New Amharic Standard Version

ኢዮብ 1:1-22

መግቢያ

1ዖፅ በሚባል አገር የሚኖር ኢዮብ የተባለ ሰው ነበረ፤ ይህ ሰው ነቀፋ የሌለበት፣ ቅን፣ እግዚአብሔርን የሚፈራና ከክፋት የራቀ ነበር። 2እርሱም ሰባት ወንዶችና ሦስት ሴቶች ልጆች ነበሩት። 3ሀብቱም ሰባት ሺህ በጎች፣ ሦስት ሺህ ግመሎች፣ አምስት መቶ ጥማድ በሬዎችና አምስት መቶ እንስት አህዮች ነበረ፤ እጅግ ብዙ ባሮችም ነበሩት፤ በምሥራቅ አገር ከሚኖሩትም ሰዎች ሁሉ ይልቅ እጅግ ታላቅ ሰው ነበረ።

4ወንዶች ልጆቹም ተራ በተራ በየቤታቸው ግብዣ ያደርጉ ነበር፤ ከእነርሱም ጋር እንዲበሉና እንዲጠጡ ሦስቱን እኅቶቻቸውን ይጋብዙ ነበር። 5የግብዣው ጊዜ ካለፈ በኋላ ኢዮብ ልኮ ያስመጣቸውና፣ “ምናልባት ልጆቼ ኀጢአት ሠርተው እግዚአብሔርንም በልባቸው ረግመው ይሆናል” በማለት ጠዋት በማለዳ ስለ እያንዳንዳቸው የሚቃጠል መሥዋዕት በማቅረብ ያነጻቸው ነበር፤ ኢዮብ ይህን ዘወትር ያደርግ ነበር።

የመጀመሪያው የኢዮብ ፈተና

6አንድ ቀን መላእክት1፥6 በዕብራይስጡ የእግዚአብሔር ልጆች ይላል በእግዚአብሔር ፊት ሊቆሙ በመጡ ጊዜ፣ ሰይጣንም1፥6 ሰይጣን ማለት ከሳሽ ማለት ነው መጥቶ በመካከላቸው ቆመ። 7እግዚአብሔርም ሰይጣንን፣ “ከወዴት መጣህ?” አለው።

ሰይጣንም፣ “በምድር ሁሉ ዞርሁ፤ ወዲያና ወዲህም ተመላለስሁባት” ብሎ ለእግዚአብሔር መለሰ።

8እግዚአብሔርም ሰይጣንን፣ “አገልጋዬን ኢዮብን ተመለከትኸውን? በምድር ላይ እንደ እርሱ ነቀፋ የሌለበት፣ ቅን፣ እግዚአብሔርን የሚፈራና ከክፋት የራቀ ሰው የለም” አለው።

9ሰይጣንም፣ ለእግዚአብሔር እንዲህ ሲል መለሰለት፣ “ኢዮብ እግዚአብሔርን የሚፈራው እንዲሁ ነውን? 10በእርሱና በቤተ ሰቦቹ፣ ባለው ንብረትስ ሁሉ ዙሪያ ዐጥር ሠርተህለት የለምን? የበጎቹና የላሞቹ መንጋ ምድርን ሁሉ እስኪሞሉ ድረስ የእጁን ሥራ ባርከህለታል። 11እስቲ፣ እጅህን ዘርግተህ ያለውን ሁሉ ንካበት፤ በእርግጥ ፊት ለፊት ይረግምሃል።”

12እግዚአብሔርም ሰይጣንን፣ “እነሆ፤ እርሱ ያለው ሁሉ በእጅህ ነው፤ እርሱን ራሱን ግን እንዳትነካው” አለው።

ከዚህ በኋላ ሰይጣን ከእግዚአብሔር ፊት ወጥቶ ሄደ።

13አንድ ቀን የኢዮብ ወንዶችና ሴቶች ልጆች በታላቅ ወንድማቸው ቤት ተሰብስበው ይበሉና የወይን ጠጅ ይጠጡ ነበር፤ 14መልእክተኛም ወደ ኢዮብ መጥቶ እንዲህ አለው፤ “በሬዎች እያረሱ፣ አህዮችም በአጠገባቸው እየጋጡ ሳሉ፣ 15ሳባውያን ጥቃት አድርሰውባቸው ይዘዋቸው ሄዱ፤ አገልጋዮቹንም በሰይፍ ገደሉ። እኔም ብቻዬን አመለጥሁ፤ ልነግርህም መጣሁ።”

