New Amharic Standard Version

ኢያሱ 9:1-27

የገባዖን ሰዎች የፈጸሙት ማታለል

1በዮርዳኖስ ምዕራብ ባለው በተራራማው አገር፣ በቈላማው ምድር እንዲሁም እስከ ሊባኖስ በሚደርሰው በመላው በታላቁ ባሕር9፥1 የሜድትራኒያን ባሕር ነው። ዳርቻ የነበሩት የኬጢያውያን፣ የአሞራውያን፣ የከነዓናውያን፣ የፌርዛውያን፣ የኤዊያውያን፣ የኢያቡሳውያን ነገሥታት ይህን በሰሙ ጊዜ፣ 2ኢያሱንና እስራኤልን ለመውጋት በአንድነት መጡ።

3የገባዖን ሰዎች ግን ኢያሱ በኢያሪኮና በጋይ ላይ ያደረገውን በሰሙ ጊዜ፣ 4ለማታለል ፈለጉ፤ ስለዚህም ያረጀ ስልቻና የተጣፈ አሮጌ9፥4 አብዛኞቹ የዕብራይስጥ ቅጂዎች ከዚህ ጋር ይስማማሉ፤ ነገር ግን አንዳንድ የዕብራይስጥ ቅጂዎች፣ የቩልጌት፣ የሱርስቱ ትርጒም እንዲሁም የሰብዓ ሊቃናት ቅጂ፣ “የሚያስፈልጋቸውን ነገር አዘጋጁ፤ በአህዮቻቸውም ላይ ጫኑ” ይላሉ። የወይን ጠጅ አቊማዳ በአህያ የጫነጀ መልእክተኛ መስለው ሄዱ። 5ሰዎቹም ያረጀና የተጠጋገነ ነጠላ ጫማ አድርገዋል፤ አሮጌ ልብስ ለብሰዋል፤ ለስንቅ የያዙት እንጀራም በሙሉ የደረቀና የሻገተ ነበር። 6ከዚያም ኢያሱ ወደ ሰፈረበት ወደ ጌልገላ ሄደው ኢያሱንና የእስራኤልን ሰዎች፣ “የመጣነው ከሩቅ አገር ነው፤ ከእኛ ጋር ቃል ኪዳን ግቡ” አሏቸው።

7የእስራኤልም ሰዎች ለኤዊያውያኑ፣ “እናንተ የምትኖሩት እዚሁ ቅርብ ቢሆንስ? ታዲያ ከእናንተ ጋር እንዴት ቃል ኪዳን እንገባለን?” አሏቸው።

8እነርሱም ኢያሱን፣ “እኛ ባሪያዎችህ ነን” አሉት።

ኢያሱ ግን፣ “እናንተ እነማን ናችሁ? የመጣችሁትስ ከየት ነው?” ሲል ጠየቃቸው።

9እነርሱም እንዲህ ብለው መለሱለት፤ “እኛ ባሪያዎችህ የአምላካህን የእግዚአብሔርን ዝና ሰምተን፣ እጅግ ሩቅ ከሆነ አገር መጥተናል፤ ዝናውንና በግብፅ ያደረገውንም ሁሉ ሰምተናል፤ 10እንዲሁም ከዮርዳኖስ ማዶ ባሉት በሁለቱ የአሞራውያን ነገሥታት ማለትም በሐሴቦን ንጉሥ በሴዎን፣ አስታሮትን ይገዛ በነበረው በባሳን ንጉሥ በዐግ ያደረገውን ሁሉ ነው። 11ሽማግሌዎቻችንና በአገራችን የሚኖሩት ሁሉ፣ ‘ለመንገዳችሁ የሚሆን ስንቅ ያዙ፤ ሄዳችሁም ተገናኟቸው፤ እኛ ባሮቻችሁ እንሆናለን፤ ከእኛ ጋር ቃል ኪዳን ግቡ በሉአቸው’ አሉን። 12ይህ የያዝነው እንጀራ ወደ እናንተ ለመምጣት ከቤታችን በተነሣንበት ቀን ትኵስ ነበር፤ አሁን ግን እንዴት እንደ ደረቀና እንደሻገተ ተመልከቱ። 13እነዚህ የወይን ጠጅ አቍማዳዎቻችን ያን ጊዜ ስንሞላቸው አዲስ ነበሩ፤ አሁን ግን እንዴት እንደተ ቀዳደዱ ተመልከቱ፤ ልብሳችንና ጫማችንም ብዙ መንገድ በመጓዛችን አልቀዋል።”

