New Amharic Standard Version

ኢያሱ 15:1-63

ለይሁዳ ነገድ የተመደበው ድርሻ

15፥15-19 ተጓ ምብ – መሳ 1፥11-15

1ለይሁዳ ነገድ በየጐሣቸው በዕጣ የተመደበው ድርሻ እስከ ኤዶም ምድር የሚወርድ ሲሆን፣ በስተ ደቡብ መጨረሻ እስከ ጺን ምድረ በዳ ድረስ ይዘልቃል።

2የደቡብ ወሰናቸው፣ ከጨው ባሕር15፥2 በዚህና በቍጥር 5 ላይ የሙት ባሕር ማለት ነው። ደቡባዊ ጫፍ ካለው የባሕር ወሽመጥ ይነሣል፤ 3ከዚያም የአቅረቢምን መተላለፊያ በማቋረጥ በጺን በኩል እስከ ቃዴስ በርኔ ደቡባዊ ክፍል ይደርሳል፤ ደግሞም ሐጽሮንን አልፎ ወደ አዳር ይወጣና ወደ ቀርቃ ይታጠፋል፤ 4በአድሞን በኩል አድርጎም ወደ ግብፅ ደረቅ ወንዝ ይገባና መቆሚያው ባሕሩ ይሆናል፤ እንግዲህ በደቡብ በኩል ያለው ወሰናቸው15፥4 ዕብራይስጡ ወስናችሁ ይላል። ይህ ነው።

5በምሥራቅ በኩል ያለው ወሰናቸው ደግሞ የጨው ባሕር ሲሆን፣ ይህም የዮርዳኖስ ወንዝ እስከሚሠርግበት ይደርሳል።

በሰሜን በኩል ያለው ወሰንም የዮርዳኖስ ወንዝ ከሚሠርግበት የባሕር ወሽመጥ ይነሣና 6ሽቅብ ወደ ቤትሖግላ ይወጣል፤ ከዚያም በሰሜናዊው ቤትዓረባ በኩል አድርጎ የሮቤል ልጅ የቦሀን ድንጋይ እስካለበት ይደርሳል። 7ከዚያም ድንበሩ ከአኮር ሸለቆ ወደ ዳቤር ይወጣና ከወንዙ በስተ ደቡብ ባለው በአዱሚም መተላለፊያ ፊት ለፊት አድርጎ በስተ ሰሜን ወደ ጌልገላ ይታጠፋል፤ በዓይንሳሚስ ምንጭ በኩል አልፎም ወደ ዓይንሮጌል ይወጣል። 8እንደዚሁም የሄኖምን ልጅ ሸለቆ አልፎ ይሄድና የኢያቡሳውያን ከተማ እስከ ሆነችው እስከ ኢየሩሳሌም ደቡባዊ ተረተር በመዝለቅ፣ በራፋይም ሸለቆ ሰሜን ጫፍ በኩል አድርጎ ከሄኖም ሸለቆ በስተ ምዕራብ ካለው ኰረብታ አናት ላይ ይደርሳል። 9ከዚያም በመቀጠል ከተራራው አናት ተነሥቶ ወደ ኔፍቶ ምንጮች በማምራት፣ በዔፍሮን ተራራ ላይ ያሉትን ከተሞች አልፎ ይወጣና ቂርያትይዓሪም ተብሎ ወደሚጠራው ወደ በኣላ ቊልቊል ይወርዳል፤ 10ከዚያም ከበኣላ በምዕራብ በኩል አድርጎ ወደ ሴይር ይታጠፍና ክሳሎን ተብሎ በሚጠራው በይዓሪም ኰረብታ ሰሜናዊ ተረተር አልፎ ቊልቊል ወደ ቤትሳሚስ በመውረድ ወደ ተምና ይሻገራል። 11ደግሞም በአቃሮን ሰሜናዊ ተረተር አድርጎ ወደ ሽክሮን ይታጠፍና በበኣላ ተራራ ላይ አልፎ እስከ የብኒኤል ይደርሳል፤ ከዚህ በኋላ ወሰኑ ባሕሩ ላይ ይቆማል።

