New Amharic Standard Version

ኢያሱ 21:1-45

ለሌዋውያን የተመደቡ ከተሞች

21፥4-39 ተጓ ምብ – 1ዜና 6፥54-80

1የሌዋውያን ቤተ ሰብ አለቆች ወደ ካህኑ ወደ አልዓዛር፣ ወደ ነዌ ልጅ ወደ ኢያሱና ወደ ሌሎቹ የእስራኤል ነገድ አባቶች ዘንድ ቀረቡ፤ 2በከነዓን ምድር በሴሎም፣ “እግዚአብሔር የምንኖርባቸውን ከተሞች፣ ከብቶቻችን ከሚሰማሩባቸው ቦታዎች እንድትሰጡን በሙሴ በኩል አዞልን ነበር” አላቸው። 3ስለዚህ እስራኤላውያን ከወረሱት ምድር ላይ የሚከተሉትን ከተሞችና መሰማሪያዎች እግዚአብሔር ባዘዘው መሠረት ለሌዋውያኑ ሰጡ፤

4የመጀመሪያው ዕጣ ለቀዓት ዘሮች በየጐሣቸው ወጣ፤ የካህኑ የአሮን ዝርያዎች ለሆኑት ሌዋውያን ከይሁዳ፣ ከስምዖንና ከብንያም ነገዶች ዐሥራ ሦስት ከተሞች በዕጣ ተመደቡላቸው። 5ለቀሩት ለቀዓት ዘሮች ደግሞ ከኤፍሬምና ከዳን ነገድ ጐሣዎች፣ እንዲሁም ከምናሴ ነገድ እኩሌታ ጐሣዎች ዐሥር ከተሞች በዕጣ ተመደቡላቸው።

6ለጌርሶን ዝርያዎች ከይሳኮር፣ ከአሴር፣ ከንፍታሌም ነገድ ጐሣዎችና ባሳን ውስጥ ካለው ከምናሴ ነገድ እኩሌታ ጐሣዎች ዐሥራ ሦስት ከተሞች ተመደቡላቸው።

7ለሜራሪ ዝርያዎች በየጐሣቸው ከሮቤል፣ ከጋድና ከዛብሎን ነገዶች ዐሥር ከተሞች ተመደቡላቸው።

8ስለዚህ እስራኤላውያን እግዚአብሔር በሙሴ በኩል ባዘዘው መሠረት፣ እነዚህን ከተሞችና መሰማሪያቸውን ለሌዋውያኑ በዕጣ መደቡላቸው።

9ከይሁዳና ከስምዖን ነገዶች ደግሞ ከዚህ በታች በስም የተጠቀሱትን ከተሞች በዕጣ መደቡላቸው። 10እነዚህም ከተሞች የሌዊ ልጆች፣ የቀዓት ጐሣዎች ለሆኑት ለአሮን ዝርያዎች ተመደቡ፤ ይህም የሆነው የመጀመሪያው ዕጣ ለእነርሱ ስለ ወጣላቸው ነበር፤

11እነርሱም በተራራማው የይሁዳ ምድር ያለችውን ኬብሮን የተባለችውን ቂርያት አርባቅን በዙሪያዋ ካለው መሰማሪያ ጋር ሰጧቸው፤ አርባቅ የዔናቅ አባት ነበረ። 12ይሁን እንጂ በከተማዪቱ ዙሪያ ያሉትን ዕርሻዎችና መንደሮች ለዮፎኒ ልጅ ለካሌብ ርስት አድርገው ሰጡት። 13እንደዚሁም ለነፍስ ገዳይ መማጠኛ የሆነችውን ኬብሮንንና ልብናን ከነ ማሰማሪያቸው ለካህኑ ለአሮን ልጆች ሰጧቸው፤ 14ደግሞም የቲርን፣ ኤሽትሞዓን፣ 15ሖሎንን፣ ዳቤርን፣ 16ዐይንን፣ ዮጣንና ቤትሳሚስን ከነ ማሰማሪያቸው ሰጧቸው፤ እነዚህ ዘጠኙ ከተሞች ከሁሉ ነገዶች ይዞታ ላይ ተከፍለው የተሰጡ ናቸው።

17ከብንያም ነገድ ገባዖን፣ ጌባዕ፣ 18ዓናቶትና አልሞን የተባሉትን አራት ከተሞች ከነ ማሰማሪያዎቻቸው ሰጧቸው።

19ለካህናቱ ለአሮን ዝርያዎች ከነ ማሰማሪያቸው የተሰጧቸው ከተሞች ዐሥራ ሦስት ነበሩ።

20የሌዊ ልጅ የቀዓት ጐሣዎች ለሆኑት ለሌሎቹ ደግሞ ከኤፍሬም ነገድ ላይ ተከፍለው የሚከተሉት ከተሞች በዕጣ ተመደቡላቸው።

21በተራራማው በኤፍሬም ምድርም ለነፍሰ ገዳይ መማጠኛ የሆነችው ሴኬምና ጌዝር፣ 22ቂብጻይሞና ቤትሖሮን ከነመሠማሪያዎቻቸው አራት ከተሞች ተሰጡአቸው።

