New Amharic Standard Version

አሞጽ 6:1-14

ተዘልላ ላለችው እስራኤል የተሰጠ ማስጠንቀቂያ

1በጽዮን ተዘልላችሁ የምትቀመጡ፣

በሰማርያ ተራራ ያለ ሥጋት የምትኖሩ፣

የእስራኤልም ሕዝብ ለርዳታ ወደ እናንተ የሚመጡባችሁ፣

እናንት የአሕዛብ አለቆች ሆይ፤ ወዮላችሁ!

2ወደ ካልኔ ሂዱ፤ እርሱንም ተመልከቱ፤

ከዚያም ወደ ታላቂቱ ሐማት ሂዱ፤

ወደ ፍልስጥኤም ከተማ ወደ ጌትም ውረዱ፤

እነዚህ ከሁለቱ መንግሥታቶቻችሁ ይሻላሉን?

የምድራቸውስ ስፋት ከእናንተ ይበልጣልን?

3ክፉውን ቀን ለምታርቁ፣

የግፍንም ወንበር ለምታቀርቡ ወዮላችሁ!

4በዝሆን ጥርስ ባጌጠ ዐልጋ ላይ ለምትተኙ፤

በድንክ ዐልጋችሁ ላይ ለምትዝናኑ፣

ከበጎች መንጋ ጠቦትን፣

ከጋጣም ጥጃን ለምትበሉ፤

5ባልተቃኘ በገና ለምትዘፍኑ፣

በሙዚቃ መሣሪያ ለመጫወት ለምትሹ፣

6በፋጋ የወይን ጠጅ ለምትጠጡ፣

ምርጥ ሽቱም ለምትቀቡ፣

ስለ ዮሴፍ መከራ ግን ለማታዝኑ ወዮላችሁ!

7ስለዚህ እናንተ በመጀመሪያ በምርኮ ከሚወሰዱት መካከል ናቸሁ፤

መፈንጠዛችሁና መዝናናታችሁም ያበቃል።

እግዚአብሔር የእስራኤልን ትዕቢት ይጸየፋል

8ጌታእግዚአብሔር “የያዕቆብን ትዕቢት ተጸይፌአለሁ፤

ምሽጎቹንም ጠልቻለሁ፤

ከተማዪቱንና በውስጥዋ ያለውን ሁሉ፣

አሳልፌ እሰጣለሁ” ሲል በራሱ ምሎአል፤

ይላል የሰራዊት አምላክ እግዚአብሔር

9በአንድ ቤት ውስጥ ዐሥር ሰዎች ቢቀሩ እነርሱም ይሞታሉ። 10በድኖቹንም ከቤት አውጥቶ ማቃጠል ያለበት አንድ ዘመድ መጥቶ ተደብቆ ያለውን ሰው፣ “ከአንተ ጋር የቀረ ሌላ ሰው አለን?” ሲለው፣ እርሱም “የለም” ይለዋል፤ ከዚያም በኋላ፣ “ዝም በል፤ የእግዚአብሔርን ስም መጥራት አይገባንም” ይለዋል።

11እነሆ፤ እግዚአብሔር ትእዛዝ ሰጥቶአልና፤

ታላላቅ ቤቶችን ያወድማቸዋል፤

ትንንሾቹንም ያደቅቃቸዋል።

12ፈረሶች በጭንጫ ላይ ይሮጣሉን?

ሰውስ እዚያ ላይ በበሬ ያርሳልን?

እናንተ ግን ፍትሕን ወደ መርዝነት፣

የጽድቅንም ፍሬ ወደ መራራነት ለወጣችሁ።

13እናንተ ሎዶባርን6፥13 ትርጒሙ ምንም ማለት ነው። በማሸነፋችሁ ደስ ያላችሁ፣

“ቃርናይምን6፥13 ቃርናይም ትርጒሙ ቀንዶች ማለት ነው፤ ቀንድ የጥንካሬ ምልክት ነው። በራሳችን ብርታት ይዘናል” የምትሉ፣

14ሁሉን የሚገዛ አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፣

“የእስራኤል ሕዝብ ሆይ፤ እነሆ፤ እኔ ከሐማት መግቢያ6፥14 ወይም ከመግቢያው ጀምሮ እስከ ዓረባ ሸለቆ ድረስ፣

የሚያስጨንቃችሁን ሕዝብ፣ በእናንተ

ላይ አስነሣለሁ።”

Korean Living Bible

아모스 6:1-14

시온과 사마리아에 대한 경고

1시온에서 안일하게 살고 사마리아에서 마음 편하게 지내며 이스라엘 백성 가 운데서도 유명하여 인기를 얻는 자들아, 너희에게 화가 있을 것이다.

2너희는 갈레성으로 가서 무슨 일이 일어나고 있는지 보아라. 그리고 거기서 큰 하맛으로 가고 또 블레셋 사람의 성인 가드로 내려가 보아라. 그 나라들이 유다와 이스라엘보다 나은가? 그들의 토지가 너희 토지보다 넓은가?

3너희는 재앙의 날이 다가오고 있음을 인정하지 않으려고 하지만 너희 행위는 그 날을 더 가까이 오게 하고 있다.

4너희는 상아 침대에 눕고 호화스러운 안락 의자에서 기지개를 켜며 제일 좋은 양고기와 송아지 고기를 먹고

5다윗처럼 즉석에서 노래를 지어 수금에 맞춰 흥얼거리며

6대접으로 포도주를 마시고 귀한 향수를 몸에 바르면서도 이스라엘이 당할 파멸에 대해서는 슬퍼하지 않는다.

7그러므로 너희가 제일 먼저 사로잡혀갈 것이다. 6:7 또는 ‘기지개 켜는 자의 떠드는 소리가 그치리라’호의 호식하면서 빈둥거리던 너희 생활이 끝장날 것이다.

8전능하신 하나님 주 여호와께서 맹세하며 말씀하신다. “내가 이스라엘 백성의 교만을 싫어하고 그들의 호화로운 저택을 경멸한다. 그러므로 내가 이 성과 성 안에 있는 모든 것을 그 대적에게 넘겨 주겠다.”

9한 집에 열 사람이 남아 있어도 다 죽을 것이다.

10죽은 사람의 시체를 묻을 친척이 그 시체를 집 밖으로 가져가면서 그 집에 아직 숨어 있는 자에게 “너와 함께 있는 자가 있느냐?” 하고 물었을 때 그가 아무도 없다고 대답하면 저가 그에게 “조용히 하라! 우리가 여호와의 이름을 불러서는 안 된다” 하고 말할 것이다.

11여호와께서 명령을 내리시면 큰 집이 갈라지고 작은 집은 박살날 것이다.

12말이 바위산에서 달릴 수 있으며 사람이 소로 그 곳을 경작할 수 있겠느냐? 그러나 너희는 정의를 독약으로, 의의 열매를 쓸개로 바꾸고

136:13 히 ‘로-데발’헛된 것을 기뻐하며 보잘것없는 너희 힘을 자랑하고 있다.

14전능하신 하나님 여호와께서 말씀하신다. “이스라엘 백성아, 내가 한 나라를 일으켜 너희를 치겠다. 그 나라가 북으로 하맛 고개에서부터 남으로 아라바 시내에 이르기까지 너희를 괴롭힐 것이다.”