12የምድሪቱ ምዕራባዊ ወሰን የታላቁ ባሕር15፥12 በዚህና በቍጥር 47 ላይ የተጠቀሰው የሜድትራንያን ባሕር ነው። ጠረፍ ነው።

እንግዲህ በየጐሣው የተደለደለውን የይሁዳን ሕዝብ በዙሪያው የከበቡት ወሰኖቹ እነዚሁ ናቸው።

13ኢያሱ እግዚአብሔር ባዘዘው መሠረት፣ ከይሁዳ ድርሻ ላይ ከፍሎ ኬብሮን የተባለችውን ቂርያት አርባቅን ለዮፎኒ ልጅ ለካሌብ ሰጠው፤ አርባቅም የዔናቅ አባት ነበረ። 14ካሌብም ሦስቱን የዔናቅን ዘሮች ሴሲንን፣ አኪመንንና ተላሚንን ከኬብሮን አሳደዳቸው፤ 15ከዚያም በዳቤር ሕዝብ ላይ ዘመተ፤ ዳቤር ቀድሞ ቂርያትሤፍር ትባል ነበር። 16ካሌብ፣ “ቂርያትሤፍርን ወግቶ ለሚይዝ ሰው ልጄን ዓክሳን እድርለታለሁ” አለ። 17ስለዚህ የካሌብ ወንድም የቄኔዝ ልጅ ጎቶንያል ከተማዪቱን ያዛት፤ ካሌብም ልጁን ዓክሳን ዳረለት።

18ዓክሳ ወደ ጎቶንያል በመጣች ጊዜም፣ ከአባትዋ ላይ የእርሻ መሬት እንዲለምን አጥብቃ ነገረችው።15፥18 ዕብራይስጥና አንዳንድ የሰብዓ ሊቃናት ትርጒሞች ከዚህ ጋር ይስማማሉ፤ ብዙ የሰብዓ ሊቃናት ትርጒሞች ግን (መሳ 1፥14 ይመ) አጥብቆ ነገራት ያላሉ። ከአህያዋ ላይ እንደ ወረደች ካሌብ፣ “ምን እንዳደርግልሽ ትፈልጊያለሽ?” ሲል ጠየቃት።

19እርስዋም፣ “እባክህ፤ በጎ ነገር አድርግልኝ፤ በኔጌብ መሬት እንደ ሰጠኸኝ ሁሉ፣ አሁንም የውሃ ምንጭ ጉድጓዶች ስጠኝ” አለችው፤ ካሌብም የላይኛውንና የታችኛውን ምንጮች ሰጣት።

20ለይሁዳ ነገድ በየጐሣቸው የተሰጣቸው ርስት ይህ ነው፤

21በኔጌብ አካባቢ በኤዶም ድንበር ላይ በወሰኑ ጫፍ የሚገኙት የይሁዳ ነገድ ደቡባዊ ከተሞች እነዚህ ነበሩ፤

ቀብስኤል፣ ዔዴር፣ ያጉር፣ 22ቂና፣ ዲሞና፣ ዓድዓዳ፣ 23ቃዴስ፣ ሐጾር፤ ዩትናን፣ 24ዚፍ፣ ጤሌም፣ በዓሎት፣ 25ሐጾርሐዳታ፣ ሐጾር የምትባለው ቂርያትሐጾር 26አማም፣ ሽማዕ፣ ሞላዳ፣ 27ሐጻርጋዳ፣ ሐሽሞን፣ ቤትጳሌጥ፣ 28ሐጸር ሹዓል፣ ቤርሳቤህ፣ ቢዝዮትያ 29በኣላ፣ ዒዪም፣ ዓጼም፣ 30ኤልቶላድ፣ ኪሲል፣ ሔርማ፣ 31ጺቅላግ፣ ማድማና፣ ሳንሳና 32ልባዎት፣ ሺልሂም፣ ዓይንና ሪሞን ናቸው፤ ባጠቃላይም ከተሞቹና መንደሮቻቸው ሃያ ዘጠኝ ናቸው።

