New Amharic Standard Version

አሞጽ 9:1-15

እስራኤል ትጠፋለች

1ጌታን በመሠዊያው አጠገብ ቆሞ አየሁት፤ እርሱም እንዲህ አለ፤

“መድረኮቹ እንዲናወጡ፣

ጒልላቶቹን ምታ፣

በሕዝቡም ሁሉ ራስ ላይ ሰባብራቸው፤

የቀሩትን በሰይፍ እገድላቸዋለሁ፤

ከእነርሱ አንድም ሰው አይሸሽም፤

ቢሸሽም የሚያመልጥ የለም።

2መቃብር9፥2 ዕብራይስጡ ሲዖል ይለዋል። በጥልቀት ቈፍረው ቢወርዱም፣

እጄ ከዚያ ታወጣቸዋለች፤

ወደ ሰማይ ቢወጡም፣

ከዚያ አወርዳቸዋለሁ።

3በቀርሜሎስ ጫፍ ላይ ቢሸሸጉም፣

አድኜ ፈልጌ ከዚያ አወርዳቸዋለሁ፤

እይዛቸዋለሁም፤

በጥልቅ ባሕር ውስጥ ከእኔ ቢሸሸጉም፣

በዚያ እባቡ እንዲነድፋቸው አዘዋለሁ፤

4በጠላቶቻቸው ተነድተው ለምርኮ ቢወሰዱም፣

በዚያ እንዲገድላቸው ሰይፍን አዛለሁ፤

ለመልካም ሳይሆን ለክፉ፣

ዓይኔን በእነርሱ ላይ አደርጋለሁ።

5ጌታ፣ እግዚአብሔር ጸባኦት፣

ምድርን ይዳስሳል፤

እርሷም ትቀልጣለች፤

በውስጥዋ የሚኖሩ ሁሉ ያለቅሳሉ፤

የምድር ሁለመና እንደ ዐባይ ወንዝ ይነሣል፤

እንደ ግብጽ ወንዝም ይወርዳል።

6መኖሪያውን9፥6 ዕብራይስጡ ለዚህ ሐረግ የሰጠው ትርጒም ምን እንደሆነ አይታወቅም። በሰማይ የሚሠራ፣

መሠረቱንም9፥6 ዕብራይስጡ ለዚህ ሐረግ የሰጠው ትርጒም ምን እንደሆነ አይታወቅም። በምድር የሚያደርግ፣

የባሕርን ውሃ የሚጠራ፣

በምድርም ገጽ ላይ የሚያፈስ፣

እርሱ ስሙ እግዚአብሔር ነው።

7“እናንት እስራኤላውያን፣

ለእኔ እንደ ኢትዮጵያውያን አይደላችሁምን?”

ይላል እግዚአብሔር

“እስራኤልን ከግብጽ፣

ፍልስጥኤማውያንን ከከፍቶር9፥7 በላይኛው ዐባይ አካባቢ ያለ ሕዝብ ነው

ሶርያውያንንም ከቂር አላወጣሁምን?

8“እነሆ፤ የጌታ እግዚአብሔር ዐይኖች፣

በኀጢአተኛ መንግሥት ላይ ናቸው፤

ከምድር ገጽ፣ ፈጽሜ አጠፋዋለሁ፤

የያዕቆብን ቤት ግን፣ ሙሉ በሙሉ

አልደመስስም፤”

ይላል እግዚአብሔር

9“እነሆ፤ ትእዛዝ እሰጣለሁ፤

እህል በወንፊት እንደሚነፋ፣

የእስራኤልን ቤት፣

በሕዝብ ሁሉ መካከል እንዲሁ አደርጋለሁ፤

ነገር ግን አንዲት ቅንጣት በምድር ላይ አትወድቅም።

10በሕዝቤ መካከል ያሉ፣

‘ክፉ ነገር አያገኘንም ወይም አይደርስብንም’ የሚሉ፣

ኀጢአተኞች ሁሉ፣

በሰይፍ ይሞታሉ።

የእስራኤል መመለስ

11“በዚያ ቀን፣

የወደቀውን የዳዊትን ድንኳን አነሣለሁ፤

የተሰበረውን እጠግናለሁ፤

የፈረሰውን ዐድሳለሁ፤

ቀድሞ እንደነበረም አድርጌ እሠራዋለሁ፤

12ስለዚህ የኤዶምን ትሩፍ፣

በስሜ9፥12 ዕብራይስጡ እንደ ሰብዓ ሊቃናቱ ትርጒም የሕዝቡ ትሩፋንና ስሜን የሚሸከሙ ሁሉ፣ እግዚአብሔርን ይፈልጋሉ የተጠሩትንም ሕዝቦች ሁሉ ይወርሳሉ፤”

