New Amharic Standard Version

ኤርምያስ 52:1-34

የኤርምያስ ቃል እዚህ ላይ ይፈጸማል።

የኢየሩሳሌም መውደቅ

52፥1-3 ተጓ ምብ – 2ነገ 24፥18-20፤ 2ዜና 36፥11-16

52፥4-16 ተጓ ምብ – ኤር 39፥1-10

52፥4-21 ተጓ ምብ – 2ነገ 25፥1-21፤ 2ዜና 36፥17-20

1ሴዴቅያስ ሲነግሥ ዕድሜው ሃያ አንድ ዓመት ነበረ፤ በኢየሩሳሌም ዐሥራ አንድ ዓመት ነገሠ፤ የእናቱም ስም አሚጣል ሲሆን፣ እርሷም የሊብና ሰው የኤርምያስ ልጅ ነበረች። 2ሴዴቅያስም ኢዮአቄም እንዳደረገው ሁሉ፣ በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ነገር አደረገ። 3እግዚአብሔር በኢየሩሳሌምና በይሁዳ ላይ ይህን ሁሉ ያደረሰውንና በመጨረሻም ከፊቱ ያስወገዳቸው ከቍጣው የተነሣ ነበር።

ሴዴቅያስም በባቢሎን ንጉሥ ላይ ዐመፀ። 4ስለዚህ ሴዴቅያስ በነገሠ በዘጠነኛው ዓመት በዐሥረኛው ወር፣ ከወሩም በዐሥረኛው ቀን፣ የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ሰራዊቱን ሁሉ አስከትቶ በኢየሩሳሌም ላይ ዘመተ፤ ከተማዪቱንም ከበቧት፤ በዙሪያውም የዐፈር ድልድል ሠሩ። 5ከተማዪቱም እስከ ንጉሡ እስከ ሴዴቅያስ ዐሥራ አንደኛ ዘመነ መንግሥት ተከባ ነበር።

6በአራተኛው ወር በዘጠነኛው ቀን በከተማዪቱ ራብ ጸንቶ ስለ ነበር ሕዝቡ የሚበላውን አጣ፤ 7የከተማዪቱም ቅጥር ተነደለ፤ ሰራዊቱም ሁሉ ኰብልሎ ሄደ። ባቢሎናውያን52፥7 ወይም ከለዳውያን፤ ቍ 17 ይመ። በከተማዪቱ ዙሪያ ቢኖሩም፣ በንጉሡ የአትክልት ስፍራ አጠገብ በሁለት ቅጥሮች መካከል ባለው በር በሌሊት ከተማዪቱን ጥለው ሸሹ፤ ወደ ዓረባም52፥7 ወይም ዮርዳኖስ ሸለቆ አመሩ። 8የባቢሎናውያንም52፥8 ወይም ከለዳውያን፤ ቍ 14 ይመ። ሰራዊት ንጉሥ ሴዴቅያስን ተከታትሎ በማሳደድ በኢያሪኮ ሜዳ ደረሱበት፤ ወታደሮቹም ሁሉ ከእርሱ ተለይተው ተበታትነው ሳለ፣ ንጉሡን ያዙት።

9እርሱም በሐማት ምድር በሪብላ ወደ ነበረው ወደ ባቢሎንም ንጉሥ ተወሰደ፤ የባቢሎን ንጉሥ በዚያ ፈረደበት። 10በሪብላም የባቢሎን ንጉሥ፣ የሴዴቅያስን ወንዶች ልጆች በአባታቸው ፊት ዐረዳቸው፤ የይሁዳንም ባለ ሥልጣኖች ሁሉ ገደላቸው፤ 11የሴዴቅያስንም ዐይኖች አወጣ፤ በናስ ሰንሰለትም አስሮ ወደ ባቢሎን ወሰደው፤ በዚያም እስከ ዕለተ ሞቱ በእስር ቤት አቈየው።

12የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር በነገሠ በዐሥራ ዘጠነኛው ዓመት በአምስተኛው ወር፤ ከወሩም በዐሥረኛው ቀን፣ የባቢሎን ንጉሥ ባለሟል የክብር ዘበኞች አዛዥ የነበረው ናቡዘረዳን ወደ ኢየሩሳሌም መጣ። 13የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስና የንጉሡን ቤተ መንግሥት እንዲሁም በኢየሩሳሌም የነበሩትን ቤቶች ሁሉ በእሳት አቃጠለ፤ ሌሎች ትልልቅ ሕንጻዎችንም በእሳት አወደመ። 14በክብር ዘበኞቹ አዛዥ ሥር የነበሩት የባቢሎናውያን ሰራዊት ሁሉ በኢየሩሳሌም ዙሪያ ያለውን ቅጥር በሙሉ አፈረሱ። 15የዘቦቹ አዛዥ ናቡዘረዳን አንዳንድ ድኾችንና በከተማዪቱ የቀረውን ሕዝብ፣ የእጅ ጥበብ ያላቸውንና52፥15 ወይም ተራው ሕዝብ ሸሽተው ወደ ባቢሎን ንጉሥ የተጠጉትን አፈለሳቸው። 16ነገር ግን የክብር ዘበኞቹ አዛዥ ናቡዘረዳን ሌሎች የምድሪቱን ድኾች ወይን ተካዮችና ዐራሾች እንዲሆኑ አስቀራቸው።

17ባቢሎናውያን በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ የነበሩትን የናስ ዐምዶች፣ ተንቀሳቃሽ ማስቀመጫዎችንና ከናስ የተሠራውን የውሃ ገንዳ ሰባበሩ፤ ናሱንም ሁሉ ወደ ባቢሎን ይዘው ሄዱ። 18ከእነዚህም ሌላ ምንቸቶቹን፣ መጫሪያዎቹን፣ መኰስተሪያዎቹን፣ ወጭቶችን፣ ጭልፋዎቹንና ለቤተ መቅደስ አገልግሎት የሚውሉትን የናስ ዕቃዎች በሙሉ ወሰዱ። 19የክብር ዘበኞቹ አዛዥ ከንጹሕ ወርቅና ከንጹሕ ብር የተሠሩትን ዕቃዎች ሁሉ ጐድጓዳ ሳሕኖችን ጥናዎችን፣ ወጭቶችን፣ ምንቸቶችን፣ መቅረዞችን፣ ጭልፋዎችንና ለመጠጥ ቍርባን ማቅረቢያ የሚሆኑ ወጭቶችን ይዞ ሄደ።

20ንጉሥ ሰሎሞን ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ከናስ ያሠራቸው፦ ሁለቱ ዐምዶች፣ ትልቁ የውሃ ገንዳ፣ ከሥሩ ያሉት ዐሥራ ሁለት ወይፈኖችና ተንቀሳቃሽ ማስቀመጫዎች ክብደታቸው ሚዛን ከሚችለው በላይ ነበር። 21እያንዳንዱም ዐምድ ከፍ ታውዐሥራ ስምንት ክንድ ዙሪያ ክቡም52፥21 ከፍታው 27 ጫማ (8.1 ሜትር) እና ዙሪያ ክቡ 18 ጫማ (5.4 ሜትር) ገደማ ነው። ዐሥራ ሁለት ክንድ ነበረ፤ ውስጡ ክፍት ስለ ሆነ የእያንዳንዱ ከንፈር ውፍረት አራት ጣት ነበረ። 22በአንዱ ዐምድ ዐናት ላይ ያለው የናስ ጒልላት ቁመት አምስት ክንድ52፥22 7½ ጫማ (2.3 ሜትር) ገደማ ነው። ሲሆን፣ ዙሪያውንም ሁሉ የሮማን ቅርጽ ባላቸው የናስ ጌጣጌጦች የተዋበ ነበር፤ ሌላውም ዐምድ የሮማኑን ጌጣጌጥ ጨምሮ ከዚሁ ጋር አንድ ዐይነት ነበር። 23ዘጠና ስድስቱ ሮማኖች ከጐን በቀላሉ የሚታዩ ሲሆኑ፣ በአጠቃላይ በዙሪያው ካለው ጌጥ በላይ ያለው የሮማኖች ቍጥር አንድ መቶ ነበር።