33በምዕራቡ በኰረብታዎች ግርጌ ያሉት ደግሞ እነዚህ ናቸው፤ ኤሽታኦል፤ ጾርዓ፣ አሽና 34ዛኖዋ፣ ዓይንገኒም፣ ታጱዋ፣ ዓይናም፣ 35የርሙት፣ ዓዶላም፣ ሰኰት፣ ዓዜቃ፣ 36ሽዓራይም፣ ዓዲታይም፣ ግዴራ፣ ግዴሮታይም ናቸው፤ ከተሞቹም ከነ መንደሮቻቸው ዐሥራ አራት ናቸው።

37ጽናን፣ ሐዳሻ፣ ሚግዳልጋድ፣ 38ዲልዓን፣ ምጽጳ፣ ዮቅትኤል፣ 39ለኪሶ፣ ቦጽቃት፣ ዔግሎን፣ 40ከቦን፣ ለሕማስ፣ ኪትሊሽ፣ 41ግዴሮት፣ ቤትዳጎን፣ ናዕማና መቄዳ ናቸው፤ ከተሞቹም ከነ መንደሮቻቸው ዐሥራ ስድስት ናቸው።

42ልብና፣ ዔትር፣ ዓሻን 43ይፍታሕ፣ አሽና፣ ንጺብ፣ 44ቅዒላ፣ አክዚብና መሪሳ ናቸው፤ ከተሞቹም ከነ መንደሮቻቸው ዘጠኝ ናቸው።

45አቃሮን በዙሪያዋ ካሉ ሰፈሮችና መንደሮቿ ጋር፣ 46እንዲሁም ከአቃሮን በስተ ምዕራብ በአሽዶድ አካባቢ ያሉ ሰፈሮችና መንደሮቻቸው ሁሉ፣ 47አሽዶድ በዙሪያዋ ካሉ ሰፈሮችና መንደሮች ጋር፣ ጋዛ እስከ ግብፅ ደረቅ ወንዝና እስከ ታላቁ ባሕር ጠረፍ በመለስ ካሉት ሰፈሮቿና መንደሮቿ ጋር።

48በኰረብታማዋም አገር የሚገኙ ከተሞች ደግሞ እነዚህ ናቸው፤ ሳምር፣ የቲር፣ ሶኮ 49ደና፣ ዳቤር የምትባለው ቂርያትስና 50ዓናብ፣ ኤሽትሞዓ፣ ዓኒም፣ 51ጎሶም፣ ሖሎንና ጊሎ፤ እነዚህም ዐሥራ አንዱ ከተሞችና መንደሮቻቸው ናቸው።

52አራብ፣ ዱማ፣ ኤሽዓን፣ 53ያኒም፣ ቤትታጱዋ፣ አፌቃ 54ሑምጣ፣ ኬብሮን የተባለችው ቂርያትአርባቅና ጺዖር ናቸው፤ እነዚህም ዘጠኝ ከተሞችና መንደሮቻቸው ናቸው።

55ማዖን፣ ቀርሜሎስ፣ ዚፍ፣ ዩጣ 56ኢይዝራኤል፣ ዮቅድዓም፣ ዛኖዋሕ፣ 57ቃይን፣ ጊብዓና ተምና ናቸው፤ እነዚህም ዐሥር ከተሞችና መንደሮቻቸው ናቸው።