ይላል ይህን የሚያደርግ እግዚአብሔር

13እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤

“እነሆ፤ ዐጫጁ ዐጭዶ ሳይጨርስ፣

ዐራሹ በላዩ የሚደርስበት፣

ችግኝ ተካዩም ገና ተክሎ ሳይጨርስ፣

ወይን ጨማቂው የሚደርስበት ጊዜ ይመጣል፤

አዲስ የወይን ጠጅ ከተራሮች ይንጠባጠባል፤

ከኰረብቶችም ሁሉ ይፈሳል።

14የተሰደደውን9፥14 ወይም ዕጣ ፈንታቸውን አድሳለሁ ሕዝቤን እስራኤልን እመልሳለሁ፤

እነርሱም የፈራረሱትን ከተሞች መልሰው ሠርተው በውስጣቸው ይኖራሉ።

የወይን ተክል ተክለው፣ ጠጁን ይጠጣሉ፤

አትክልት ተክለው ፍሬውን ይበላሉ።

15እስራኤልን በገዛ ምድራቸው እተክላቸዋለሁ፤

ከሰጠኋቸውም ምድር፣ ዳግመኛ

አይነቀሉም”

ይላል አምላክህ እግዚአብሔር

Japanese Contemporary Bible

アモス書 9:1-15

9

滅ぼされるイスラエル

1私は、主が祭壇のそばに立っているのを見ました。

主はこう言いました。

「柱の頭を打って神殿を揺り動かし、

柱が崩れて屋根が下にいる人々の上に

落ちかかるようにせよ。

彼らは逃げようにも逃げられず、一人残らず死ぬ。

2彼らが地獄まで下っていっても

わたしは引っ張り上げ、天に上っても、引き降ろす。

3たとえカルメル山の頂の岩間に隠れても、

見つけ出して捕まえる。

深海に身を潜めても、海蛇を送ってかみ殺させる。

4自ら進んで国外へ捕らえ移されても、

剣に命じて、そこで殺させる。

彼らが善ではなく悪を受け取るのを、

しっかりと見届ける。」

5全能の主が地に触れると、

地は溶け、そこに住む人々はみな嘆き悲しみます。

地はエジプトのナイル川のように盛り上がり、

また沈みます。

6その住まいの階上は天にあり、

一階は地の上にあります。

その方は海から蒸気を呼んで、

地に雨として降らせます。その名は主です。

7「イスラエルの民よ。わたしにとって、

あなたがたはエチオピヤ人より大切であろうか。

確かにあなたがたをエジプトから連れ出したが、

ほかの民も同じようにしたのだ。

ペリシテ人をカフトルから、

シリヤ人をキルから連れ出した。

8わたしの目は、罪深い国イスラエルに向けられている。

わたしはイスラエルを根元から抜いて、

世界にまき散らす。

しかし、永久に根こそぎにはしないと約束した。

9わたしが命じたとおり、穀物をふるいにかけるように、

本物の穀粒はなくさないように、

イスラエルを他の国々にふるわせる。

10しかし、『神は私たちに手を下さない』

と言っている罪人は、みな剣によって死ぬ。

イスラエルの回復

11その時には、今は荒れ果てたままになっている

ダビデの町を再建し、以前のように栄えた町にする。

12イスラエルは、エドムの残りの者と、

私に属するすべての国の残りの者とを所有する。」

このすべてを計画した主が、このように言うのです。

13「大豊作で、やっと収穫が終わると思ったら、

息つく暇もなく別の種をまく有様で、

イスラエルの丘のぶどう畑は

甘いぶどう酒をしたたらせる時がくる。

14わたしは、わたしの民イスラエルの繁栄を回復する。

彼らは荒れた町々を建て直し、

再びそこに住んで、ぶどうや果樹を栽培する。

自分たちの収穫した物を食べ、ぶどう酒を飲む。

15わたしは彼らを、

わたしが与えた地にしっかり植えつける。

彼らは、再び引き抜かれることがない。」

あなたの神、主がこう言うのです。