New Amharic Standard Version

ኤርምያስ 1:1-19

1የኬልቅያስ ልጅ፣ ኤርምያስ የተናገረው ቃል ይህ ነው፤ አባቱ በብንያም አገር በዓናቶት ከሚገኙት ካህናት አንዱ ነበረ። 2የእግዚአብሔር ቃል የይሁዳ ንጉሥ፣ የአሞን ልጅ ኢዮስያስ በነገሠ በዐሥራ ሦስተኛው ዓመት ወደ ኤርምያስ መጣ፤ 3ደግሞም በይሁዳ ንጉሥ፣ በኢዮስያስ ልጅ በኢዮአቄም ንግሠ ዘመን፤ እንዲሁም በይሁዳ ንጉሥ፣ በኢዮስያስ ልጅ በሴዴቅያስ ንግሠ ዘመን፤ እስከ ዐሥራ አንደኛው ዓመት መጨረሻ ድረስ የኢየሩሳሌም ሕዝብ ተማርኮ እስከ ሄደበት እስከ አምስተኛው ወር ድረስ ወደ እርሱ ይመጣ ነበር።

የኤርምያስ መጠራት

4የእግዚአብሔር ቃል ወደ እኔ መጣ፤ እንዲህም አለኝ፤

5“በማሕፀን ሳልሠራህ ዐወቅሁህ፤

ከመወለድህ በፊት ለየሁህ፤1፥5 ወይም መረጥሁህ

ለሕዝቦችም ነቢይ እንድትሆን ሾምሁህ።”

6እኔም፣ “ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፤ እንዴት እንደምናገር አላውቅም፤ ገና ሕፃን ልጅ ነኝና” አልሁ።

7እግዚአብሔር ግን እንዲህ አለኝ፤ “ ‘ገና ሕፃን ልጅ ነኝ’ አትበል፤ ወደምልክህ ሁሉ ሄደህ፣ ያዘዝሁን ሁሉ ትናገራለህ፤ 8እኔ አድንህ ዘንድ ከአንተ ጋር ነኝና አትፍራቸው” ይላል እግዚአብሔር

9እግዚአብሔርም እጁን ዘርግቶ አፌን ዳሰሰና እንዲህ አለኝ፤ “እነሆ፤ ቃሌን በአፍህ አኑሬአለሁ፤ 10እንግዲህ፣ እንድትነቅልና እንድታፈርስ፣ እንድታጠፋና እንድትገለብጥ፣ እንድታንጽና እንድትተክል በአሕዛብና በመንግሥታት ላይ ዛሬ ሾምሁህ።”

11የእግዚአብሔር ቃል፣ “ኤርምያስ ሆይ፣ ምን ታያለህ?” ሲል ወደ እኔ መጣ።

እኔም፣ “የለውዝ በትር አያለሁ” አልሁ።

12እግዚአብሔርም፣ “ትክክል አይተሃል፤ ቃሌን እፈጽመው ዘንድ እተጋለሁና”1፥12 እተጋለሁ ለሚለው የዕብራይስጡ አነባብ የለውዝ በትር ከሚለው ጋር ይመሳሰላል። አለኝ።

13ዳግመኛም የእግዚአብሔር ቃል፣ “ምን ታያለህ?” ሲል ወደ እኔ መጣ።

እኔም፣ “አንድ የሚፈላ ማሰሮ አያለሁ፤ አፉም ከሰሜን ወደዚህ ያዘነበለ ነው” አልሁ።

14እግዚአብሔርም እንዲህ አለኝ፤ “ከሰሜን በምድሪቱ በሚኖሩ ሁሉ ላይ ድንገት መዓት ይወርድባቸዋል። 15እነሆ፤ የሰሜን መንግሥታትን ሕዝቦች ሁሉ እጠራለሁ” ይላል እግዚአብሔር