58ሐልሑል፣ ቤትጹር፣ ጌዶር፣ 59ማዕራት፣ ቤትዓኖትና ኤልትቆን ናቸው፤ እነዚህም ስድስት ከተሞችና መንደሮቻቸው ናቸው።

60ቂርያትይዓሪም የተባለችው ቂርያ ትበኣልና ረባት፤ እነዚህም ሁለት ከተሞችና መንደሮቻቸው ናቸው።

61በምድረ በዳው ደግሞ እነዚህ ናቸው፤ ቤትዓረባ፣ ሚዲን፣ ስካካ፣ 62ኒብሻን፣ የጨው ከተማና ዓይንጋዲ፤ እነዚህም ስድስት ከተሞችና መንደሮቻቸው ናቸው።

63ነገር ግን የይሁዳ ዘሮች በኢየሩሳሌም የሚኖሩትን ኢያቡሳውያን ከቦታቸው ሊያስለቅቋቸው አልቻሉም፤ ኢያቡሳውያንም እስከ ዛሬ ድረስ ከይሁዳ ሕዝብ ጋር በኢየሩሳሌም አብረው ይኖራሉ።

Korean Living Bible

여호수아 15:1-63

유다 지파가 분배받은 땅

1유다 지파가 집안별로 제비 뽑아 얻은 땅은 에돔 경계선과 진 광야 최남 단까지였다.

2그들의 남쪽 경계선은 사해 남단에서부터

3아그랍빔 비탈 남쪽을 지나 진 광야에 이르고 또 가데스 – 바네아 남쪽으로 올라가서 헤스론을 지나 앗달로 올라갔으며 갈가 쪽으로 돌아

4거기서 아스몬에 이르고 이집트 국경의 시내를 따라 지중해 연안에 가서 끝났다.

5그리고 동쪽 경계선은 요단 강물이 흘러들어오는 사해이다. 북쪽 경계선은 사해 북단에서

6벧 – 호글라로 올라가서 벧 – 아라바 북쪽을 지나 르우벤의 아들인 보한의 돌에 이르고

7또 아골 골짜기에서부터 드빌을 지나 북으로 올라가서 그 골짜기 남쪽에 있는 아둠밈 비탈 맞은편의 길갈을 향해 북쪽으로 돌아 엔 – 세메스의 우물들이 있는 곳을 지나 엔 – 로겔에 이르고

8거기서 힌놈 골짜기로 올라가 예루살렘성이 위치한 여부스 남쪽 언덕에 이르고 다시 거기서 힌놈 골짜기 서쪽에 있는 산꼭대기로 올라갔는데 이 곳은 르바임 골짜기 북쪽 끝이었다.

9그리고 거기서 넵도아 샘물까지 이르러 에브론산 부근의 성들에 미치고 또 기럇 – 여아림이라고도 하는 바알라에 이르러

10그 곳 서쪽을 돌아 세일산에 미치고 또 여아림산 북쪽에 위치한 그살론성을 지나 벧 – 세메스로 내려가서 딤나를 지난다.

11또 그 경계선은 거기서 에그론 북쪽 비탈로 가서 식그론에 이르러 바알라산을 지나고 얍느엘을 지나 지중해 연안에서 끝났다.

12그리고 서쪽 경계선은 바로 지중해 연안이었다. 이상은 유다 지파가 집안별로 분배받은 땅의 경계선이다.

13여호수아는 여호와께서 명령하신 대로 유다 지파의 땅 일부를 여분네의 아들 갈렙에게 주었는데 그 땅은 기럇 – 아르바 곧 헤브론성이었으며 이 아르바는 아낙의 조상이었다.

14갈렙은 그 성에서 아낙의 후손인 세새와 아히만과 달매 자손들을 쫓아낸 다음

15본래 기럇 – 세벨이라고 부른 드빌성을 치러 갔다.

16그때 갈렙은 “누구든지 기럇 – 세벨을 쳐서 점령하는 자에게 내 딸 악사를 아내로 주겠다” 하고 선언하였다.

17그러자 갈렙의 조카이며 그나스의 아들인 옷니엘이 그 성을 점령하였다. 그래서 갈렙은 자기 딸 악사를 그에게 아내로 주었다.