23እንዲሁም ከዳን ነገድ ኤልተቄን፣ ገባቶን፤ 24ኤሎንና ጋትሪሞን ከነመሰማሪያዎቻቸው አራት ከተሞች ተሰጧቸው።

25ከምናሴ ነገድ እኩሌታ ደግሞ ታዕናክና ጋትሪሞን ከነ ማሰማሪያዎቻቸው ሁለት ከተሞች ተሰጧቸው።

26እነዚህ ዐሥር ከተሞች ሁሉ ከነ ማሰማሪያዎቻቸው ለተቀሩት የቀዓት ጐሣዎች ተሰጧቸው።

27የጌርሶን ወገኖች ለሆኑት ለሌሎቹ የሌዊ ጐሳዎች የተሰጧቸው የሚከተሉት ናቸው፤

ከምናሴ ነገድ እኩሌታ በባሳን ውስጥ ለነፍሰ ገዳይ መማጠኛ የሆነችው ከተማ ጎላንና በኤሽትራ እነዚህ ሁለት ከተሞች ከነመሰማሪያዎቻቸው፤

28ከይሳኮር ነገድ፣

ቂሶን፣ ዳብራት፣ 29የርሙትና ዓይን ጋኒም፣ እነዚህ አራት ከተሞች ከነመሰማሪያዎቻቸው፤

30ከአሴር ነገድ፣

ሚሽአል፣ ዓብዶን፣ 31ሔልቃትና ረአብ እነዚህ አራት ከተሞች ከነመሰማሪያዎቻቸው፤

32ከንፍታሌም ነገድ፣

በገሊላ ውስጥ ለነፍሰ ገዳይ መማጠኛ የሆነችው ከተማ ቃዴስ፣ ሐሞትዶርና ቀርታን እነዚህ ሦስት ከተሞች ከነመሰማሪያዎቻቸው፤

33ለጌድሶናውያን ጐሣዎች የተመደቡት ከተሞች ሁሉ ከነ ማሰማሪያዎቻቸው ዐሥራ ሦስት ነበሩ።

34የሜራሪ ጐሣዎች ለሆኑት ለተቀሩት ሌዋውያን የተሰጧቸው የሚከተሉት ናቸው፤

ከዛብሎን ነገድ ዮቅንዓም፣ ቀርታ፣ 35ዲሞናና ነህላል፣ እነዚህ አራት ከተሞች ከነመሰማሪያዎቻቸው፤

36ከሮቤል ነገድ፣

ቦሶር፣ ያሀጽ፣ 37ቅዴሞትና ሜፍዓት፣ እነዚህ አራት ከተሞች ከነመሰማሪያዎቻቸው፤

38ከጋድ ነገድ፣

በገለዓድ ውስጥ ለነፍሰ ገዳይ መማጠኛ የሆነችው ከተማ ራሞት መሃናይም፣ 39ሐሴቦንና ኢያዜር፣ እነዚህ አራት ከተሞች ከነመሰማሪያዎቻቸው፦

40የሜራሪ ጐሣዎች ለሆኑት ለተቀሩት ሌዋውያን የተመደቡት ከተሞች ሁሉ ዐሥራ ሁለት ነበሩ።

41እንግዲህ እስራኤላውያን ርስት አድርገው ከያዙት ምድር ለሌዋውያኑ የተሰጧቸው ከተሞች ከነ ማሰማሪያዎቻቸው ባጠቃላይ አርባ ስምንት ነበሩ። 42እነዚህም ከተሞች እያንዳንዳቸው በዙሪያቸው ማሰማሪያዎች ነበሯቸው፤ ማሰማሪያ የሌለው ከተማ አልነበረም።

43ስለዚህ እግዚአብሔር ለቀድሞ አባቶቻቸው ይሰጣቸው ዘንድ የማለላቸውን ምድር ሁሉ ለእስራኤል ሰጠ፤ እነርሱም ምድሪቱን ወረሱ፣ መኖሪያቸውም አደረጓት። 44እግዚአብሔር ለቀድሞ አባቶቻቸው እንደ ማለላቸው በዙሪያቸው ካሉት አሳረፋቸው፤ አንድም ጠላት ሊቋቋማቸው አልቻለም፤ እግዚአብሔር ጠላቶቻቸውን ሁሉ አሳልፎ በእጃቸው ሰጥቶአቸዋልና። 45እግዚአብሔር ለእስራኤል ቤት ከሰጠው መልካም የተስፋ ቃል አንዳችም አልቀረም፤ ሁሉም ተፈጽሞአል።

