በልዳዶስ
1ሹሐዊውም በልዳዶስ እንዲህ ሲል መለሰ፤
2“ገዥነትና ግርማ የእግዚአብሔር ናቸው፤
በሰማይም ከፍታ ሥርዐትን ያደርጋል።
3ሰራዊቱ ሊቈጠር ይችላልን?
ብርሃኑስ የማይወጣው በማን ላይ ነው?
4ሰው በእግዚአብሔር ፊት ጻድቅ ይሆን ዘንድ፣
ከሴትስ የተወለደ ንጹሕ ይሆን ዘንድ ይችላልን?
5በፊቱ ጨረቃ እንኳ ብሩህ ካልሆነች፣
ከዋክብትም ንጹሓን ካልሆኑ፣
6ይልቁን ከብል የሚቈጠር የሰው ልጅ፣
ትል የሆነውማ ሰው ምንኛ ያንስ!”
© 2011-2023 Biblica. All Rights Reserved Worldwide. 300 General Palmer Dr #4, Palmer Lake, CO 80133 • 719.488.9200
Terms of Use | Privacy Policy