16እርሱም እየተናገረ ሳለ፣ ሌላ መልእክተኛ መጥቶ፣ “የእግዚአብሔር እሳት ከሰማይ ወረደች፤ በጎችንና አገልጋዮችንም በላች፤ እኔም ብቻዬን አመለጥሁ፤ ልነግርህም መጣሁ” አለው።

17እርሱም እየተናገረ ሳለ፣ ሌላ መልእክተኛ መጥቶ፣ “ከለዳውያን በሦስት ቡድን መጥተው ጥቃት አደረሱ፤ ግመሎችህንም ይዘው ሄዱ፤ አገልጋዮቹን በሰይፍ ገደሉ፤ እኔም ብቻዬን አመለጥሁ፤ ልነግርህም መጣሁ” አለው።

18እርሱም እየተናገረ ሳለ፣ ሌላ መልእክተኛ መጥቶ እንዲህ አለው፤ “ወንዶችና ሴቶች ልጆችህ በታላቅ ወንድማቸው ቤት ተሰብስበው እየበሉና እየጠጡ ሳሉ፣ 19እነሆ፤ ታላቅ ዐውሎ ነፋስ ከምድረ በዳ መጣ፤ የቤቱንም አራት ማእዘናት መታ፤ እርሱም በልጆቹ ላይ ወድቆ ገደላቸው። እኔም ብቻዬን አመለጥሁ፤ ልነግርህም መጣሁ።” 20ኢዮብም ተነሣ፤ ልብሱን ቀደደ፤ ራሱን ተላጨ፤ በምድርም ላይ ተደፍቶ ሰገደ፤ 21እንዲህም አለ፤

“ዕራቍቴን ከእናቴ ማሕፀን ወጣሁ፤

ዕራቍቴንም እሄዳለሁ።1፥21 ወይም ወደዚያ እመለሳለሁ

እግዚአብሔር ሰጠ፤ እግዚአብሔር ነሣ፤

የእግዚአብሔር ስም ቡሩክ ይሁን።”

22በዚህ ሁሉ፣ ኢዮብ አልበደለም፤ በእግዚአብሔርም ላይ ክፉ አልተናገረም።

Thai New Contemporary Bible

โยบ 1:1-22

บทนำ

1ในดินแดนอูสมีชายคนหนึ่งชื่อโยบ เป็นคนดีเพียบพร้อม เที่ยงธรรม ยำเกรงพระเจ้า และหลีกห่างจากความชั่ว 2เขามีบุตรชายเจ็ดคนและบุตรสาวสามคน 3และเขามีแกะถึงเจ็ดพันตัว อูฐสามพันตัว วัวผู้ห้าร้อยคู่ ลาห้าร้อยตัว และมีคนรับใช้มากมาย เขาเป็นคนยิ่งใหญ่ที่สุดในบรรดาชาวตะวันออก

4บุตรชายของโยบจะผลัดกันจัดงานเลี้ยงในบ้านของตน และเชิญพี่น้องชายหญิงมาร่วมในงานด้วย 5เมื่องานเลี้ยงเสร็จสิ้นลงแต่ละครั้ง โยบจะให้พวกเขามาชำระตัว ตั้งแต่เช้าตรู่โยบจะถวายเครื่องเผาบูชาให้บุตรแต่ละคนโดยระลึกว่า “บางทีลูกของเราอาจทำบาปหรือแช่งด่าพระเจ้าอยู่ในใจ” นี่คือธรรมเนียมปฏิบัติของโยบเสมอมา

การทดสอบโยบครั้งแรก

6วันหนึ่งบรรดาทูตสวรรค์1:6 ภาษาฮีบรูว่าบรรดาบุตรของพระเจ้ามาชุมนุมกันต่อหน้าองค์พระผู้เป็นเจ้า ซาตาน1:6 แปลว่า ผู้กล่าวหาก็มาด้วย 7องค์พระผู้เป็นเจ้าตรัสถามซาตานว่า “เจ้ามาจากที่ไหน?”