14የእስራኤልም ሰዎች ከስንቃችው ላይ ጥቂት ወሰዱ፤ ስለ ጒዳዩ ግን እግዚአብሔርን አልጠየቁም ነበር። 15ኢያሱም በሰላም ለመኖር የሚያስችላቸውን ቃል ኪዳን ከእነርሱ ጋር አደረገ፤ የጉባኤውም መሪዎች ይህንኑ በመሓላ አጸኑላቸው።

16እስራኤላውያን ከገባዖን ሰዎች ጋር ቃል ኪዳኑን ካደረጉ ከሦስት ቀን በኋላ፣ ሰዎቹ እዚያው አጠገባቸው የሚኖሩ ጎረቤቶቻቸው መሆናቸውን ሰሙ። 17ስለዚህ እስራኤላውያን ተጒዘው በሦስተኛው ቀን ገባዖን፣ ከፊራ፣ ብኤሮትና ቂርያትይዓይሪም ወደተባሉት የገባዖን ሰዎች ወደሚኖሩባቸው ከተሞች መጡ። 18ሆኖም እስራኤላውያን አልወጓቸውም፤ የጉባዔው መሪዎች በእስራኤል አምላክ በእግዚአብሔር ስም ምለውላቸው ነበርና።

ማኅበሩም ሁሉ በመሪዎቹ ላይ አጒረመረሙ፤ 19ነገር ግን መሪዎቹ ሁሉ ለማኅበሩ እንዲህ ሲሉ መለሱ፤ ‘በእስራኤል አምላክ በእግዚአብሔር ስም ስለማልንላቸው፣ አሁን ጒዳት ልናደርስባቸው አንችልም፤ 20እንዲህ እናደርግላቸዋለን፤ የገባንላቸውን መሓላ በማፍረስ ቊጣ እንዳይደርስብን፣ በሕይወት እንዲኖሩ እንዲሁ እንተዋቸዋለን፤ 21ነገር ግን ለማኅበረ ሰቡ በሙሉ ዕንጨት እየቈረጡ ውሃ እየቀዱ ይኑሩ።” ስለዚህ መሪዎቹ የገቡላቸው ቃል ተጠበቀ።

22ከዚያም ኢያሱ የገባዖንን ሰዎች ጠርቶ እንዲህ አላቸው፤ “እዚሁ አጠገባችን መኖራችሁ የታወቀ ሆኖ ሳለ፣ ‘የምንኖረው ከእናንተ በራቀ ስፍራ ነው’ ብላችሁ ያታለላችሁን ለምንድን ነው? 23ስለዚህ አሁን የተረገማችሁ ናችሁ፤ ጥቂቶቻችሁም ለአምላኬ ቤት ምንጊዜም ዕንጨት ቈራጭ፣ ውሃ ቀጂ ባሮች ትሆናላችሁ።”

24እነርሱም ለኢያሱ እንዲህ ብለው መለሱለት፤ “አምላክህ እግዚአብሔር ባሪያውን ሙሴን እንዳዘዘው፣ ምድሪቱን በሙሉ ለእናንተ እንደሚሰጣችሁና ነዋሪዎቿንም ከፊታችሁ እንደሚያጠፋቸው በእርግጥ ለእኛ ለባሪያዎችህ ተነግሮናል፤ ስለዚህ ከእናንተ የተነሣ ለሕይወታችን በመሥጋት ይህን አድርገናል። 25እነሆ፤ አሁን በእጅህ ውስጥ ነን፤ በጎና ትክክል መስሎ የታየህን ነገር ሁሉ አድርግብን።”

26ስለዚህ ኢያሱ የገባዖንን ሰዎች ከእስራኤላውያን እጅ አዳናቸው፤ እነርሱም አልገደሏቸውም። 27በዚያችም ዕለት ኢያሱ የገባዖንን ሰዎች ለማኅበረ ሰቡና እግዚአብሔር በሚመርጠው ስፍራ ለሚቆመው የእግዚአብሔር ለሆነው መሠዊያ እስከ ዛሬ ድረስ ዕንጨት ቈራጮችና ውሃ ቀጂዎች አደረጋቸው።

