New Amharic Standard Version

ኢያሱ 20:1-9

የመማጠኛ ከተሞች

20፥1-9 ተጓ ምብ – ዘኁ 35፥9-34፤ ዘዳ 4፥41-43፤ 19፥1-14

1ከዚያም እግዚአብሔር ኢያሱን እንዲህ አለው፤ 2“በሙሴ በኩል በነገርኋችሁ መሠረት የመማጠኛ ከተሞች እንዲለዩ ለእስራኤላውያን ንገራቸው፤ 3ሳያስበው ድንገት ሰው የገደለ ማንኛውም ሰው ወደዚያ በመሸሽ ከደም ተበቃዩ እንዲያመልጥ ከተማዪቱ መጠለያ ትሁን። 4“ገዳዩ ከነዚህ ከተሞች ወደ አንዲቱ በሚሸሽበት ጊዜ፣ በከተማዪቱ መግቢያ በር ላይ ቆሞ ጒዳዩን ለከተማዪቱ ሽማግሌዎች ይንገራቸው፤ ከዚያም እነርሱ ወደ ከተማቸው አስገብተው የሚኖርበትን ስፍራ ሰጥተውት አብሮአቸው ይቀመጥ። 5ደም ተበቃዩ ተከታትሎት ቢመጣ፣ ሆን ብሎና በክፋት ተነሣሥቶ ወንድሙን የገደለው ባለመሆኑ፣ ሰዎቹ ነፍሰ ገዳዩን አሳልፈው አይስጡት። 6በማኅበሩ ፊት ለፍርድ እስኪቀርብና በዚያ ጊዜ የሚያገለግለው ሊቀ ካህናት እስኪሞት ድረስ በዚያች ከተማ ይቆይ። ከዚያም ወደ ቤቱ፣ ሸሽቶ ወደ መጣበት ከተማ ሊመለስ ይችላል።”

7ስለዚህም በኰረብታማው በንፍታሌም ምድር በገሊላ ቃዴስን፣ በኰረብታማው በኤፍሬም ምድር ሴኬምን፣ በኰረብታማው በይሁዳ ምድር ኬብሮን የምትባለውን ቂርያት አርባቅን ለዩ። 8እንደዚሁም ከዮርዳኖስ ማዶ ከኢያሪኮ20፥8 ምናልባት፣ ዮርዳኖስ ዘኢያሪኮ የዮርዳኖስ ወንዝ የጥንት መጠሪያ ሊሆን ይችላል። በስተምስራቅ በሮቤል ነገድ ይዞታ ውስጥ ከፍታ ባለው ምድረ በዳ ያለችውን ቦሶርን፣ በጋድ ነገድ ይዞታ ውስጥ ባለችው በገለዓድ የምትገኘውን ራሞትንና በምናሴ ነገድ ይዞታ ውስጥ በባሳን የምትገኘውን ጎላንን ለዩ። 9ሳያስበው በድንገት ሰው የገደለ ማንኛውም እስራኤላዊ ወይም በመካከላቸው የሚኖር ማንኛውም መጻተኛ ወደ ተለዩት ከተሞች መሸሽ ይችላል፤ በማኅበሩ ፊት ከመቆሙ አስቀድሞም በደም ተበቃዩ መገደል የለበትም።

Thai New Contemporary Bible

โยชูวา 20:1-9

เมืองลี้ภัย

(กดว.35:9-34; ฉธบ.4:41-43; 19:1-14)

1แล้วองค์พระผู้เป็นเจ้าตรัสกับโยชูวาว่า 2“จงสั่งประชากรอิสราเอลให้กำหนดเมืองลี้ภัยตามที่เราได้สั่งโมเสสไว้ 3ผู้ใดกระทำให้คนตายโดยไม่เจตนาและเป็นอุบัติเหตุสามารถหนีมายังเมืองเหล่านี้ และได้รับความคุ้มครองให้พ้นจากผู้แก้แค้น

4“เมื่อผู้ถูกกล่าวหาหนีมายังเมืองลี้ภัยแห่งใดแห่งหนึ่ง เขาต้องยืนอยู่ตรงทางเข้าประตูเมืองและชี้แจงคดีต่อหน้าบรรดาผู้อาวุโสของเมืองนั้น ผู้อาวุโสจะต้องยินยอมให้ผู้นั้นเข้ามาและให้ที่พักอาศัยแก่เขา 5หากผู้แก้แค้นไล่ตามมา อย่ามอบตัวผู้ถูกกล่าวหาให้แก่ผู้แก้แค้น เพราะเขาฆ่าเพื่อนบ้านโดยไม่ตั้งใจและไม่ได้คิดมุ่งร้ายไว้ก่อน 6เขาจะต้องอาศัยอยู่ในเมืองนั้นจนกระทั่งได้รับการไต่สวนต่อหน้าชุมนุมประชากร และจวบจนมหาปุโรหิตซึ่งดำรงตำแหน่งในช่วงเกิดเหตุนั้นสิ้นชีวิต เขาจึงจะกลับภูมิลำเนาเดิมที่เขาหนีมาได้”

7เมืองที่เขาตั้งเป็นเมืองลี้ภัยคือเคเดชแห่งกาลิลีในแถบเทือกเขาแห่งนัฟทาลี เชเคมในแดนเทือกเขาแห่งเอฟราอิม และคีริยาทอารบา (คือเฮโบรน) ในแถบเทือกเขาแห่งยูดาห์ 8ทางฟากตะวันออกของจอร์แดนแห่งเยรีโค20:8 อาจจะเป็นชื่อโบราณของแม่น้ำจอร์แดน พวกเขากำหนดเมืองเบเซอร์ในถิ่นกันดารบนที่ราบสูงในเขตเผ่ารูเบน เมืองราโมทในกิเลอาดในเขตเผ่ากาด และเมืองโกลานในบาชานในเขตเผ่ามนัสเสห์ 9เมืองลี้ภัยเหล่านี้สำหรับทั้งชาวอิสราเอลและคนต่างด้าวที่อาศัยอยู่ท่ามกลางพวกเขา เพื่อผู้ใดก็ตามที่ทำให้คนตายโดยไม่เจตนา สามารถไปหลบอยู่ที่เมืองเหล่านี้โดยไม่ถูกฆ่าล้างแค้นก่อนที่จะได้รับการไต่สวนคดีต่อหน้าชุมนุมประชากร