New Amharic Standard Version

ኢያሱ 16:1-10

ለኤፍሬምና ለምናሴ ነገድ የተመደበው ድርሻ

1ለዮሴፍ ዝርያዎች የተመደበው ድርሻ፣ ከዮርዳኖስ ኢያሪኮ16፥1 ምናልባት፣ ዮርዳኖስ ዘኢያሪኮ የዮርዳኖስ ወንዝ የጥንት መጠሪያ ሊሆን ይችላል። ማለት ከኢያሪኮ ምንጮች በስተ ምሥራቅ ይነሣና፣ ምድረ በዳውን በማቋረጥ በኰረብታማው አገር አድርጎ ወደ ቤቴል ይወጣል። 2ሎዛ ከምትባለው ከቤቴል ይነሣና በአጣሮት ወደሚገኘው ወደ አርካውያን ግዛት ይሻገራል፣ 3በዚያም በምዕራብ በኩል ቊልቊል ወደ የፍሌጣውያን ግዛት እስከታችኛው ቤትሖሮን ምድር ይወርድና ወደ ጌዝር ዘልቆ ባሕሩ ላይ ይቆማል። 4ስለዚህ የዮሴፍ ዘሮች ምናሴና ኤፍሬም ርስታቸውን ተቀበሉ።

5ለኤፍሬም ወገን በየጐሣ በየጐሣቸው የተሰጣቸው ድርሻ ይህ ነው፤

ድንበሩ በምሥራቅ በኩል ከአጣሮት አዳር ተነሥቶ እስከ ላይኛው ቤትሖሮን ይወጣና፣ 6እስከ ባሕሩ ይዘልቃል። በስተ ሰሜን ደግሞ ከሚክምታት ተነሥቶ በምሥራቅ በኩል ወደ ተአናት ሴሎ ይታጠፍና ከዚያ በማለፍ እስከ ኢያኖክ ምሥራቅ ይዘልቃል፤ 7ከኢያኖክም በመነሣት ወደ አጣሮትና ወደ ነዓራት ቊልቊል ይወርድና በኢያሪኮ በኩል አድርጎ ዮርዳኖስ ላይ ብቅ ይላል። 8ድንበሩ አሁንም ከታጱዋ በምዕራብ በኩል አድርጎ ወደ ቃና ወንዝ ይወርድና ከባሕሩ ላይ ይቆማል። እንግዲህ የኤፍሬም ነገድ በየጐሣ በየጐሣቸው የተካፈሉት ርስት ይህ ነበር። 9ይህም በምናሴ ነገድ ርስት ውስጥ ለኤፍሬም ዘሮች የተመደቡትን ከተሞች በሙሉና መንደሮቻቸውን የሚያጠቃልል ነው።

10ይህ ሁሉ ሆኖ የኤፍሬም ዘሮች በጌዝር የሚኖሩትን ከነዓናውያን ከዚያ አላባረሯቸውም ነበር፤ ከነዓናውያን እስከ ዛሬ ድረስ ከኤፍሬም ዘሮች ጋር አብረው ይኖራሉ፤ ይሁን እንጂ የጒልበት ሥራ እንዲሠሩ ይገደዳሉ።

Chinese Contemporary Bible (Simplified)

约书亚记 16:1-10

约瑟子孙分到的土地

1约瑟的子孙抽签所得的地方是从耶利哥附近的约旦河,就是耶利哥水泉的东面开始,穿过旷野,直到伯特利山区; 2又从伯特利,即路斯,沿着亚基人的边境,直到亚他绿3然后西下至押利提人的疆土,远至伯·和仑地区,经基色直到地中海。 4约瑟的儿子玛拿西以法莲得了自己的产业。

5以下是以法莲的子孙按宗族分到的土地:东面从亚他绿·亚达到上伯·和仑6地中海,又向北至密米他,然后向东绕到他纳·示罗,到雅挪哈东部, 7再到亚他绿拿拉,经耶利哥直到约旦河; 8又从他普亚往西到加拿河,直到地中海。这就是以法莲的子孙按宗族所分的产业。 9此外,他们又从玛拿西人的产业中,分到部分城邑以及附近的乡村。 10他们没有赶走住在基色迦南人,迦南人至今还住在以法莲人当中,为他们服劳役。