New Amharic Standard Version

አሞጽ 7:1-17

አንበጣ፣ እሳትና ቱንቢ

1ጌታ እግዚአብሔር ይህን አሳየኝ፤ የንጉሡ የመከር እህል ከተሰበሰበ በኋላ ገቦው መብቀል በጀመረ ጊዜ፣ እርሱ የአንበጣ መንጋ እንዲፈለፈል አደረገ። 2አንበጦች የምድሩን ሣር ግጠው ከጨረሱት በኋላ፣ “ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፤ ይቅር እንድትል እለምንሃለሁ፤ ያዕቆብ ይህን እንዴት ሊቋቋመው ይችላል? ታናሽ ነው እኮ!” አልሁ።

3እግዚአብሔርም ስለዚህ ነገር ተጸጸተ፤ እግዚአብሔርም ይህ አይፈጸምም አለ።

4ጌታ እግዚአብሔር ይህንም አሳየኝ፤ ጌታ እግዚአብሔር በእሳት ሊፈርድ ተዘጋጀ፤ እሳቱም ታላቁን ጥልቅ አደረቀ፤ ምድሪቱንም በላ። 5ከዚያም በኋላ፣ “ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፤ እንድትተወው እለምንሃለሁ፤ ያዕቆብ ይህን እንዴት ሊቋቋመው ይችላል? ታናሽ ነው እኮ! አልሁ።

6እግዚአብሔር ስለዚህ ነገር ተጸጸተ፤ ጌታ እግዚአብሔር፣ “ይህም ደግሞ አይፈጸምም” አለ።

7ይህንም ደግሞ አሳየኝ፤ ጌታ በእጁ ቱምቢ ይዞ በቱምቢ በተሠራ ቅጥር አጠገብ ቆሞ ነበር። 8እግዚአብሔር፣ “አሞጽ፣ የምታየው ምንድ ነው?” አለኝ።

እኔም፣ “ቱምቢ” አልሁ።

ጌታም እንዲህ አለ፤ “እነሆ፤ በሕዝቤ በእስራኤል መካከል ቱምቢ እዘረጋለሁ፤ ከእንግዲህም ወዲያ አልምራቸውም።

9“የይስሐቅ ማምለኪያ ኮረብታዎች ባድማ ይሆናሉ፤

የእስራኤል መቅደሶች ይፈርሳሉ፤

በኢዮርብዓምም ቤት ላይ በሰይፌ እነሣለሁ።”

አሞጽና አሜስያስ

10ከዚህ በኋላ የቤቴል ካህን አሜስያስ ወደ እስራኤል ንጉሥ ወደ ኢዮርብዓም እንዲህ ሲል መልእክት ላከ፤ “አሞጽ በእስራኤል ቤት መካከል በአንተ ላይ እያሤረ ነው፤ ምድሪቱም ቃሉን ሁሉ ልትሸከም አትችልም፤ 11አሞጽ እንዲህ ሲል ተናግሮ ነበርና፤

“ ‘ኢዮርብዓም በሰይፍ ይሞታል፤

እስራኤልም በእርግጥ ከትውልድ አገሩ

ተማርኮ ይሄዳል።”

12አሜስያስም፣ አሞጽን እንዲህ አለው፤ “አንተ ባለ ራእይ ከዚህ ሂድ! ከይሁዳ ምድር ሽሽ፤ እዚያም እንጀራህን ብላ፤ በዚያም ትንቢት ተናገር። 13ከእንግዲህ ወዲያ ግን በቤቴል ትንቢት አትናገር፤ የንጉሡ መቅደስ፣ የመንግሥቱም መኖሪያ ነውና።”

14አሞጽም ለአሜስያስ እንዲህ ሲል መለሰ፤ “እኔ እረኛና የባሉጥ ፍሬ ለቃሚ ነኝ እንጂ ነቢይ ወይም የነቢይ ልጅ አይደለሁም፤ 15እግዚአብሔር ግን የበግ መንጋ ከምጠብቅበት ቦታ ወስዶ፣ ‘ሂድና ለሕዝቤ ለእስራኤል ትንቢት ተናገር’ አለኝ፤ 16እንግዲህ የእግዚአብሔርን ቃል ስማ።

አንተ፣ “ ‘በእስራኤል ላይ ትንቢት አትናገር፤

በይስሐቅም ቤት ላይ አትስበክ’ ትላለህ።

17“ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤”

‘ሚስትህ በከተማዪቱ ውስጥ ጋለሞታ ትሆናለች፤

ወንዶችና ሴቶች ልጆችህም በሰይፍ ይወድቃሉ፤

ምድርህም እየተለካ ይከፋፈላል፤

አንተ ራስህ በረከሰ7፥17 ዕብራይስጡ ርኩስ ይለዋል። ምድር ትሞታለህ፤

እስራኤልም ከትውልድ አገሩ፣

ተማርኮ ይሄዳል።’ ”

Chinese Contemporary Bible (Traditional)

阿摩司書 7:1-17

各種災禍的異象

1以下是主耶和華讓我看見的異象:看啊,祂造了一大群蝗蟲。那時,王室的作物已經收割,第二季作物剛開始發苗。 2蝗蟲吃盡地上的青苗時,我說:「主耶和華啊,求你赦免!雅各那麼弱小,他怎麼受得了呢?」 3於是,耶和華心生憐憫,說:「我不降這災了。」

4以下是主耶和華讓我看見的異象:看啊,主耶和華降下審判的大火。大火燒乾了深海,正在吞噬土地。 5那時,我說:「主耶和華啊,求你停止吧!雅各那麼弱小,他怎麼受得了呢?」 6於是,耶和華心生憐憫,說:「我也不降這災了。」

7以下是祂讓我看見的異象:看啊,主站在一道按照準繩建造的牆邊,手裡拿著準繩。 8耶和華對我說:「阿摩司,你看見什麼?」我答道:「一條準繩。」主說:「我要在我的以色列子民中吊起準繩,量度他們,我不會再饒恕他們。 9以撒子孫的邱壇必遭毀壞,以色列的廟宇必成廢墟,我要用刀攻擊耶羅波安王朝。」

阿摩司被逐

10伯特利的祭司亞瑪謝派人告訴以色列耶羅波安:「阿摩司以色列家圖謀背叛你,我們國家無法容忍他的言論。 11因為阿摩司這樣說,『耶羅波安將喪身刀下,以色列人必被擄去,遠離家鄉。』」

12亞瑪謝對我說:「先見啊,走吧!逃回猶大去吧!你要在那裡掙吃的,在那裡說預言。 13不可再在伯特利說預言,這裡是王的聖所,是國廟。」

14我答道:「我本不是先知,也不是先知的門徒。我只是一個牧人,也替人看護桑樹。 15但耶和華不再讓我看守羊群,祂對我說,『去!向我的以色列子民說預言。』 16亞瑪謝啊,你說,『不要說攻擊以色列的預言,不要傳講攻擊以撒子孫的信息。』現在你要聽耶和華對你說的話。 17耶和華說,『你的妻子必在這城裡淪為妓女,你的兒女必喪身刀下,你的田地必被人丈量、瓜分,你自己必死在異鄉7·17 異鄉」希伯來文是「不潔之地」,指不信上帝的國家。以色列人必被擄去,遠離家鄉。』」