ซาตานทูลตอบองค์พระผู้เป็นเจ้าว่า “ท่องเที่ยวไปมาในโลกพระเจ้าข้า”

8องค์พระผู้เป็นเจ้าจึงตรัสกับซาตานว่า “เจ้าสังเกตดูโยบผู้รับใช้ของเราบ้างหรือไม่? ทั่วโลกนี้ไม่มีใครเหมือนเขา เขาเป็นคนดีเพียบพร้อม เที่ยงธรรม ยำเกรงพระเจ้า และหลีกห่างจากความชั่ว”

9ซาตานทูลตอบว่า “โยบยำเกรงพระเจ้าโดยไม่หวังอะไรเลยหรือ? 10พระองค์ทรงล้อมรั้วป้องกันเขาและครอบครัวกับทรัพย์สินทุกอย่างของเขาไม่ใช่หรือ? พระองค์ทรงอวยพรกิจการทุกอย่างที่เขาทำ ดังนั้นฝูงสัตว์ทั้งหลายของเขาจึงขยายทั่วแผ่นดิน 11ลองพระองค์ยื่นพระหัตถ์ออกทำลายทรัพย์สินทุกอย่างของเขาสิ รับรองว่าเขาจะแช่งด่าพระองค์ต่อหน้าเลยทีเดียว”

12องค์พระผู้เป็นเจ้าตรัสกับซาตานว่า “เอาเถิด ทุกอย่างที่เขามีก็อยู่ในมือของเจ้าแล้ว แต่อย่าแตะต้องตัวเขาก็แล้วกัน”

ซาตานจึงทูลลาองค์พระผู้เป็นเจ้าไป

13วันหนึ่งขณะที่บุตรชายบุตรสาวของโยบกำลังกินเลี้ยงกันอยู่ที่บ้านของพี่ชายคนโต 14ก็มีคนหนึ่งมาบอกโยบว่า “วัวของท่านกำลังไถนาอยู่และลากินหญ้าอยู่ใกล้ๆ 15ก็มีพวกเสบามาปล้น ต้อนสัตว์ไปและฆ่าฟันคนเลี้ยงตายหมด มีข้าพเจ้าเพียงคนเดียวหนีรอดมาเรียนท่าน!”

16ขณะที่คนนั้นพูดยังไม่ทันขาดคำ ก็มีอีกคนมาบอกว่า “ไฟของพระเจ้าตกลงมาจากท้องฟ้าเผาผลาญฝูงแกะและคนเลี้ยงของท่านวอดวาย มีข้าพเจ้าเพียงคนเดียวหนีรอดมาเรียนท่าน!”

17ก่อนที่คนนั้นจะพูดจบ ก็มีอีกคนมาบอกว่า “กองโจรชาวเคลเดียสามกองมาไล่ต้อนอูฐของท่านไปและฆ่าฟันบ่าวไพร่ของท่าน มีข้าพเจ้าเพียงคนเดียวหนีรอดมาเรียนท่าน!”

18ขณะที่เขายังพูดอยู่ก็มีอีกคนหนึ่งเข้ามาบอกว่า “บุตรชายบุตรสาวของท่านกำลังกินเลี้ยงกันอยู่ที่บ้านพี่ชายคนโต 19ทันใดนั้นก็มีพายุใหญ่พัดจากทะเลทรายซัดกระหน่ำจนบ้านพังลงมาทับพวกเขาตายหมด มีข้าพเจ้าเพียงคนเดียวหนีรอดมาเรียนท่าน!”

20เมื่อโยบได้ยินดังนั้น เขาจึงลุกขึ้น ฉีกเสื้อคลุม และโกนศีรษะ เขาซบกายลงกับพื้นนมัสการพระเจ้า 21และกล่าวว่า

“ข้าพเจ้าออกมาจากครรภ์มารดาตัวเปล่า

และข้าพเจ้าจะจากไป1:21 หรือกลับไปที่นั่นตัวเปล่า

องค์พระผู้เป็นเจ้าประทานและองค์พระผู้เป็นเจ้าทรงเอาไป

สรรเสริญพระนามของพระยาห์เวห์”

22ในเหตุการณ์ทั้งหมดนี้ โยบไม่ได้ทำบาปโดยกล่าวโทษพระเจ้าเลย