24የክብር ዘበኞቹ አዛዥ የካህናት አለቃ የነበረውን ሠራያን፣ ምክትሉንም ካህን ሶፎንያስንና ሦስቱን በር ጠባቂዎች አስሮ ወሰዳቸው፤ 25በከተማው ውስጥ ከቀሩትም ሕዝብ፣ የተዋጊዎቹ ኀላፊ የነበረውን መኰንን፣ ሰባቱን የንጉሡን አማካሪዎች ከአገሬው ሕዝብ ወታደር የሚመለምለውን መኰንን ጸሓፊና በከተማው ውስጥ የተገኙትን ሌሎች ስድሳ ሰዎች ወሰደ። 26የክብር ዘበኞቹ አዛዥ ናቡዘረዳን እነዚህን ሁሉ ይዞ የባቢሎን ንጉሥ ወደነበረበት ወደ ሪብላ አመጣቸው። 27ንጉሡም በሐማት ምድር በነበረችው በሪብላ ፈጃቸው።

ይሁዳም በዚህ ሁኔታ ከምድሯ በምርኮ ተወሰደች። 28ናቡከደነፆር ማርኮ የወሰደው ሕዝብ ቍጥር እንደሚከተለው ነው፦

በነገሠ በሰባተኛው ዓመት፣

ሦስት ሺህ ሃያ ሦስት አይሁድ፤

29ናቡከደነፆር በነገሠ በዐሥራ

ስምንተኛው ዓመት፣ ስምንት መቶ ሠላሳ ሁለት ሰዎች ከኢየሩሳሌም፤

30ናቡከደነፆር በነገሠ በሃያ ሦስተኛው ዓመት፣ የክብር ዘበኞች አዛዥ ናቡዘረዳን

ሰባት መቶ አርባ አምስት አይሁድ ማርኮ ወስዶአል፤

በአጠቃላይ አራት ሺህ ስድስት መቶ ሰዎች ነበሩ።

የዮአኪን መፈታት

31የይሁዳ ንጉሥ ዮአኪን በተማረከ በሠላሳ ሰባተኛው ዓመት፣ ዮርማሮዴክ52፥31 እንዲሁም አሜልማርዱክ ተብሎ ይጠራል። በባቢሎን ነገሠ፤ በዚሁ ዓመት፣ በዐሥራ ሁለተኛው ወር ከወሩም በሃያ አምስተኛው ቀን የይሁዳን ንጉሥ ዮአኪንን አሰበው፤ ከእስር ቤትም አወጣው፤ 32በመልካምም ቃል አናገረው፤ ከእርሱም ጋር በባቢሎን በምርኮ ከነበሩት ነገሥታት ይልቅ ከፍ ባለ የክብር ቦታ አስቀመጠው። 33ዮአኪንም እስር ቤት ለብሶት የነበረውን ልብሱን አውልቆ ጣለ፤ በቀረውም የሕይወቱ ዘመን ሁሉ ከንጉሡ ማእድ ይበላ ነበር። 34የባቢሎንም ንጉሥ፣ ዮአኪን እስኪሞት ድረስ፣ በሕይወት ዘመኑ ሁሉ ሳያቋርጥ በየዕለቱ ቀለቡን ይሰጠው ነበር።

Bibelen på hverdagsdansk

Jeremiasʼ Bog 52:1-34

Historisk oversigt over Jerusalems fald

1Zidkija var 21 år gammel, da han blev konge, og han regerede i Jerusalem i 11 år. Hans mor hed Hamutal og var datter af Jirmeja fra byen Libna. 2Han gjorde, hvad der var ondt i Herrens øjne, ligesom Jojakim havde gjort. 3Til sidst var Jerusalems og Judas oprør og ugudelighed blevet så voldsom, at Herren var nødt til at straffe dem og sende dem i eksil. Det varede ikke længe, før Zidkija gjorde oprør imod den babyloniske konge.