Japanese Contemporary Bible

ヨシュア記 21:1-45

21

レビ人の町

1さて、レビ族の指導者たちはシロに出向いて来て、祭司エルアザルやヨシュア、および他部族の族長に相談を持ちかけました。 2その申し出は、「主がモーセによって指示なさったことだが、われわれにも住む家と家畜用の放牧地とを確保してもらいたい」というものでした。

3そこで、征服したばかりの幾つかの町が、放牧地も含めて、レビ人に与えられることになりました。 4町は十三でしたが、初めにユダ、シメオン、ベニヤミンの各部族に割り当てられたものです。これらの町は、レビ族の中でも、アロンの子孫であるケハテ氏族の祭司たちに与えられました。 5このほかのケハテの人々には、エフライム、ダン、マナセの半部族の各領地から十の町が与えられました。 6同様にゲルション氏族は、くじによってバシャンにある十三の町を譲り受けました。その町は初め、イッサカル、アシェル、ナフタリの各部族と、マナセの半部族に与えられたものでした。 7メラリ氏族は、ルベン、ガド、ゼブルンの各部族から十二の町を譲り受けました。 8モーセへの主のご命令どおり、これらの町と放牧地は、くじによって、レビ人に割り当てられたのです。

9-16最初に割り当てを受けたのは、祭司、つまりレビ人のうちでもケハテ氏族の中のアロンの子孫でした。その領地の内訳を見ると、ユダとシメオンの部族から、次にあげる九つの町が、周囲の放牧地とともに与えられたのでした。まず、ユダの山地内の、避難用の町でもあるヘブロン。別名を、アナクの父アルバの名にちなんで、キルヤテ・アルバともいいます。ただし、町の畑と周辺の村々は、エフネの子カレブのものです。ほかに、リブナ、ヤティル、エシュテモア、ホロン、デビル、アイン、ユタ、ベテ・シェメシュ。

17-18また、次にあげる四つの町と放牧地が、ベニヤミン族から譲られました。ギブオン、ゲバ、アナトテ、アルモン。 19以上の合計十三の町が、アロンの子孫である祭司に与えられたのです。

20-22ケハテの他の諸氏族は、エフライム族から、次の四つの町と放牧地を譲り受けました。避難用の町シェケム、ゲゼル、キブツァイム、ベテ・ホロン。

23-24ダン部族からは、次にあげる四つの町と放牧地が譲られました。エルテケ、ギベトン、アヤロン、ガテ・リモン。

25マナセの半部族は、タナク、ガテ・リモンの町と周囲の放牧地を譲りました。 26以上、ケハテの他の諸氏族が受けた町と放牧地の数は、全部で十に上ります。

27レビ人に属するゲルション氏族は、マナセの半部族から、次の二つの町と放牧地を譲り受けました。バシャンにある避難用の町ゴラン、ベエシュテラ。

28-29イッサカル族は、次の四つの町と放牧地を譲りました。キシュヨン、ダベラテ、ヤルムテ、エン・ガニム。

30-31アシェル族は、次の四つの町と放牧地を譲りました。ミシュアル、アブドン、ヘルカテ、レホブ。

32ナフタリ族は、次の三つの町と放牧地を譲りました。ガリラヤにある避難用の町ケデシュ、ハモテ・ドル、カルタン。

33こうして、合計十三の町と放牧地がゲルション氏族の所有となったのです。

34-35レビ人のもう一つの氏族であるメラリ氏族には、ゼブルン部族から、次の四つの町と放牧地が譲られました。ヨクネアム、カルタ、ディムナ、ナハラル。

36-37ルベン族は、次の四つの町と放牧地を譲りました。ベツェル、ヤハツ、ケデモテ、メファアテ。

38-39ガド族は、次にあげる四つの町と放牧地を譲りました。避難用の町ラモテ、マハナイム、ヘシュボン、ヤゼル。

40これでメラリ氏族は、合計十二の町を与えられたことになります。

41-42レビ人に与えられた町と放牧地の数は、全部で四十八でした。

43このようにして主は、イスラエルの先祖に約束した地をすべてイスラエル人に与えました。そこで、人々はその地を占領して住みついたのです。 44約束どおり平和が訪れ、立ち向かって来る敵は一人もいませんでした。敵という敵はすべて、主の助けによって滅ぼし尽くしたからです。 45主がイスラエルに約束された良いことはみな、そのとおりに実現したのです。