Japanese Contemporary Bible

ヨシュア記 9:1-27

9

ギブオン人の策略 

1-2さて、エリコでの出来事を耳にした周辺国の王たちは、さっそく連合し、ヨシュアとイスラエル軍に全力を挙げて対抗しようとしました。ヨルダン川の西側で、北はレバノン山脈までの地中海沿岸に住む、ヘテ人、エモリ人、カナン人、ペリジ人、ヒビ人、エブス人の王たちでした。

3-5しかしギブオンの住民は、エリコとアイでの一部始終を聞いて、何とか生き延びようと策略を巡らし、使者をヨシュアのもとへ送りました。使者の一行は、いかにも遠い国から旅して来たかのように、ぼろぼろの服を着て、繕ったくつをはき、風雨にさらされた袋と、つぎはぎだらけのぶどう酒の皮袋と、かび臭い乾ききったパンをろばに積んでいました。 6一行はギルガルのイスラエルの陣営に着くと、ヨシュアと人々にこう言ったのです。「私どもは、友好条約を結んでいただきたくて、遠い国からまいりました。」

7人々は、このヒビ人たちに答えました。「あなたたちがこの近くに住んでいないという確証はない。このあたりの住民を滅ぼせと主から命じられている以上、条約を結ぶわけにはいかない。」

8「私どもを奴隷にしてくださってもけっこうです。」

「それにしても、あなたたちはいったい何者だ。どこから来たのか」とヨシュアは尋ねました。 9「私どもは遠い国からまいりました。あなたの神、主の偉大なお力と、エジプトでなさったすべてのことは知っております。 10それに、あなたがエモリ人の二人の王、あのヘシュボンの王シホンとバシャンの王オグとを、どんな目に会わせられたかもよく知っております。 11それで、私どもの長老や住民がこう言うのです。『さあ、長旅の用意をして、イスラエルの人々を訪ねてくれ。そして、奴隷になると申し上げて、和平を求めて来るように』と。 12このパンなど、出発した時には焼き立てのほかほかでしたが、今はごらんのとおり、すっかりひからびて、かび臭くなっております。 13このぶどう酒の皮袋も新品でしたが、今は古びて、破れてしまっておりますし、着物もくつも、難儀な長旅ですっかりぼろぼろになってしまいました。」

14-15このことばに、ヨシュアもほかの指導者たちも、とうとうその一行を信用し、主の指示を仰ぐこともせず、和を講じてしまったのです。そして、厳粛な誓いを立てて協定を結びました。

16それから三日たって、彼らが近くの者だという事実が明らかになりました。 17イスラエル軍は直ちに調査を開始し、三日目に彼らの町々に踏み込みました。その町の名は、ギブオン、ケフィラ、ベエロテ、キルヤテ・エアリムです。 18しかし、イスラエル軍は彼らを攻撃しませんでした。イスラエルの指導者たちが、先に主にかけて誓っていたからです。しかし、治まらないのは会衆で、協定を結んだことで、指導者たちに不平を鳴らしました。 19指導者たちは言いました。「われわれはイスラエルの神、主の前で、彼らに手を下さないと誓ってしまったのだ。だから手出しはしないでくれ。 20どうしても生かしてやらなければならないのだ。もし誓いを破れば、主の怒りが下る。」 21こういうわけで、ギブオンの住民は、イスラエル人の奴隷として、たきぎを割ったり、水をくんだりして暮らすことになったのです。

22ヨシュアは彼らを呼んで、問いただしました。「あなたたちは、私たちの近くに住んでいながら、なぜ遠い国から来たなどと、だますようなまねをしたのか。 23今にのろいが降りかかり、あなたたちはこの後いつまでも、私たちの奴隷となり、私たちの神に仕えて、たきぎを割り、水をくむことになるだろう。」

24「私どもがあんなことをしたのは、イスラエルの神様が忠実なしもべモーセ様に、『この全土を征服し、住民を皆殺しにしなさい』とお命じになったことを、はっきり知っていたからです。殺されるのが怖かったのです。お赦しください。 25どうぞ、どのようにでもお気のすむようになさってください。」

26そこでヨシュアは、彼らを殺すことを禁じました。 27彼らはイスラエル人のため、また、やがて主の選ぶ場所に築かれる祭壇のためにたきぎを割り、水をくむ者となりました。それは今も続いています。