4Derfor mobiliserede kong Nebukadnezar igen sin hær og drog mod Jerusalem. I kong Zidkijas niende regeringsår, på den tiende dag i den tiende måned, begyndte den babyloniske hær en svær belejring af byen. De byggede angrebsramper op imod bymuren. 5Belejringen varede til kong Zidkijas 11. regeringsår. 6På den niende dag i den fjerde måned af det år var alt spiseligt sluppet op og befolkningen totalt udsultet. 7På det tidspunkt brød fjenden hul gennem bymuren og den judæiske hær prøvede at flygte. Nogle forlod byen om natten gennem paladsets have, igennem en korridor mellem to mure, ud af en port i bymuren og videre i retning af Jordandalen. Men de babyloniske tropper holdt vagt rundt omkring byen, 8og de satte efter kong Zidkija og indhentede ham på sletten ved Jeriko. Hans soldater flygtede i alle retninger, 9men han selv blev fanget og ført til den babyloniske konge i byen Ribla i Hamat-området, hvor han blev anklaget og dømt. 10Han blev tvunget til at overvære sine sønners og nærmeste embedsmænds henrettelse, 11hvorefter hans øjne blev stukket ud. Så blev han lagt i lænker og ført til Babylon, hvor han blev holdt fængslet til sin død.

12På den tiende dag i den femte måned i kong Nebukadnezars 19. regeringsår kom Nebuzaradan til Jerusalem fra Babylon. Nebuzaradan var chef for den babyloniske konges livvagt. 13Han nedbrændte Herrens tempel, kongens palads og alle byens mest betydningsfulde bygninger, 14hvorefter han beordrede sine tropper til at rive Jerusalems bymur ned. 15Så samlede han resten af byens indbyggere, håndværkerne og de, der havde overgivet sig, for at føre dem til Babylon i eksil. 16Kun de fattigste lod Nebuzaradan blive tilbage, så der var nogen til at dyrke jorden og passe vingårdene.

17Babylonierne slog templets bronzesøjler, bronzehavet og alle rullebordene i stykker og tog alt metallet med sig hjem til Babylon. 18De tog alt, hvad der var lavet af bronze: askebakkerne, skovlene, vægesaksene, fadene, skålene og de bronzeredskaber der blev brugt ved ofringerne i templet. 19Nebuzaradan tog selv, hvad der var af guld og sølvting: skålene, bakkerne til gløder, stænkeskålene, fadene, lysestagerne og de forskellige drikofferskåle. 20Det hele blev vejet, undtagen de to søjler, bronzehavet, de 12 bronzetyre og rullebordene, som kong Salomon i sin tid havde ladet fremstille til Herrens tempel. De var for store til at blive vejet. 21Søjlerne var 8,1 m høje og 5,4 m i omkreds. De var hule med en tykkelse på fire fingre. 22Foroven havde de et søjlehoved på 2,25 m med en dekoration af fletværk og granatæbler i bronze. 23På siderne var der 96 granatæbler og øverst på søjlehovedet yderligere 100 granatæbler hele vejen rundt.

24Af tempelpersonalet tog Nebuzaradan følgende krigsfanger: Ypperstepræsten Seraja, andenpræsten Zefanja og de tre dørvogtere. 25Fra byen tog han den øverstkommanderende officer, en rekrutteringsofficer, syv af kongens tidligere rådgivere og 60 andre betydningsfulde mænd, som var gået under jorden. 26Han førte disse mænd til den babyloniske konge i Ribla i Hamat-området, 27hvor de alle blev henrettet. Judas folk var nu ført bort fra deres land og måtte leve i eksil.

28I Nebukadnezars syvende regeringsår blev i alt 3023 judæere ført i eksil, 29i hans 18. regeringsår yderligere 832 fanger fra Jerusalem, 30og i hans 23. regeringsår bortførte Nebuzaradan 745 fanger fra Juda, alt i alt 4600 fanger.

Jojakin får bedre forhold under sit fangenskab

31Mange år senere kom der en ny konge på tronen i Babylon, som hed Evil-Merodak. Han besluttede at benåde Jojakin og løslade ham fra fængslet. Det skete den 27. dag i den 12. måned i Jojakins 37. år i fangenskab. 32Den nye konge behandlede Jojakin venligt, bedre end de andre konger, som også var i fangenskab. 33Jojakin fik nyt tøj i stedet for fangedragten, og han spiste i kongens palads indtil sin dødsdag. 34Så længe han levede, gav kongen ham fra dag til dag, hvad han havde brug for.