“ንጉሦቻቸው ይመጣሉ፤

ዙፋናቸውን በኢየሩሳሌም መግቢያ በሮች፣

በቅጥሮቿ ዙሪያ ሁሉ፣

በይሁዳም ከተሞች ሁሉ ይዘረጋሉ።

16እኔን በመተው ክፋት ስለ ሠሩ፣

ለሌሎች አማልክት ዕጣን ስላጠኑ፣

እጆቻቸው የሠሯቸውን ስላመለኩ፣

በሕዝቤ ላይ ፍርድን ዐውጄአለሁ።

17“አንተ ግን ወገብህን ታጠቅ፤ ተነሥተህም ያዘዝሁን ሁሉ ንገራቸው፤ አትፍራቸውም፤ አለዚያ በፊታቸው አስፈራሃለሁ። 18እነሆ፤ ዛሬ በመላዪቱ ምድር ላይ አስነሣሃለሁ ይኸውም የይሁዳን ነገሥታት፣ አለቆቿን፣ ካህናቷንና የምድሪቱን ሕዝብ ሁሉ መቋቋም እንድትችል የተመሸገ ከተማ፣ የብረት ምሰሶና የናስ ቅጥር አድርጌሃለሁ። 19ይዋጉሃል፤ ዳሩ ግን አድንህ ዘንድ እኔ ከአንተ ጋር ነኝና አያሸንፉህም” ይላል እግዚአብሔር

Korean Living Bible

예레미야 1:1-19

1이것은 베냐민 땅의 아나돗에 살던 제사장들 중 한 사람이었던 힐기야의 아들 예레미야의 말이다.

2아몬의 아들인 유다의 요시야왕 13년에 여호와께서 예레미야에게 말씀하시고

3요시야의 아들인 여호야김이 왕이 되었을 때 여호와께서는 다시 예레미야에게 말씀하셨다. 그 후에 요시야의 아들인 유다의 시드기야왕 11년까지 여호와께서 그에게 수차례에 걸쳐 말씀하셨는데 그 해 5월에 예루살렘 주민들이 포로로 잡혀갔다.

예레미야를 부르심

4여호와께서 나에게 이렇게 말씀하셨다.

5“내가 모태에서 네 형태를 만들기 전에 너를 알았고 네가 태어나기도 전에 너를 구별하여 온 세상의 예언자로 세웠다.”

6그때 나는 “여호와 하나님이시여, 나는 아직도 어려서 말할 줄도 모릅니다” 하고 대답하였다.

7그러나 여호와께서는 나에게 이렇게 말씀하셨다. “너는 어리다고 말하지 말고 내가 너를 누구에게 보내든지 너는 가서 내가 명령한 것을 다 말하라.

8너는 그들을 두려워하지 말아라. 내가 너와 함께하여 너를 1:8 또는 ‘구원하리라’보호하겠다. 이것은 나 여호와의 말이다.”

9그러고서 여호와께서는 손을 내밀어 내 입에 대시며 말씀하셨다. “보라, 나는 지금 네가 해야 할 말을 일러 주고 있다.

10내가 오늘 너에게 많은 민족과 나라를 다스리며 그들을 뽑고 파괴하고 파멸시키고 넘어뜨리고 건설하며 심는 권한을 주겠다.”

11또 여호와께서 나에게 “예레미야야, 네가 무엇을 보느냐?” 하고 물으셨다. 그때 나는 “살구나무 가지를 봅니다” 하고 대답하였다.

12그러자 여호와께서는 “잘 보았다. 이것은 내 말을 이루기 위한 것이다” 하고 말씀하셨다.

13여호와께서 다시 나에게 “네가 무엇을 보느냐?” 하고 물으셨다. 그래서 나는 “끓는 가마를 보고 있는데 1:13 원문에는 ‘북에서부터’북에서 남쪽으로 기울어졌습니다” 하고 대답하였다.

14그때 여호와께서 나에게 말씀하셨다. “재앙이 북쪽에서 일어나 이 땅의 모든 백성에게 미칠 것이다.

15내가 북쪽에 있는 모든 민족을 부를 것이니 그들의 왕들이 와서 예루살렘 성문 입구에 제각기 자리를 잡고 그 성과 유다의 모든 성들을 칠 것이다.

16내가 내 백성을 심판하여 벌하려고 하는 것은 그들이 나를 버리고 다른 신들에게 분향하며 자기들의 손으로 우상을 만들어 섬김으로 범죄하였기 때문이다.

17이제 너는 일어나 떠날 준비를 하고 가서 내가 너에게 명령한 모든 것을 그들에게 말하라. 너는 그들을 조금도 두려워하지 말아라. 그렇지 않으면 내가 너를 그들 앞에서 당황하게 하겠다.

18보라, 이 땅에 있는 모든 사람들, 곧 유다의 왕들과 지도자들과 제사장들과 모든 백성이 너를 대적할 것이다. 그러나 내가 너에게 그들과 맞서 싸울 힘을 주겠다. 너는 그들 앞에서 요새화된 성과 쇠기둥과 놋성벽과 같을 것이다.

19그들이 너를 대적하여도 이기지 못할 것이다. 이것은 내가 너와 함께하여 너를 구할 것이기 때문이다. 이것은 나 여호와의 말이다.”