18악사가 친정을 떠나는 날 자기 아버지께 밭을 요구하라고 남편에게 조르며 나귀에서 내리자 갈렙이 딸에게 “네가 무엇을 원하느냐?” 하고 물었다.

19그때 악사는 “아버지, 한 가지 부탁이 있습니다. 아버지께서 건조한 네겝 지방의 땅을 나에게 주셨으니 샘물도 나에게 주세요” 하고 대답하였다. 그래서 갈렙은 윗샘과 아랫샘을 딸에게 주었다.

20유다 지파가 집안별로 분배받은 성과 그 주변 부락들은 다음과 같다:

21에돔 경계선 일대의 남쪽 네겝 지방에 있는 유다 지파의 성들은 갑스엘, 에델, 야굴,

22기나, 디모나, 아다다,

23게데스, 하솔, 잇난,

24십, 델렘, 브알롯,

25하솔 – 하닷다, 그리욧 – 헤스론 곧 하솔,

26아맘, 세마, 몰라다,

27하살 – 갓다, 헤스몬, 벧 – 벨렛,

28하살 – 수알, 브엘세바, 비스요댜,

29바알라, 이임, 에셈,

30엘돌랏, 그실, 홀마,

31시글락, 맛만나, 산산나,

32르바옷, 실힘, 아인, 림몬으로 모두 29개의 성과 그 주변 부락들이었다.

33저지대에 있는 유다의 성들은 에스다올, 소라, 아스나,

34사노아, 엔 – 간님, 답부아, 에남,

35야르뭇, 아둘람, 소고, 아세가,

36사아라임, 아디다임, 그데라 곧 그데로다임 – 이상의 14개 성과 그 주변 부락들;

37스난, 하다사, 믹달 – 갓,

38딜르안, 미스바, 욕드엘,

39라기스, 보스갓, 에글론,

40갑본, 라맘, 기들리스,

41그데롯, 벧 – 다곤, 나아마, 막게다 – 이상의 16개 성과 그 주변 부락들;

42립나, 에델, 아산,

43입다, 아스나, 느십,

44그일라, 악십, 마레사 – 이상의 9개 성과 그 주변 부락들;

45그리고 에그론과 그 주변의 모든 부락과 마을들,

46에그론에서부터 지중해에 이르기까지 아스돗 부근의 모든 성과 그 부락들,

47이집트 시내와 지중해 연안까지 뻗어 있는 아스돗과 가사와 그 주변 일대의 모든 부락과 마을들이었다.

48산간 지대에 있는 유다 지파의 성들은 사밀, 얏딜, 소고,

49단나, 기럇 – 산나 곧 드빌,

50아납, 에스드모, 아님,

51고센, 홀론, 길로 – 이상의 11개 성과 그 주변 부락들;

52아랍, 두마, 에산,

53야님, 벧 – 답부아, 아베가,

54훔다, 기럇 – 아르바 곧 헤브론, 시올 – 이상의 9개 성과 그 주변 부락들;

55마온, 갈멜, 십, 윳다,

56이스르엘, 욕드암, 사노아,

57가인, 기브아, 딤나 – 이상의 10개 성과 그 주변 부락들;

58할훌, 벧 – 술, 그돌,

59마아랏, 벧 – 아놋, 엘드곤 – 이상의 6개 성과 그 주변 부락들;

60기럇 – 바알 곧 기럇 – 여아림, 랍바 – 이상의 2개 성과 그 주변 부락들이었다.

61광야에 있는 유다 지파의 성들은 벧 – 아라바, 밋딘, 스가가,

62닙산, 소금성, 엔 – 게디 – 이상의 6개 성과 그 주변 부락들이었다.

63그러나 유다 지파는 예루살렘성에 살던 여부스 사람만은 쫓아낼 수 없었다. 그래서 여부스 사람이 오늘날까지 유다 자손과 함께 거기서 그대로 살고 있다.