

13这些人到死都满怀信心。他们虽然没有得到上帝所应许的,却从远处望见了,就欢喜快乐,承认自己在世上不过是寄居的异乡人。 14他们抱这样的态度,表明他们正在寻找一个家乡。 15如果他们想念的是自己离开的家乡,就找机会回去了。 16然而,他们渴慕的是天上更美的家乡。所以,上帝不以被他们称为上帝为耻,因为祂已经为他们预备了一座城。

17亚伯拉罕被试验时凭信心把以撒献为祭物,承受应许的亚伯拉罕当时献上了自己的独生子。 18论到这儿子,上帝曾说:“以撒生的才可算为你的后裔。” 19他认定上帝能使死人复活,从象征意义上说,他也确实从死亡中得回了以撒

20以撒凭信心指着将来的事为雅各以扫祝福。

21雅各凭信心在临终之时分别为约瑟的两个儿子祝福,并拄着拐杖敬拜上帝。

22约瑟临终之时凭信心提到以色列人将来要离开埃及,并交代要如何处理自己的骸骨。

23摩西生下来时,他父母见他长得俊美,就凭信心把他藏了三个月,不怕违抗王的命令。

24摩西长大成人后,凭信心拒绝做法老之女的儿子, 25宁愿与上帝的子民一同受苦,也不肯享受一时的罪中之乐。 26在他眼中,为基督所受的凌辱远比埃及的财富更有价值,因为他盼望的是将来的赏赐。 27他凭信心离开埃及,不怕王的愤怒。他坚忍不拔,好像看见了肉眼不能看见的主。 28他凭信心守逾越节,行洒血的礼,免得那位杀长子的伤害以色列人。

29以色列人凭信心渡过红海,如履干地,埃及人试图过去,却被海水淹没。 30以色列人凭信心绕着耶利哥城走了七天,城墙就倒塌了。

31妓女喇合凭信心善待以色列的探子,没有与那些不顺服的人一同灭亡。

32我还要再说下去吗?我没有时间一一细说基甸巴拉参孙耶弗他大卫撒母耳和众先知的事了。 33他们凭信心战胜了敌国,行了公义,得到了应许,堵住了狮子的口, 34熄灭了猛烈的火焰,刀下逃生,由软弱变为刚强,作战勇猛,击退外敌。

35有些妇女得回了从死里复活的亲人;有些人受尽严刑拷打,仍不肯苟且偷生,为要得到一个复活后更美好的生命。 36有些人遭受戏弄和鞭打,还有些人遭受捆锁和囚禁。 37他们被人用石头打死,受威逼利诱11:37 有圣经抄本在此处无“受威逼利诱”。,被锯成两截,丧生刀剑之下,披着绵羊和山羊的皮四处奔跑,受尽贫乏、迫害和虐待, 38在旷野、群山、山洞和地穴中漂流不定。他们是世界不配有的!

39这些人都因信心而获得赞许,但他们并未得到上帝的应许, 40因为上帝为我们预备了更美的,要叫他们与我们一同得到才算完美。